👉 የዳዕዋ አካሄድ
ክፍል 2⃣
قُلْ هَٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
يوسف ( 108)
«ይህች መንገዴ ናት ፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን ፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል ፡፡
ከዚህ የቁርኣን አንቀፅ የምንረዳው የዳዕዋ አካሄድ ሁለተኛው : –
2 – አል ሑጀቱ ወል በያን የሚለው ሲሆን : –
" عَلَىٰ بَصِيرَةٍ "
" በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን "፡፡
ከሚለው የተወሰደ ነው ። አንድ ዓሊም ወይም ዳዒ የሚያዝበት ሆነ የሚከለክልበት ነገር መረጃ ሊኖረው ይገባል ። መረጃ የሚባለው የቁርኣን ወይም የሐዲስ እንዲሁም የዑለሞች ኢጅማዕ ነው ። የቁርአንና ሐዲስ መረጃም በሰለፎች ግንዛቤ መሆን አለበት ። መጀመሪያ መረጃው ከሚያዝበት ወይም ከሚከለክለው ነገር ጋር የሚገናኝ መሆኑን መጤን አለበት ። ከዛ በኋላ ሰለፎች ያን የቁርኣን ወይም የሐዲስ ነስ እንዴት እንደ ተረዱት ማወቅ ግድ ነው ። መረጃ አለኝ ብቻ ማለቱ በቂ አይደለም ። መረጃው በሰለፎች ግንዛቤ መረጃ አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል ።
አንድ ወደ ሱና የሚጣራ ዳዒ ስለ ማንኛውም ሑክም ወይም ብይን ሲናገር ለዛ ብይን ከቁርኣን ወይም ሐዲስ መረጃ መጥቀስ ግድ ይለዋል ። አንድን ብይን እንዲህ ነው ብሎ ተናግሮ መረጃህ ምንድነው ሲባል ሸይኽ እገሌ እንዲህ ብሏል ‼ ማለት የሰለፎችን አካሄድ መኻለፍ ነው ። በመሆኑም የሸይኹን መረጃ አይቶ ትክክል ከሆነ መረጃውን ጠቅሶ ብይኑ ይህ ነው መረጃውም ይህ ነው በዚህ ጉዳይ ላይ እነሸይኽ እገሌ እንዲህ ብሏል ማለት ነው ያለበት ።
ከአንቀፁ የምናገኘው ሶስተኛው የዳዕዋ አካሄድ :–
3 – ሉዙሙል ኢትቲባዕ የሚለው ሲሆን እሱም : –
" أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي "
" እኔም የተከተለኝም ሰው "
ከሚለው እናገኘዋለን ። አንድ ዳዒ ወይም ዓሊም በዳዕዋ ሂደቱ ነብዩን መከተል ግድ ይለዋል ። ይህም የሚባለው ዳዕዋ ዒባዳ ስለሆነና ዒባዳ ደግሞ ነብዩ ባዘዙት መልኩ ወይም የሳቸውን ፈለግ ያልተከተለ ከሆነ ወደ ባለቤቱ ተመላሽ ስለሚሆን ነው ።
ብዙ አንጃዎችና ግለሰቦች የነብዩን ፈለግ ትተው የራሳቸው መመሪያ ቀርፀው ወደ ዳዕዋ ሜዳ ይገባሉ ። የዳዕዋውን ይዘት ስትመለከት በፍልስፍና የተሞላ አለ ተባለ ወይም ትርክት ሆኖ ታገኘዋለህ ። ብዙ ሳአት በወሰደ ዳዕዋ ወይም ትልቅ መፅሐፍ አላህ እንዲህ ብሏል ። ነብዩ እንዲህ ብሏል ። የሰለፍ ዑለሞች እንዲህ ብሏል የሚል አታገኝም ። የሰዎች አመለካከትና ዝንባሌን መሰረት ያደረገ ከቅናቻ ይልቅ ወደ ጥመት የቀረበ ነው ።
ዳዒ የሆነ ሰው ዳዕዋው ፍሬያማ እንዲሆን ኢኽላስና ሙታባዓ ያስፈልገዋል ። ይህ ከሆነ ለቅናቻ ሰበብ መሆን ይችላል ። የሰለፍዮች ዳዕዋ ከሌሎች የጥሜት አንጃዎች ዳዕዋ የሚለየው አካሄዱ የነብዩን ፈለግ የተከተለ በመሆኑ ነው ።
አላህ በተከበረው ቃሉ የአላህ መልእክተኛም በሐዲሳቸው አማኞች እሳቸውን መከተል እንዳለባቸው የተናገሩበት መረጃ ስፍር ቁጥር የለውም ። አላህ ልቡን ለሐቅ ክፍት ያደረገለት አንድ አንቀፅ ወይም ሐዲስ ይበቃዋል ። ካልሆ ግን በግመል የሚጫን መረጃ ቢመጣም አይጠቅምም ።
አንድ ዳዒ ወይም ዓሊም ነብዩን ለመከተል የሚችለው የሳቸውን የህይወት ታሪክ ሲያውቅ ነው ። በመሆኑም ወደ ዳዕዋ ሜዳ የሚገባ ዓሊም ወይም ዳዒ የነብዩን ህይወት ታሪክ ማወቅ ቅድሜያ የሚሰጠው ተግባሩ ሊሆን ይገባል ። ለዚህ ዋነኛው መፍትሄ ቁርኣንን ማጥናት ነው ።
በዳዕዋው አካሄድ ነብዩን የሚከተል ከስሜት : ከዝንባሌ : ከፍልስፍናና ከድካም : ይጠበቃል ። ምክንያቱም ከነብዩ መንገድ ውጪ ያሉ መንገዶች በሙሉ አድካሚ ስለሆኑ ። የሚገርመው ድካሙ ዱንያ ላይ ብቻ ቢሆን መልካም ነበር ። ግን ትልቁ ድካም አኼራ ላይ ነው ያለው ።
አላህ ለመልእክተኛው ባሳያቸው መንገድ ዳዕዋ ማድረግ የፈለገ ሰው እሳቸውን መከተል አለበት ።
ይቀጥላል : –
https://t.me/bahruteka