👉
የዳዕዋ አካሄድ ክፍል አንድ
የስሜትና ዝንባሌን መከተል ማእበል ኡማውን እያናወጠ ባለበት ፣ ሁሉም የጥመት አንጃ የራሱ የሆነ የዳዕዋ መስመር ዘርግቶ ይህ ነው ትክክል ሌላው ባጢል ነው በሚልበት ፣ ተራው ሰው ቀርቶ ወደ ዒልምና ዳዕዋ ራሳቸውን ያስጠጉና ትክክለኛ ዳዕዋ ማድረግ አየፈለጉ ሚዛን አጥተው ግራ በተጋቡበት በአሁኑ ወቅት ትክክለኛውን የዳዕዋ አካሄድ ማዋቅ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው ።
አላህ ይህን የመሰለ ትልቅ መርህ ወደ ማንኛውም አንጃ ወይም ግለሰብ የአእምሮ ጭማቂ አላስጠጋውም ። በማያሻማና ግልፅ በሆነ መልኩ በተከበረው ቃሉ ለመልእክተኛው ነግሯቸዋል ።
ይህ መለኮታዊ የሆነው የዳዕዋ አካሄድ መመሪያ በሚከተለው ቃሉ እናገኘዋለን : –
قُلْ هَٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ يوسف ( 108)
«ይህች መንገዴ ናት ፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን ፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል ፡፡
በዚህ የቁርኣን አንቀፅ አላህ ለነብዩ በዳዕዋቸው ላይ አራት የዳዕዋ አካሄድ መስመሮችን አሳይቷቸዋል ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው : –
1 – አል ውዱሕ ወል በያን ( በዳዕዋ ላይ ግልፅነት)
2 – አል ሑጀቱ ወል ቡርሃን ( ዳዕዋ በመረጃ መሆን እንዳለበት )
3 – ሉዙሙል ኢቲባዕ ( በዳዕዋ ላይ ነብዩን መከተል ግድ መሆኑ )
4 – አትተመዩዝ ( በዳዕዋ ላይ መለየት አስፈላጊ መሆኑ )
እነዚህ መሰረታዊ የዳዕዋ አካሄድ መርሆች እየአንዳንዱ ወደ ሱና የሚጣራ ዳዕዋው ውጤታማ እንዲሆን የሚፈልግ ዓሊም ወይም ዳዒ ሊከተላቸው ይገባል ።
እነዚህን ነጥቦች በተወሰነ መልኩ ለማብራራት ያክል : –
1 – አል ውዱሕ ወል በያን
قُلْ هَٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ከሚለው ቃል የምንወስደው ነው ።
በዚህ አንቀፅ ላይ አላህ ለመልእክተኛው ጥሪያቸው ወዴት እንደሆነ ግልፅ ማድረግ እንዳለባቸው ነው ያመላከታቸው ። ጥሪዬ ወደ አላህ ነው በል ።
ይህ ማለት አንድ ዳዒ የዳዕዋው ግብ ለራሱ ግልፅ ከሆነለት በኋላ ጥሪ ለሚያደርግላቸው ምእመናንም ግልፅ ማድረግ እንዳለበት ያሳየናል ። ወደ አላህ ነው ማለት :–
ከሽርክና ቢዳዓ እንዲሁም ከማንኛውም አላህ እርም ካደረገው ነገር በማስጠንቀቅ ወደ ተውሒድና ሱና በግልፅ መጣራት ግዴታ መሆኑን ያስገነዝበናል ።
የሽርክ ተግባራትን ባጠቃላይ ሽርክ መሆናቸውን ፣ የቢዳዓ ተግባራትም ባጠቃላይ ቢዳዓ መሆናቸውና ሐራም የሆኑ ነገሮችም ሐራም በማለት ዳዕዋው ግልፅነት የጎደለው እንዳይሆን በማድረግ መሄድ ይኖርበታል ።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ በረቃኢቅና ተርጚብ ላይ ያተኮረ ዳዕዋ የሚያደርግ ከሆነ ይን መለኮታዊ መርህ ከመኻለፉም በላይ በዙሪያው ያሉት ሰዎች ፈተና በሚመጣ ጊዜ ትተውት ሄደው ቅጠሉ እንደረገፈ ዛፍ ብቻውን መቅረቱ አይቀርም ።
አንድ ዳዒ ወይም ዓሊም እሱ ጋር ቁጭ ብለው የሚማሩ ሰዎች በማያሻማ ሁኔታ የሱ ዳዕዋ ምን አይነት እንደሆነና ወዴት እንደ ሚጣራ ማወቅ አለባቸው ። የተለያዩ አይነት ሙኻሊፎች ከነሙኻለፋቸው ሰምተውት ደስ ሲል ካሉ ዳዒው ወይም ዓሊሙ ራሱን መፈተሽ አለበት ። ምክንያቱም ቁርኣንም ሆነ ሐዲስ ሁሉንም አላስደሰቱም ። ከሃዲያን ፣ ሙናፊቆችና ሙብተዲዖች አልተደሰቱበትም ።
የአንድ ወደ ሱና እጣራለሁ የሚል ዳዒ ዳዕዋ ሁሉም ሙኻሊፍ ካስደሰተ ቁርአንና ሐዲስን የኻለፈ ነው ማለት ነው ። ይህ ማለት ዳዕዋው ግልፅ አይደለም ማለት ነው ። ወይም በሌላ አባባል አላህ ባዘዘው መልኩ የተደረገ ዳዕዋ አይደለም ማለት ነው ።
ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ለመስላሀ ብለን ነው ሊሉ ይችላሉ መልሳችን
{
قُلْ أَأَنتُمْ أَعْلَمُ أَمِ اللَّهُ }
البقرة ( 140)
« እናንተ ታውቃላችሁን? ወይንስ አላህ ?» በል ።
የሚል ነው የሚሆነው ።
በአላህ ዲን ላይ አላህ ካዘዘው አካሄድ ወጥቶ ለመስላሀ ነው ማለት አላህን ማስዋሸት ነው የሚሆነው ።
እነ ካሚል ሸምሱና ሳዲቅ ሙሐመድ አልከሶ መስጂድ ውስጥ እንጨት በሚመለክበት ቦታ ላይ ሆነው ከኛ ምን ትፈልጋላችሁ ? ያሉት በመስላሀ ስም ነው ።
ኢብኑ መስዑዶች አደባባይ ላይ ከአሕባሽ ፣ ከሱፍይና ኢኽዋን ጋር እጅ ለእጅ ተጨባብጠው ሰለፍይ ፣ ኢኽዋንይ ፣ ተብሊጝይ የሚባል ነገር የለም ሁላችንም የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ነን ‼ ያሉት በመስላሀ ስም ነው ።
አህባሽ ኢኽዋንና ሱፍዮች በነሳራዎች ጥምቀት በዓል ጊዜ ከእነርሱ ጋር ሆነው አስፓልት የሚጠርጉት በመስላሀ ስም ነው ። አሕባሾችና ሱፍዮች አብረው ታቦት ሲሸኙ ሙመዪዓና ኢኽዋኖች ዝም የሚሉት በመስለሀ ስም ነው ።
ለማን መስላሀ ይሁን ለዲን ?
መልሳችን
{
قُلْ أَأَنتُمْ أَعْلَمُ أَمِ اللَّهُ }
البقرة ( 140)
« እናንተ ታውቃላችሁን? ወይንስ አላህ ?» በል ።
የሚል ነው ።
ሰለፍዮች ዳዕዋችሁን ግልፅ ከማድረግ መስላሀ ነው የከለከለን ካላችሁ ይመለከታችኋል ።
ይቀጥላል : –
https://t.me/bahruteka