እንተዋወስ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አሏህ ሆይ! እኛን ወይም መስጂዶቻችንን እና ሙስሊሞችን በክፉ የሚሻ፣በነፍስ ስጋው አሰቃየው።
አምላካችን ሆይ! ሀገራችንን ክፉ የሚፈልግ ከራሱ ጋር ያዘው እቅዱን እና ሴራውን ወደ ጉሮሮው  መልስልን እቅዱ ለርሱ መጥፊያ አድርግልን አላህ ሆይ! ሀገራችንን እና የሙስሊም ሀገራትን ከክፉ እና ከረብሻ ሁሉ ጠብቅልን።

አላህ ሆይ! ጨቋኞችን ቅጣልን፣ ለሌሎች መማሪያ ይሆኑ ዘንድ አምባገነኖችን ልክ አስገባልን። አሏህ ሆይ! ንፁሀንን የገደሉ፣ ደም ያፈሰሱ፣ አዛውንቶችን፣ ህጻናትን እና ሴቶችን ቤት አልባ ያደረጉ ወንጀለኞችን የእጃቸውን ስጥልን፣ አንተ ዱዓ ሰሚ ነህ! ያሰሚዑ ዱዓእ!


“ዱዓ ማድረግ በፍፁም አትተው!
በነፍሶቻችሁም የምታውቁት ወንጀልና ከትእዛዝ ወደ ኋላ መቅረትሀ ዱዓእ ከማድረግ ሊከለክላችሁ አይገባም።
ሸይጧን የፍጥረቱ ሁሉ ክፉ ሆኖ ሳለ አላህ የርሱን ዱዓ ሰምቶ ምላሽ ሰጥቶታልና።”

ኢብኑ ዑየይናህ/ሹዐቡ አል ኢማን [2/53

*ሙሲባውን አላህ እንዲመለስልን በዱዓእ እንበርታ! በተለይም ከአሱር በኋላ ባለው ጊዜ ዱዓእ ሙስተጃብ ነው ተብሏልና!

🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል).
____
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
___


@BedrAreb_1


ሐስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል! «በቂያችን አላህ ነው ምንኛ ያማረ መጠጊያ!» ኢብራሂም -አለይሂ ሰላም - ወደ እሳት በተጣሉ ጊዜ ይህን ዱዓ ያደረጉ ሲሆን  ነብያችንና ሰይዳችን ሙሐመድ - ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - ሰዎች ለእናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» በተባሉ ግዜ ይበልጥ ኢማናቸው ጨመረ፣ (ሐስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል) «በቂያችንም አላህ ነው ምንኛ ያማረ መጠጊያ! » አሉ። (አል-ዒምራን 173)

@BedrAreb_1


የራሱን አላዋቂነት ማን ያውቃል?!

▪️"ከማንም በላይ እኔ አውቃለሁ" ከማለት የበለጠ አላዋቂነት የለም።
ዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ዘንግተህ የሰዎች ዓይን ውስጥ ያለን ስንጥር ከማየት የበለጠ እውርነትም የለም።
كَدَعواكِ كُلٌّ يَدَّعي صِحَّةَ العَقلِ-
وَمَن ذا الَّذي يَدري بِما فيهِ مِن جَهل.
"ልክ እንዳንቺ ሙጉት ሁሉም ሰው የዓቅሉንና የአስተሳሰቡን ትክክለኛነት ይሞግታል፣ እራሱ ዘንድ ያለን አላዋቂነትና ሞኝነት ማን ያውቃል?!"ላለውና በ354 ዓ.ሂ ለሞተው የገጣሚዎች አሚር "አል-ሙተነቢ-አላህ ይዘንለት- ልክ ብሏልና።

▪️እራሳችን ዘንድ ትልቅ ሰው፣ አላህ ዘንድ ግን ትንሽና ወራዳ ሰው ከመሆን አላህ እራሱ ይጠብቀን
።የግንባር ዓይን እንደሰጠን ሁሉ የልብም ዓይን ይስጠን።

▪️የሰው ልጅ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተጨለፈ የእውቀቱ መጠን አናሳ በሆነና ዲንና ኢማኑ በሳሳ ቁጠር በሆነ ባልሆነው አፉን ይከፍታል፣ የመሰለውንና የመጣለትንም ሁሉ ያወራል።የምላስንና የንግግርን አደገኛነት ጠንቅቆ ያወቀ ሰው ግን አፉን ከመክፈቱና ምንም ነገር ከመናገሩ በፊት ልብና አዕምሮውን ተጠቅሞ በሚገባ ያስባል፣ ንግግሩ አላህን የሚያስደስት፣ ለሰው ልጆች የሚጠቅምና ፍትሃዊ ንግግር መሆኑን አረጋግጦ እንጂ አይናገርም።

🔅("በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካምን ይናገር፣ ካልሆነ ዝምምም ይበል") አርዓያችን ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ በሌላም ሐዲሣቸውም የሚከተለውን ብለዋል፣
(إِنَّ الْعَبْدَ لَيَتَكَلَّمُ بِالْكَلِمَةِ مَا يَتَبَيَّنُ فِيهَا يَنْزِلُ بِهَا فِي النَّارِ أَبْعَدَ مِمَّا بَيْنَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ")
"አንድ ሰው ያላረጋገጣትን/እርግጠኛ ያልሆነበትን አንዲትን (አላህን የምታስቆጣ) ቃል በመናገሩ ምክንያት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሚበልጥን ርቀት የጀሀነም እሳት ላይ ወደ ታች ይወርዳል/ይጣላል" ብለዋል።
📚ሐዲሡንም ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል።

▪️ሙስሊም ሆይ ኢማንህ እንዲስተካከል ከፈለግክ ቀድመህ ልብህን አስተካክል፣ አንድ ሰው ምላሱን እስካላስተካከለና እስካልተቆጣጠረ ድረስ ደግሞ መቼም ልቡ ሊስተካከል አይችልም።ልብ ሳይስተካከል ደግሞ መቼም ኢማን አይስተካከልም።

✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ  ሸይኽ ኣደም @ዛዱል መዓድ
17/6/1442ዓ.ሂ


https://t.me/+xBNi3Or3YoI4N2Y0


إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ ۖ وَإِن تَكُ حَسَنَةً يُضَاعِفْهَا وَيُؤْتِ مِن لَّدُنْهُ أَجْرًا عَظِيمًا

(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 40)
አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበድልም፡፡ መልካም ሥራ ብትኾንም ይደራርባታል፡፡ ከእርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል፡፡

فَكَيْفَ إِذَا جِئْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ بِشَهِيدٍ وَجِئْنَا بِكَ عَلَىٰ هَـٰؤُلَاءِ شَهِيدًا

(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 41)
ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን ባመጣን ጊዜ አንተንም በእነዚህ ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ (የከሓዲዎች ኹኔታ) እንዴት ይኾን

يَوْمَئِذٍ يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَعَصَوُا الرَّسُولَ لَوْ تُسَوَّىٰ بِهِمُ الْأَرْضُ وَلَا يَكْتُمُونَ اللَّهَ حَدِيثًا

(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 42)
በዚያ ቀን እነዚያ የካዱትና መልክተኛውን ያልታዘዙት በእነሱ ምድር ብትደፋባቸው ይመኛሉ፡፡ ከአላህም ወሬን አይደብቁም፡፡


https://t.me/+xBNi3Or3YoI4N2Y0


ክፉ ሸክም !

አላህ እንዲህ ይላል፥
"مَنْ أَعْرَضَ عَنْهُ فَإِنَّهُ يَحْمِلُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وِزْرًا' خَالِدِينَ فِيهِ ۖ وَسَاءَ لَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ حِمْلًا(100-101) " سورة طه.
"ዱኒያ ላይ ቁርኣንን ችላ ያለ (ያላመነበት እና ያልሰራበት) ሰው ኣኺራ ላይ ከባድ ቅጣትን የሚያስከትል ወንጀል ተሸክሞ አላህ ፊት ይቀርባል። ቅጣቱ ውስጥም ይዘወትራል፤ በዛ ቀን የሚሸከሙት ሸክም ከፋ!።" ጣሃ 100-101።

በዘመናችን ቁርኣንን ችላ እንድንል የሚያደርጉ ነገሮች በጣም በዝተዋልና ልባችንን ወደ ቁርኣን እናዙር፤ እንቅራው፣ እናድምጠው፣ ትርጉሙን እንወቅ፣ ህግጋቱን ህይወታችን ላይ እንተግብር። ይህን ካደረግን በዱኒያም በኣኺራም እንከብራለን።ካልሆነ ግን ቁርኣን እራሱ መስክሮብን አላህ ዘንድ መዋረዳችን አይቀርም።

✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም@ዛዱል መዓድ
ዙልሒጃ 21/1442ዓሂ

https://t.me/+xBNi3Or3YoI4N2Y0


በተግባር ከታላላቆች እንሁን!

ከታላላቅ ዑለማዎች ተምሬያለሁ ያለ በሙሉ የነሱን ትክክለኛ መንገድ ይከተላል፣ በዕውቀትም የነሱ ወራሽ ይሆናል ማለት አይደለም።
ይህማ ቢሆን ኖሮ እግር ጥሎት ቁጭ ብሎ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ መድረካቸው ላይ የታደመ በሙሉ የነሱ ተማሪ ነኝ ብሎ መናገር በቻለ ነበር!
ዋናው ቁም ነገር የታላላቆችን አካሄድ መሄዱ እንጂ ያላዋቂ ስራ እየሰሩ እራስን ወደ ታላላቆች ማስጠጋት አይደለም።
ለመማሩ እንኳ ኸዋሪጆችም ከሰሓባዎች ተምረው ነበረ!
ግን መልሰው ሰሓባዎችን አክፍረዋል-ገድለዋልም።
ልብ ላይ ጠብ የሚልና ከአላህ ጋር የሚኖርን ግንኙነት የሚያሳምር ዕውቀት አላህ ያድለን "ኣሚን"።

#@BedrAreb_1


ጀግናና አሸናፊ ማነው?

ታላቁ አሸናፊነት ስሜትን ማሸነፍ ነው።
የሽንፈት ሁሉ ሽንፈት ለጊዜያዊ ደስታ ብሎ የኣኺራን ደስታ የሚያሳጣ ወይም የሚቀንስ ነገር ማድረግ ነው።

ጀግና ማለት በሩጫ ወይም በትግል ሰዎችን ሁሉ የሚያሸንፍ ሳይሆን በሁሉም ነገርና ቦታዎች ላይ አላህን መፍራት ነው።



@BedrAreb_1


ያኔ በዳይና ተበዳይ..!

🔹የነቢዩላህ ዩሱፍ ዐለይሂስ'ሰላም ወንድሞች ዩሱፍን እራሳቸው አውቀው ጥልቅ ጉድጎድ ውስጥ ጥለውት ከሄዱ በኋላ  አባታቸው ጋ እያለቀሱ ቀርበው "ዩሱፍን ተኩላ በላው!" ብለዋል።
ችግር ደረሰብኝ ብሎ ያወራና ያለቀሰ ሁሉ እውነተኛ ነው ማለት አይደለም!

🔸ሙስሊም ሆይ  በምንም መልኩ እንደ ዩሱፍ ወንድሞች አታድርግ።
ከሰዎች የተሸሸገውንና አንተም ልትደብቀው የምትሞክረውን ሁሉ የዓለማቱ ጌታ... ሁሉን አዋቂው አላህ ያውቀዋልና!
ፍርድና ውሳኔውም የርሱ ነው! መመለሻችንም ወደርሱ ነው።
ያኔ በዳይም ተበዳይም... እውነተኛና ውሸታሙም በትክክል ይለያል።

🔹ሙስሊም ሆይ ወሬን ከአንድ ወገን ብቻ ሰምተህ ፍርድ አትስጥ... አቋም አትያዝ... ወንድምህን እህትህን በመጥፎ አትጠርጥር።
ይልቅ አላህ ቁርኣን ላይ ባዘዘው መሰረት (አጣራ/አረጋግጥ)

ዘመናችን ውሸት የበዛበትና ሐያእ የቀነሰበት ዘመን ነው።

ሳያጣራ ወሬን የተቀበለ (ሰውን እንደሚበድልና ባደረገውም ነገር ኋላ ላይ  ሊጸጸት እንደሚችል አላህ ነግሮናል።

ሱረቱል-ሑጁራትን አንብቡ!

✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
19/4/1441ዓ.ሂ@ዛዱል መዓድ
🔸🔹🔸🔹🔸🔹

@BedrAreb_1


📮የቁርኣን ምክር  7⃣

💥አላህ ቁርኣንን ሲገልጸው እንዲህ ብሏል፣ („ይህ መጽሐፍ ከአላህ ለመሆኑን ምንም ጥርጥር የለበትም እርሱም አላህን ለሚፈሩ መሪ ነው„) ሱረቱል-በቀራህ 2 ።

💥ቁርኣን ለሰው ልጆች በሙሉ የሁለቱንም ዓለም ህይወት የሚያስተካክልና ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመራ መጽሐፍ ነው።

💥ቁርኣን በመሰረቱ ምንም እንኳ ለመላው የሰው ልጅ መመሪያ ቢሆንም ሰበብ ያላደረሱና አላህን የማይፈሩ ግን ቁርኣን ሊመራቸውና ሊያስተካክላቸው አይችልም።
ለዚህም ነው፣ < َهُدى لِلْمُتَّقِيْن> ያለው።

💥ቁርኣንን እየቀራንና እየሰማን የማንገሰጸውና የማንለወጠውም ውስጣችን ላይ የአላህ ፍራቻ በመጥፋቱ ወይም በመቀነሱ ምክንያት ነው።
ልብ ላይ ትንሽም ቢሆን "ተቅዋ/የአላህ ፍራቻ" ካለ ቁርኣን ያሳድገዋል፣ አካላትም ለመልካም ስራ ይነሳሳሉ፣ ከወንጀልም ይታቀባሉ።
ልብ ሲደርቅና አላህን ሲረሳ ግን ቁርኣን መስማቱም ይሁን ማንበቡ ልሙጥ ድንጋይ ላይ ውኋ እንደ ማፍሰስና ብረትን በብረት እንደ መምታት ይሆናል።
💥ይህ በእንዲህ እንዳለ ቁርኣን የሚያስተካክለው የሰዎችን የኣኺራህ ህይወት ብቻ ሳይሆን በሚገባ ካጠናነውና ከተከተልነው የዱኒያ ህይወትንም ጭምር የሚያስተካክል መሪ መጽሐፍ ነው።

ቁርኣንን የቀራና የተረዳ ሰው ቤትኛውም ዘመንና ሀገር ቢኖር ኋላ ቀርና ሞኝ አይሆንም!።
ምክንያቱም አላህ- "አላህን ለሚፈሩ መሪ ነው" ሲል፤ መሪነቱን በምንም አልገደበውም።
ይህ ደግሞ "ቁርኣን ለሰው ልጆች በሚያስፈልጉ ነገሮች ላይ በሙሉ አማኞችን ወደ ትክክለኛው ጎዳና የሚመራና ለስኬት የሚያበቃ መሪ መሆኑን ነው የሚያሳየው"
ለዚህም ነው፣ "ልጅህን ቁራኣን አስተምረው ቁርኣን ደግሞ ሁሉንም ነገር ያስተምረዋል" የተባለው።

አለምስ ቢሆን የተቀየረችውና ህይወትን ያቀለሉ ግኝቶች የተገኙት ቁርኣን ከወረደ በኋላ አይደል?!
ከቁርኣን መውረዱና ከነቢዩ ሙሐመድ* መላክ በፊት ስልጣኔ የሚባል ነገር ነበረ?!
ብዙ የሳይንስ ምርምር ውጤቶችስ ቢሆን ቁርኣን ቀድሞ ገልጿቸው የለ?!

"ታዲያ ወዴት ትሄዳላችሁ?! ቁርኣን ለሁሉም የሰው ልጆች መገሰጫና መማሪያ እንጂ ሌላ አይደለም"

ወደ ቁርኣን እንመለስ!

@BedrAreb_1


📮የቁርኣን ምክር  6⃣

💥(„አፈሩ መልካምና ጥሩ የሆነ ሀገር ምርቱ በአላህ ፈቃድ ያማረ ሆኖ ይወጣል/ይበቅላል፤ መጥፎ መሬት ደግሞ ምርቱ ደካማና የማይጠቅም ይሆናል...„)
ከሱረቱል-አዕራፍ  አንቀጽ 58 የተወሰደ መልእክት።

💥ይህ የሙእሚንና የካፊር፣ ልቡ በኢማን የተስተካከለና ልቡ ያልተስተካከለ ሰው ምሳሌ ነው።

💥በቁርኣንና በዲን ህግጋት መጠቀም የሚችለው ቀድሞ ልቡን ያስተካከለና እውነትን ለመቀበል ልቡን ክፍት ያደረገ ሰው ነው።

ዝናብ ለምና ቀድሞ የተዘጋጀ/የታረሰ መሬት ላይ ካላረፈ በስተቀር እንደ ማይጠቅመው ሁሉ ለኢማንና መልካም ስራ እራሱን ላላዘጋጀ ሰው የቁርኣንና የሐዲሥ ምክሮች ምንም አይጠቅሙም።

💥ልሙጥና ደረቅ ድንጋይ ላይ የሚፈስ ዝናብ/ውኃ ወደ ውስጡ መግባት እንደ ማይችለው ሁሉ አላህን በማመጽና ኣኺራን በመርሳት ልቡ የደረቀ ሰውም የቁርኣን ምክሮች ወደ ልቡ አይዘልቁም።

ከቆሻሻዎችና ከስሜት የጠራ ንጹህ ልብ፤
ቁርኣንን መቅራትና ማድመጥ አይጠግብም፣ ከርሱ ውጪም ለታመመና ለተራበ ልቡ መድሐኒትና ምግብ  አይሻም።

ልባችንን ዘውትር እንፈትሸው፣ ከቆሸሸም በቁርኣን እናጽዳው!

ልብ ከተስተካከለ በትንሽ መልካም ስራ ጀነት መግባት ይቻላል።
ልብ ካልተስተካከለ ግን የስራ መብዛት ብዙም ዋጋ አይኖረውም።


ወደ ቁርኣን እንመለስ!

@BedrAreb_1


📮የቁርኣን ምክር 5⃣

[{የአላህን ብርሃን ማን ችሎ ያጠፋል?!}]

💥(„የአላህን ብርሃን/ ኢስላምን በአፎቻቸው/ በንግግራቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህ ደግሞ ከሃዲያን ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን/ዲኑን መሙላትን እንጂ ሌላን አይፈልግም። አጋሪዎች/ ከሃዲያን ቢጠሉም፣ አላህ ኢስላምን ከሃይማኖቶች ሁሉ የበላይ ያደርግ ዘንድ፤ መልዕክተኛውን "ሙሐመድን صلى الله عليه وسلم
ትክክለኛና ጠቃሚ እውቀት እና ትክክለኛ እምነትና ስራ ላይ የተመሰረተን ሃይማኖት/ኢስላምን አሲዞ ልኳቸዋል
„)
ከሱረቱ-አት'ተውባህ አንቀጽ 32እና 33የተወሰደ መልእክት።

💥ኢስላምን ለማጥፋትና የኢስላምን ነቢይ ለማጠልሽት የሚደረግ ሙከራ በሙሉ ትርፉ ድካምና እራስን መጉዳት ብቻና ብቻ ነው።

💥እነሱ ኢስላምን ለማጥፋት ይጥራሉ፣ አላህ ደግሞ ዲኑን ሙሉና የበላይ ማድረግ እንጂ ሌላን አይፈልግም አይፈቅድምም! አላህ አሸናፊና የሻውን ሰሪ ነው። ነገሮች በሙሉ በርሱ ቁጥጥር ስር ናቸው! ድከም ያለው ዝም ብሎ ይደክማል!። በከንቱ እየለፉ በአፍ ከመለፍለለፍና ከመቅጠፍ፣ በእጅም ከመሳልና ከመፃፍ የዘለለ ኢስላምና ነቢዩ ላይ የሚያደርሱት ምንም ዓይነት ጉዳት አይኖርም።
የጸሃይን ብርሃን ሙሉ በሙሉ መጋርድ ወይም ማስወገድ የሚችል ማንም እንደሌለው ሁሉ የኢስላምን ብርሃን ማጥፋት የሚችል አይኖርም!።


ሙእሚኖች ይህን አውቀው ይጽናኑ፣ ከሃዲያንም ተስፋ ይቁረጡ!

💥ከአንቀጹ እንደምንረዳው፣ ኢስላም የበላይ የሚሆነው "በትክክለኛና ጠቃሚ እውቀት፣ በመልካም ስራና ስነ-ምግባሮች ነውና እነዚህ ነገሮች ላይ እንበረታ"

ወደ ቁርኣን እንመለስ!

@BedrAreb_1


📮የቁርኣን ምክር 4⃣

💥(„ምድርን አላህ አስተካክሎና ለነዋሪዎች የምትመች፣ የሚያስፈልጋቸውንም ነገር በሙሉ የያዘች አድርጎ ከፈጠራት በኋላ በምትሰሩት ወንጀል ምክንያት አታበላሿት።
አላህንም በፍርሃትና በተስፋ መካከል ሆናችሁ ተገዙት/ለምኑት፣ የአላህ እዝነትና ችሮታ እምነትና ስራዎቻቸውን ከሚያሳምሩ ሰዎች ቅርብ ነው።„)

ከሱረቱል-አዕራፍ አንቀጽ 56የተወሰደ መልእክት

💥ወንጀል ምድርን፣ የሰዎችን ስነ-ምግባርና ስራ፣ ያበላሻል።
የብስም ይሁን ባህር ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች በሙሉ ምክንያታቸው የሰው ልጆች ወንጀልና ጥፋት እንደሆነና፣
💥ሰዎች ምድር ላይ ሲኖሩ በሁሉም ነገር አላህን ከፈሩ፤ ምድር እንደምታምር፣ የሰዎች ሲሳይ እንደሚሰፋ፣ ስራና ስነ-ምግባራቸውም እንደሚስተካከልና ዓለም ላይ ሰላም እንደሚሰፍን ቁርኣን ይነግረናል።


ወደ ቁርኣን እንመለስ!

@BedrAreb_1


📮የቁርኣን ምክር 3⃣

💥ሙእሚኖች ጀነት ሲገቡ፤ („...የጀነትን መንገድና ጀነት ለመግባትም ያበቃንን መልካም ስራ ለመስራት ለመራን ጌታችን አላህ ምስጋናና ውዳሴ ይገባው!
አላህ ባይመራን ኖሮ አንመራም ነበር፣ የጌታችን መልእክተኞችም እውነትን ይዘው ነበር ወደኛ የመጡት።„
ይላሉ! "ይህች ትሰሩት በነበረው መልካም ስራችሁ ምክንያት የታደላችኋት/ በምሪት የተሰጠቻችሁ ጀነት ናት" ይባላሉ።)
ከሱረቱል-አዕራፍ አንቀጽ 43 የተወሰደ መልእክት።

💥ጀነት የሚገባው -በአላህ ፍቃድ- በስራ እንደሆነና ለውዷ ጀነት ውድ ጊዜአችንን በመስጠት የተለያዩ መልካም ስራዎችን በብዛት መስራት እንዳለብንና በስራችን ከመደነቅ ታቅበን ለመልካም ስራዎች ሁሉ ያበቃንና የመራንን አላህን ማመስገን እንደሚገባን ቁርኣን ይመክረናል


💥የዱኒያ ባለስልጣን አንድን ሰው ቢወደው ወይም ቢያደንቀው ነገ ትቶት የሚሞትን ወይም የሚፈርስን ምድራዊ ቤት ነው የሚሰጠው!
አላህ ግን ባሪያውን ሲወደው መሞትና መሰደድ የሌለባትንና መቼም የማትፈርሰዋን ጀነት ነው የሚያድለው
!።

ذَٰلِكَ فَضْلُ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ.

نسأل الله من فضله!

@BedrAreb_1


📮የቁርኣን ምክር 2⃣

💥(„...ሰዎችን ሊያጠም ያለ እውቀት አላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጥፍ ሰው የበለጠ በዳይ ማን አለ?! አላህ በደለኛ ሰዎችን ቀናውን መንገድ አይመራቸውም።„)
ከሱረቱል-አንዓም አንቀጽ 144 የተወሰደ።

💥ውሸትን በራሱ እንድንጠነቀቅና ይበልጥ ደግሞ ያለ በቂና ትክክለኛ እውቀት ዲን ላይ በመናገር (ሐላል..ሐራም በማለት)  አላህና መልእክተኛው ላይ መዋሸትና መቅጠፍን እንድንርቅ ቁርኣን አጥብቆ ይመክረናል!

መመለስ አሻፈረኝ ብለን ያለ እውቀት እየተመራንና እየመራን ከቀጠልን ከራሳችን አልፎ ሰዎችንም መበደላችን አይቀርም።
አላህ ደግሞ በደለኛን በዱኒያ ወደ ሐቅ ጎዳና፣ በኣኺረህ ደግሞ ወደ ጀነት መንገድ አይመራውም!
ስለዚህ አላህ ቀናውን መንገድ እንዲመራንና እንዲያስተካክለን ቀድመን እኛ እሱ ከከለከለን ነገሮች መከልከል ይገባናል


💥ከበደልና አላህ ላይም ይሁን ሰዎች ላይ ከመዋሸት አላህ እራሱ ይጠብቀን!።

@BedrAreb_1


📮የቁርኣን ምክር 1⃣

💥(„...ከሰዎች ውስጥም ብዙዎች ያለ እውቀትና ማስረጃ በዝንባሌ፣ በስሜትና በግምት ብቻ ሰዎችን ያጠማሉ፤ ጌታህ ወሰን አላፊዎች እነማን እንደሆኑ ያውቃል። „)
ከአል-አንዓም አንቀጽ 119 የተወሰደ።

💥ወሰን ከማለፍም ይሁን፣ ከወሰን አላፊዎችና በግምትና በስሜት ከሚነዱ ሰዎች እንድንጠነቀቅ ቁርኣን ይመክረናል!


💥በስሜት ከመመራትና ጠሞ ከማጥመም አላህ ይጠብቀን

@BedrAreb_1


ስድብና መጥፎ ንግግር ያላዋቂ መሳሪያ ነው

ለጃሂል/አላዋቂ ለሆነ ሰው ትርፍ ንግግር መልስ መስጠት ጥንብን ደጋግሞ እንደመነካከት ነው።
ካላዋቂ ጋር መከራከርን መተው ልብና ሰውነትን ማሳረፍ ነው።
የማይጠቅም ወይም መሰረተ-ቢስና የሰውን ክብር የሚነካ ወሬ ለማውራት ምላስህ ከበላህ ነገ ቀብር ውስጥ ምላስህን ትል እንደሚበላው አስታውስ!፤ ይሄኔ ምላስህ አደብ ይዛል!
"የወራዶች መሳሪያ መጥፎ ንግግር ነው سلاح اللئام قبيح الكلام"
ተብሏልና ሁሌም ንግግራችንን እንለካ።
ሐዲሡም (ሙስሊም ማለት ከእጁና ከምላሱ ጣጣ ሙስሊሞች የዳኑ ሰው ነው)።... (በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካምን ንግግር ይናገር፤ ካልሆነ ዝም ይበል) ይላል።
@BedrAreb_1

16 last posts shown.

86

subscribers
Channel statistics