ተውሒድ እና ሽርክ
ክፍል አስራ አራት
የሽርክ ምሳሌዎች ፦
11.1. በውዴታ ማጋራት ውዴታ ከአምልኮ ክፍሎች ውስጥ ነው።አምለኮታዊ ውዴታ ለአላህ ብቻ ነው የሚገባው። ከአላህ ወጭ ያሉትን ለአላህ ስንል ነው የምንወዳቸው። ለምሳሌ መላኢካዎችን ጅብሪልን ይመስል፣ነብያትን፣ነብዩ ሙሐመድን ﷺ ይመስል፣ደጋጎችን አቡ - በክር፣ዑመር፣ዑስማን፣ዐልይ፣ሰሃባዎች እና የመሳሰሉትን አማኞች የምንወዳቸው ለአላህ ስንል ነው።
ከሰዎች ግን በውዴታ የሚያጋሩ አሉ።አላህ እንዲህ ይላል፦
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَندَادًۭا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ ٱللَّهِ ۖ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَشَدُّ حُبًّۭا لِّلَّهِ
ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡[አል-በቀራህ:165] እዚህ ጋር አንድ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር አለ ወዴታ ሁለት አይነት ነው።
✅
አምልኮታዊ ውዴታ፦ አምልኮታዊ ላይ አላህ ብቻ ነው ለዛቱ ሲባል ሊወደድ የሚገባው
✅
ተፈጥሯዊ ወዴታ ፦አላህ የሰው ልጅ ላይ ስሜትና ባህርይ አድርጎለታል። ሰለዚህ አንድ ወንድ ሚስቱን ቢወድ ሺርክ ሰራ አይባልም።አንድ ሚስት ባልዋን ብትወደው፣ቤተሰብ ልጁን ቢወድ፣ልጆች ወላጆቻቸውን ቢወዱ ሺርክ ሰሩ አይባልም።ምክንያቱም ይሄ ተፈጥሯዊ ህግ ነውና።
ለአላህ እና ለመልክተኛው ﷺ ያለንን ውዴታ የምንገልፀው እነሱ ያዘዙንን በመፈፀም ፣የከለከሉንን በመከልከል ነው።ሰለ ወዴታ ከተነሳ አይቀር ከሱና ጋር የተቆራኘውን የፈተና አንቀፅ እንያት።
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»[አል-ኢምራን
11.2. በመታዘዝ ማጋራት በመታዘዝ ማጋራት የሚለው ላይ መጠቆም የፈለኩት በብዛት ከጭፍን ተከታይነት የሚመጣውንና ሰዎች ሸይክ፣ዑለማ ወይንም አሚር ብለው የወሰዱትን አካል አላህ ሀራም ያደረገውን ሃላል ሲያደርግላቸው አሚን ብለው ይቀበሉታል። ከዛም አልፎ ይፈፅሙታል።ይሄ በአላህ ላይ ከማጋራት ውስጥ ነው። እስቲ የሚከተለውን ግልፅ መለኮታዊ ቃል በደምብ እንየው፦
ٱتَّخَذُوٓا۟ أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَٰنَهُمْ أَرْبَابًۭا مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَٱلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَمَ وَمَآ أُمِرُوٓا۟ إِلَّا لِيَعْبُدُوٓا۟ إِلَٰهًۭا وَٰحِدًۭا ۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَٰنَهُۥ عَمَّا يُشْرِكُونَ
ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡[አት-ተውባህ:31]
የተሰመረበትን በደንብ መመልከት ይሻል።የታዘዙትን አላህ ሃላል ያደረገውን ሃላል በማድረግ፣አላህ ሃራም ያደረገውን ሃራም በማድረግ፣ያለ ማጋራት አንድን አምላክ ሊገዙ ነው።እነርሱ ግን ይህን ትተው ከአላህ ውጭ ያሉትን ተገዙ።ይህ ትምህርት በደንብ እንዲገባን ታላቁ አስተማሪያችን ነብዩ ሙሐመድ
ﷺ ዘንድ ዐዲይ ኢብን ሃቲም የተባለ ሰሃባ መጥቶ እሳቸው ይህንን አንቀፅ ሲያነቡ“
እነሱ እኮ አያመልኳቸውም ” አላቸው። ነብዩም ﷺ “
አላህ ሐራም ያደረገውን ሐላል ሲያደርጉላቸው አላህ ሐላል ያደረገውን ሐራም ሲያደርጉባቸው ይቀበሉ የለምን? አሉ። እርሱም “
አዎን” አለ። እሳቸውም፦ “
ታድያ ይህ እኮ ነው እነሱን ማምለክ ማለት” አሉ። ስለዚህ ከዚህም ኡማ ይህን ተግባሮ የሚፈፅም ካለ ተመሳሳይ ጥፋት (ማጋራት) ላይ ወድቋል ማለት ነው።
እንግዲህ ነብዩ ﷺ የሺርክን አይነቶች አንድም ሳይቀር እንዲህ ፍንትውና ብትንትን አድርገው አስረድተዋል።
✍
ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
(ተውሒድ እና ሽርክ ገፅ 27-30)
“ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide