ፍኖተ ቅዱሳን ዘ ተዋህዶ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified



Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የህሊና ፀሎት_
በመምህር_ሳሙኤል_አስረስ አዳምጡ መልካም ቆይታ


✝ በስመ አብ ወ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

✝ ታላቅ መንፈሳዊ ንግስ ጉዞ✝
፦ ሰኔ 30 መጥምቀ መለኮት ቅዳስ ዮሐንስ በዓለ ልደቱ በደማቁ ይከበራል

✝✝ ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ✝✝

ጉዞ ስላዘጋጀን ምዝገባ ላይ ነን ሳይሞላ ይደውሉ ይመዝገቡ ትኬቱን ባሉበት እናቀርባለን

ለበለጠ መረጃ ፦ 0922-40-01-80/0967-11-8787

አዘጋጅ ፦ማህበረ ፍኖተ ቅዱሳን ዘ ተዋህዶ

♥ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡


Forward from: Teddy


Forward from: Teddy
ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፤ ድኽነትህም አይደለም። ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም፣ ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ እንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው።

አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
አምስቱ የንስሓ መንገዶች፥ ገጽ 9)


Forward from: Teddy
✍ "እውነተኛ ክርስቲያን አባቱ ክርስቶስን ይመስላል፤ ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፤ ይሰደባል እንጂ አይሳደብም፤ የጠፉትን ፍለጋ ይደክማል እንጂ ይባስ ብሎ አይገፈትርም፤ በወንድሙ ውድቀት ያለቅሳል እንጂ አይደሰትም፤ እንዲህ ካልሆነ ግን አባቱ ሌላ ነው፤ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና በጊዜውም ያለ ጊዜውም ሊሆን ይገባል፤ ባገኘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባጣንም ጊዜ፤ ባለጤና በሆንን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በታመምንም ጊዜ፤ ሲሳካልን ብቻ ሳይሆን ባልተሳካልንም ጊዜ ማመስገን መለማመድ አለብን፤ የምስጋናችን ምንጭ የሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን ስለ አምላካችን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፤ ይህን ማድረግ ስንለማመድ በክብር ላይ ክብር ይጨመርልናል፤ እንደ አባታችን ኢዮብ የዲያብሎስን አፍ እንዘጋለን፤ ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን? እንኪያስ በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፤ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፤ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፤ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፤ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፤ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው"

📌ምንጭ
✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


Forward from: Teddy
📌 ትሑትና ትዕግሥተኛ ሁን

❖ በምድረ ገጽ ላይ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት የነበረውን ነቢዩን ሙሴን ምሰል

✍️“ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ”
📖ዘኁ 12፥3

❖ ሁል ጊዜ መሐሪ እና ይቅር ባይ ለመሆን ሞክር ሐዋርያው

✍️ “ለማንም ስለ ክፉ ፋንታ ክፉን አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ... ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ ለቁጣ ፋንታ ስጡ እንጂ ...”  ብሏልና።
📖 ሮሜ 12፥17-19

❖ እንዲሁም ቁጣን ጊዜያዊ ስሜትን እና ንዴትን እንድናስወግድ
✍️“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ” በማለት ይጠይቀናል።
📖ሮሜ 12፥21

❖ በእርግጥ መታገስ የሚችል ሰው ዕድለኛ ሲሆን ይህንን የማይችል ግን ደካማ ነው፤ ለዚህ ነው ሐዋርያውም
✍️“እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል” ያለው።
📖ሮሜ 15፥1

❖ ሌሎች አንተ እንዳሰብካቸው ፍጹም የሚስማሙ እንዲሆኑ አትፈልግ ነገር ግን መሆን እንዳለባቸው ሳይሆን እንደሆኑት አድርገህ ተቀበላቸው ሁላችንም ተፈጥሮን እንደራሷ አድርገን ተቀብለናል፤ ወቅቶችን ዝናባማ፤ ማዕበላማም ይሁን ሞቃታማ ተፈጥሮ ራሱን እንዲለውጥ ሳንጠይቅ ተቀብለነዋል፤ ከሰዎችም ጋርም ልክ እንዲሁ እናድርግ።

❖ ሰዎች ሁሉ ጻድቅና መልካም አይደሉም፤ ብዙዎቹ ድክመቶች ወይም የተወሰኑት ባሕርያቸውን ተቆጣጣሪ የሆነ አመሎች አሉባቸው፤ ሰዎች የተለያዩ ዓይነቶች ናቸው፤ ከእነዚህ አንዳንዶች ሁከተኞች ናቸው፤ ስለዚህ በጠባያቸው ተጽዕኖ እንደማይደረግበት ተመልካች እንሁን፤ ባሕሪያቸውንም በጥበብ እንቀበላቸው።

📌 ምንጭ
✍️ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ


Forward from: ♪♫•*¨*•.¸¸hena21¸.•*¨*•♫♪


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown
አይተን ከተደነቅንበት ከእመጓ ቅዱስ ኡራኤል መዳረሻ እይታ  አንዱ የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፈረሱ የእግሩ ዱካ


Forward from: ዝክረ ቅዱሳን ዘወልደ ዋህድ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Forward from: "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
#ኹሉንም_ነገር_ለእግዚአብሔር_እንስጠው

ወርቅን የሚያነጥር ሰው አንዲትን የወርቅ ቅንጣት ወደ እሳት ውስጥ ጨምሮ እጅግ ንጹህ እስክትኾን ድረስ ይጠብቃታል፡፡ እግዚአብሔርም ልክ እንደዚሁ ሰዎች እስኪነጹ፣ እስኪለወጡና ባገኛቸው ነገር ጥቅም እስኪያገኙ ድረስ ፈተና ውስጥ እንዲቆዩ ይፈቅዳል፡፡ ይህ ደግሞ ከጥቅምም እጅግ ከፍ ያለ ጥቅም ነው፡፡

ስለዚህ ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም ተስፋ ሊቈርጥ አይገባውም፡፡ ያ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያኽል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኵሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንሔድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቈርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡

ይህን በማስመልከትም ጠቢቡ ሰው እንደዚህ ሲል መክሮናል፡- “ልጄ ሆይ! ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሔድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ፤ ልብህን አቅና፤ ኹልጊዜ ታገሥ፤ አታወላውልም፤ በመከራ ብትጨነቅም አትጠራጠር” /ሲራ.2፥1-2/፡፡ “ኹሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ስጠው፡፡” ለምን? እግዚአብሔር ከዚያ መከራ መቼ እኛን ማውጣት እንዳለበት ያውቃልና፡፡ ስለዚህ ኹሉንም ለእርሱ ልንሰጥ፣ ዘወትር እርሱን ልናመሰግን፣ ኹሉንም ነገር - ጥቅምም ይኹን ቅጣት - በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፤ ይህም ቢኾን ለእኛ ረብሕ የሚኾን ነውና፡፡ አንድ ሐኪም፥ ሐኪም የሚባለው ታካሚውን ገላዉን ሲያጥበውና ሲመግበው እንዲሁም ደስ ወደሚያሰኝ ስፍራ ሲወስደው ብቻ አይደለም፤ በእርሱ (በታማሚው) ሰውነት ላይ የቀዶ ጥገና ምላጭና ቢላ ሲያሳርፍም ጭምር ሐኪም ነው፡፡ አባትም አባት የሚባለው ልጁን ሲንከባከብ ብቻ አይደለም፤ የገዛ ልጁን ከቤት ሲያስወጣው፣ ሲገሥጸው፣ ሲገርፈውም ያው አባት ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔር ከሐኪሞችም በላይ ሰውን ወዳጅ እንደ ኾነ በማወቅ፥ ምን ዓይነት የሕክምና ዓይነት እንደሚሰጠን በጥልቀት አንጠይቅ፤ ወይም ደግሞ ለደረሰብን መከራ እርሱን ተጠያቂ አናድርግ፡፡ ከዚህ ይልቅ እርሱ የወደደውን ነገር - ቅጣትም ይኹን ቅጣት የሌለው ነገር - ብቻ ምንም ይኹን ምን በአኰቴት ልንቀበል ይገባናል፡፡ በየትኛውም መንገድም ቢኾን የእርሱ ፈቃድ እኛ እንድንድንና ከእርሱ ጋር አንድ እንድንኾን ነውና፡፡ የትኛው መንገድ ለእኛ እንደሚጠቅምም እርሱ ያውቋል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የትኛው መንገድ ወደ እርሱ እንደሚመልሰው ያውቃል፡፡ ኹላችንም እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ልንድን እንደምንችል ያውቃል፡፡ በመኾኑም የሚመራን በዚህ እኛ በምንድንበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ወደየትኛውም መንገድ ቢወስደንም - ልክ እንደ መጻጉዑ - እርሱ እንደሚያዘ’ን ተከትለን መሔድ እንጂ ትልቁ ጉዳያችን በለስላሳና በቀላል አልያም ደግሞ በከባድና በሸካራ ጎዳና እንድንሔድ የሚያዘ’ንን ትእዛዝ መኾን የለበትም (ልንሔድበት የሚገባ’ው መንገድ እርሱ ስለሚያውቀው እንዲሁ መታዘዝ እንጂ የመንገዱን ከባድነት ወይም ቀላልነት የእኛ አጀንዳ ሊኾን አይገባውም፡፡)

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ወደ_ኦሎምፒያስ_የተላኩ_መልእክታት መጽሐፍ
#በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ከተተረጎመው


Forward from: "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
🔮 ምክረ ቃል 🔮

🔅 አንድ ሰው በጾም ወራት በየዕለቱ ጥሩ ጥሩ ምግቦች እየበላና የሚናፍቀውን ምግብ ለሰውነቱ እየሰጠ የሥጋውን ፈቃድ እንዴት ሊቆጣጠር ይችላል? አይችልም። መንፈሳዊው ሰው የጾም ትክክለኛ ፍቺ ሥጋን በማዋረድ የምግብን ፋላጎት ድል ለማድረግ ካበቃ በኋላ ከቁሳዊው ዓለም በላይ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ያውቃል። በመሆኑም የጾም ምግቦችን መብላት ብቻ መሆን የለበትም እርሱ በሚጾምበት ጊዜ ግድ የሚለው መታቀብ ነው ። ይህም ማለት የሚመገበው ሙሉ ለሙሉ የጾም ምግብ ቢሆንም ሥጋው ሊያገኛቸው የሚናፍቃቸውን ነገሮች በሙሉ መከልከል ማለት ነው ።

🔅 ብዙ ሰዎች የሚጾሙት በልምድ ወይም በፊደል ስለሆነ ምንም የሚጠቀሙት ነገር የለም ። እነዚህ ሰዎች ጾምን መለኮታዊ ዓላማውን በመገንዘብ ስለማይጀምሩት ወደ ጾም መንፈሳዊነት ወይም ስለ ትእዛዙ መንፈሳዊነት ሊገቡ አይችሉም። በመሆኑም ሰውነታቸው ይጹም እንጂ መንፈሳቸው አይጾምም።
   ✨💧✨💧✨💧✨💧

  ✍  አቡነ ሸኖዳ


Forward from: "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
“#መንፈሳዊው_ገበሬ”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

“አንድ ገበሬ ዘር መዝራት ስላለበት ብቻ እንዲሁ አይዘራም፡፡ አስቀድሞ መሬቱን ማረስ፣ ማለስለስ አለበት፡፡ ካረሰ ካለሰለሰ በኋላ ዘሩን ይዘራዋል፡፡ አሁንም ግን መዝራቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የዘራውን ዘር አፈር ሊያለብሰው ይገባዋል፡፡ እንዲያ ካላደረገ ወፎች መጥተው ይለቅሙታልና፡፡

ልክ እንደዚሁ እኛ ክርስቲያኖችም በእኛ ላይ የተዘራውን ዘር (ቃለ እግዚአብሔር) በየጊዜው እንደ ገበሬው የማንከታተለው ከሆነ በአየር ላይ እንደተዘራ ዘር ይሆንብናል፡፡ ሰይጣን ይለቅምብናል፤ የራሳችን ስንፍና እንዲጠወልግ ያደርጓል፤ ፀሐይ ያደርቋል፤ ጐርፍ ይወስዷል፤ እሾክ አንቆ ይይዟል፡፡

ስለዚህ ዘር ዘርቶ ዞር ማለት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ በየጊዜው መኮትኮት፣ ወፎችን ማባረር፣ የበቀለ አረም ካለ ማረም፣ ጭንጫ የበዛበት አከባቢ ካለ የለሰለሰ አፈር መጨመር፣ በየጊዜው መከታተል፣ አጥር ማጠር፣ እንዲሁም ማንኛውም የተዘራውን እህል ሊያበላሹ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ምናልባት በሰብሉ እርሻ የገበሬው ትጋት ብቻ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መሬቱ ግዑዝ ነገር ስለሆነ፡፡

በመንፈሳዊው እርሻ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ኃላፊነቱ የገበሬው ማለትም የመምህሩ ብቻ አይደለም፡፡ ከግማሽ ወይም ከዚያ በላይ የደቀመዝሙሩ (የምእመኑ) ኃላፊነት ነው፡፡ በርግጥ መምህሩ ዘሩን መዝራት አለበት፡፡ ነገር ግን ደቀ መዝሙሩ የተነገረውን ቃል ሁል ጊዜ መስማት ብቻ ሳይሆን ማድረግም አለበት፤ በግብር ፍሬ ማፍራት አለበት፤ የበቀሉ አረሞች ካሉ በየጊዜው መንቀል አለበት፡፡…የገበሬ ልጆች በሰብሉ መካከል የበቀለ አረም ካለ እንዲሁ ጫፍ ጫፉን ብቻ አይቈርጡትም፡፡ ከሥር ይነቅሉትና በመጨረሻም በእሳት ያቃጥሉታል እንጂ፡፡ በእኛ ላይ የበቀሉ አረሞችም (ጥርጥሮች፣ ክሕደቶች፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ማነቆ የሆኑብንን ነገሮች…) ከሥራቸው ነቅለን ልናቃጥላቸው ይገባናል።


Forward from: "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
በዓለ መንፈስ ቅዱስ / ጰራቅሊጦስ

ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡

ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡

በዚያም ዕለት  በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡” በማለት አስተማራቸው፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡

በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!


Forward from: "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
✝✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

+"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+

=>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::

+ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው::

+መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::

+ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)

+ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-

1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::

+ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::

+ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::

+ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::

+በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::

+በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::

+ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::

+በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::

+እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::

=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::

=>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ)
3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)

>


Forward from: "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፤ ድኽነትህም አይደለም። ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም፣ ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ እንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው።

አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
አምስቱ የንስሓ መንገዶች፥ ገጽ 9)


Forward from: መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
መልካም ዜና

መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከእስር ተፈተዋል።


ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተይዘው በአዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ በእስር ላይ የነበሩት መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከእስር መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን አሳውቀዋል።


Forward from: ፍኖተ ቅዱሳን ዘ ተዋህዶ
በስመ አብ ወ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ክርስቶስ ተንሥሐ እሙታን -----?
አሰሮ ለሰይጣን ---------------- ?
ሰላም -------------------------------?
ኮነ -----------------------------------?

በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን

ከ ማህበረ ፍኖተ ቅዱሳን ዘ ተዋህዶ ማህበር
የፊታችን 28 ቅዱስ አማኑኤል ነድያን መመገቢያ ትኬት እንሸጣለን ለበረከት ብላቹ የወሰዳቹ ትኬቱ ቢያልቅም ባያልቅም አስረክቡን
የመጨረሻው ቀን ግንቦት 24/25/ መሆኑን እናሳውቃለን

፦ አልባሳት ያላቹ እንድታቀብሉን እንጠይቃለን የነፍስ ዋጋ ያርግልን

2, የበረከት ሥራ ፀጋ ያላቹ የፊታችን
ቅዳሜና እሁድ ፀጉር መቁረጥና
ገላ ማጠብ ሰኞ ነድያንን መመገብ አለን

3, የበረከት ሥራ ፀጋ ያላቹ የፊታችን
* አርብ /ቅዳሜ /እሁድ
የበረከት ሥራ አለን ደውሉልን

4, በማንኛውም የበረከት ሥራ መሳተፍ የምትፈልጉ ደውሉልን
*በገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ
*በአስቤዛ
*በጉልበት
* በማስተባበር

0922400180/0967118787

በ በረከቱ ሥራ ለ አጥያት መደምሰሻ ለዳቢሎስ ድል መንሻ ለመንግስቱ መውረሻ ያድርግልን አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡


Forward from: "ልጆቼ የቤተክርስቲያንን ነገር አደራ"
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡

እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቆጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሐኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡

ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት (ልንቀበላት)ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ



20 last posts shown.

185

subscribers
Channel statistics