إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ
➪➩➪➩➪➩➪➩➪➧
✅ አስፈሪ እና በጣም ከባድ ትኩረትን የሚፈልጉ መስጠንቀቂያ እና ገለፃዎች
☜ 《 يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمْ وَاخْشَوْا يَوْمًا لَا يَجْزِي وَالِدٌ عَنْ وَلَدِهِ وَلا مَوْلُودٌ هُوَ جَازٍ عَنْ وَالِدِهِ شَيْئًا إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ فَلا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا وَلا يَغُرَّنَّكُمْ بِاللَّهِ الْغَرُورُ》
➲ እናንተ ሰዎች ሆይ ! ጌታችሁን ፍሩ ቀንንም ፍሩ ወላጅ ለልጁ የመይመነዳበትን ልጅም ለዋላጅ ምንም አይነት ምንዳ ከፋይ የማይሆንበትን ቀን የኣሏህም ቃል ክዳን ሀቅ ነውና ቅርብቷ ህይወት እንዳታታላችሁ በጌታችሁም ላይ የተታለለው ሸይጧን እንዳያታላችሁ!
☞አላሁ አክበር ፦ የአሏህ ባሮች ሆይ እናስተውል ዋላጆች ለልጃቸው ዱንያ ላይ የሚከፍሉት ዋጋ ይታወቃል ግን በጉዱ ቀን ነገሩ እንዳልተጠበቀ ከባድ ስለሆነ እናት ልጆቿን አታስብም ፣አባት ልጆቹን አይል ፣ ወንድም ወንድም እህቱን አያስብ፣ ባል ባለቤቱን አይጠቅም ባለ ቤት ባሏን አትል ወዳጅ ዘመድ ባአጠቃላይ ነገሩ ከበዶት ሁሉንም ነገር በመተው ለእራሱ ለነፍሱ የሚጨነቅበት ቀንን ነው አሏሁ ተዓላ እየስገነዘበን ያለው።
የአሏህም መልእክተኛ ሠለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት ነገሩን ገልፀውልናል ፦
☜ "أكثِروا ذِكْرَ هادمِ اللذات"
➭ደስታን ሁሉ ደርማሽ የሆነውን ሞትን መስታወሱን አብዙ።
➧የአላህ ባሮች ሆይ ይህ የጌታችን አና የነቢያችን ምክር ነው
⇒ ምናልባት እጃችን ላይ ያለውን ሰዓት አና ቀለበት አኛ ለብሰነው የሚያወልቀው ወራሻችን ሊሆን ይችላል።
➞ምናልባት የመኪናህን በር በእጅህ ዘግተሀው አዛው ሞተህ በሩን የሚከፍተው ግን ቲራፊቅ ሊሆን ይችላል።
⇨ ምናልባትም ቀሚስህን ለብሰህ ዚፑን አና ቁልፉን አንተው አድርገህ ሊሆን ይችላል የሚከፍተው ግን ጀናዛህን ለማጠብ የመጣው አጣቢ ይሆናል።
➧ቤታችን ክላሳችን ፎቃችን ውስጥ በመሆን በእንቅልፍ ምክንያት አይናችን ዘግተነው ሊሆን ይችላል በጣም ይገርማል የምንከፍተው ግን ቀብራችን ውስጥ ሆነን ከማለእኮች ፊት ይሆናል።
➭የአላህ በሮች እዛ ጋር ዝምድናው ይጠፋል የለም!
☜ فلا أنساب بينهم ولا يتسائلون
☞የነበረን የማቆላጫ ስማችን ይቀራል በመጀመሪያ ከኛ የሚቀረው የሚወድቀው ስመሰችን ነው ።
☜ فيقولون أين ⪻الجثة⪼أين الجنازة أين الميت ...؟!
⇨እሬሳው የትነው? ጀናዛው የት ሆነ ?ሟቹ የት አለ? ይባላል። ሶላትን በላያችን መስገድ ሲፈልጉ ጀናዘውን አምጡት ይሰገድበት ይባላል ልብ እንበል የኔ የንተ የንቺ ስም ነው የቀራው ያ የምንቆላመጥበት ስም ነው የተቀየረው!ወገኔ⪼ ስንቀበር መይቱን አምጡት ሲባል አልሰማህም እኛን ነው የጠበቀው ምንድንነው እየቀበርን መሳቅ እየቀበርን በቅለድ መሳለቅ ወደየት እየሄድን ነው ወገኖቼ?
➧ስለሀብትህስ ምንድነው ምታሰበው አንተን ሸኝተው እንደተመለሱ ወራሾች የምትወዳቸው የምትጠላቸው የሚያቀርቡኽ የሚያርቁኽ ኣንድ በኣንድ ይከፋፈሉታል። ልብ በል ወደድክም ጠላህ ያን ለታ የኔ የንተ መብት አይደለም ከእጃችን ወጥቶ ወደ ሌላ ተሸጋግሮዋል!
➣ወገኔ ባንተ ለቅሶ ሰዎች ተሰብስበው ምንድነው ያሚያደርጉት ?ለምን ማስተዋል ተሳነን?
☜ يشربون القهوة والشاي ويأكلون القات الشجرة الأثيمة ويتحدثون عن غلاء الأسعار ويغتابون الناس ويأكلون لحومهم !! ثم يمضي كل منهم لشغله!
➻ ቡና ሻይ ይጠጣሉ የወንጀል ሁሉ እናት የሆነቿዋን የጫት ዛፍ ይበላሉ ስለ ኑሮ ውድነት ይነጋገራሉ ሰዎችን ያማሉ ስጋቸውን ቁጭ ብለው ይበላሉ በቃ አለቀ ሁሉም ለስራው ይበተናል አየህ ያንተ ለቀረሶ ለሸር ድግስ ሆኖዋል። አንተን በዱዓቸው የምተያስታውሱት ባጣም አናሳ ናቸው።
↩️ فيا أحبتي في الله فلنبادر بالتوبة قبل أن تغادر فكلنا جنائز مؤجلة !
➭ዱንያን ከመልቀቅ በስተፊት በተውበት እንቸኩል ሁላችንም የቀጠሮ ጀናዘ ነንና ።
┈┈┈┈•◈◉✹❒❁❒✹◉◈•┈┈┈
📝 በኡስታዝ አቡ አብዱረህማን አብዱልቃድር ሐሰን ሃፊዘሁሏህ
-------------------------------------
https://t.me/abuabdurahmenhttps://t.me/abuabdurahmen➭
https://t.me/AbuYehyaAselefy/7267