ሙስሊሞችን ያለአግባብ በከሃዲነት መወረፍ ከሚያስከትላቸው መዘዞች ሁለቱን እነሆ!
* አንደኛ፦👇
የአንድን ሙስሊም ክብር ያለ አግባብ ማጉደፍ ጉዳዩን የተመለከቱ ሸሪዓዊ ትዕዛዛትን መጣስ ከመሆኑ ባሻገር ለከፋ ቅጣትም ያጋልጣል።عن ابن عمر، عن النبي -صلى الله عليه وسلم- أنه قال: «...مَنْ قَالَ فِي مُؤْمِنٍ مَا لَيْسَ فِيهِ، أَسْكَنَهُ اللَّهُ رَدْغَةَ الْخَبَالِ حَتَّى يَخْرُجَ مِمَّا قَالَ».
=
ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ዘገባ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦«በአንድ አማኝ ላይ የሌለበትን የተናገረ ከንግግሩ ጣጣ እስኪወጣ ድረስ አላህ የ“ጥፋት ማጥ” ውስጥ ያኖረዋል!»
[
አሕመድ (ቁጥር፡ 5385)፣ አቡ ዳዉድ (ቁ. 3597) እና ሌሎችም የዘገቡት ትክክለኛ ሐዲሥ ነው፤ “ሲልሲለቱ’ል-አሓዲሥ አስ-ሰሒሓህ” (ቁ. 437) ይመልከቱ።]
በሌላ አጋጣሚ ሰሓቦች «የ“ጥፋት ማጥ” (رَدْغَة الْخَبَالِ) ምንድነው?» ብለው ሲጠይቁ ነብያችንም «የእሳት ነዋሪዎች እዥ!» ብለው መልሰዋል።
[ኢብኑ ማጃህ (ቁ.3377)]
- «ሙስሊምን መሳደብ አመፅ ነው!» የሚለው የነብያችን ንግግር [
አል-ቡኻሪይ (ቁ. 46)፣ ሙስሊም (ቁ. 64)] ማንኛውንም አግባብ-የለሽ ስድብ የተመለከተ ከሆነ ጭራሽ እምነት ላይ የሚያነጣጥር ዘለፋ ደግሞ ከዚህ የከፋ መዘዝ እንደሚጎትት ግልፅ ነው።
☞ ሸይኹ'ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ-ያህ እንዲህ ይላሉ፦فإذا كان من يقضي بين الناس في الأموال والدماء والأعراض إذا لم يكن عالما عادلا كان في النار؛ فكيف بمن يحكم في الملل والأديان وأصول الإيمان والمعارف الإلهية والمعالم الكلية بلا علم ولا عدل..
«በንብረት፣ በነፍስና በክብረ ስብእና ጉዳዮች ላይ በሰዎች መሃል የሚዳኝ ሰው አዋቂና ፍትኸኛ ካልሆነ የእሳት የሚሆን ከሆነ ስለ እምነት መንገዶች፣ ስለ ሀይማኖቶች፣ ስለ እምነት መሰረቶች፣ ስለ መለኮታዊ የእውቀት ዘርፎችና አጠቃላይ እሴቶች ያለ እውቀትና ያለ ፍትህ የሚፈርድስ እንዴት ይሆናል?!» [
"አል-ጀዋቡ አስ-ሶሒሕ.." (1/108)]ይህንን የሚያጠናክረው ሁለተኛው ነጥብ ነው፦
* ሁለተኛ:-👇
አንድ ሙስሊምን ያለ አግባብ “ከሃዲ፣ የአላህ ጠላት፣ ሙናፊቅ..” ብሎ መጥራት እምነትን ለአደጋ የሚያጋልጥ አደገኛ ጠንቅ ነው።عن ابْنَ عُمَرَ، قَالَ رَسُولُ اللهِ -صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ-: « أَيُّمَا امْرِئٍ قَالَ لِأَخِيهِ: يَا كَافِرُ، فَقَدْ بَاءَ بِهَا أَحَدُهُمَا، إِنْ كَانَ كَمَا قَالَ، وَإِلَّا رَجَعَتْ عَلَيْهِ
= ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ዘገባ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦«ወንድሙን “አንተ ከሃዲ” ያለ ማንኛውም ግለሰብ = ከሁለቱ አንዳቸው ይህን ተሸክሞ ይመለሳል፤ እርሱ እንዳለው ካልሆነ በስተቀር (ፍርዱ ወይም መዘዙ) ወደ ራሱ ይመለሳል!»
[አል-ቡኻሪይ (ቁ.6104)፣ ሙስሊም (ቁ. 60)]
-
አቡ ዘር ባስተላለፉት ሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ፦«..وَمَنْ دَعَا رَجُلًا بِالْكُفْرِ، أَوْ قَالَ: عَدُوُّ اللهِ وَلَيْسَ كَذَلِكَ إِلَّا حَارَ عَلَيْهِ»
= «..አንድን ሰው በከሃዲነት የፈረጀ ወይም “አንተ የአላህ ጠላት!” ብሎ የጠራው እርሱ እንዳለው ካልሆነ (ፍርዱ ወይም መዘዙ) ወደራሱ መመለሱ አይቀርም!» ብለዋል።
[
አል-ቡኻሪይ (ቁ.6045)፣ ሙስሊም (ቁ. 61)]- ሣቢት ኢብኑ አድ-ዶሕ-ሓክ በሚያስተላልፉት ሐዲሥ ደግሞ፦
«... وَمَنْ رَمَى مُؤْمِنًا بِكُفْرٍ فَهُوَ كَقَتْلِهِ»
= «አንድን አማኝ በከሃዲነት የወነጀለ እርሱን እንደ ገደለው ነው!» ብለዋል።
[አል-ቡኻሪይ (ቁ.6105)]
ቻናል:-https://t.me/ibnuyasir11