ከራድዮን🕊🕊


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


╱◥██████◣
│∩│🌄▤│▤▤│
-✅እንኳን ደህና መጡ
ከራድዮን — የጥበብ ድምፅ!
​በልጅ ስሉጥ እና በሌሎች ገጣሚዎች የሚቀርቡ፡
👉​ልብ የሚነኩ ትረካዎች
👉​የማይረሱ ግጥሞች
👉​የሕይወት ፍልስፍናዎች
👉 የውሎ ገጠመኞች
​ይቀላቀሉን፣ በጥበብ ይርኩ!
​
​የብዕር ጠብታ የሀሳብ ጋሪ
ከራድዮን ነው የጥበብ አዝማሪ
ኑ አብረን እንደግ

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
በህይወት እስካለን እንጠያየቅ🤲🤗


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።


— የማርቆስ ወንጌል 11:24

Amharic Bible Bot


እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።


— መጽሐፈ ምሳሌ 19:23

Amharic Bible Bot


Forward from: 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
ክፍል አስራ ሁለት
ፍቅር ወይንስ እምነት
#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

"ምን?!"
ብለን በአንድ ድምፅ ጮህን።
አብሱ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳች።
"ታዲያ ማን ነሽ?"
ሴትየዋ እንባዋን እየጠረገች...
"እኔ.....እ

         ከብዙ ዓመታት በፊት የአባታችሁ ''ሚስት'' ነበርኩ።

  የሴትየዋ ቃል ከተሰማ በኋላ ለጥቂት ሰከንዶች ማንም አልተናገረም።
አብሱ በድንጋጤ ቆማ...
"ይሄ እንዴት ይሆናል?" አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ።
"እናቴ ብቻ ናት የአባቴ ሚስት ብዬ የማውቀው።"
ሴትየዋ ለመነጋገር እራስዋን እያዘጋጀች

"እናታችሁን ከማግባቱ በፊት ... እኔና አባታችሁ ለአጭር ጊዜ ተጋብተን ነበር። ከዚያ ግን ተለያየን።"

እህቷ... ወዲያው ጠየቀቻት...
"ታዲያ ለምን እስከ ዛሬ ዝም አልሽ?"

ሴትየዋ አንገቷን ደፋች።
"ምክንያቱም ይህህ  ደብዳቤ ።"

ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረ።
አብሱም በጥሞና ታዳምጣት ነበር።
"ምን ማለትሽ ነው?" አለች
ያቺ አረፍተ ነገር እንደ መብረቅ በቤቱ ውስጥ ወደቀ።

አብሱ በድንጋጤ ከቆመችበት ወደ ኋላ አፈገፈገች።
"ምን አልሽ?" አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ።
ሴትየዋ እንባዋን እየጠረገች ዝም ብላ...
"እውነት ነው... ከብዙ ዓመታት በፊት እኔና አባታችሁ—"
"ዝም በይ!"
እህቷ በንዴት ጮኸችባት።
"አንድ ደቂቃ ! ቀብር ላይ መጥተሽ የአባታችን እህት ነኝ አልሽ፤ አሁን ደግሞ ሚስቱ ነበርኩ ትያለሽ! ቀጥሎ ምን ልትይ ነው?"

ሴትየዋ... ለመናገር ሞከረች።
..."እባክሽ አዳምጪኝ..."
እህቷ..."አላዳምጥሽም!"
አለች በቁጣ።
አብሱም... በሀዘንና በድንጋጤ መካከል ተወጥራ...
"እንዴት እናምንሻለን?" አለች።
"እስከ ዛሬ የት ነበርሽ? አባቴ ሲታመም? ሲቸገር? እኛ ስናድግ?"
ሴትየዋ አንገቷን ደፋች።
"እኔም ስቃይ ነበረብኝ..."
እህቷ.."እኛስ?"   አለች እህቷ በቁጣ              እየተንቀጠቀጠች።

"እኛ ስንቸገር የት ነበርሽ? አሁን ደግሞ ከሞተ በኋላ...  ?"
ክፍሉ በውጥረት ተሞላ።
እኔ... ጣልቃ ልግባ አልፈለኩም፤ ነገር ግን ሁኔታው እየከፋ ነበር።
ሴትየዋ... እንባዋን አፈሰሰች።
"እውነቱን ለመናገር መጥቻለሁ ብቻ..."
"አይ!"
በንዴት በሩን አመለከተች።
"እኛ አሁን እውነትም ሆነ ውሸት መስማት አንፈልግም። ከቤታችን ውጪ!"
"እባክሽ—"
"ከቤታችን ውጪ አልኩሽ!"
አለች በጩኸት።

አብሱ... ምንም ባትናገርም ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው ነበር።
ሴትየዋ... አብሱን ተመለከተች።
"ልጄ..."
ብላ ስትናገር አብሱ ወዲያው ፊቷን አዞረች።

ያኔ ሴትየዋ ምንም ሳትናገር ፖስታውን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች።
"አንድ ቀን እውነቱን ማወቅ ከፈለጋችሁ... በውስጡ ሁሉም ነገር ተጽፎበታል።"
ብላ በዝግታ ወደ በሩ አመራች።

እህቷ በቁጣ ቆማ እያየቻት ነበር።
ሴትየዋ ደጃፉ ላይ ደርሳ ለመጨረሻ ጊዜ ዞር ብላ አብሱን ተመለከተች።
"ይቅርታ..."
ብቻ አለቻት ።

ከዚያም ወጥታ ሄደች።
በሩ እንደተዘጋ ክፍሉ በከባድ ፀጥታ ተዋጠ።
አብሱ ዝም ብላ ፖስታውን ትመለከት ነበር

እህቷ ግን አሁንም በቁጣ እየተንፈረፈረች ነበር።
እኔ ደግሞ ጠረጴዛው ላይ የተተወውን ፖስታ እያየሁ ነበር።
ምክንያቱም ያ ፖስታ...
የሁላችንንም ሕይወት የሚቀይር ሚስጥር የያዘ መስሎ ተሰምቶኛል...
 
       .........ይቀጥላል.........


           @Rufaylen13 💫
                       ✍️ ህላዌ💕


የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን።


— መዝሙረ ዳዊት 28:6

Amharic Bible Bot




ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።

— ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:19




Forward from: ⛧‌⁠⁠⁠⁠⁠⁠⁠⁠⁠⁠⁠ ከቀን የተቀዳ 🌎🌛
የዋልንበት ቦታ ሁሉ ያለን እየመሠላቸው ፤ ስንቶች በዋልንበት ፈረጁን………

                 📚ዙበይዳ


Have a nice day fam🙌

https://t.me/love_words_qutes


በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤


— ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10

Amharic Bible Bot




የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።


— ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:11

Amharic Bible Bot




ትጉና ጸልዩ👈
እንዳይሆን ፀልዩ ስደቱ በሰንበት
እንዲምረን ጌታ እኛን ባለንበት

ትንቢቱ ሲፈጸም በአይናችን እያየን
የአምላካችንን ቃል ማመን እያቃተን
ከመፀለይ ይልቅ ጦርነትን መረጥን

መንግስት በመንግስት እያየን ሲነሳ

ወንድም ለወንድሙ መሳሪያ ሲያነሳ

በቅዱሳን ፀሎት እንዳለን አንርሳ

እኛ ካልፀለይን ማረን ማረን እያልን
ብዙ ነገር አለ በእኛ ላይ የሚሆን

አእምሯችን ቢመስል የክፋት ተራራ
ልባችንም ቢሆን የሀጢያት ጎተራ
ትልቅ አባት አለን ለኛ የሚራራ



by @senay_kal12


https://t.me/Kenako_12


ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።


— ሰቆቃው ኤርምያስ 3:22-23

Amharic Bible Bot


Forward from: 🕯️የህላዌ ብዕር✍️
ክፍል አስር
ፍቅር ወይንስ እምነት

#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

ነገር ግን እሷን ለመውቀስ አልቻልኩም።

ምክንያቱም እሷ የልቤን ሚስጥር አታውቅም ነበር።

    እህቷ ከኔ ተለይታ ከሄደች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ በሆስፒታሉ አደባባይ ውስጥ እየተዘዋወርኩ ቆየሁ። አዕምሮዬ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን እያሰበ ነበር።

"እብሱ ወንድሜ ነው ያለችኝ..."
ያቺ አንዲት አረፍተ ነገር አሁንም በጆሮዬ ውስጥ እያስተጋባች ነበር።

አብሱ ለእኔ ያላትን ስሜት ባላውቅም፣ ቢያንስ እኔ ያለኝን ስሜት ለእሷ እንኳን እንዳልገለጽኩላት ሳስብ ራሴን ወቀስኩ።

ቀስ ብዬ አብሱ ወደ ተኛችበት ክፍል ገባሁ... ተኝታለች
  አልጋው ጫፍ ካለው ወንበር ላይ ተቀምጬ አይን አይኗን መመልከት ጀመርኩ እንዴት ግን እንደምታምር አላህ አዳልቶባታል...

በተቀመጥኩበት ስለሷ ሳስብ ስልኬ ጠራ አብዱ ነው ድምፁን አጥፍቼ ስለነበር ስልኬ አልቀሰቀሳትም

ቀስ ብዬ ስልኩን ይዤ ወጣሁ
ከበሩ ራቅ ብዬ ከአንድ ጥግ ቆሜ አነሳና...
አብዱ...አሰላም አለይኩም እንዴት ነህ ግን...በናፍቆት ድምፅ
እኔ...ደህና ነኝ አልሃምዱሊላህ
አብዱ...ባለፎ የሮጥክበት ጉዳይ ከምን ደረሰ... አንተማ በአላህ ብዙ ነገር ደብቀኸኛል
እኔ...አንድም ጥያቄውን ለማለፍ...አንድም የኔን እንዲመልስ ብዬ...መስጊድ ምን ተባለ ሌላ ነገር ስለኔ... ምንም አልነገሩህም
አብዱ...ሁኔታዬ ገብቶታል... እሱን እኮ ነው ምልህ ምን ላይ ነህ ኡስታዝ አሊን አናግርያቸው...አላህን የሚያስቆጣ ተግባር እንደፈፀምክ ነገረኝ
እኔ...ምን ስለምን...ሰለ አብሱ መሆን አለበት.(በውስጤ)
አብዱ...ምንነቱን እንኳ አልነገረኝም ጓደኛህ አይደል እየዋሸህለት ነው አሉኝ
እስኪ ንገረኝ...
እኔ...ስመጣ ሁሉን ነግርሀለሁ...
ከጀርባዬ በቅርብ ርቀት ስጠራ ዞርኩ ሀኪሙ ነበር...
እኔ...አብዱ በቃ ሲመቸኝ እደውላለሁ
አብዱ...ኢብሮ እንዳዘጋው መች ጨረስን እየተቆጣ
ኢብራሂም በአላህ ንገረኝ...
....ዘጋሁበት....

በፍጥነት ወደ ሀኪሙ ሄድኩ...

ከሰዓታት በኋላ ዶክተሩ አብሱ ከሆስፒታል መውጣት እንደምትችል ነገረኝ
   በሆስፒታሉ ያሉብንን ብር ከፋፍለን ወጣን...ድጋሚ ቀጠሮ ሰጡን
አብሱንም ምግብ ፈሳሽ በደንብ መውሰድ እንዳለባት መከራት...

ከአብሱ ጋ አብረን ወደ መኪናው አመራን።
መንገዱን በሙሉ አብሱ ዝም ብላ ነበር።
ከአልፎ አልፎ የምትጠርገው እንባ ብቻ የውስጧን ስቃይ ይገልጥ ነበር።

አብሱ ከሆስፒታል ከወጣች በኋላ ቀጣዮቹ ቀናት እንደ ህልም አለፉ።

የአባቷ ቀብር፣ የሀዘን ተጋሪዎች መምጣትና መሄድ፣ የቤቱ ጭንቀት... ሁሉም ነገር ተደበላልቆ ነበር።

...እኔም ከእነሱ ጎን ለመሆን የምችለውን ሁሉ አደርግ ነበር።ነገር ግን ከቀብሩ በላይ የሚያስጨንቀኝ አንድ ነገር ነበር።

"የአብሱ እህት"

ከሆስፒታሉ ጀምሮ የምታየኝ አይኗ የተለየ ነው።ልቤ ውስጥ የደበቅኩትን ሁሉ እንደምታውቅ ይሰማኛል።

አንዳንድ ጊዜ አብሱን ስመለከት እሷ ወደ እኔ እያየች ትይዘኝ ነበር።ያኔ ደግሞ ልቤ በፍጥነት ይመታል።

"ዛሬ ነገረቻት ይሆን?"
"ወይስ ገና አልነገረቻትም?"
የሚለው ሀሳብ አልተወኝም እያሰቃየኝ ነው።

ከቀብሩ ማግስት በኋላ ቤታቸው የሚመጡት ሰዎች እየተቀነሱ መጡ።

የሆነ ቀን ግን አብሱ፣ እህቷ እና እኔ ብቻችንን በሳሎኑ ተቀምጠን ሳለን
የውጭው በር በሀይል ተንኳኳ።

            .........ይቀጥላል.........


                  ✍️ ህላዌ💕


እንዲህ ነው የሰው ምክር ... 🔥🩵
ፍቅር አያስቀጥል ፍቅርን አያስኖር🥺

https://t.me/love_words_qutes




በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።


— የዮሐንስ ወንጌል 3:15-16

Amharic Bible Bot


Forward from: 📚ትንሽ እንወቅ📚
አንድ ታካሚ ከባድ የሆነ የወገብ አደጋ ደርሶበት ዶክተር ጋር በጠዋቱ
ይመጣል:-
ዶ/ር:- "ወገብህ እንዲህ እስኪሆን ድረስ ምን ገጥሞህ ነው?"
ታካሚ:- "ይሄወልህ ዶክተርዬ ስራዬ ሌሊት ነው ታዲያ ዛሬ ጠዋት ኮንዶሚኒዬም ቤታችን ስገባ መኝታቤት ከሚስቴ ጋር የሆነ ሰው ሲያንኮሻኩሽ ሰማሁኝ: መኝታ ቤቱን ከፍቼ ዘው ብዬ ስገባ ሚስቴ ብቻ ነው ያለችው።
🚢🚢🚢
የቤቱ ሁኔታ ግን የሆነ ሰው እንደነበረ ያስታውቃል: ከመኝታ ቤት ወጣሁና
በረንዳው ላይ ሆኜ ወደታች ስመለከት የሆነ ሰው ሱሪውን እየታጠቀ ሲሮጥ
አየሁኝ... ዶክተርዬ በጣም ተናድጄ ስለነበር ጉልበቱን ከየት እንዳገኘሁ ሣላውቅ ሳሎን ያለውን ፍሪጅ አንስቼ ወረወርኩበት... ያንን ከባድ ፍሪጅ ሳነሳ ነበር ታዲያ ወገቤን ያመመኝ"
ዶክተሩ ይሄን ታካሚ ካከመ በሁዋላ ሌላ ታካሚ መኪና የተገጨ በሚመስል
ሁኔታ ሰውነቱ ቆሳስሎ ይገባል:-
ዶ/ር:- ምንድነው የመጀመሪያው ታካሚዬ ሲገርመኝ ያንተ ደግሞ ባሰ! ምን
ሆነህ ነው?
🚢🚢🚢
ታካሚ 2:- "ይሄውልህ ዶክተር ዛሬ አዲሱን ስራዬን የምጀምርበት ቀን ነበር
ድንገት አርፍጄ ተነሳሁኝና ከቤቴ ስወጣ ሱሪዬን እየለባበስኩኝ እየሮጥኩ እያለ
ከየት መጣ ያላልኩት ፍሪጅ ላዬ ላይ ወደቀብኝ!"
ዶክተሩ ይሄንንም አክሞ ከሸኘ በሁዋላ ሌላ ታካሚ ይገባል:-
ይሄኛው ታካሚ ደግሞ ከሁለቱ በባሰ እና በሚዘገንን ሁኔታ ቆሳስሎ ነበር
የገባው:-
ዶ/ር:- ኧረ ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው!? አንተ ደግም ምን ሆነህ ነው?
ታካሚ 3:- "ዶክተር ለምን? እንዴት? ማን? ብለህ እንዳትጠይቀኝ: ዛሬ ጠዋት
ፍሪጅ ውስጥ ገብቼ እያለ ከፎቅ ላይ ተከስክሼ ነው!
😶

20 last posts shown.

367

subscribers
Channel statistics