🕯️የህላዌ ብዕር✍️


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


😋መፃፍ ውስጤ ነው…🤗
🕯️ስሜትን በቅኔ፣ ልብን በቃል እተርካለሁ።✍️
❤️ ለፍቅር
🤍 ለይቅርታ
🕊️ ለሐዘን
🎂 ለልደት
⛪ መንፈሳዊም…
✨ ርዕስ ስጡኝ፤
ቃላትን አበባ አድርጌ እሸልማችኋለሁ 🌸
“የልባችሁን ጥልቅ ቃል በብዕር አበራዋለሁ፣
ያልተነገረ ስሜት በግጥም እናገራለሁ…” ✍️🖤
@Rufaylen13 💫

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በህይወት እስካለን እንጠያየቅ🤲🤗


አጭር  ወግ
         
        ከልጅነት ትዝታ....(ፈጣኑ🏃‍♂️)

ዛሬ እለተ ቅዳሜ የነ ማሙሽ(ማሜ) የሰፈር ጓደኞቹ ያወጡለት ስያሜ ነው እናቱም ከነሱ ለምዳ አልፎ አልፎ ትጠራዋለች....ዛሬ የነሱ ቤት ቡና የሚያፈሉበት ተራቸው ነው...
  
  ገና ጨለማ ሙሉ ለሙሉ ለብርሃን እጁን ሳይሰጥ እትዬ አበቡ እሳቱን ለማቀጣጠል ከእንጨቱ ጋ ትግል ጀምራለች

ማሙሽን ላለመቀስቀስ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ከነበረው እንጨት ነው የወሰደቹ ማታ ዘንቦ ነው መሰል እንጨቱ ረጠብ ይላል...

     ኡፍ... ኡፍፍ...ብልጭ እያለ እሳቱ ጥፍት ይላል እንጨቱም ትንሽ እርጥበት ስላለው አስቸግሯታል በመጨረሻ ግን ማሙሽን ቀሰቀሰቹ ማሙሼ ልጄ ማሜ ጭንቅላቱን በቀስታ እየነቀነቀች...

በሶስተኛው ጥሪ እ ወይ ነጋ እንዴ? አይኖቹን ለመግለጥ በእጆቹ እያሸሻ... አው ነግቷል ቶሎ ተነስና ከእዛ እ ከብቶቹ ቤት ደረቅ እንጨት ሰብስበህ ይዘህልኝ ና አልያያዝ አለኝ

  እ እሺ  ቶሎ በል! ሰምቶኛል ብላ እትዬ አበቡ ወደ ማጀት ቤት ገብታ እቃ ማስተካከል ጀመረች

   ማሜ ግን መልሶ እንቅልፍ ወሰደው እትዬ አበቡ መልሳ ስትመጣ  ማሜን ስታየው አንተ ማሜ አልተነሳህም በጩኸት ስትናገረው

   ቶሎ ብሎ ብንን.. የለበሳትን ፎጣ ብድግ አርጎ ዘለል ብሎ ያቺን  አሮጌ ሸበጥ በእግሩ አጥልቆ ወደ ከብቶቹ በረት በሩጫ ሄደ...

    ከከብቶቹ ውስጥ ጥቁር እና ነጭ ላሚትዋን በጣም ስለሚወዳት ጭንቅላቷን ካሻሸ በኋላ... እንጨቱን ለቅሞ የሚችለውን ያህል ይዞ ወደ እናት ወዳለችበት ቤት ሄደ...እትዬ አበቡ ቤቱን በጭራሮ መሰል ነገር  በተሰራ እጅ መጥረጊያ እየጠረጉ ነበር

   ማሜን ሲያዩት ከእጁ ለመቀበል ወደሱ ሄዳ የተወሰነውን ተቀብላ መሬት እያረገች ኸረ ማሜ ይህህ ብቻማ ያንሳል... እሺ አመጣለሁ ብሎ ተመለሰ አሁንም በፍጥነት ጨምሮ ይዞ መጣ

   ይኸው አመጣሁ ጎበዝ የኔ ልጅ እዚህ ጋ አስቀምጠው እሺ ምን ላግዝሽ የእንጨቱ ጭስ የእናቱን አይን ሲያስለቅስ እያየ...

   እናት ቶሎ በል ከብቶቹን ጋጣው ቦታ አድርሳቸው  ና ና ቶሎ ቡና ትጠራልኛለህ...

      እሺ ብሎ ማሜ ከብቶቹን ከማደርያቸው እያወጣ ለምለሙ ቦታ ላይ ጓደኛው እንዲያይለት ነግሮት ወደ ቤት ተመለሰ...

    እናት ቶሎ በመምጣቱ ደስስ እያላት ጎሽ የኔ ልጅ እንካ ይቺን አየገመጥክ(ሽልጦ) ቡና ጥራልኝ ና ቶሎ ቶሎ ሀክ ቱ ይቺ ምራቄ ሳደርቅ...

ማሜ ሁለት ጉርሻ ከጎረሰ በኋላ ውሀ ጠጥቶ  የተቀረውን ሽልጦ እየጎረሰ እነማንን ልጥራ እማይ...

እናት...እነ አካሉ...እነ ሽፈራው...እናት አው አዎ ቶሎ በልና ና ደሞ ማንንም እንዳረሳ
  ከነ አማሩ ቤት ጀምሮ ጠራቸው
ኑ እማዬ ቡና ጠጡ ብላለች...

... እሺ ብሎ የእናቱን ቃል ለማክበር ተመልሶ ወደ እናቱ በሩጫ ተመለሰ እያለከለከ  መጣሁ እናም ብሎ አየሮጥኩ ወደ እናቴ ጋ ስገባ ከተወሰኑ ሴቶች ቀድመው ከተገኙት ጋ እያወራች ነበር ማሜን ስታይ በወሬ መሃል እንዳይገባ ጥቂት እየተኮሳተረች በቃ ጎሽ የኔ ልጅ ይኽው ምራቄ ሳይደርቅ መጣህ የደረቀውን መሬት እያሳየችኝ መጣህ ቶሎ በል

... ከብቶቹ ጋ ሂድ እሺ ብዬ በፍጥነት አጠገቧ ካለው ቆሎ ወስጄ እየቆረጠምኩ ወጣሁ...ማሜ ከጣራው ላይ በካልሲ የሰራውን  ኳሱን በመሬት ላይ እየጠለዘ በሩጫ ወጣ...



#ቀጣይ ክፍል የለውም ደግማችሁ አንብቡ 😄(ማሜ ይንገራቹ እየሮጣችሁ ድረሱበት)

  @Rufaylen13 💫
                       ✍️ ህላዌ💕




ክፍል አስራ ሁለት
ፍቅር ወይንስ እምነት
#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

"ምን?!"
ብለን በአንድ ድምፅ ጮህን።
አብሱ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳች።
"ታዲያ ማን ነሽ?"
ሴትየዋ እንባዋን እየጠረገች...
"እኔ.....እ

         ከብዙ ዓመታት በፊት የአባታችሁ ''ሚስት'' ነበርኩ።

  የሴትየዋ ቃል ከተሰማ በኋላ ለጥቂት ሰከንዶች ማንም አልተናገረም።
አብሱ በድንጋጤ ቆማ...
"ይሄ እንዴት ይሆናል?" አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ።
"እናቴ ብቻ ናት የአባቴ ሚስት ብዬ የማውቀው።"
ሴትየዋ ለመነጋገር እራስዋን እያዘጋጀች

"እናታችሁን ከማግባቱ በፊት ... እኔና አባታችሁ ለአጭር ጊዜ ተጋብተን ነበር። ከዚያ ግን ተለያየን።"

እህቷ... ወዲያው ጠየቀቻት...
"ታዲያ ለምን እስከ ዛሬ ዝም አልሽ?"

ሴትየዋ አንገቷን ደፋች።
"ምክንያቱም ይህህ  ደብዳቤ ።"

ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረ።
አብሱም በጥሞና ታዳምጣት ነበር።
"ምን ማለትሽ ነው?" አለች
ያቺ አረፍተ ነገር እንደ መብረቅ በቤቱ ውስጥ ወደቀ።

አብሱ በድንጋጤ ከቆመችበት ወደ ኋላ አፈገፈገች።
"ምን አልሽ?" አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ።
ሴትየዋ እንባዋን እየጠረገች ዝም ብላ...
"እውነት ነው... ከብዙ ዓመታት በፊት እኔና አባታችሁ—"
"ዝም በይ!"
እህቷ በንዴት ጮኸችባት።
"አንድ ደቂቃ ! ቀብር ላይ መጥተሽ የአባታችን እህት ነኝ አልሽ፤ አሁን ደግሞ ሚስቱ ነበርኩ ትያለሽ! ቀጥሎ ምን ልትይ ነው?"

ሴትየዋ... ለመናገር ሞከረች።
..."እባክሽ አዳምጪኝ..."
እህቷ..."አላዳምጥሽም!"
አለች በቁጣ።
አብሱም... በሀዘንና በድንጋጤ መካከል ተወጥራ...
"እንዴት እናምንሻለን?" አለች።
"እስከ ዛሬ የት ነበርሽ? አባቴ ሲታመም? ሲቸገር? እኛ ስናድግ?"
ሴትየዋ አንገቷን ደፋች።
"እኔም ስቃይ ነበረብኝ..."
እህቷ.."እኛስ?"   አለች እህቷ በቁጣ      እየተንቀጠቀጠች።

"እኛ ስንቸገር የት ነበርሽ? አሁን ደግሞ ከሞተ በኋላ...  ?"
ክፍሉ በውጥረት ተሞላ።
እኔ... ጣልቃ ልግባ አልፈለኩም፤ ነገር ግን ሁኔታው እየከፋ ነበር።
ሴትየዋ... እንባዋን አፈሰሰች።
"እውነቱን ለመናገር መጥቻለሁ ብቻ..."
"አይ!"
በንዴት በሩን አመለከተች።
"እኛ አሁን እውነትም ሆነ ውሸት መስማት አንፈልግም። ከቤታችን ውጪ!"
"እባክሽ—"
"ከቤታችን ውጪ አልኩሽ!"
አለች በጩኸት።

አብሱ... ምንም ባትናገርም ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው ነበር።
ሴትየዋ... አብሱን ተመለከተች።
"ልጄ..."
ብላ ስትናገር አብሱ ወዲያው ፊቷን አዞረች።

ያኔ ሴትየዋ ምንም ሳትናገር ፖስታውን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች።
"አንድ ቀን እውነቱን ማወቅ ከፈለጋችሁ... በውስጡ ሁሉም ነገር ተጽፎበታል።"
ብላ በዝግታ ወደ በሩ አመራች።

እህቷ በቁጣ ቆማ እያየቻት ነበር።
ሴትየዋ ደጃፉ ላይ ደርሳ ለመጨረሻ ጊዜ ዞር ብላ አብሱን ተመለከተች።
"ይቅርታ..."
ብቻ አለቻት ።

ከዚያም ወጥታ ሄደች።
በሩ እንደተዘጋ ክፍሉ በከባድ ፀጥታ ተዋጠ።
አብሱ ዝም ብላ ፖስታውን ትመለከት ነበር

እህቷ ግን አሁንም በቁጣ እየተንፈረፈረች ነበር።
እኔ ደግሞ ጠረጴዛው ላይ የተተወውን ፖስታ እያየሁ ነበር።
ምክንያቱም ያ ፖስታ...
የሁላችንንም ሕይወት የሚቀይር ሚስጥር የያዘ መስሎ ተሰምቶኛል...
 
       .........ይቀጥላል.........


           @Rufaylen13 💫
                       ✍️ ህላዌ💕




Forward from: ማር እስከ ጧፍ🙊😘🥰😜🙉
ተነጋግረን አናውቅም ብቻ ንፍቅ ስትለኝ ዘወር ዘወር ብዬ አይኖቿን ቃኝቼ እመለሳለሁ ትኩረቷ ሙሉ ስራ ብቻ ነው እኔም ደሞ እፈራታለሁ😠 ያለች ልጅ ናት

አይገባትም እንደማልወዳት ታስባለች ላናግራት ስሞክር እንደ ሀውልት ደርቃ መልስ ራሱ ሰጥታኝ አታውቅም አልፈለገችም ይሆናል ብዬ ዝም እላለሁ

ደስታዋን ነው የምፈልገው ትውደደኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም ግን ታምናላችሁ ሁለታችንም ባለ ትዳር ነን ግን የውሸት ነው በቃ አለ ለማለት

ከተወለድኩ እለት ጀምሮ ከሷ ውጪ ያፈቀርኩት ሰው የለም ግን አብረን መሆን አልቻልንም ለምን ለሚለው መልስ የለኝም

የሚገርመኝ እኮ ከሁሉ በላይ ዛሬም ሳያት እንደ አዲስ ልቤ መምታቱ ነው ሁሌ ትናፍቀኛለች ራሴን ራሱ በሷ ልክ እንደምወደው እጠራጠራለሁ


አንድ ቀን ነው እንግዲህ ለስሙ ማግባቴን ነግሬያችኋለሁ ሚስት ተብዬዋ እኮ ለኔ ቦታ አላት ግን ደሞ

አውቃለሁ ብል አዲስ ህይወት
ተስኖኛል ምላሽ መስጠት
ምንም ሳይኖር ያጣሁባት
አልቻልኩም እንዳንቺ እኔ ልሆንላት

በነገራችሁ ላይ ወንድሜ ይሄ ነገር ፍቅር ብቻ አይደለም ብሎ ያልወሰደኝ ፀበል የለም ፍቅር እንደ መንፈስ ጮኾ የሚወጣ ነገር አልሆን አለ እንጂ

ብቻ ለብዙ ጊዜ ትመኝ የነበረውን ነገር ልንገራችሁ ፊልም የመስራት እድል ማግኘት እናም አንድ ቀን እድል አገኘች አላመነችም እና ቀይ ፊቷ በርበሬ መስሎ ነው ስራ የመጣችው

ደስታዋን አፍናዋለች ብቻ ያ ፊልም አልቆ ሲወጣ ግን ደስታዋን ማፈን ከባድ ሆነባት ተፍለቀለቀች ከብዙ ጊዜ ቡሀላ ሳቋን ማየት ብርቅ ነበረ የሆነብኝ

እኔ የማቃት ፍቅሬ ሳቂታ ብትሆንም ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ኮስታራ ሆና ነበረ

ኡፋ ሳቅ ለካስ ያሳሳል!!!
የኔ ጨረቃ ጨለማዬን ሁሉኮ በሳቋ አፈካችው

አንድ አባዜ አለባት ደስ ሲላት የምታረገውን አታውቅም እንጃ ብቻ ያስቀባጥራታል ዛሬም እንደዛ ሆናለች ሰው ሚስጥር የሚያወጣው ሲጠጣ ነዋ እሷ ግን ስትደሰት ነው


መጣች እላችኋለሁ እየሳቀች ስትቀርበኝ ሳቋ ደስታን ከመጫር ዘሎ ልቤ መጨነቅ ጀመረ ምን ጭንቀት ብቻ ጭራሽ ወደ ሰውነቴ ደም መሄዱ የቆመ ይመስል በቃ ሰውነቴ stack ቢያረግስ


"ስማማ በናትህ እየው ፊልሙን በማርያም እይ ጎበዝ ነኛ ነፍሴ ምነው አየክ ካራቴኮ ለመድኩ"


ነገሩን አበላሸችው ድሮ ነበረ ነፍሴ የምትለኝ እና ነፍሴ ስትለኝ ድሮም በቃ ሌላ ነገር ነው የሚያረገኝ ፀጥ አልኳት

"ነፍሴ ምነው አትፈልግም እንዴ ኡፍፍ እሺ አንተ ካልወደድከው ማን ሊወደው ነው ለምን አታየውም አስጠልቼሀለሁ እንዴ"

አላልኩም በቃ እሷ ደስ ሲላት በኖርማል ጊዜ የምትደብቀውን ስሜት ሳይቀር መዘርገፍ ነው ከዛ ልጅ ደስታዋን ጨርሳ ያወራችውን ስታስታውስ በሀፍረት ቆማ ራሱ አትሄድም

"የምትወዳትን ተዋናይ ለመምሰል ነበረኮ እንደሷ መሆን አልችልም አይደል እኔን አታደንቀኝም ማለት ነው"

ከአይኖቿ እንባ ጠብ ጠብ ሲል ሳይ የመጀመሪያዬ ነው ምክንያቱም እሷ ብትሞት ሰው ፊት አታለቅስም ነበረ

እንባ ይማርካል??? እስኪ ንገሩኝ እንባ ያሳሳል???

አሁን የሚያሳስበኝ ፊልም አለመሆኑ ቢገባት ኖሮ እንደናፈቀቺኝ ቢገባት ኖሮ አሁንም ለመናገር አልደፈርኩም አንገቴን አቀረቀርኩ ከዚ በላይ እሷን እያየሁ ራሴን መቆጣጠር አልችልም


"ፊልም የሰራሁት እኮ አንተ የምትወዳትን የምታደንቃትን ተዋናይ ለመሆን ነበረ"

ትታኝ ለመሄድ ስትነሳ ግን አልቻልኩም ምን ላርግ እንዲ እያለቺኝ ዝምታዬን መቀጠል በረዶ ውስጥ ከመታሸግ በላይ ያንዘፈዝፋል

ተጣድፌ ሳምኳት ስንት ሰአት ብስማት ነው ቆይ በረዶ ያጠላበት ልቤ የሚሞቀው ልክ ደንግጣ ፊቷን ስታዞር ብርዱ ጀመረኝ


"ነፍሴ ልክ አልሰራንም እኔ ነኝ ጥፋተኛ ሲጀምር ደስ እንዳለኝ እያወቅኩ መምጣት አልነበረብኝም ስላሳሳትኩት ይቅርታ"

"አትሂጂ"

ፊቷን እንዳዞረች "ለምን"


ተጠግቼ ከኋላ አቀፍኳት "ናፍቀሺኛል በናትሽ ዛሬን ብቻ ከኔ ጋር ሁኚ ዛሬን ብቻ ልለምንሽ"

"ነፍሴ" ድምጿ ደክሟል ግን እኔም ደክሞኛል እሷ የሌለችበት ህይወት ደክሞኛል አቅሜ ዝሏል ይዣት ወጣሁ ወደ ቤቴ ነውኮ ሚስቴ ቤት መኖሯን አውቃለሁ

ግን ከንፈሯ አስክሮኛል በሰአቱ እንኳን ሚስቴ እናቴ ፊት ራሱ እስማት ነበረ ቤት ስገባ ሚስቴ ሽክ ብላ ለብሳለች ያለ ወትሮዋ የሆነ ወረቀት ከፊቴ ወርውራ በተሰበረ ድምፅ

"እኔ ልብህን እንጂ አካልህን አልፈልግም ደስተኛ ሁነህ ኑርልኝ" ብላኝ ሄደች አይሰማም ትርጉም አልባ ቃላቶች ነበረ አሁን ሊሰማኝ የሚችለው የፍቅሬ ድምፅ ብቻ ነው


እንደ ህፃን ደረቷን ተደግፌ ከወገቧ አጥብቄ አቅፌያት ተቀመጥኩ ፍላጎቴ እሱ አልነበረም ግን ደሞ ፍቅሬን በስሜት ማርከስ ሆነብኝ ስለሳምኳት ሲከፋት አይቻለሁ

እንዴት ብዬ ሌላ ነገር ላስብ የሆነ ነገር መጥቶ ይነጥቅሀል የተባልኩ መሰለኝ ለካ እንዲ ናፍቃኛለች ተጣድፌ "በናትሽ አግቢኝ እኔኮ አፈቅርሻለሁ"

መልስ የለም ዝምታዋን እፈራዋለሁ
"ንገሪኝ ባል ስላለሽ ነው ትወጂዋለሽ እኔን ከምትወጂኝ በላይ ትወጂዋለሽ"

"ከባሌጋ እኮ በፊልሙ ምክንያት ተጣልተናል"

"ማለት ለምን"

"ላንተ ብዬ እንደምሰራው ሲያውቅ ዘላለም የማልለወጥ ነፍሴ ነፍሴ ምን ገገማ መሆኔን ነገሮ ትቶኝ ሄደ"

አሁን ካልተጋባችሁ ምድር ትጠፋለች የተባልኩ ይመስል ቃላት ላይ ቃል እየደራረብኩ ዘባረቅኩ ግን የአንዳንዱን ቃላት ትርጉም አላውቀውም.......


https://t.me/haniyen1621
🥱🥱🥱🥱🥱 በቃ እንቅልፌ መጣ


ክፍል አስራ አንድ
ፍቅር ወይንስ እምነት
#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

የውጭው በር በሀይል ተንኳኳ።
የበሩ ድምፅ በቤቱ ውስጥ የነበረውን ፀጥታ ሰብሮ አለፈ። እኔ፣ አብሱ እና እህቷ በአንድ ጊዜ ወደ በሩ ዞር ብለን ተመለከትን።

እህቷ ቀስ ብላ ተነሳች።
"በዚህ ሰዓት ማን ይሆን?" ብላ እያጉረመረመች ወደ በሩ ሄደች።
በሩን እንደከፈተች ግን በድንጋጤ ወደ ኋላ አፈገፈገች።

"እንዴት መጣሽ አለቻት?!"  በመደነቅ።
እኔም ተነስቼ ወደ ደጃፉ ተመለከትኩ።

የቆመችው ሴት በቀብሩ ቀን የተመለከትናት ሰው ነበረች። ራሷን "የአባታችሁ እህት ነኝ" ብላ ያስተዋወቀችው ሴት ናት።

    (.... ስለሷ ባለፎ አልነገርኳቹም አይደል አብሱ ልክ ከሀኪም ቤት እነደገባች ከአክስትየዋ ጋ ከብዙ ሰአት ጭቅጭቅ በኋላ ባይስማሙም አብሱ የአባቷ ቀብር ከተፈፀመ በኋላ ሶስት ቀን ቆይታ ተጣልተው ከቤት ወጣች እንደውም የሆነ ስልክ ተደውሎላት በምክንያት ከሄደች በኋላጨዛሬ ድጋሚ ስትመጣ ነው...) ያው የተጣሉበትን ጉዳይ በግልፅ ባላቅም ከዚህ ጊዜ በኋላ  ለምን ሲሞት ጠብቀሽ መጣሽ በሚል ነው...

...አብሱ እንዳየቻት ፊቷ ተቀየረ።
አብሱ..."አሁንስ ምን ፈልገሽ መጣሽ?" አለቻት በቁጣ የተሞላ ድምፅ።
አክስትየዋ ግን የአብሱን ቁጣ እንዳልሰማ ዝም እቤቱ ውስጥ ሰተት ብላ ሶፋው ላይ ተቀመጠች። ዓይኖቿ ቀይ ሆነው ይታዩ ነበር።

አክስትየው..."ይቅርታ... መምጣት አልፈለኩም ነበር። ግን የግድ መምጣት ነበረብኝ።"
አለች በተሰበረ ድምፅ።

እህቷ እጆቿን አጣጥፋ፣
   ..."ምን ማለት ነው?" ብላ ጠየቀቻት።
አክስትየዋ...ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ አሮጌ ፖስታ አወጣችና።
"ይህን ከመሞቱ በፊት አባታችሁ ተሰጥቶኝ ነበር።"
አለች።
አብሱ ፖስታውን እያየች ቀረች።
አብሱ..."ከአባቴ?"
አክስት..."አዎ።"
አብሱ..."ለምን እስከ አሁን ደበቅሽው?"
አክስት... ትንፋሽ አወጣች።
"ምክንያቱም የነገረኝ ጊዜው ሲደርስ ብቻ እንድሰጣችሁ ነበር።"

ክፍሉ በድንገት ፀጥ አለ።
አብሱ በሚንቀጠቀጡ እጆች ፖስታውን ከፈተችው...
ውስጡ የታጠፈ ወረቀት እና አሮጌ ፎቶግራፍ ነበር።
ፎቶውን እንዳየች ዓይኖቿ ተከፈቱ።
"ይሄ... አባዬ ነው!"
አለች በድንጋጤ።
እህቷም ፎቶውን ተመለከተች።
ነገር ግን ከአባታቸው አጠገብ የቆሙትን ሁለት ልጆች አላወቀቻቸውም።
"እነዚህ እነማን ናቸው?" አለች በፍጥነት።

ሴትየዋ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለች።
ከዚያም የሚከብዳትን ነገር ልታወጣ እንደምትሞክር አወኩ።

"እውነቱን ለመናገር ከባድ ነው..."
አለች።
"ግን ከእንግዲህ መደበቅ አልችልም።"
እኔም ሆንኩ አብሱና እህቷ በጥሞና እየተመለከትናት ነበር።

"እኔ የአባታችሁ እህት አይደለሁም..."
አለች ቀስ ብላ።
የተናገረችው ቃል እንደ መብረቅ በቤቱ ውስጥ ወደቀ።

"ምን?!"
ብለን በአንድ ድምፅ ጮህን።
አብሱ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳች።
"ታዲያ ማን ነሽ?"
አክስትየዋ እንባዋን እየጠረገች...
"እኔ.....እ

.........ይቀጥላል.........


@Rufaylen13 💫
                       ✍️ ህላዌ💕






Forward from: ❄snow girl❄
አሁን ለስምምነት አንድ እጃችሁን ስጡን።"ብሎ ሁለቱንም እጆቹን ዘረጋላቸው።ሜሪም ለመጨረሻ ጊዜ ልጇን ዘወር ብላ አየችው።ልጇ የጠቆረው አይኑ እና ቆጃው ወደድሮው እየተመለሰለት መሆኑን እና የከሳው ሰውነቱ መወፈር መጀመሩን አይታ የጠንቋዩን ግራ እጅ ግርማ ደግሞ የጠንቋዩን እጅ ያዙት።ወድያው ክፍሉ በብዙ ብርሀን እና በከባድ ንፋስ ተሞላ።ብርሀኑ እና ነፋሱ ልጁን እና የግርማን አባት ወደራሳቸው መለሳቸው እና መንቃት ጀመሩ።የጠንቋዩ ግማሽ ጎን ወደ ሜሪ ግማሹ ጎን ደግሞ ወደ ግርማ ገባ።ወድያው የነበረው ነፋስ እና ብርሀን ጠፋ።ክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሜሪ ግርማ የግርማ አባት እና ልጁ ብቻ ነበሩ፤ጠንቋዩ አልነበረም።አራቱም እርስ በእርስ ተያዩ፤ሁሉም ደህና መሆናቸው ገርሟቸው ነበር።ትንሽ እንደቆየ ሜሪ የበላችውን ምግብ ማስታወክ ጀመረች።ሰውነቷ ውስጥ ያለው ምግብ ሲያልቅ ደም መትፋት ጀመረች።ሁሉም ደንግጠው ይመለከቷት ነበር።ያ የሚያምረው ዘንፋላ ጥቁር ፀጉር አጥሮ እና ልስላሴው ጠፍቶ ተንጨበረረ።የቆዳ ቀለሟ ወደ ነጭነት ተቀየረ።አይኗ ስር ያለው ቆዳዋ፣ከንፈሯ እና ጥፍሮቿ ወደ ጥቁር ቀለም ተቀየሩ።ቆዳዋ ተሸበሸበ እና ድምጿም ተቀየረ።ከተንበረከከችበት ተነሳች እና አፏን በእጇ እየጠራረገች ከቤት ለመውጣት መራመድ ጀመረች።ግርማም ተነስቶ ቆመ እና"ሜሪ?ወዴት ልትሄጂ ነው?"ብሎ ጠየቃት።መልስ ሳትሰጠው መራመዷን ቀጠለች።ልጁ ግን ወደትክክለኛ ሰውነት ስለተመለሰ እናቱን "እማዬ?"ብሎ ጠራት።ግርማም የልጁን ጥሪ ሲሰማ ሮጦ ሄደ እና የልጁን አፍ አፈነውና"ልጄ ምንም አትናገር ዝም በል!"አለው።ጠንቋዩ ልጃችሁ እማዬ ወይም አባዬ ብሎ እንዳይጠራችሁ ብሎ ያስጠነቀቀው ትዝ ብሎት።ሜሪ ግን የልጇን ድምፅ ስትሰማ መራመዷን አቁማ ወደልጇ ዘወር አለች።ወድያው አዞራት እና ወደመሬት በጉልበቷ ተንበረከከች፤በዛቹ ቅፁበት ፀጉሯ ወደድሮ እርዝመት እና ልስላሴ ተመለሰ።የጠቆረው አይኗ እና ጥፍሮቿ ወደድሮው ውበታቸው ተመለሱ፤የተሸበሸበው ቆዳዋም ወደድሮው ልስላሴያቸው ተመለሱ።ግርማም ልጁን ለቀቀው እና ሮጦ ሜሪን አቀፋት።ሁሉም ነገር ያለቀ መስሎት ነበር ግን አመድ የመሰለ ነገር ከሜሪ ሰውነት ሲቦል ተመለከተ።ወድያው ለቀቃት እና ሚስቱን ሲመለከታት ሜሪ እንደአመድ እየቦለለች እየጠፋች ነበር።ሁሉም ሰውነቷ አመድ ሆነ እና አስክሬኗ እስከማይገኝ ድረስ አመድ ሆና ጠፋች።ግርማም በሀዘን እና በንዴት ተንበርክኮ በጣም እየጮኸ ማልቀስ ጀመረ።በመሀል ድምፁ ተቀየረበት፤ድምፁ እንደተቀየረበት ሲያውቅ ማልቀሱን አቆመ።ሆዱ ሲገለባበጥ ይሰማው ጀመረ።ሜሪ እንደሆነችው ሊሆን እንደሆነ ገባው እና ወደ አባቱ ዘወር ብሎ 

"አባዬ!.....ልጁን ይዘኸው ከዚህ ሂድ ካልሆነ ያ ሰይጣን ልጄን ይገድለዋል።"አለው በተቀየረው ድምፅ።

"አንተስ?አብረን ከዚህ እንሂድ!.....ብቻህን ትቼህ አልሄድም።"አለው አባቱ።

ግርማም በቁጣ "አሁኑኑ ከዚህ ውጡ!ለልጁ የቀረኸው አንተ ብቻ ነህ ስለዚህ በደንብ አሳድገው፤ልጄ የኔን መለወጥ ሳያይ ከዚህ ሂድ!"ብሎ የበላውን ምግብ ልክ እንደሜሪ ማስመለስ ጀመረ።የግርማ አባት የልጁን ልጅ ይዞ በፍጥነት ከዚያ ቤት ወጣ፤ግርማም መልኩ ተቀያይሮ ያንን ጠንቋይ መሰለ፤እሱም ድጋሚ ላይመለስ ያንን ቤት ለቆ ሄደ።በነገው እለት ቄሶቹ ወደግርማ ቤት ሄዱ።የጊቢው በር ተከፍቶ ስለነበር ከፍተው ወደውስጥ ገቡ፤ጊቢው ውስጥ ማንም አልነበረም፤ወደ ቤቱ በር ሲመለከቱም በሩ ተበርግዶ ነበር።ወደውስጥ እየገቡ  ቤቱን ቃኙት።የቤቱ እቃዎች በሙሉ መሬት ላይ ተበታትኖ ወዳድቀው ነበር።መሬት ላይ ያስመለሱትን እና የሜሪን አመድ ተመለከቱ።

"በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ!ምንድነው የተፈጠረው?"ብሎ መጀመሪያ መጥቶ የነበረው ቄስ አማተበ።

አለ የተባለው ቄስም ቀጠል አድርጎ "አይታይህም እንዴ?ሁሉም ነገር አብቅቷል!.....አሁን ሁሉም የሉም።"አለው።
..................ሙሉውን ለማንበብ ይቀላቀሉን!🙏

ምርጥ ምርጥ ታሪክ ያላቸውን ድርሰቶች ይቀርባሉ።እናንተም ተቀላቀሉን እና አዳዲስ ታሪኮችን ያንብቡ፤ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛዎ በማጋራት ትብብር አድርጉልን🙏🙏
https://t.me/vikinovels




Forward from: 𝖇𝖊𝖋𝖔𝖗𝖊 𝓭𝓮𝓪𝓽𝓱
✨ተመስገን👐🏼


   "..ለምን...ለምን ነሳኸኝ!" ከቤተክርስቲያኑ ውስጥ ባሉት እድሜ ጠገብ ዛፎች በአንዱ ተደግፌ ... ወደ ስዕለ አድኅኖው እያዬሁ አማርራለሁ..፤..ስላጣዃቸው ፣ስለተነፈግኳቸው ነገሮች አብሰለስላለሁ...ቲኒሽ ቆይቼ የያዝኩትን ዳዊት እንደነገሩ አነብንቤ..'አድነኝ' የሚል ጥቅስ ሳይ ከሰመጥኩበት ማማረር እዬባነንኩ አነበንባለሁ።

  ሰው ነጠላ ለብሼ ስመላለስ ወድጄው ይመስለዋል...ምድረ ሞኝ!። 'ቄሴ' የሚለው የሰፈር ስምም በዚሁ ነው የወጣልኝ ...ፈጣሪን የወደድኩት መስሏቸው...ምድረ ጅል!።

እንዲሁ ያልተሟላልኝን እያብሰለሰልኩ ቅዳሴው አለቀ። ፊት ለፊቴ የነበሩት ሽማግሌ ቅዳሴውን ሙሉ ቆሜ ማስቀደሴ አስደንቋቸው "እንዳንተ  ያለው ነው በምልክት ብቻ ፈጣሪውን ያልተከተለ...ተባረክ፣  ብሩክ ሁን" ብለው መርቀው ከያዙት የቅዳሴ ፀበል አካፍለውኝ ሄዱ....እንዲሞላልኝ ብዬ እንጂ መች እሱን ወደድኩት.. ያሰብኩትን ቢያሳካልኝ የማቱሳላን እድሜ እራሱ ቢሰጠኝ ተመልሼ እንደማልመጣ ማን በነገራቸው.... ንግግራቸው ግን ደስታን ጭሮብኛል።

   የሰጡኝን ፀበል በአንድ ትንፋሽ ጨርሼ እዬወጣሁ ሳለ...የሻገተ ዳቦ ይዞ የሚያለቅሰውን ልጇን ወተት የነጠፈበትን ጡቷን የምትለግስ አንዲት የኔቢጤ አዬሁ...ተመስገን ልል ቃጣኝ...እንደሱ ሆኜ አድጌ ቢሆንስ?...ያለኝ ከእሱ አንፃር የተሻለ ነው ..ለኔስ ተመስገን ለሱስ?!..እንዲህ እዬተወዛገብኩ ቆሜ ሳያት ...
  
አስቀዳሹ አማኝ ቤቱ ተመልሶ አልቆ ኖሮ ...የተጣሉላትን እርባና ቢስ ሳንቲሞች ለቃቅማ ..."ዳቦ" እያለ የሚያላዝንባትን  ህፃን እያባበለች ....ቲኒሽ ሳንቲሞችን ሙዳዬ ምፅዋቱ ውስጥ አስገብታ ወደ ማደሪያዋ አቀናች...።

  ....ደርቄ ቀረሁ....'አርግ' ብሎ ከሰጠኝ ትዕዛዛት አንዱንም አለመጠበቄ ታወሰኝ
...በራሴ አፈርኩ።


እራሴን አጎደልኩ እንጂ ያጎደለብኝ የለም...የጎደለበት የለም።

" ያንተ ልሁን ብቻ...መሻቴ ባይሞላም"

..    አይደል ያለው  ዘማሪው።

#ተመስገን 🤲🏽

✍🏽𝕥𝕠𝕣𝕡𝕒

https://t.me/torpanism


ክፍል አስር
ፍቅር ወይንስ እምነት

#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

ነገር ግን እሷን ለመውቀስ አልቻልኩም።

ምክንያቱም እሷ የልቤን ሚስጥር አታውቅም ነበር።

    እህቷ ከኔ ተለይታ ከሄደች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ በሆስፒታሉ አደባባይ ውስጥ እየተዘዋወርኩ ቆየሁ። አዕምሮዬ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን እያሰበ ነበር።

"እብሱ ወንድሜ ነው ያለችኝ..."
ያቺ አንዲት አረፍተ ነገር አሁንም በጆሮዬ ውስጥ እያስተጋባች ነበር።

አብሱ ለእኔ ያላትን ስሜት ባላውቅም፣ ቢያንስ እኔ ያለኝን ስሜት ለእሷ እንኳን እንዳልገለጽኩላት ሳስብ ራሴን ወቀስኩ።

ቀስ ብዬ አብሱ ወደ ተኛችበት ክፍል ገባሁ... ተኝታለች
  አልጋው ጫፍ ካለው ወንበር ላይ ተቀምጬ አይን አይኗን መመልከት ጀመርኩ እንዴት ግን እንደምታምር አላህ አዳልቶባታል...

በተቀመጥኩበት ስለሷ ሳስብ ስልኬ ጠራ አብዱ ነው ድምፁን አጥፍቼ ስለነበር ስልኬ አልቀሰቀሳትም

ቀስ ብዬ ስልኩን ይዤ ወጣሁ
ከበሩ ራቅ ብዬ ከአንድ ጥግ ቆሜ አነሳና...
አብዱ...አሰላም አለይኩም እንዴት ነህ ግን...በናፍቆት ድምፅ
እኔ...ደህና ነኝ አልሃምዱሊላህ
አብዱ...ባለፎ የሮጥክበት ጉዳይ ከምን ደረሰ... አንተማ በአላህ ብዙ ነገር ደብቀኸኛል
እኔ...አንድም ጥያቄውን ለማለፍ...አንድም የኔን እንዲመልስ ብዬ...መስጊድ ምን ተባለ ሌላ ነገር ስለኔ... ምንም አልነገሩህም
አብዱ...ሁኔታዬ ገብቶታል... እሱን እኮ ነው ምልህ ምን ላይ ነህ ኡስታዝ አሊን አናግርያቸው...አላህን የሚያስቆጣ ተግባር እንደፈፀምክ ነገረኝ
እኔ...ምን ስለምን...ሰለ አብሱ መሆን አለበት.(በውስጤ)
አብዱ...ምንነቱን እንኳ አልነገረኝም ጓደኛህ አይደል እየዋሸህለት ነው አሉኝ
እስኪ ንገረኝ...
እኔ...ስመጣ ሁሉን ነግርሀለሁ...
ከጀርባዬ በቅርብ ርቀት ስጠራ ዞርኩ ሀኪሙ ነበር...
እኔ...አብዱ በቃ ሲመቸኝ እደውላለሁ
አብዱ...ኢብሮ እንዳዘጋው መች ጨረስን እየተቆጣ
ኢብራሂም በአላህ ንገረኝ...
....ዘጋሁበት....

በፍጥነት ወደ ሀኪሙ ሄድኩ...

ከሰዓታት በኋላ ዶክተሩ አብሱ ከሆስፒታል መውጣት እንደምትችል ነገረኝ
   በሆስፒታሉ ያሉብንን ብር ከፋፍለን ወጣን...ድጋሚ ቀጠሮ ሰጡን
አብሱንም ምግብ ፈሳሽ በደንብ መውሰድ እንዳለባት መከራት...

ከአብሱ ጋ አብረን ወደ መኪናው አመራን።
መንገዱን በሙሉ አብሱ ዝም ብላ ነበር።
ከአልፎ አልፎ የምትጠርገው እንባ ብቻ የውስጧን ስቃይ ይገልጥ ነበር።

አብሱ ከሆስፒታል ከወጣች በኋላ ቀጣዮቹ ቀናት እንደ ህልም አለፉ።

የአባቷ ቀብር፣ የሀዘን ተጋሪዎች መምጣትና መሄድ፣ የቤቱ ጭንቀት... ሁሉም ነገር ተደበላልቆ ነበር።

...እኔም ከእነሱ ጎን ለመሆን የምችለውን ሁሉ አደርግ ነበር።ነገር ግን ከቀብሩ በላይ የሚያስጨንቀኝ አንድ ነገር ነበር።

"የአብሱ እህት"

ከሆስፒታሉ ጀምሮ የምታየኝ አይኗ የተለየ ነው።ልቤ ውስጥ የደበቅኩትን ሁሉ እንደምታውቅ ይሰማኛል።

አንዳንድ ጊዜ አብሱን ስመለከት እሷ ወደ እኔ እያየች ትይዘኝ ነበር።ያኔ ደግሞ ልቤ በፍጥነት ይመታል።

"ዛሬ ነገረቻት ይሆን?"
"ወይስ ገና አልነገረቻትም?"
የሚለው ሀሳብ አልተወኝም እያሰቃየኝ ነው።

ከቀብሩ ማግስት በኋላ ቤታቸው የሚመጡት ሰዎች እየተቀነሱ መጡ።

የሆነ ቀን ግን አብሱ፣ እህቷ እና እኔ ብቻችንን በሳሎኑ ተቀምጠን ሳለን
የውጭው በር በሀይል ተንኳኳ።

            .........ይቀጥላል.........

@Rufaylen13
                  ✍️ ህላዌ💕




ክፍል ዘጠኝ
               ፍቅር ወይንስ እምነት

#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

        እህትየዋ ደሞ በፍጥነት ከኔ ፊት ቀደም ብላ ወደ ክፍሉ ገባች....

   እህትየዋ ከኔ ቀደም ብላ ገብታ አብሱን ተጠምጥማ አቅፋት ከሳመቻት በኋላ አጠገቧ ተቀመጠች አሁንም አይኖቼ በተደናገጠ መንፈስ በጭንቅላቴ ከአሁን አሁን ነገረቻት ብዬ ልቤ በአፌ ሊወጣ ደረሰ.. ከአብሱዬ አልጋ አጠገብ ቆሜ እኔም እንደእህትየው ላቅፋት ልስማት ፈልጌ ነበር ግን እንደምንም እራሴን ቆጠብኩት

እኔ...እንዴት ነሽ ምን እየተሰማሽ ነው አልኳት(እህትየው እንዴት እንደምታፈጥብኝ)
አብሱ... ደህና ነኝ አስጨነኳቹ አይደል?  እህቷ...ኸረ አላስጨነቅሽንም ብላ ወሬ ልቀጥል ስትል...አባ..
አብሱ...አባዬን ብቻውን ተውኩት አይደል (ማልቀስ ጀመረች)
እህቷ...ተነሳችና እያቀፈቻት ተይ እንደዚህ አትበይ መጠንከር አለብን ያላንቺ ማን አለኝ?
አብሱ...እሺ...ስለ ቀብሩ ምን አረግሽ ነይ ወደ ቤት እንሂድ...
እኔ...በነሱ ወሬ ጣልቃ ላለመግባት ዝም ብዬ ዝም ብዬ እንሂድ ሰትል ግን...
አይ አሁን አንቺ አትሄጂም!

አብሱ...እሄዳለሁ እንጂ አባዬን እኮ ብቻውን አስቀረሁት(እያለቀሰች)
እህቷ...የራሷንም የእህቷንም እንባ እየጠረገች ደሞ አባዬ ብቻውን አይደለም
አብሱ...  እንባዋን እየዋጠች እና ከማን ጋ ነው?
እህቷ...አንዲት የአባዬ እህት ነኝ ባይ ለመቅበር መታለች
አብሱ....የአባዬ እህትእ?

       አባዬ እህት የለኝም ነበር አይደል እንዴ ያለን ደሞ ማናት? እስከዛሬ ያልጠየቀቹ ለመቅበር የምትመጣው... ኮስተር ብላ

እህቷ...እሱን በደንብ እንጠይቃታለን አብረን እኔም ብዙ ላለመጨቃጨቅ ብዙም ጥያቄ አልጠየኳትም
አብሱ...ወደኔ  እያየች እና አሁን አልወጣም መች ልወጣ ነው?
እኔ...ወደ ከሰአት በኋላ ትወጫለሽ ጭንቀት አታብዢ አሁን
እህቷ...ደሞ ጓደኛሽን እስከዛሬ መች አስተዋወቅሽኝ
አብሱ...ጥቂት ፈገግ ለማለት እየሞከረች ውይ አቤኒን ነው እሱ ወንድሜ ማለት ነው
እህቷ...በግልምጫ እየተመለከተችኝ...እ ደሞ ማን አልሽኝ ስሙን
እኔ... የምናገው ቃል ጠፍቶብኝ ድንግጥ ብዬ አፌ ተሳስሯል
አብሱ...አቤኒ(አቤኔዘር) እሱ እንደ ወንድሜ የማየው ነው

....እኔ እዛ ቆሜ አንድም እህትየው ከአሁን አሁን ጉዴን ተናገረችኝ እያልኩ አንድም ደሞ አብሱ እሱ ወንድሜ ነው ያለቹ አባባል ባለሁበት ፍዝዝ ድርቅ አርጎኝ በቆምኩበት...

አብሱ...አቤኒ ተዋወቃት እንጂ አላወካትም...ያቺ የምሳሳላት  ታናሽ እህቴ እኮ ናት።
...  ስትለኝ ነቃ ብዬ...

እኔ...አይ አወኳት በመልክም በጣም ነው የምትመሳሰሉት(ሁለቱንም በአይኔ እያስተያየሁዋቸው
እህቷ...አንተም የአብሱ ጓደኛ ወንድም መሆንህን አወኩኝ...
እኔ... ይህን ቃል ባላወጣ ይሻለኝ ነበር ግን አንገቴን ወደ መሬት እያቀረቀርኩ በደከመ ድምፅ... አው...አልኳት

ነርሷ መታ አሁን ውጡ አለችን...

እህቷ...አብሱን እየተመለከተቻት በቃ አሁን እኛ እንውጣ አንቺ እረፍት አርጊ ብላ እኔም ተሰናብቻት አብረን ከክፍሉ ወጣን...አብሱ እየወጣን እያለ እህቷን ወደ ኋላ እንድዞር ጠራቻት... እና እህትየው ተመለሰች እኔ ወጥቼ ከበሩ አጠገብ ቆምኩኝ....
ምን እንደተባባሉ አላውቅም እህትየው ከጥቂት ቆይታ በኋላ ወጣች....ሄደች ለመውጣት እኔም እንደምንም አስቆምኳት እንድታወራኝ ብዬ
እኔ...ምን አልሻት ነገርሻት እንዴ?
እህቷ...ኮስተር ብላ አልነገርኳትም ግን እነግራታለሁ!
እኔ... ልቤ በፍጥነት እየመታ ነበር።
"ምን ማለትሽ ነው? ምን ልትነግሪያት ነው?" አልኳት በተጨነቀ ድምፅ።
እህቷ.. ለጥቂት ሰከንዶች ፊቴን ትኩር ብላ አየችኝ ና
"ኢብራሂም... እህቴን በጣም እንደምትወዳት አውቃለሁ።"

እኔ...ይህን ቃል እንደሰማሁ ደሜ በአንድ ጊዜ ወደ ፊቴ ተምዘገዘ።
"እኔ... ምን እያልሽ ነው?" ብዬ ለመካድ ሞከርኩ።
እህቷ..."አትድከም። ከዓይንህ ይነበባል። ከድሮ ጀምሮ ስለ አንተ አውቃለሁ"
እኔ...አንገቴን ወደ ታች ደፍቼ ዝም አልኩ።
እህቷ..."ግን..." አለች ድምፇን በመቀነስ፣ "አሁን የምታስብበት ጊዜ አይደለም። እሷ አባቷን አጥታለች። በጣም ተጎድታለች።"
እኔ..."አውቃለሁ..." አልኩኝ በቀስታ።
እህቷ..."ስለዚህ የምነግራት ነገር ካለ አሁን አይደለም። ግን አንተም ከልብህ የምትፈልጋት ከሆነ እስክትረጋጋ ጠብቅ።"
...ይህን ብላ ከኔ ዞራ ሄደች።

እኔ ግን በሆስፒታሉ ኮሪደር መሀል እንደ ሰው ሳልሆን እነደ ሀውልት ቆሜ ቀረሁ።
እህቷ ያወቀችው ነገር አንድ ብቻ አይደለም ...ለአመታት የሸሸግኩት ጉዴን ነው....

እህቷ ከኔ ተለይታ ከሄደች ከቆይታ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ መስኮት ተጠግቼ ቆምኩ።
አሁንም የአብሱ ድምፅ በጆሮዬ ውስጥ ይደጋገም ነበር።

"እሱ ወንድሜ ማለት ነው..."

ያቺ አንዲት አረፍተ ነገር ከብዙ ዓመታት ጀምሮ በልቤ የገነባሁትን ተስፋ በአንድ ጊዜ ያፈረሰች መሰለኝ።

ነገር ግን እሷን ለመውቀስ አልቻልኩም።

ምክንያቱም እሷ የልቤን ሚስጥር አታውቅም ነበር።


.........ይቀጥላል.........

                @Rufaylen13 💫
                       ✍️ ህላዌ💕




አርሲ የደም ምድር



የኤፍራጥስ ወንዝ ደርቆ ደማችን ሆኖ ጅረት
የክርስቶስ በጎች ታረዱ ያለ አንዳች ምህረት
በገዛ ምድራቸው ላይ የሞት ጥላ ሲያንዣብብ
የጻድቃኑ ደም ሲፈስ ሀዘን መከራው ሲደራረብ

​ጊዮርጊስ ሆይ ተመልከት ስለሰባቱ ዓመት መከራህ
ብዙ ጊዜ ሞተህ ብዙ ጊዜ የተነሳህ
ዛሬ ግን የአንተ ልጆች በራሳቸው ምድር
ስለ ጌታህህ ተሰየፉ ሳይኖራቸው ምንም ክብር

​አርሴማ ቅድስት እናት የሰማዕታት እመቤት
ስለ አምላክሽ ፍቅር ብለሽ አንገትሽን የሰጠሽለት

ዛሬ በየሜዳው ላይ እህቶቻችን ሲታረዱ
የምህረት አይኖችሽ ከቶ ወዴት ሄዱ??


​የእምነት መሠረት አትናቴዎስ የሃይማኖት ጀግናው
ኢ አማኒን ያሳፈርከው እውነትንም የሰበከው
ዛሬ እኮ እውነት ጠፋች በሀሰት ተተካችና
የክርስቲያን ደም መፍሰሱ አልታሰበም እንደ ቁና

​ያ የብርሀን ፋኖስ አቡነ ጴጥሮስ አባታችን
"ለሀሰት አልገዛም" ብሎ የሞተው ሰማዕታችን
ዛሬ መቃብሩ ቢያይ የልጆቹን መታረድ መጨነቅ
እኮ ምን ይል ይሆን እንዴትስ ይደነቅ?


እንጃልን እንጃልን ብቻ.......


ደሞ እኮ......

​ታቦቱ ሲሰደድ አየን ቅዱሳኑ ሲቃጠሉ
የእግዚአብሔር ማደሪያዎች በጨካኞች ፊት ሲጣሉ

ሰማዩ በጭስ ተጋርዶ ቤተክርስቲያን ተቃጠለች
የቅዱሳኑ ማኅደር ሲነድ ተይዞ በክፉዎች

​ስዕለ አድኖው ሲቀደድ መስቀሉ መሬት ሲጣል
የክርስቲያን ልብ ይሰበራል
አንገት አስደፍቶ ያስለቅሳል

ቤተክርስቲያን ስትቃጠል የእሳት ነበልባል ሲወጣ
ድምፅሽን ማንም አልሰማው ልጆችሽ አልቆሙም ለቁጣ

​
ይህ ዝምታ ይሰበር ድንጋዩም ይጩህ አሁን
የሰማዕታት አምላክ ሆይ እስከመቼ ነው ይህ የሚሆን?
ደማቸው ከምድር ላይ ወደ አንተ ይጮኻልና
ኢትዮጵያን ታደጋት ጌታ ሆይ ፍረድልን ቶሎ ና

​የክርስቲያን ደም ፈሶ መቼ ከንቱ ሆኖ ያውቃል?
ከሰማዕታቱ ጋር ስማቸው በወርቅ መዝገብ ይፃፋል.....



​ዋይ! ዋይ! ብላ ታለቅሳለች ቤተክርስቲያን ቆማ ዛሬ
ልጆቿ ሲታረዱባት ጠፍቶባት የደስታ ወሬ


ግና ደሞ......
ተዋህዶ አትጠፋም በእሳትም ብትቃጠል
የክርስቶስ መንጋ በአምላኩ ፀንቶ ዘላለም ይኖራል......


🖌 የናንተው ስሉጥ




አቤቱ የሆነብንን አስብ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭



https://t.me/Kenako_12


ሥውር ልብ


ሠዉን እያዳነ
ርሡ እየደበነ
ፍቅር እየራበው ፍቅር እየለገሠ
እንባን እያበሠ እንባው የፈሰሰ
.............ተገኘ ሥውር ልብ
ለራሡ ተርቦ ለሠው እሚያጠግብ


{ስሉጥ}


https://t.me/Kenako_12




ሰላም ውዶቼ❤

ከድንቅ ልጅ ድንቃድንቅ የሆኑ ግጥሞች😘

🌺እርግቤ🕊️

አጠር አጠር ያሉ ግጥሞች ፣ጥቅሶች እንዲሁም መጣጥፎችን ይገኙበታል።

እናንተ ብቻ join በሉ 😇🙏

https://t.me/Markal_274

20 last posts shown.

270

subscribers
Channel statistics