Forward from: ዝምተኛው የግጥም ቤተ-መጽሐፍ
ልረሳሽ ነው መሰል
ባፈቀርሁሽ መጠን
ልረሳሽ ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
እኔም መሳቅ ጀመርሁ
አለምም ካንች ውጭ ይታየኝ ጀመረ
ልረሳሽ ነው መሰል
ይኧው ቃልሽን
አትጠጣ ያልሽኝን
ጠላ ከአረቄ ጋር ቀላቅየ ጠጣሁ
እርሷ የት ነች ሲሉኝ
አለች ማለት ትቼ
ነበረች የሚል ቃልካፌ ላይ አወጣሁ
ልረሳሽ ነው መሰል
ካንች መለየቱን ችየ ተቀበልሁት
ተሰባብሮም ቢሆን
ስትሄጅ ያጣሁትን ልቤን አገኘሁት
ልረሳሽ ነው መሰል
ያኔ የማለ ልብ ሊረሳሽ አስቧል
ያረግሁት ቀለበት ከጣቴ ላይ ጠቧል
ልረሳሽ ነው መሰል ከልቤ ልትወጭ
ጥርሴ ስቆ ታየ ይኧው ካንች ውጭ
✍ ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
ባፈቀርሁሽ መጠን
ልረሳሽ ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
እኔም መሳቅ ጀመርሁ
አለምም ካንች ውጭ ይታየኝ ጀመረ
ልረሳሽ ነው መሰል
ይኧው ቃልሽን
አትጠጣ ያልሽኝን
ጠላ ከአረቄ ጋር ቀላቅየ ጠጣሁ
እርሷ የት ነች ሲሉኝ
አለች ማለት ትቼ
ነበረች የሚል ቃልካፌ ላይ አወጣሁ
ልረሳሽ ነው መሰል
ካንች መለየቱን ችየ ተቀበልሁት
ተሰባብሮም ቢሆን
ስትሄጅ ያጣሁትን ልቤን አገኘሁት
ልረሳሽ ነው መሰል
ያኔ የማለ ልብ ሊረሳሽ አስቧል
ያረግሁት ቀለበት ከጣቴ ላይ ጠቧል
ልረሳሽ ነው መሰል ከልቤ ልትወጭ
ጥርሴ ስቆ ታየ ይኧው ካንች ውጭ
✍ ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI