"አማራነትህ ተዋርዶ የምታስከብረው ግለሰባዊ መብት የለህም" ሀይሉ ቢታኒያ
በደንብ ይገለጥልን!
ፅኑ የአማራ ታጋይ ለመሆን ትልቁ ቅድመ ሁኔታ ፅኑ የአማራ ብሄርተኛ መሆን ነው፡፡ ፅኑ የአማራ ብሄርተኛ ለመሆን ቅድመ ሁኔታው ደግሞ የብሄርተኝነትን መሰረታዊያንን (the basics) ጠንቅቆ ማወቅ ነው፡፡ ፍንትው ያለ አታጋይ ርእዮት ካለን ጠንካራ ድርጅቶችን ለመገንባት አንቸገርም፡፡ የአቅጣጫ መምታት አይገጥመንም። ስለዚህ ሁልጊዜም ብሄርተኝነትን ለማወቅ እናትጋ!
ለምሳሌ የብሄርተኝነትን እና የሶሻሊስቶችን ሁኔታ መገንዘብ ብዙ ነገርን ይቀይራል፡፡ ሶሻሊስቶች ብሄርተኝነትን የሰራተኛው ደላይ ህሊና (false consciousness) የሚፈጥረው አላፊ-ጠፊ ነገር እንደሆነ አድርገው ነበር የሚቆጥሩት፡፡ አቅሙን አሳንሰውና አቃለው ነበር የሚገነዘቡት፡፡ በእነሱ እምነት የአንድ ብሄር ድሃ እና ሀብታም ጠላት ናቸው፡፡ ጠላትነታቸው ደግሞ ስር የሰደደና ሊፈታ የማይችል ነው፡፡ ለሶሻሊስቶች አቶ ብዙአየሁ ታደሰ (የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤት) እና አንድ የአማራ ድሃ ሰራተኛ ጠላት ናቸው፡፡ ወንድማማቾች አይደሉም፡፡ ቅራኔያቸውም የማይታረቅ ነው፡፡
ብሄርተኝት የነ ማርክስን ፍልስፍና ፉርሽ ያደረገ ነው፡፡ ከዘመናዊነት ጋር ይጠፋል ሲባል የኮምኒዝምን ሥርአተ ቀብር አውጆ ግንግኖ የወጣ ርእዮት ነው፡፡ የሶሻሊስቶችን ብቻ ሳይሆን የሊብራል ሉላዊያኑን (liberal globalists) ትንታኔ ፉርሽ ያደረገ ሃያል ርእዮት ነው፡፡
የብሄርተኝነት ልዩ ባህሪው የአንድን ብሄር ድሃና ሀብታም፣ አርሶ አደርና ከተሜ፣ ዲያስፖራና የሀገር ቤት ነዋሪ፣ ሙስሊምና ክርስቲያን ወዘተ አንድ የሚያደርግ ርእዮት መሆኑ ነው፡፡ እከሌ ባለ ሀብት ነው ብለህ እንደ ሶሻሊስቶቹ በጥርጣሬ አትመለከተውም፡፡ እንዲያውም የበለጠ ሀብታም እንዲሆንና ብዙ ሀብታሞች እንዲወጡ ትፈልጋለህ፡፡ እንዲያውም ትመካበታለህ፡፡ እከሌ ሙስሊም ወይም ክርስቲያን ነው ብለህ እምነቱን አጀንዳ አታደርገውም፡፡ በአማራነቱ ብቻ ትወደዋለህ፡፡ የሃይማኖት ነጻነቱ እንዲከበር ትታገልለታለህ፡፡
አማራ የሆነን ሁሉ ያለ ልዩነት የሚያስወድድህ የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ ሁሉም እንደ ወንድምህና እህትህ እንዲሰማህ የሚያደርግህ የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ ያለማንም ቀስቃሽ ለአማራ ወገንህ እንድትደርስ የሚያደርግህ የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ እሱን አጥብቀህ ያዝ፡፡ ህልውናህ የሚከበረው፣ ሃይማኖትክን በነጻነት ማምለክ የምትችለው አማራነትህ ሲከበር ነው፡፡ አማራነትህ ተዋርዶ የሚከበር ግለሰባዊ ማንነት የለህም!!!
https://t.me/MEREWA_MEDIA