መረዋ ሚድያ (Merewa Media)


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


አዲስ ተስፋ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ትውልድ።
ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
ለመቀላቀል
@MEREWA_MEDIA

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🔥#ዓይግዜ_ክፋቱ‼️

ጽንፈኛ ነው አልከኝ❓
""""""""""""""""""""""""
እሰይ!! ግድ የለም ይበለኝ
እንዲህ ነው ውለታ ብድር መላሽ ያርገኝ
ውርደትን ከሞትህ ነብስን በታደኩኝ
አገርና ወገን ክብሩን ባስጠበኩኝ
ምነው በአደባባይ ጽንፈኛ ነው አልከኝ
ላይሆን መተናነስ  እንዴትስ ብትለካኝ
ባነሰ ማንነት አንሰህ ያሳነስከኝ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
ያኔ የጭንቅለት ሰው ልከህ ከደጀ
ንገሩልኝ ብለህ እንድደርስ ማልጀ
ሞትክን ስንሞትልህ ስወድቅ ተገድጀ
ምነው ተዘነጋህ እረሳህ ወዳጀ
ቀኝ መላሽ ጀግና በግራ ጠምጀ
ጠላትን ሳንጓልለው ነብስያየን ክጀ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
ግድ የለም ልንገርህ አድምጠኝ በሞቴ
ፋኖ ማለት እኮ ይታገሱ እሸቴ
ዋጋ የከፈለው ልቅደም ብሎ አባቴ
ያስከበረህ ጀግና ሸዋ መራቢቴ
እሱ እኮ ነው ፋኖ ምን ነካሽ ገለቴ።

ምየ ትቸዋለሁ እንባ ባይኔ ላይፈስ
ወደቀ ያሉኝ ለት ፋኖ እሸቴ ሞገስ
እምነተ ጠንካራ ፊቱ እማይመለስ
በቅዱስ ሚካኤል ምሎ የሚተኩስ
ክንደ ነበልባሉ አንገት የሚበጥስ
አነጣጥሮ ተኳሽ ልክ እንደይታገስ
ጠላት አስረግዶ ወራሪ እሚመልስ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
ተወርዋሪው ኮከብ በድል የሚያበራ
የነገስታቱ ልጅ ተራራው አማራ
ፈጥኖ የሚደርሰው ከአስቸጋሪው ጎራ
ምድር ስትጨነቅ ሰሜኑ ሲጣራ
ዲሽቃና መትረጌስ በመድፍ እያጓራ
ነፍጠኛው ጎንደሬ ዳባት ጃናሞራ
ወልቃይት ጠገዴ መተማና ቋራ
እብናት በለሳ አጅሬ ጃኖራ
መገን ሊቦ ከምከም ደራና ፎገራ
በሮ የሚደርሰው ያ ንስር አሞራ
የሞተ ለክብሩ ለአንዲት ለባንዴራ።

ፋኖ ነው መሳፍንት አርበኛው አረጋ
የነጻነት ታጋይ ለለውጥ የሚተጋ
ልክ እንደ አባቶቹ ወገን ያረጋጋ
አገርን ያዳነ ከጠላት መንጋጋ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
እረ ወዴት ወዴት ወዴት ነው አንተየ
ጽንፈኛ ነው ያልከው ፋኖ ነው አጋየ
የመንግስትህ ክብር ልክ እንደገብርየ
ከሞት የሚታደግ ልክ እንደተክልየ
ዝምተኛው ጀግና ጠላት ያደባየ።

ጎጃም ያበቀለው ውችንፍሩ ዘሜ
እጅ ስጥ አሉተኝ የማንም ወፈፌ
እጅ ይዞ ሊወሰድ አይ እነፍንፍኔ
አለመማራቸው ታሪክን በቅኔ
አባይ ተሻገሩ እነ ኦነግ ሸኔ
ደጀን ከአፋፉ ላይ የተኛውን በሬ
ነካክተው ነካክተው አደረጉት አውሬ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
የነጻነት ኮከብ የትግላችን ሻማ
ወልቃይት ጠገዴ ያፈራችው ታማ
ሺ ባንዳ የሚጥል ድምጹ ሳይሰማ
ፋኖ ነው ደመቀ ላልሰማው አሰማ
ጽንፈኛ ነው ያልከው ወየሁ ጉድ ሲሰማ
ከሰውነት ወርደህ በዘር ስትገማ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
ይመስክር ወልደያ እራያ አላማጣ
እረመጡ ምሬ የለለበት ጣጣ
ጠላትን ለብልቦ ነጻ የሚያወጣ።

መርሳ አባ ገትየ በል እንሂድ ወሎ
የትግላችን ዓርማ ያ ምሬ ወዳጆ
ና ላሳይ ጎበዝ የአርበኞችን ውሎ
ዲሽቃ የሚማርክ መገን ጃሎ ብሎ
ፋኖ አሰን ከሪሙ ጀግናው አጋሚዶ።

የወንበዴ ምሽግ እሳቱን ተራምዶ
በል ላሳይህ ጀግና ውረድ ወደ ዳውዶ
እንዲህ ነው አማራ ለማን ተንበርክኮ
በድል ይመለሳል ጠላቱን አንድዶ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
ይመስክር አገሬው ኮሙቦልቻና ደሴ
ጣምራ በር ይናገር አጣየ ኬሚሴ
የአርበኝነት ልኩ ቆራጡ በለሴ
ፋኖ ነው አማራ ወንዱ አስቻለው ደሴ
ስሙ የሚያጸና ልክ እንደ ስላሴ።

ተራማጁ ጀግና ወደፊት ገስግሶ
አሳምነው ጽጌ የላከው መርቆ
እንዳባቶቻችን ታሪክ ስራ ብሎ
እሄ ነው አርበኛ የፋኖወች ውሎ
ነዳው እንደ በሬ ጠላቱን ሆ ብሎ።

ጽንፈኛ ነው አልከኝ?
ይሁን ግድ የለኝም ያሻህን ብትለኝ
አገር የምጠብቅ አርበኛው እኔ ነኝ
ድጌን አደግድጌ ትጥቄን ያጠበኩኝ
ምሽግ ተራማጁ ቦንብ እያመከንኩኝ
አርበኛውን ፋኖ ጽንፈኛ ነው አልከኝ።

ለሃገሬ ክብር ሰንደቋን ለብሼ
በእፍኝ ጥርኝ ውሃ አንዴ ጎርሼ
ዳገት ቁልቁለቱን ወጥቸ ወርጀ
ሃሩር ቸነፈሩን በረሃውን ጥሸ
ነጻ የማወጣ ጠላትን ደምስሼ
ዓማራ ነኝ አንተ ልንገርህ መልሼ
እቢ አልደመርም ካንተ ትናንሽ።

እቆማለሁ ገና ታሪኬን አድሼ
የተረኛ ሴራ ትብታብ በጣጥሼ
ገና ታየኛለህ ክብሬን አስመልሼ።

ወልቃይት ጎንደር ነው ጎንደርም ዓማራ
እራያም ወሎ ነው ወሎም ላሊበላ
እረፍ ባለ ጊዜ ተው እርምህን አውጣ
አንሰጥም ክብራችን የመጣው ቢመጣ።
""""""""""""""'''"'''''''''''''''
@ መረዋ ሚድያ

https://t.me/MEREWA_MEDIA


በጠላት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ የበላይነት የተወሰደበት የ"100 ተራሮች ዘመቻ" በዐማራ ፋኖ በጎጃም ‼️

የዐማራ ፋኖ በጎጃም በ5 ኛ ክ/ጦር ቡሬ ዳሞት ደጃች አሰቦ ብርጌድ በአስር አለቃ ጌታቸው ታረቀኝ እየተመራ በ"100 ተራሮች ዘመቻ" በተቆጣጠራቸው ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ በማድረግ የህዝብዊ ምክክርና ቃለ ምህላ ፈጽሟል ‼️

የነቃውን ማደራጀት እና ያልነቃውን ማህበረሰብ በማንቃት ለዐማራ የህልውና ትግል አጋር እና አካል ለማድረግ ማህበረሰቡ ላይ የግንዛቤ ፈጠራ፣ ማህበረሰቡን ከትግሉ እና ከታጋዮች ጋር ማስተዋወቅና ማነጋገር ወሳኝ በመሆኑ ፤ ብርጌዱ የቁጭና የአካባቢውን ማህበረሰብ ስለትግሉ አግባብነት አጠቃላይ ግንዛቤ ፈጥሯል።

በዚህ መርሀግብርም ብርጌዱ በአስር ከለቃ ጌታቸው ታረቀኝ እየተመራ ከቁጭ እና አካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመመካከር ወደፊት ሰፊው የዐማራ አርሶአደር ለጠላት ምሳር ሁኖ ልጆቹን እንዳያሳድድና ከፋኖ ጎን በመሆን የህልውና ትግሉን እንዲደግፍ በዚህ መልኩ በቃለ ምህላ አጽድቀዋል።

የዐማራ ፋኖ በጎጃም በ"100 ተራሮች ዘመቻ" ካሳካቸው የመጀመሪያ ቀን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ግቦች መካከል ይሄ አንዱና ትልቁ ማሳያ ነው። በዚህ ማህበረሰብ ትክሻ ተሰግስጎ የኖረን ሚሊሻ፣ አድማ ብተናና የብልጽግና ወታደር ወደ ፍርስራሽነት በመቀየር ነፍሰ  ወከፍ መሳሪያ በመማረክ ትልቅ ወታደራዊ ድል ሲወስድ ፤ ማህበረሰቡን ሰብስቦ ለነገ የጠላት ምሽግ እና መንገድ መሪ የሚሆን ሚሊሻ እንዳይኖር የፖለቲካ ግንዛቤና መተማመን በመፍጠር ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ አግኝቷል።

አዲስ ተስፋ
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ !!
ድል ለመላው የዐማራ ህዝብ !

©️ ይድነቃቸው ሽዋንግዛዉ

https://t.me/MEREWA_MEDIA


ሰበር ዜና!

በዛሬው ዕልት ሙሉ ቀን በተደረገ ውጊያ ሲደረግ ውሎ ከመሸ የምንጃር ሸንኮራ ንዑስ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን
#ባልጪ ከተማን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌድ ከጠላት እጅ ነፃ አውጥቶ ሙሉ ለሙሉ ፋኖ ተቆጣጥሯል::

ምንጃር አረርቲ ከተማም የትላንትናው ውጊያ ዛሬም እንደቀጠለ እንደሆነ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ፋኖ ንጋቱ ይታፈሩ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

©️ ኢትዮ 251 ሚዲያ


https://t.me/MEREWA_MEDIA


#እስክንድር ነጋ የተባለ ሰው ወደ ሸዋ ምድር ከገባ በኋላ ሸዋ ላይ ይሄ ነው የሚባል ውጊያ አልተካሄደም።

ይልቁንም  በመንግስት ኃይሎች ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ይልቅ በሁለቱ የሸዋ እዞች መካከል የሚፈጸሙ የእርስ በርስ ጉዳቶች በርክተዋል።

#እስክንድር ለአማራ ህዝብ አሸናፊነት የሚታገል ከሆነ  ከወንድማማቾች መካከል ዘወር በማለት  ለህዝብ ለሚከፈለው መስዋትነት አስተዋጽዖ ማድረግ አለበት።

እስክንድር ብዙ አድርጓል ወደፊትም ማድረግ ይችላል። ነገር ግን በወንድማማች መካከል ገብቶ የሚያደርገው መከፋፈል ግን ቀይ መስመር ነው።

https://t.me/MEREWA_MEDIA


ለአማራ ህዝብ ህልውና የምናደርገው ተጋድሎ ብዙ አቅሞችን ይጠይቃል:: ትግሉ ከዚህ የደረሰውም በብዙወች ርብርብ ነው:: ከአቅሞቻችን መካከል አንዱ ብላቴናው ማርሸት ፀሐዩ ነው::

ዘር ከልጓም ይስባል ይባላል። ማርሸት የደምሴ አየለ የልጅ ልጅ ነው። ደምሴ አየለ በአምስቱ የአርበኝነት ዘመን ታላቅ ተጋድሎ ካደረጉት መካከል ናቸው። ደምሴ አየለ በትውልድ አካባቢያቸው የሚታወቁት በጦር ሜዳ የማረኩት ነጭ ጣሊያናዊ እረኛ ስለነበራቸው ነው።

በዘመቻው መሀል መልካም ልደት ብያለሁ! እንኳን ተወለድክ ታናሹ!

©አርበኛ አስረስ ማረ


ታዳጊዋ ባልጪ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷ ተሰማ!

ዛሬ መስከረም 27/2017 ዓ/ም ሙሉ ቀን በተደረገ ውጊያ የምንጃር ሸንኮራ ንዑስ ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ታዳጊዋ ባልጪ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ አረጋግጧል።

በከተማዋ መሽጎ የነበረውን የጠላት ኃይል አፅድተው ከተማዋን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ያደረጉት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌድ ፋኖዎች መሆናቸውንም ነው ሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ለጣቢያችን የገለፀው።

በተመሣሣይ፡ በምንጃር አረርቲ ከተማ ትላንት መስከረም 26/2017 ዓ/ም እኩለ ቀን ገደማ አከባቢ የተጀመረው ውጊያ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉ ተሰምቷል።

https://t.me/MEREWA_MEDIA


ዘመቻ መቶ ተራሮች
አምስተኛ ቀን

ቢጎሽ አይበርደው፣ቢነድ አይሞቀው
የዳሞቴው ልጂ አስሩጦ አነቀው።

ዛሬ ደጋ ዳሞት እየተደረገ ባለ ውጊያ ጠላትን በክላሽ፣በብሬንና በዲሽቃ ቀጥቅጠውት አላረካ ያላቸው የጀነራል ዝናቡ የመንፈስ ወራሾች ጠላትን እያስሮጡ ከነነፍሱ በእጂ ሲይዙት ውለዋል።
-ከ አርባ በላይ ክላሽ ተማርኳል
-ለቁጥር የሚታክት ተተኳሽ ተማርኳል
-ሶስት ምሽግ ተሰብሯል
-አራተኛው ምሽግ ላይ ትንቅንቁ ቀጥሏል።
ከአርበኛ ዘመነ ካሴ የተወሰደ

አርበኛ ዝናቡ ልንጠረው


ጎንደር አሁን‼️

አሁን ከመሸ ሚሊሻ ና አድማ በታኝ" ቅድምያ እሱ ይዝመት አንተ ዝመት" በሚል የተነሳ ጭቅጭቅ አደማ በታኝ ና ሚሊሻ ባነሱት ጭቅጭቅ በተና ተኩስ አራት ሚሊሻ ና ሁለት አድማ በታኝ ሲገደሉ ከአራት የማያንሱ ከሁለቱም ወገን በከባድ ቆስለዋል ።


#ደብረማርቆስ‼

አመሻሽሹን የሚሊሻና ፖሊስ አባላት ፋኖን መስለው ሲቪል ልብስ ለብሰው መሳሪያ ይዘው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ስካርፍ ጠምጥመው በከተማው ዋና ዋና እና ውስጥ ለውስጥ  መንገዶች ተሰማርተው ተመልክተናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አምስኪሎ ንግድ ባንክ አብማ ቅርንጫፍ፤አብማ ሆቴል፤ትልቅ ሆቴል፤ኮሌጅና፤ፍቅር ተራ አካባቢ ወጣቶችን በ ሳይህ አላማርከኝም አይነት ፍረጃ ከ 11:00ጀምሮ እያፈሱ እንደነበረ አረጋግጠናል።

#ዘመቻ_መቶ_ተራሮች
እናሸንፋለን!!


https://t.me/MEREWA_MEDIA


በዛሬው ዕለት መስከረም 27/2017 ዓ.ም

ገንዳ ውሃ የአራዊት ሠራዊቱ መካነ መቃብር፤ በምዕራብ ጎንደር ዞን፣ ገንዳ ውሃ ከተማ የመሸገውን የጠላት ጦር የሽምቅ ተልዕኮን ይዘው በገቡ ፋኖዎች እንደ ቅጠል ረግፏል።

የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ አጣናው ዋሴ ክ/ጦር፣ አበራ ጎባው ብርጌድ ከሻለቃዎች በተውጣጡ ክንደ ነበልባሎች አማካይነት ረፍት ነስተውት ውለዋል። በዚህም ለቁጥር የሚያዳግት የአገዛዙ ግሪሳ ሠራዊት ምሽጉ ውስጥ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
በረመጦቹ በኩል ግን አንዳችም የደረሰ ጉዳት የለም።


ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
     አርበኛ ባዬ ቀናው

https://t.me/MEREWA_MEDIA


ሰበር ዜና!

ዘመቻ መቶ ተራሮች ግራ አዝማች ሞኜ ስንሻው !!

◾የአማራ ፋኖ በጎጃም ዘመቻ መሪ በሆነው መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን በተሰጠ ትዛዝ በ8ኛ/በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው ደበይ ጮቄ ብርጌድ በዛሬው እለት በደበይ ጥላትገን ወርዳ ቁይ ከተማን ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በተደረገዎ የጨበጣ ውጊያ ቁይ ከተማን ፋኖ ተቆጣጥሮ ውሎአል።

◾በዘመቻ መቶ ተራሮች በተሰጠው ትዛዝ መሰረት  መስከርም 26/2017ዓም በደበይ ጥላትገን ወርዳ ቁይ ከተማን ከጠላላት ነፃ ለማድረግ ብዙ ገድሎችን ሲሰሩ የነበሩ ብርጌዶች ውስጥ ደበይ ጮቄ ብርጌድ ፣የአባ ኮስትር ብርጌድ አካል የሆነችው 1ኛ/ጠቅልና 4ኛ/ሻለቃ እንዲሁም በቀጠናዊ ትስስር ለማጠናከር ትዘዝ ተቀብሎ በግዳጁ ተሳታፌ የነበረው የ7ኛ/ሀዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር እስፔሻል ፎርስ ጥቁረ አንበሳ፣የቦቅላ አባይ ብርጌድ፣የእነ ሞጨራ አረሶ አደር በቁይ ከተማ ጠለትን እንደ እባብ ቀጥቅጠው ታሪካዊ አሻራቸውን አሳልፈዋል።

◾የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ/በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር በአካሄደው ውጊያ በደበይ ጥላትገን ወርዳ ቁይ ከተማ አስንዳቦ ማረያም ሰፈረ፣ጨንጎር ሰፈር ጠላት መሽጎበት የነበረውን ምሽግ በመስበረ በርካታ ተተኮሽ እና ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችን በፋኖ እጅ ገቢ ተደርገዋል።የ8ኛ/በላይ ዘለቀ ክፈለ ጦር አቦ ሸማኔ የሆነው የደበይ ጮቄ ብርጌድ ፣የአባ ኮስትር ብርጌድ እና የደበይ ጥላትገን ህዝበዊ ማዕበል ወደ ጠላት አለባቸው ካንፖች ድረስ በመሄድ የጠላትን ስነ ልቦና በመስበረ  ጠላት ተቀምጦባት የነበርቸውን ቁይ ከተማ በፋኖ ቁጥጥረ ሰረ ውላለች።በዚህ ውጊያ በጀግኖቹ አቦ ሸማኔዎች ከጠላት የማረኳቸው ዝርዝር ይህን ይመስላሉ።
፨80 የሞተ የጠላት ሀይል
፨33 የጠላት ሀይል ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ
፨32 የነፍስ ወከፍ ክላሽ እንኮ መሳሪያ
፨ 31 የተማረከ የጠላት ሀይል
፨71 በጥርነፋ የነበረ የአድማ ብተና የእጅ ስልክ
፨1,000 የብሬን ጥይት
፨ 500 የክላሽ ጥይት
፨ የጠላት ወታደራዊ አልባሳት በሙሉ
፨ 63 ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ ፍራሽ
፨ ጠላት ይጠቀምበት የነበር 400 ሊትር ናፍታ
፨ 8 መኪናዎች በቁይ ከተማ ከጥቅም ውጭ ተደርጎዋል
፨ 2 የብሬን ተቀያሪ አፈሙዝ በፋኖ
፨ የፖሊስ ጣበቢያ 2 ጥቁረ ክላሽ
፨ 5 ክላሽ እንኮብ
፨ 7 የቃታ መመሳሪያ ተማረከዋል።
፨ በቁይ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ያሉ ማቴሪያሎችን ፋኖ ይዞ ወጥቶል።
፨በጠላት እጅ የነበሩ 15 ንፁሀን እስረኛ አስፈተናል።

◾በሌላ የውሎ የውጊያ መረጃ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ /በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው ዛንበራ ብረጌድ ደጀን አብሪ ሻለቃ ከሌሊቱ 12:30 በሁለት አቅጣጫ በጠላት ሀይል ላይ ውጊያ ከፍቶ ውሎዓል።በደጀን ከተማ እና ደጀን ወረዳ ኩራር እንደጅረ ቀበሌ በተደርገው ውጊያ አስራ አምስት የጠላት ሀይል እስከወዳኜው ሲሸኙ 8 ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ በሁለት አንንቡላስ ወደ ደጀን ከተማ ይዘው ሄደዋል።

◾የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ/በላይ ዘለቀ ክፈለ ጦር ከግንደዮን ከተማ በመነሳት ወደ እናረጅእናውጋ ወረዳ ፈለገ ብረሀን ከተማ ኮሶ ዙሪያ ቀበሌ የጠላት ሀይል ለመግባት ቢሞክረም የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አካል የሆነው ሶማ ብረጌድ ጫኔ አለው ሻለቃ፣ 1ኛ ሻለቃ፣ 2ኛ ሻለቃ፣ ይናጭ ሻለቃ እና የሶማ ብርጌድ እስፔሻል ፎርስ በጋራ በመሆን የጠላትን ሀይል እያሮራጡ ወደ ነበረበት ቦታ መልሰውታል።

መረጃው የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ተኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይበልጣል ጌጤ ነው!


ህወሀት 🤣


#ጎጃም‼️

ሸበል በረንታ ==ሽፈረው ገርባው ብርጌድ
በመቶ ተራሮች ዘመቻ ታምር ሰርቷል።
የነዚያ ዘር በረኸኞቹ እየመጡ ነው።

አርበኛ እስቲበል አለሙ ዘሪሁን


https://t.me/MEREWA_MEDIA




ሰበር  ዜና❗️

የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ባንዳ አድማ ብተናና ሚሊሻ ላይ በደብረብርሃን ከተማ መብረቃዊ ጥቃት ሰነዘረ።

የአማራ ህዝብን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋለሁ በሚል ድንፋታ ወደ አማራ ክልል ዘው ብሎ የገባው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ወራሪ ሰራዊት በተለያዬ ቦታ የእሳት እራት ከመሆን አልዳነም።

ይህንን ፕሮጀክት በውጤታማነት ለመፈፀም ይረዳ ዘንድ ባንዳ አድማ ብተና፣ ሚሊሻ እና ፓሊስን እራሱን መከላከያ ብሎ ከሚጠራው መንጋ ጋር  በማቀናጀት በተደጋጋሚ ወደ አማራ ምድር ቢያቀናም ወደ አፈርነት ከመቀየር ሊታደጉት አልቻሉም።

በዛሬው እለትም በአራቱ የአማራ ግዛቶች የምንገኝ የአማራ አደረጃጀቶች ማለትም የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ፣ የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ በጎጃም ያስተላለፉትን የመንገድ ክልከላ ተግባር ለማስከበር ደብረብርሃን ከተማ ልዩ ስሙ  ሰን ሻይን ካምፕ ጀርባ አካባቢ በተሰማሩ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ አባላት ላይ ጥቃት ለመሰንዘርና መንገዱን ለማስከፈት መነሻውን መሀል ደብረብርሃን ያደረገ በ4 አይሱዙ የተጫኑ ባንዳ አድማ ብተናና ሚሊሻ በ2 ፓትሮል የተጫነ አመራርና ሎጀስቲክ በነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ በተመራ የልዩ ዘመቻ ቡድን ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ ተሽከርካቹን  ከጥቅም ውጭ ማድረግ ተችሏል።

በዚህ ልዩ ኦፕሬሽንም ፋኖ በረከት ወርቁ ታደሰና በረኸት ወርቁ በታሪክ የሚመዘገብ ጀብዱ ፈፅመዋል።

via:የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል


"አማራነትህ ተዋርዶ የምታስከብረው ግለሰባዊ መብት የለህም" ሀይሉ ቢታኒያ

በደንብ ይገለጥልን!

ፅኑ የአማራ ታጋይ ለመሆን ትልቁ ቅድመ ሁኔታ ፅኑ የአማራ ብሄርተኛ መሆን ነው፡፡ ፅኑ የአማራ ብሄርተኛ ለመሆን ቅድመ ሁኔታው ደግሞ የብሄርተኝነትን መሰረታዊያንን (the basics) ጠንቅቆ ማወቅ ነው፡፡ ፍንትው ያለ አታጋይ ርእዮት ካለን ጠንካራ ድርጅቶችን ለመገንባት አንቸገርም፡፡ የአቅጣጫ መምታት አይገጥመንም። ስለዚህ ሁልጊዜም ብሄርተኝነትን ለማወቅ እናትጋ!

ለምሳሌ የብሄርተኝነትን እና የሶሻሊስቶችን ሁኔታ መገንዘብ ብዙ ነገርን ይቀይራል፡፡ ሶሻሊስቶች ብሄርተኝነትን የሰራተኛው ደላይ ህሊና (false consciousness) የሚፈጥረው አላፊ-ጠፊ ነገር እንደሆነ አድርገው ነበር የሚቆጥሩት፡፡ አቅሙን አሳንሰውና አቃለው ነበር የሚገነዘቡት፡፡ በእነሱ እምነት የአንድ ብሄር ድሃ እና ሀብታም ጠላት ናቸው፡፡ ጠላትነታቸው ደግሞ ስር የሰደደና ሊፈታ የማይችል ነው፡፡ ለሶሻሊስቶች አቶ ብዙአየሁ ታደሰ (የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤት) እና አንድ የአማራ ድሃ ሰራተኛ ጠላት ናቸው፡፡ ወንድማማቾች አይደሉም፡፡ ቅራኔያቸውም የማይታረቅ ነው፡፡

ብሄርተኝት የነ ማርክስን ፍልስፍና ፉርሽ ያደረገ ነው፡፡ ከዘመናዊነት ጋር ይጠፋል ሲባል የኮምኒዝምን ሥርአተ ቀብር አውጆ ግንግኖ የወጣ ርእዮት ነው፡፡ የሶሻሊስቶችን ብቻ ሳይሆን የሊብራል ሉላዊያኑን (liberal globalists) ትንታኔ ፉርሽ ያደረገ ሃያል ርእዮት ነው፡፡

የብሄርተኝነት ልዩ ባህሪው የአንድን ብሄር ድሃና ሀብታም፣ አርሶ አደርና ከተሜ፣ ዲያስፖራና የሀገር ቤት ነዋሪ፣ ሙስሊምና ክርስቲያን ወዘተ አንድ የሚያደርግ ርእዮት መሆኑ ነው፡፡ እከሌ ባለ ሀብት ነው ብለህ እንደ ሶሻሊስቶቹ በጥርጣሬ አትመለከተውም፡፡ እንዲያውም የበለጠ ሀብታም እንዲሆንና ብዙ ሀብታሞች እንዲወጡ ትፈልጋለህ፡፡ እንዲያውም ትመካበታለህ፡፡ እከሌ ሙስሊም ወይም ክርስቲያን ነው ብለህ እምነቱን አጀንዳ አታደርገውም፡፡ በአማራነቱ ብቻ ትወደዋለህ፡፡ የሃይማኖት ነጻነቱ እንዲከበር ትታገልለታለህ፡፡

አማራ የሆነን ሁሉ ያለ ልዩነት የሚያስወድድህ የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ ሁሉም እንደ ወንድምህና እህትህ እንዲሰማህ የሚያደርግህ የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ ያለማንም ቀስቃሽ ለአማራ ወገንህ እንድትደርስ የሚያደርግህ የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ እሱን አጥብቀህ ያዝ፡፡ ህልውናህ የሚከበረው፣ ሃይማኖትክን በነጻነት ማምለክ የምትችለው አማራነትህ ሲከበር ነው፡፡ አማራነትህ ተዋርዶ የሚከበር ግለሰባዊ ማንነት የለህም!!!

https://t.me/MEREWA_MEDIA


መረጃ ባህር ዳር‼️‼️

27/01/2017
ባህር ዳር ቀበሌ 10 የብልፅግና ታጣቂዎች ወጣቶችን እያፈሱ ነው ጥንቃቂ ወይ ይዘህ ውደቅ ከተያዝክ አትመለስም‼️

https://t.me/MEREWA_MEDIA




መረጃ!

በአማራ ክልል ከሰሞኑ በገፍ እየታደኑ የታፈኑት የዩኒቨርስቲ መምህራን፣ ተሰሚነት ያላቸው የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ባለሀብቶች እና ሌሎችም በአራቱም ቀጠና ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ከማነኛውም ጠያቂ ተከልክለው ታጉረው ይገኛሉ።
በጎጃም ቀጠና የታሰሩት ዳንግላ እና ብርሸለቆ፣ በጎንደር ቀጠና የታሰሩት ጭልጋ ሰራባ ወታደራዊ ካምፕ፣ በወሎ ቀጠና ኮምቦልቻ ጮሪሳ ከሚገኝ ካምፕ፣  በሸዋ ቀጠና ደብረ ብርሃን አካባቢ በሚገኝ ካምፕና ኦሮሚያ ክልል መታሰራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

የታሳሪዎቹ ቁጥር ከ7000 እንደሚበልጥም ታውቋል!

belay manaye

https://t.me/MEREWA_MEDIA


ሰበር  ዜና
የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ባንዳ አድማ ብተናና ሚሊሻ ላይ በደብረብርሃን ከተማ መብረቃዊ ጥቃት ሰነዘረ።
       መስከረም 27/2017 ዓ/ም
       ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ
የአማራ ህዝብን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋለሁ በሚል ድንፋታ ወደ አማራ ክልል ዘው ብሎ የገባው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ወራሪ ሰራዊት በተለያዬ ቦታ የእሳት እራት ከመሆን አልዳነም።ይህንን ፕሮጀክት በውጤታማነት ለመፈፀም ይረዳ ዘንድ ባንዳ አድማ ብተና፣ሚሊሻ እና ፓሊስን እራሱን መከላከያ ብሎ ከሚጠራው መንጋ ጋር  በማቀናጀት በተደጋጋሚ ወደ አማራ ምድር ቢያቀናም ወደ አፈርነት ከመቀየር ሊታደጉት አልቻሉም።
በዛሬው እለትም በአራቱ የአማራ ግዛቶች የምንገኝ የአማራ አደረጃጀቶች ማለትም የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ፣የአማራ ፋኖ በወሎ፣የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ በጎጃም ያስተላለፉትን የመንገድ ክልከላ ተግባር  ለማስከበር ደብረብርሃን ከተማ ልዩ ስሙ  ሰን ሻይን ካምፕ ጀርባ አካባቢ በተሰማሩ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ አባላት ላይ ጥቃት ለመሰንዘርና መንገዱን ለማስከፈት መነሻውን መሀል ደብረብርሃን ያደረገ በ4 አይሱዙ የተጫኑ ባንዳ አድማ ብተናና ሚሊሻ በ2 ፓትሮል የተጫነ አመራርና ሎጀስቲክ በነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ በተመራ የልዩ ዘመቻ ቡድን ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ ተሽከርካቹን  ከጥቅም ውጭ ማድረግ ተችሏል።
በዚህ ልዩ ኦፕሬሽንም ፋኖ በረከት ወርቁ ታደሰና በረኸት ወርቁ በታሪክ የሚመዘገብ ጀብዱ ፈፅመዋል።
ዝርዝሩን እመለስበታለሁ።

     "ድላችን በክንዳችን"

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል!

https://t.me/MEREWA_MEDIA

20 last posts shown.