Репост из: Nathan's perspective
መላዕክትን የሚያጸናው መልዓክ
ነቢዩ ዳንኤል ለ ሶስት ሱባዔ በ ጾም እና በብዙ ጸሎት ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጥያቄውን አቀረበ ። ጸሎትን የሚመልስ እግዚአብሔርም የሱባዔውን መልስ በ መልዓኩ እጅ ወደ ባርያው ወደ ዳንኤል ላከ።
"ፊቱ እንደ መብረቅ አይኖቹም እንደ ነበልባል ፋና" የሚያበሩለትን የዛን መልዓክ ግርማ ባየ ጊዜ ዳንኤል ጸንቶ መቆምን አልቻለም ከመልዓኩ ግርማ የተነሳ ምንም ሃይል አልቀረለትም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፋ
ብርሃናዊው መልዓክ እጁን ልኮ በዳሰሰው ጊዜ ዳንኤል ሃይልን አጊኝቶ ቀጥ ብሎ ቆመ "በርታ ጽና" ብሎ መልዓኩ በስልጣን ተናግሮታልና ዳንዔል በረታ ጸናም።
ዳንኤልን ያበረታው ሌላ መልዓክ አለቃው ስለ ሚሆን ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲል መሠከረ "የጸሎትህን መልስ ሊያስቀር ዲያቢሎስ በ አየር በተዋጋኝ ጊዜ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።" ዳንኤልን እንዲረዳ የተላከውን መልዓክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳው ዳንኤልን በአፉ ቃል "ጽና" ብሎ ያጸናውን መልዓክ ቅዱስ ሚካኤል በእውነት አጸናው። መልዓኩም እንዲህ ብሎ መሰከረ"“ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።”
— ዳንኤል 10፥21