የሱና ቤት አጫጭር መጣጥፎችና ምክሮች ለኛ 📖✍


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана



Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


✍بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ 〰〰〰

" የሐጅና ኡምራ አፈፃፀም ከትናቱ የቀጠለ (ክፍል⑦)„„„„„„„„„„„✍

📌በዚህ የቁርአን አንቀጽ ሐጅ ላይ አሏህ ሶስት ነገሮችን ከልክሏል„„„„„„„„1ኛው ,,ረፈስ,, ነው. ረፈስ ማለት ግብረ„ስጋ ግንኙነት ሲሆን. ወደዛ የሚወሰወዱ ነገሮችን ፣ጸያፍ ንግግሮችንና ተግባሮችንም ያካትታል።

2ኛው፣ ፋሱቅ ነው,ፋሱቅ ፣ማለት ከአሏህ ትዕዛዝ ማፈንገጥ ሲሆን ሁሉንም የወንጀል አይነቶች ያካትታል ፣ለምሳሌ ወለድ መብላት፣መስረቅ ፣ሀሜትና ፣ወሬ ማመላለስ ይገኙበታል በመሰረቱ እነዚህ ነገሮች ከሃጅ ውጭም የተከለከሉ ናቸው ሀጅ ላይ ሆኖ እነዚህን ወንጀሎች መፈጸም ደግሞ ቅጣቱ የከፍ ይሆናል።

3ኛው፣ "ዲጃል ነው"ድጃል ፣ማለት ክርክር ማለት ሲሆን በዚህ ስር ማንኛውንም ለግጭትና ለቁጣ ሰበብ. ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ ይካተታል።አሏህ ከነዘከህ ክልከላዎች አስከትሎም እንድንፈራው ፣አዞናል።የአሏህ ፍራቻ ተግባራዊ የሚሆነው ደግሞ ያዘዘውን በመከልከል የከለከለውን በመከልከል ነው ።ነብዪ ሰሏህ አይህ ወሰለም ሐጅና ኡምራ ውጊያ የለለበት ጂሃድ እንደሆነ ተናግረዋል።ሐጅ ስነ ምግባራችንን የምናሻሽልበት. ነፍሳችንንም የምንገመግምበት አጋጣሚ ነው።ከዚህም በተጨማሪ ትዕግስት በተግባር የምንማርበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። ይህንንም የሀጅ ስነ ስርአትና ህደት ላይ ሊገጥሙን የሚችሉ ውጣ ውረዶችን በመቋቋም እንድሁም ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩና የየራሳቸው ባህል ካላቸው ሰዎች ጋር በረካታ ቦታዎች ላይ በምንገኝበት ጊዜ ትዕግስትና መልካም ባህሪ ከመቼውም ባላይ ይበልጥ አገብጋቢ ይሆናል ።በተለይም መጥፎ ባህሪ ያላቸው ሰዎች ሲገጥሙን ላሳዪን መጥፎ ባህሪይ ተመሳሳይ አጻፍ ከመመለስ ታቅበን. ትክክለኛውን የሙስሊም ስነ ምግባር ልናሳያቸው ይገባል እንደዚሁ ከሀገር ወጥተው. አስከሚመለሱ ድረስ ሊገጥሙን በሚችሉ ነገሮች ከመበሳጨት መታቀብ ተገቢ ነው ።ከላይ እንደተጠቀሰው ሐጅና ኡምራ ውጊያ የለለው ጅሃድ ነው። ለጅሃድ ወጥቶ ሳይደክምና ውጣ ውረዶች ሳይገጥሙት የሚመለስ. ሰው የለምና ታገሱ!አሏህም ታጋሾችን ይወዳል።ለአሏህ ተብሎ የሚደረግ ጉዞና እቅስቃሴ ላይ የሚገጥሙ ችግሮችም የወንጀል ማበሻና የደረጃ ከፍ ማድረጊያ ናቸው ።
"አሏህ ከታጋሾች ጋር ያድርገን "

"ሚቃት ,ሐጅና ኡምራ የሚጀመርባው ወቅትና ቦታዎች በሚል ይቀጥላል


ሰለፍያ ቢንት አህመድ ✍

⤴️አንብበው ሲጨርሱ ሸር ማድረግን አይዘጉ
↙↙↙:⇊
https://t.me/Bint_Ahmed_aselefy


◼️እውቀትን አሰራጭ‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖

➲ዳኢ ሆነህ ሰዎችን መጥራት ባትችል፦ የዱአቶችን ዳእዋ ለሌሎች አድርስ።

➲ኡለማ ሆነህ ሌሎችን መጥቀም ባይሆንልህ፦ የኡለማዎችን ጠቃሚ ምክር ለሌሎች አሰራጭ።

➲ሙፍቲ ሆነህ ፈትዋ መስጠት ቢያቅትህ፦ የሙፍቲዎችን ፈትዋ ላልሰሙት አስተላልፍ።

↪️ በዚህ ፊትና በበዛበት፣ ሰዎች የሚይዙትና የሚጨብጡት ባጡበትና የጥመት ሰዎች በተበራከቱበት በዚህ ከባድ ዘመን፦ የሱና ኡለማዎች፣ መሻይኾችና ዱአቶች ዳእዋ፣ ምክር፣ ፈትዋና ፅሁፍ በቻልከው መጠን ማሰራጨትህ እንደ ቀላል አትመልከተው። ይህ ኢኽላስ ከታከለበት ትልቅ ስራ መሆኑን ተገንዝብ።

↪️ ይህ ማድረግህ ተውሂድና ሱና እየረዳህ፣ ቢድአና ሽርክን እያወደምክ፣ የሱና ሰዎች የበላይ እያደረክ መሆኑን አትዘንጋ። በዚህ ላይ የቢድአና የስሜት ተከታዮች ሊበልጡህ በፍፁም አይገባም።

💦ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ።

✅ ከሞተ በኋላ ስራው እንዳይቋረጥ የፈለገ ሰው ኢልም በማሰራጨት ላይ ይጠንክር።
📚{ التذكرة (55)}

💦ኢብኑ ባዝ አላህ ይማራቸውና እንዲህ ብለዋል።

✅ ሙስሊሙ ወንድሜ ሆይ❗️ኢልም ለሰዎች በማሰራጨት ላይ ልትጓጓ እንዲሁም ጥሩ ነሻጣና አቅም ሊኖርህ ይገባል። የባጢል ሰዎች ባጢልን በማሰራጨት ካንተ ሊበልጡ አይገባም። ሙስሊሞችን በዲናቸውና በዱንያቸው ጉዳይ ላይ አቅምህ በቻለው ልክ ለመጥቀም ሞክር።
📚[مجموع الفتاوى (67/6)]

👉የአላህ መልእክተኛም እንዲህ ብለዋል
【بلغوا عني ولو آية】
{ከኔ አንዲትም አንቀፅ ቢሆን አስተላልፋ}


https://t.me/IbnuTeymyaYesunawAmbesa




➡️ከአቢ ሰኢድ አል ኹድሪ ረዲየሏሁ አንሁ )ተይዞ የአላህ መልእክተኛ እንድህ ብለዋል፣

✅የሚታገስ ሰው አላህ ያስታግሰዋል ።አንድም ሰው ከትግስት የተሻለ ስጦታ አልተሰጠውም ።
📚[ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል]


🔺ما هي وصيتك لطالب العلم في هذا الزمن؟

🎙 د. عبدالعزيز بن ريس الريس


Репост из: 🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»🎀
〰〰〰✔️#ሐያእ" ✔️〰〰〰〰

ሐያእ ሰፊ ትርጉም ያለው ቃል ነው።
🔺ሐያእ ማለት ሐያት "ሕይወት" ነው ይሉታል አንዳንዶቹ አስፈላጊነቱ ከፍ ያለ መሆኑን ለማስረዳት።


✍ሐያእ ...
☞ሥርዓት መያዝ፣
☞ ትሁት መሆን፣
☞ይሉኝታ ማድረግ፣ አላህን፣ ሰውንም ሆነ ፍጥረታትን ማፈር፣
☞የራስንም ሆነ የሌሎችን ክብርና ሞገስ መጠበቅ .... ነው።


🔺ሐያእ የእስልምና ሃይማኖት ታላቁ ሥነምግባር ነው።
ነቢያችን ሰለሏሁአለይሂ ወሰለም ሁሉም ሃይማኖት ሥነ-ምግባር አለው፡፡ የኢስላም ሥነ-ምግባር ሐያእ ነው፡፡› ብለዋል ።


🔺 ሐያእ የአላህ ነቢያትና ታላላቅና ደጋግ የአላህ ባሮች የተዋቡበት ሁሉ ነገሩ መልካም የሆነ ባህሪ ነው፡፡

🔺ሐያእ ዛሬ ላይ እየተረሱ ካሉ መልካምና ምርጥ ሥነምግባራት መካከል አንዱ ነው።

♦በጥፋት አለማፈር፣

♦ በወንጀል አለማፈር፣

♦ ይሉኝታ ቢስ መሆን፣

♦ የዕውቀትና የዕድሜ ባለፀጎችን አለማክበር፣

♦ ለሰው ልጅ ክብርና ሞራል አለመጠንቀቅ

.
ሐያእ ማጣት ነው።✍

◈━━━━━━━━◈━
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya


Репост из: ኢብኑ ተይሚያ የተውሂድ የሱና ቻናል
ጧሊበል ኢልም ናቸው ወይም ትንሽ የተሻለ እውቀት አላቸው የሚባሉ አንዳንድ ሰዎች የተበላሸ አህላቅ ስትመለከት ሰለፎች ከኢልም በፊት አደብ የመማር አስፈላጊነት በተመለከተ የመከሩት ምክር አንገብጋቢነት ትረዳለህ። እውቀታችን በጨመረ ቁጥር ለአላህ ያለን ፍራቻ፣ ተዋዱእ (መተናነስ)፣ ተቅዋና አህላቃችን እየተስተካከለና እየጨመረ መምጣት አለበት።


Репост из: 🎀ጥቂት ማስታወሻ ለሙስሊሟ እህቴ🎀
ኒቃቤ

አዎ እንቁ ነኝ ሽልምልም በኒቃቤ ኩሩ

ጠላት ቢንገበገብ ቢቆጩብኝ ቢያሩ

ድንጋይን ፈንቅለው ጉድጓድ ቢቆፍሩ

ይመክትልኛል ዐልዩ ከቢሩ

ሰሚ ነኝ ታዛዥ ነኝ ጌታዬን አፍቃሪ

ነቢዩን ተከታይ በሱናቸው ሰሪ

ይህ ነው መሰረቴ የመኖሬ አላማ

አላህን ብቻ ማምለክ በዱንያው አውድማ

ነገ እንዳጭድበት የአኼራን ምንዳ

ፍጻሜዩ እንዳይበላሽ እንዳይሆን ነዳማ

ኒቃቤ! መማሬን አያቅብ መሰራቴን አይገታ

ሀራም ከሌለበት ድብልቅ ጋጋታ

አዎ አበርካች ነኝ መልካም አስተዋጾ

ትውልዶችን መልማይ በኢስላም አንጾ

ይህን የቸረኝ አምላኬ ምስጋና ተገባው

እኔስ ተደነቅኩኝ ለታላቅ ልእልናው!

ይቀጥላል ……

✍ bint hashim

https://t.me/Hanu_bint_hashim


:°• አቂዳው የተበላሸ አካል ጋር ህይወት መቀጠል እጅግ በጣም ከባድ ነው ።

°• ህይወት በዚች አለም ብቻ ሳይሆን በአኼራም ይቀጥላል ስለሆነም አቀማማጭሽን ምረጭ ትንሺ ያወቀ መስሎት የተወዛወዘ አቂዳ ተሸክሞ ትክክልኝ ነኝ ብሎ መስመሩን ያልጠበቀ ጉዞ ከያዘ አካል ጋር ህይወት ከመቀጠል ሰላም ያለው ብቼኝነት ውበት ነው።

°•• በጥመት አቂዳ አውቃለሁ ከሚለው ምንም የማያውቀው አዕምሮው በቡድተኝነት ያልተበከለው ይሻላል : ስለሆነም ትኩረት ለአቂዳችን በተለይ የኢኽዋኖችን አቂዳ የጠጣ እኳን ለትዳር ለጉርብትናም አይበጅ።

°•ህይወት ሙሉ የምትሆነው ሁላችንም የአላህን) መብት በተገቢውና በትክክለኛው መስመር ስንጠብቅ ያኔ ህይወት ሙሉ ትሆናለች።

°• ሰለፍያ ቢንት አህመድ (ኸድጃ)✍

🔎🔎https://t.me/Bint_Ahmed_aselefy


ጀግናዬ የንግግር ብቻ ሳይሆን የተግባር አቋም ይኑርህ!

ከመናገርም ከመስራትም ባሻገር
ተግባሩ ላይ ካለህ ያኔ አንተ የንጉሶች ሁሉ ንጉስ ነህ ።

የአውቀት ፍሬው ተግባር ነው!


ያ ካልሆነ ባዶ ፍከራ ከንቱ ልፍት ነው!

ቢንት አህመድ ሰለፍያ ✍

⬇️
https://t.me/Bint_Ahmed_aselefy


☑️ አንዲት ሴት ቢክራ ናት ብሎ ሊያጫት ሰው ቢመጣ ልትዋሸው አይገባም። አይፈቀድምም። ቢክራ ነሽ ወይ ስትባል ከሆነች አዎ ማለት ካልሆነች ደሞ አይደለሁም ማለት አለባት። ልትዋሽ በፍፁም አይፈቀድላትም። ምክንያቱም በኋላ ብዙ ችግር እንዲፈጠር ያደርጋልና

➡️ ነገር ግን ቢክራነቷን እንዴት እንዳጣች ሰበቡና በማን እንዳጣች መናገር የለባትም። በሀራም መልኩ እንኳ ቢሆን ያጣችው ድንግል ያለመሆኗን ከተናገረች በቂ ነው። ተውበት ካደረገች ለምን አደረግሽው ተብላ ልትወቀስም አይገባም። ወንጀል የፈለገ ቢገዝፍ ተውበት ከተደረገ አላህ ተውበት ተቀባይ ነውና።

✅ የዘመኑ ሴቶች በህክምና የሚያሰሩት ቢክራነት ይህ ፈፅሞ አይፈቀድም። ማጭበርበር ነው። ይህ ተግባር ብዙ ኢማናቸው ደካማ የሆኑ ሴቶች አታሏል። ሴቶች ወደ ዝሙት እንዲገቡ አድርጓል። የትም በመንዘላዘል ማግባት ስፈልግ ድንግልና አሰራለሁ ብለው እንዲያስቡ አድርጓል።

📚 فضيلة الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله تعالى
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru


➡️ እነዚህ ቦታዎች ላይ ከመገኘት ተጠቀቅ
➖ሽርክ የሚሰራበት
➖ቢድአ የሚፈፀምበት
➖ሙዚቃ የሚሰማት
➖ውሸት የሚዋሽበት
➖ኸምር የሚጠጣበት
➖ሰው የሚታማበት
➖ኢህቲላጥ ያለበት
➖ዝሙት የሚሰራበት
➖አላህ የሚታመፅበትና
➖ወንጀል የሚሰራበት ቦታ ላይ
☑️ ከመቀመጥና በወንጀል ከነሱ ጋር እኩል ከመጋራት ተጠንቀቅ

«መጥፎ ነገር ሲሰራ ስታይ በእጅህ ከልክል። ካልቻልክ በአፍህ አውግዝ። ካልቻልክ በቀልብህ እየጠላህ ከቦታው ዞር በል»

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru


📌بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ 〰〰 የሐጅና
ኡምራ አፈፃፀም

〰〰 (ክፍል⑥)

📒 ስነ ምግባርን ማሳመር 📒
📌የሐጅ ወይም የኡምራ ስነ ስርአት ላይ በተለያዩ የኢባዳ ስፍራዎች ላይ የምታገኛቸው የተለያየ ባህሪና ባህል ካላቸው ሰዎች ጋር ፀባይ ማሳመርና መታገስ እንድሁም.በተቻለንወመጠን እነርሱን መርዳት መሞክር አላህ ዘንድ ትልቅ ሚንዳ ከሚሰጡ ተግባሮች አንዱ መሆኑን አትዘጋ ።ጌታችን አሏህ በተከበረው ቃሉ የሚከተለውን ብሏል፣
وَاخْفِضْ جَنَاحَكَ لِلْمُؤْمِنِينَ
ክፍህን ለምዕመናን ዝቅ አድርግ ለአማኞች ተናነስ (,አል ሂጅር 88)
»በጥቅሉ ስነ ምግነባርን ማሳመር ኢስላም ላይ ትልቅ ቦታ አለው ወደ አሏህ ከሚያቃርቡ ቀላል ነገር ግን ትልቅ አጅር ከሚሠጡ ነገሮች መሃል አንዱ ነው ።ነብዩ ሰለሏህ አለይህ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል""" ከዕናተ ውስጥ ጥሩ ከሚባሉት ጸባያቸው. መልካም የሆኑ ሰዎች ናቸው. (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)〰〰〰〰〰〰


📌አሏህን ከማክበር ምልክቶች መሃል አንዱ የእርሱን ትዕዛዝና ክልከላዎችን ማክበር ነው ።የሀጅን ህግጋት ሲገልፅ አሏህ የሚከተለውን ብሏል፣
الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَاتٌ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَجِّ وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ اللَّهُ وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَى وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
📌የሐጅ ጊዜ የታወቁ ወሮች ናቸው ,ከሸዋል አንድ እስከ ዙል ሂጃ 10,ቀኖች በነዚህ ወራት ሀጅ ማድረግ የወሰነና የጀመረ ሰው ሀጁን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ከግብረ „ስጋ ግንኙነትና ወደ ዛ ከሚያደርሱ ነገሮች በሙሉ ፣ከማፈንገጥ ) ወንጀሎችን ከመዳፍር ሐቅን ለማስረዳት ካልሆነ በስተቀር ከክርክር የምትሰሩትን መልካም ነገር ሁሉ አሏህ ያውቀዋል ምንዳውንም ይሰጣችኃል ለሀጅ ጉዟችሁ የሚሆናችሁንም. ስንቅ ያዙ ከስንቆቹ ሁሉ በላጭ ግን በሁሉም ነገር አሏህን መፍራት እንደሆነ እወቁ የልቦና. ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ! (አል በቀራህ 197)*


""ይቀጥላል ኢንሻ አላህ"" ዝግጂት ኡስታዝ አህመድ አደም (ሀፊዘሁሏህ)

"ጸሐፊ ኸድጃ ቢንት አህመድ 📌

በቴሌግራም ለመከታተል
👇👇👇✍https://t.me/Bint_Ahmed_aselefy


ነገ ሰኞ ነው
የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ


Репост из: 🎀ጥቂት ማስታወሻ ለሙስሊሟ እህቴ🎀
እሷ ግን

እንቢ ያንተን መንገድ አልፈልግም ብላ፣

እሱ በውሻሸት በቅጥፈት ሲሰላ፣

ሱናን ይምረጠች ሱንይቷ እህቴ፣

በጣም ውብ እኮ ናት ታምራለች እህቴ፣

ያቺማ ተልጣ ምኑን ታምረኛለች፣

መንገዱን በሙሉ ተከባ በዝንቦች፣

ተሸፈኝ ሲሏት እናንት ሀዳድዮች፣

እስኪ ዝም በሉኝ ልቤ ከተስተካከለ ፣

ብሸፈን ብገለጥ ኢማን መስተካከል ከልቤ ውስጥ ካለ፣

መሸፈኔ ትርጉሙ አይታየኝ ለኔ፣

መልሽላት ለሷ መልስሽን በወኔ

ልብሽ ቢስተካከል ኖሮ ቀጥ ያለ ባቋሙ፣

ሌላው አካሎችሽ ምነው ባልታመሙ፣

ቢስተካከልማ ቢፀዳማ ቀልብሽ ፣

እሺ ባሉሽ ነበር ሌላው አካሎችሽ፣

ቀልብ እኮ ስትፀዳ ስትስተካከል፣

ይስተካከላል ሁሉም ሰውነት አካል፣

ይልቅ እያቸው ውቦቹን በጣም የሚያምሩትን፣

በሒጃባቸው ማይደራደሩትን፣

ዕውነቴነው እህት ውብ እንቁዎች ናቸው፣

በጣም ነው የሚያምሩት ከሩቁ ሲዩአቸው፣

ውዴታ አለኝ ለነሱ፣

በቢድዓ ላልተተራመሱ፣

ሒጃብ መርጠው ለለበሱ፣

የኩፋርን መንገድ ላልወረሱ፣

አሳሩ ሰለፍን ለወረሱ፣

ውዴታያ ነው ለነሱ፣

ለነዚያማ በቢድዓ ለተተራመሱ

የየሁዳን ፊክራ ለወረሱ፣

አሳርን ትተው በቢድዓ ለነገሱ፣

አይወደዱም ከሸሕዋቸው እስኪመለሱ፣

ከሱፍዮች መንደር ከቢድዕዮቹ

ከኢኽዋኖች መንደር ከዘላባጆቹ

ከጀምዕዮች መንደር ከማህበርተኞቹ

ፅድት ፍክት ያሉት ሰለፍይ ሴቶቹ

እኝህን ነው እኔ ውብ ናቸው ያልኳቸው

በ الله መንገድ ላይ ነው የወደድኳቸው።

الحجاب الشرعي واجب على كل النساء المسلمية.

قال الله تعالى في كتابه الكريم : يا أيها النبي قل لأزواجك وبناتك ونساء المؤمنين يدنين عليهن من جلابيبهن ذلك ادناي أن يعرفن فلا يؤذين وكان الله غفور رحيما . سورة الأحزاب

قالت أم سلمة رضي الله عنها لما نزلت [ يدنين عليهن من جلابيبهن] خرج نساء الأنصار كأن الي رءوسهن الغربان من الأكسية.

رواه ابو داود / صحيح حجاب المرأة المسلمة ص (٣٨)


https://t.me/Hanu_bint_hashim
https://t.me/Hanu_bint_hashim


✍በራሷ የምትተማመን ጀግና እንስት ሁኚ

በራስሽ ተማመኚ የህይወትሽን መጀመሪያም ይሁን የመጨረሻ እውነተኛ ለመሆን ሞክሪ ማንነትሽን ዘወር ብለሽ ፈልጊው ፈትሽው❗️

በራሷ የማትተማን ማንነቷን የማታውቅ እንስት አትሁኚ ❗️

ራስሽን ፈልጊው የኡኽታ ✍

አብዛሀኞቻችን ወሬያችን ሌላ አላማችን ሌላ ስራችን ማንነታችን ሌላ በቃ ሌላ ሌላ ነን ❗️

አላህ ከባዶ ፍከራ ይጠብቀን ✍
👇👇👇
https://t.me/Bint_Ahmed_aselefy


Репост из: 🎀ጥቂት ማስታወሻ ለሙስሊሟ እህቴ🎀
‼️በጣም ውቦች ናቸው‼️

እንዴት ነው የሚያምሩት የሱና እህቶች፣

ሒጃብ የሚደፉ ስትር ውብ እንቁዎች፣

የ اللهን ትዕዛዝ ህጉን አክባሪዎች፣

ያላታለላቸው ብጣሽ ቁራጭ ጨርቆች፣

እንዴት ነው የሚያምሩት የሱና እህቶች፣

የ الله ምልክተኛን ሱናውን ወዳጆች፣

ፀባይ የተካኑ ውብ ያማሩ እንስቶች፣

በጣም ነው የሚያምሩት ጥቁር ተሸፋኞች፣

በጣም ውቦች ናቸው ሰለፍይ ሴቶች፣

ሰለፍይ ሴቶች እንዴት ነው የሚያምሩት

እኒያ ጥቁር ሒጃብ ተከናናቢዎች

ባለ ኒቃቦቹ ሰለፍይ እንስቶች

በጣም ያስደሳሉ እኒያ ኒቃቢስቶች

ስድብ ዘለፋውን ሁሉን ተቋቁመው

የወቃሽን ውቅሻ ወደ ጎን አድርገው

የ اللهን ትዕዛዝ ለመፈፀም ቆመው

በጣም ነው የሚያምሩት ሱናን መግጠማቸው

ሀቅን ተቀብለው ህይወት መምራታቸዉ

መልዕክተኛውንም ሞዴል ማረጋቸው

ዓዒሸቱን መስለው መውጣታቸው

መራቆትን ጠልተው መሸፋፈናቸው

ከኢኽቲላጡ ቦታ ቦታን መልቀቃቸው

ስትር ዓደበኛ ቁጥብ መሆናቸው

ሀያዕ የተሞሉ ሳይቀር ባረማመዳቸው

በጣም ውቦች ናቸው ያምራሉ በጣም፣

ጁወይሒል ቢያላግጥ ቢገረም፣

ረጅሙን ጥቁሩን በመልበሷ ቁጭት አንገብግቦት፣

የሸይይጧንን መንገድ እንድትይዝ አምሮት፣

የሸቀጥ ማጣሪያ ፈልጎ ሊያደርጋት ፣

በየ ቅባቱ ላይ ፓስቸሩ ሊያደርጋት፣

ለንግድ ለሱቁ ማጣሪያ ሊያደርጋት፣

እሷ ግን ፡-

ይቀጥላል✍✍✍✍

https://t.me/Hanu_bint_hashim


◾️አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።

✅ ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ የጅሙአ ቀን ነው። በዚህ ቀን ውስጥ ኣደም ተፈጥሯል፣ ወደ ጀነትም እንዲገባ ተደርጓል፣ ከጀነትም እንዲውጣም ተደርጓል። ሰአቲቷ (ቂያማ) አትቆምም የጅሙአ ቀን ቢሆን እንጂ።

📚(ኢማሙ ሙስሊም ዘግቦታል)


ማንም ምንም ከአሏህ አይሰወርም‼️
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
▪️ትክክለኛ ስምና ማንነታችሁን ደብቃችሁ የሻችሁን የምትጽፉ የምትናገሩ ሰዎች ባያውቋችሁ !አላህ እንደሚያውቃችሁና በምታደርጉት ሁሉ እንደሚተሳሰባችሁ አትዘንጉ።

↪️አላህም በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል።
【إِذْ يَتَلَقَّى ٱلْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ ٱلْيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِيدٌ】
▪️ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡

【مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ】
▪️አንድ ሰው ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላኢካዎች) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡
📚 سورة "ق" (18-17)


https://t.me/Bint_Ahmed_aselefy


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ብቻ አላህ አይርሳህ!
~~ ~~~~
ስምህ በታሪክ መዝገብ ውስጥ መስፈር አለመስፈሩ አያስጨንቅህ። እሱ የስኬት መስፈርት አይደለም። አላህ መርጦ ከላካቸው ነብያት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው ስማቸው ለታሪክ የቀረው? ከጥቂትም በጣም ጥቂት! ጠቢቡ ጌታ እንዲህ ይላል፦
﴿وَرُسُلًا لَمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ﴾.
{ባንተ ላይ ያልተረክናቸውም መልእክተኞች (ልከናል።} [ኒሳእ፡ 164]
ግና ታሪክ ባይዘክራቸው፣ ሰው ባያውቃቸውም ሁሉ በእጁ ከሆነው ሃያል ጌታቸው ዘንድ የከበሩ ናቸው፣ ደረጃቸው ከፍ ያለ። አብዛኞቻችን የምንዘናጋበት የኢኽላስ ጉዳይ!

Показано 20 последних публикаций.

291

подписчиков
Статистика канала