ማንቂያ ደውል!!
وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ مَّاذَا تَكْسِبُ غَدًا ۖ وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ بِأَيِّ أَرْضٍ تَمُوتُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም፡፡ አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
💢ሞት ሚባለው ነገር ታመህ የምትሞት ብቻ ነው የሚመስልህ አይደል ?
ድንገተኛ ሞት ስታይ አንተጋር ሚደርስ አይመስልህም አይደል?
አስተውለህ ታቃለህ ግን???
👉በተኛህበት እኮ ሊወስድህ ይችላል ጠዋት ቤተሰቦቼ ይቀሰቅሱኛል ስትል ነኪርና ሙንከር አስደንግጠው ሚቀሰቅሱበት ቀን እኮ መች እንደሆነ አታቅም ።
⭕️እስተውል ጠዋት አነጋለሁ ብለህ
በስልክህ ሃራም ተመልክተህ
👉ሃራም ፖስት አድርገህ
ፎቶሽን በትነሽ ፎቶህን በትነህ
👉ቢዳዓ ኹራፋት በቻናል በትነህ
👉ዒሻእ ሰላት ሳሰግድ በሚዲያ ፍጥጥ ብለህ እገሌ እገሌ እያልክ ባላወቅከው ስትቀባጥር
👉ውስጥህ እንደማያገባት እያወቀ ለጊዜያዊ ስሜት እህትህን ስታባልግ ቻት ስታደርግ።
👉ቀኑ ላይ ወላጆችህን አስከፍተህ
👉ሚስትህ ካንተ ጋር እየተጨዋወተች ደስ የሚል መኝታ ልታሳልፍ ለአልጋ ፈልጋህ አንተ ግን ስልክህ ላይ አፍጥጠህ:
👉ብር ኪስህ ውስጥ አስቀምጠህ የቅርብ ቤተሰቦችህ ተርበው
♨️ጠዋት አነጋለሁ ብለህ ተኝተህ ጠዋት ላይ የቀጠርከው አላርም ወይም ቤተሰብ ስትጠብቅ ድንገት ያቺ ጠባብ ቤት ውስጥ እራስህን ካገኘህ እና ሚያስፈሩ ሁለት መላአይካ የቀሰቀሱህ ቀን ዋ ቁጭትህ!! ዋ ፀፀትህ!ዋ ድንጋጤህ
👉ወሏሂ ቢሏሂ ተላሂ ቀኑ ሩቅ አድርገህ እንዳታስበው በጣም ቅርብ ነው
አሁን ያለንበት ሁኔታ የተረዳ ሰው ስለሞት መረዳት ለሱ ቅርብ ነው ።
ስለዚህ ወንድሜ /እህቴ ንቃ/ንቂ
በዚህች ምድር የሆነን ጥፋት ካጠፋህ ፖሊስ ይዘሃል እስር ቤት ትገባለህ ሽሮ በልተህ ትወጣለህ ኻላስ
አሏህ ግን ይታገሰሃል!! ይታገሰሃል !!ይታገሰሃል!! የያዘህ ቀን ግን አያያዙ የበረታ ነው። ልብ በል
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ شَاقُّوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۖ وَمَن يُشَاقِّ اللَّهَ فَإِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን በመከራከራቸው ነው፡፡ አላህንም የሚከራከር ሰው (ይቀጣዋል)፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡(ሃሽር 4)
በሰራኸው ደሞ እያንዳንዱ ትያዛታለህ ቆም ብለህ አስብ
كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ
ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡
(አል ሙደሲር 38)
አበቃሁ ወንድሜ ይህ የታናሽ ወንድምህ ምክር ነው እስቲ አሁኑኑ ወስን ሞትን ተጠባበቃት ካለህበት ወንጀል ተላቀቅ የተውበት በሩ ሁሌም ክፍት ነው።
✍️Abu_Selman abdulalim
https://t.me/abuselmanprofile