WKU Muslim student ጀምዓ(አስ ሰለፊይ)


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


በዚህ ቻናል የጀምዓው የቂርዓት የዳዕዋ እና መሰል የጀመዓው ፕሮግራሞች ይተላለፍበታል ኢንሻአላህ።
https://t.me/WKUMuslimstudent

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ውድ ወደ ወልቂጤ  ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የሬሚዲያል ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ!!
                                    አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ

ወደ ወልቅጤ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (remedial) ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ
ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ  እንደሚታወቀው በ2016 ዓ.ም ወደ ወልቂጤ  ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የሬሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥር 27 እና 28  2016 ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል።

ስለሆነም ይህን በማስመልከት የወልቂጤ  ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ሙስሊም ወንድምና እህቶቹን ተቀብሎ ማንኛውንም ዲናዊም ሆነ አካዳሚክ  መረጃዎችን  ለመስጠት እንዲሁም ስለሌሎች ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉ አዲስ ነገሮች በሙሉ  የሚያስፈልጓችሁን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ  ሙሉ ዝግጅታቸውን አድርገው የናንተን መምጣት ብቻ  በጉጉት እየጠበቁ  ይገኛሉ።
ስለዚህ ስለሚያስፈልጋችሁ ማንኛውም አይነት ጥያቄም  ይሁን ትብብር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልኮች ደውላችሁ ሙሉ መረጃ ማግኘትና እና ያለምንም እንግድነት ስሜት ውድ ጀመዐችንን መቀላቀል ትችላላችሁ ስንል ትብብራችንን እንገልጻለን።
አላህ እኛንም እናንተንም ሰላም አድርጎ በሰላም እንዲያቀላቅለን እንጠይቀዋለን!!




             1)ወንድም Yusuf A.


              ስ.ቁ 09 67 62 30 89

                2)ወንድም AWOL A

                 ስ.ቁ 09 60 37 36 34

              3)ወንድም Abdulmejid M.

                09 14 61 01 62


NB: እህቶች ከላይ ባሉት ስልኮች በመደወል የእህቶችን ስልክ ማግኘት ትችላላቹ!!!


Kabajamtoota barattoota muslimaa sirreeffamaa haaraa Yuunivarsiitii Wolqiteetti ramadamtan hundaa!!

            Assalamu Alaikum Warahmatullahi Wobarekathu
Barattoota muslimaa sagantaa sirreeffamaati
in Yuunivarsiitii Wolqiteetti haaraa ramadamtan hundaaf, barattoonni sirreeffamaa Wolqiteetti ramadaman ta'uu beekuu barbaanna University in the year 2016 will enter on January 27 and 28, 2016. A.D. jedhamuun beekama

Kanaaf kana yaada keessa galchuun barattoonni muslimaa Yuunivarsiitii Wolqite isin obboleeyyan isaanii muslimaa ta'an isin simachuuf qophii guutuu ta'aniiru isin odeeffannoo amantaa ykn barnootaa kamiinuu yoo qabaattan, akkasumas deeggarsa fi tumsa isin barbaachisu hunda isiniif kennuuf, akkasumas dhufaatii keessan hawwii guddaan eeggachaa jirtu.
Kanaaf gaaffii ykn tumsa gosa kamiyyuu yoo barbaaddan bilbiloota armaan gaditti tarreeffaman bilbilaa, odeeffannoo guutuu argadhaatii miira keessummeessituu tokko malee Jama'aa keenya jaallatamotti makamaa



    
Obboleessa REMEDAN S.


Lakk 09 16 45 35 31


Репост из: 💢ተጅዊድ አህካም(ተጥቢቅ) እና መልእክት አዘል ፕሮፋይል።
አስፈሪ ሃዲስ
በተለይ አሁን ያለንበት ላይ ለእህቶች

(("ራሶቻቸው እንደግመል ጉብታዎች የሚያደርጉ ጀነት አይገቡም ሽታዋንም አያገኙም።"))ሙስሊም ዘግበውታል

ገርሞ ገርሞ የሚገርመው እና
ለራሴ በጣም የሚገርመኝ ነገር ስነግራችሁ


የሚያምር ምስሏቸው ከኋላቸው ትልቅ ሸክም ሚሸከሙት እህቶች ነገር እኮ ነው
የመሸከም ድካም ብቻ ቢሆን ጥሩ ነበር
👉የሸክም ድካም አንድ
👉ጀነትን ቀርቶ ሽታዋንም ያለማግኘት ኪሳራ አሏህ ይጠብቀንና

ሁለተኛ ገርሞ የሚገርመው
ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይህን ሃዲስ ሲያስተላልፉ እኮ  ሴቶች የራሳቸው ፀጉርን ከፍ እንዳያደርጉ ነበር ትኩረቱ አሁን እኮ ሆን ተብሎ ተዘጋጅቶ የሚሸጥ ትልልልቅ ከኋላ የሚደረግ ፀጉር መያዣ ተዘጋጅቶ እኮ ነው ሚሸጠው አይገርምም እሱን አንስቶ ከኋላ መጫን ምንም ላይከፈልሽ
ከዚም አልፎ እንዲህ የሚያስፈራ ሃዲስ መጥቶልሽ

ተይ እህቴ አሁንም እድሉ አለሽ ወደሱ ተመለሺ !!
በዚህ ሁኔታ አሏህን ከተገናኘሽው የከፋ ነው።

https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile


አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ይህን ሙሃደራ👆👆 ሁላችንም እናዳምጠውና እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ
ባረከላሁ ፊኩም!!!




ሱረቱል ፋቲሃን ረጋ ባለ እና በሚገርም ተጅዊድ አቀራር


ሳታደምጡት አትለፉ አቀራራቹንም አስተካክሉ

ለይበል ጥተጅዊድ አህካም
👇👇👇👇👇
https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile


Репост из: 💢ተጅዊድ አህካም(ተጥቢቅ) እና መልእክት አዘል ፕሮፋይል።
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ተጅዊድ ክፍል((( ሰባት)))

  تخليص الضاد من الطاء والتاء بكل سهولة، فمن اضطر، ثم أضطره، نضطرهم، فرضتم،  الرخاوة والاستطالة

ዷድض ስኩን ሆና ከኋላዋ ጧط ፊደል ሲመጣ እንኔት እናንብበው

ለض ኢስቲጧላ ባህሪዋን እንዴት እናንብብ ??

ዷድض  እና طጧ    ኢጥባቅالإطباق እና ኢስቲዕላዕ ባህሪያቸው እንዴት አድርገን እናንብባቸው??

🔻በጣም ጥንቃቄ ሚፈልግ ቦታነው🔻 🔻🔻🔻

ለሰከንዶች ሰብር አድርጋችሁ አድምጡት ከዛ ደጋግሙት
ከዛ ተግብሩት ባረከሏሁ ፊኩም


ተጨማሪ የተጅዊድ አህካሞችን ለማግኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ👇👇👇👇
https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile

👉ወንድም እህቶቻችን ቁርአንን በትክክል እንዲያነብ share  share አድርጉት


Репост из: 💢ተጅዊድ አህካም(ተጥቢቅ) እና መልእክት አዘል ፕሮፋይል።
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
(((ተጅዊድ)))ክፍል ሶስት

💢ቁርአን ውስጥ አንዳንድ ቦታ እንዴት አድርገን ለማንበብ ጥያቄ የሆነባችሁ ቃላቶች ለ እነዚህ ልዩ የሆኑ ቦታዎች እንዴት እናንብብ??



ለሰከንዶች ሰብር አድርጋችሁ አዳምጡት

ከዛ ተግብሩት
https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile


Репост из: 💢ተጅዊድ አህካም(ተጥቢቅ) እና መልእክት አዘል ፕሮፋይል።
((ልብ ያለው ልብ ይበል!!!))


👉ብዙ የተሰጡህ ፀጋዎችህ ስትነፈግ;
👉ብዙ የህይወት አጣብቂኝ ውስጥ ስትገባ;
👉ህይወት ስጠብህ

ለራስህ ቆም ብለህ አስብ!!

አለህን ስታምፅ ብዙ ፀጋዎችህን ታጣለህ !
ወደአሏህ ስትመለስ የተወሰዱብህ ፀጋዎችህ በአምሳያው ይመለሱልሃል!!!

ፍጠን ፀጋዎችህን አስመልስ!!

https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile


👉(((አስቸኳይ ጥያቄ)))

ሰላትህ ላይ ምን ላይ ነህ⁉️
ጭራሽ ትተኸዋል⁉️
እያቆራረጥከው ነው⁉️
ፈጅርን ዘለህ 4ቴ ብቻ ሰጋጅ ነህ⁉️


የሚገርመው እኮ ሃረጎች እና ዛፎች እኮ ያለማቋረጥ እየሰገዱ እንደሆነ ተረድተሃል❓❓

وَالنَّجْمُ وَالشَّجَرُ يَسْجُدَانِ
ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡

አንተስ ??

ወንድሜ ይቺ ንግግር ሰበብ ትሁንህ እስቲ አሁኑኑ ሞት ሳይቀድምህ ለፈጠረህ ሃያሉ ጌታህ አጎንብስ

ልብ በል ‼️
ልብ በይ‼️
👉እስቲ ስለ አስፈሪ ቅጣቱ ደግሞ (ላስታውስህ)ልጠቁምህ ቁርአን ላይ ቃለ ምልልሱ ተመልከት ሱረቱል ሙደሲር ከ41-43 👇👇👇👇👇👇
عَنِ الْمُجْرِمِينَ👉
مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ❓👉
قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ❗️👉
ከአመጸኞቹ ኹኔታ፡፡
ይሏቸዋልም) «#በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»
(እነርሱም) ይላሉ «#ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡

👉 #ከሰጋጆቹ #አልነበርንም፡፡
👉 #ከሰጋጆቹ #አልነበርንም፡፡
ልብ እንድትል ነው የደጋገምኩልህ

አበቃሁ ወንድሜ አበቃሁ እህቴ አሁኑኑ ቆርጠህ ተነስ አሁኑኑ ቆርጠሽ ተነሽ አስፈሪው ቀብር ሳያጨልምህ/ሽ

እንዳንተው ብዙ እያሰቡ ሳይመሽ የጨለመባቸው ብዙ አሉ እና ያ እጣፋንታ ሳይደርስህ ፍጠን!!!


ታናሹ ወንድምህ ✍️Abu selman
https://t.me/abuselmanprofile
https://t.me/abuselmanprofile


ማንቂያ ደውል!!

وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ مَّاذَا تَكْسِبُ غَدًا ۖ وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ بِأَيِّ أَرْضٍ تَمُوتُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም፡፡ አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

💢ሞት ሚባለው ነገር ታመህ የምትሞት ብቻ ነው የሚመስልህ አይደል ?

ድንገተኛ ሞት ስታይ አንተጋር ሚደርስ አይመስልህም አይደል?

አስተውለህ ታቃለህ ግን???
👉በተኛህበት እኮ ሊወስድህ ይችላል ጠዋት ቤተሰቦቼ ይቀሰቅሱኛል ስትል ነኪርና ሙንከር አስደንግጠው ሚቀሰቅሱበት ቀን እኮ መች እንደሆነ አታቅም ።

⭕️እስተውል ጠዋት አነጋለሁ ብለህ
በስልክህ ሃራም ተመልክተህ
👉ሃራም ፖስት አድርገህ
ፎቶሽን በትነሽ ፎቶህን በትነህ

👉ቢዳዓ ኹራፋት በቻናል በትነህ
👉ዒሻእ ሰላት ሳሰግድ በሚዲያ ፍጥጥ ብለህ እገሌ እገሌ እያልክ ባላወቅከው ስትቀባጥር
👉ውስጥህ እንደማያገባት እያወቀ ለጊዜያዊ ስሜት እህትህን ስታባልግ ቻት ስታደርግ።
👉ቀኑ ላይ ወላጆችህን አስከፍተህ
👉ሚስትህ ካንተ ጋር እየተጨዋወተች ደስ የሚል መኝታ ልታሳልፍ ለአልጋ ፈልጋህ አንተ ግን ስልክህ ላይ አፍጥጠህ:
👉ብር ኪስህ ውስጥ አስቀምጠህ የቅርብ ቤተሰቦችህ ተርበው
♨️ጠዋት አነጋለሁ ብለህ ተኝተህ ጠዋት ላይ የቀጠርከው አላርም ወይም ቤተሰብ ስትጠብቅ ድንገት ያቺ ጠባብ ቤት ውስጥ እራስህን ካገኘህ እና ሚያስፈሩ ሁለት መላአይካ የቀሰቀሱህ ቀን ዋ ቁጭትህ!! ዋ ፀፀትህ!ዋ ድንጋጤህ

👉ወሏሂ ቢሏሂ ተላሂ ቀኑ ሩቅ አድርገህ እንዳታስበው በጣም ቅርብ ነው
አሁን ያለንበት ሁኔታ የተረዳ ሰው ስለሞት መረዳት ለሱ ቅርብ ነው ።
ስለዚህ ወንድሜ /እህቴ ንቃ/ንቂ
በዚህች ምድር የሆነን ጥፋት ካጠፋህ ፖሊስ ይዘሃል እስር ቤት ትገባለህ ሽሮ በልተህ ትወጣለህ ኻላስ
አሏህ ግን ይታገሰሃል!! ይታገሰሃል !!ይታገሰሃል!! የያዘህ ቀን ግን አያያዙ የበረታ ነው። ልብ በል
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ شَاقُّوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۖ وَمَن يُشَاقِّ اللَّهَ فَإِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን በመከራከራቸው ነው፡፡ አላህንም የሚከራከር ሰው (ይቀጣዋል)፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡(ሃሽር 4)

በሰራኸው ደሞ እያንዳንዱ ትያዛታለህ ቆም ብለህ አስብ
كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ
ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡
(አል ሙደሲር 38)

አበቃሁ ወንድሜ  ይህ የታናሽ ወንድምህ ምክር ነው እስቲ አሁኑኑ ወስን ሞትን ተጠባበቃት ካለህበት ወንጀል ተላቀቅ የተውበት በሩ ሁሌም ክፍት ነው።
✍️Abu_Selman abdulalim

https://t.me/abuselmanprofile


سورة الحج


ምንኛ ያሰምጣል ሱብሃናሏህ
اللهم اجعل القرآن ربيع قلوبنا ونور صدورنا وجلاء أحزاننا


ትልቁ የቅጣት ደረጃ

https://t.me/abuselmanprofile


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
① መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🔴 ለጥንቃቄ‼️‼️

✅ ሼር በማድረግ እርሰዎን እና ሌሎቹንም ከአጭበርባሪዎች ይከለከላሉ‼️


ፈጅር ሶላት ተኝተህ እያሳለፍክ ይሁን?

https://t.me/abuselmanprofile


📍 አል-ኢማም ኸሊል ቢን አሕመድ አልፈራሒዲ'ይ :

«.. አንድ ሰው ያለ ጓደኛ ልክ ግራ እንደሌለው ቀኝ እጅ ነው .. »


«..ጓደኛን ማበላሸት ጠላትን ከማስተካከል የበለጠ ይከብዳል እንዴ ? »

ተብለው ሲጠየቁ :

«አዎ .. ልክ ልብስን መቅደድ አስተካክሎ ከመስፋት የበለጠ ቀላል እንደሆነው ! ».. አሉት።
፡፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አብዛኛውን ግዜ እውነተኛ ሷሒብን ማግኘት ከባድ ከመሆኑ ጋር ሌላ በጣም ከባድ የሆነው ነገር እንዘነጋለን ። እሱም እውነተኛ ሷሒብ መሆን ነው ! ብንሆን ኖሮ እናገኝ ነበር ።

አላህ እውነተኞች ያድርገን
ኮፒ


ልዩ ውዴታና ጥልቅ የሆነ ስሜት

https://t.me/abuselmanprofile




🟢ከሞት በኋላ ያለው ጉድ  እንደይዘነጋ።

ድንገት መከሰቱ አይቀሬ ነው።


👉የቀብር ጥያቄና መልስ

👉የቀብር ፀጋ አሊያም ቅጣት

👉ከሞት መነሳት

👉ሂሳብና ምርመራ

👉የነቢያት ተከታይ ሱኒዮች በነቢያቸው እጅ የሚጠጡትና ሙኻሊፎችና የፊትና ሰዎች የሚገፈተሩበት አጓጊው ሀውድ

👉ሁሉም የስራ ውጤቱን መገናኘቱ

👉የአላህ መምጣት

👉የአላህ በግልፅ መታየት

👉እጅግ ከባድና አስፈሪው እለተ ቂያመህ

👉ታላቋ ጀነትና አስፈሪዋ ጀሃነም

👉ሙተቆች  በጀነት ድግስ ሲንበሻበሹ

👉ሙጅሪሞች ወደ ጀሃነም ቃጠሎ ሲወረወሩ

👉የጀሃነምን ቅጣት የሚቀምሱ ወንጀለኛ ሙስሊሞች

👉ሸፋዐህ (ምልጃ) ለሚገባቸው ብቻ መኖሩ

🤲 አላህ ያለቅጣትና የለ ውርደት በጀነቱ ይሰብስበን።

📚القصيدة النونية للقحطاني
المؤلف: أبو عبد الله محمد بن صالح القحطاني،الأندلسي المالكي (ت ٣٧٨هـ)

📚ከኑኒየህ አልቀህጣኒይ ግጥም የተወሰደ

Показано 20 последних публикаций.

717

подписчиков
Статистика канала