ስለፍትሕ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ስለ ፍትህ እና የህግ የበላይነት በጋራ እንቁም

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ በተደረገ ግብር ከፋይ ላይ የሚፈፀም የታክስ ተመላሽ ሥርዓት

— የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መብት ያለው ሰው በአገር ውስጥ ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ሲያከናውን ታክሱን ከፍሎ በተመላሽ እንዲስተናገድ ይደረጋል፡፡
— የታክስ ነፃ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈፀመው በባንክ በኩል መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ካቀረበ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በሰባት ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
— የታክስ ነፃ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈፀመው በባንክ በኩል ካልሆነ በአነስተኛ ኦዲት ተጣርቶ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
https://t.me/AboutJustices
@AboutJustices


ስለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ (sales register machine) አንዳንድ መረጃዎች

1. የመሳሪያው አቅራቢ መሳሪያውን ከውጪ ማስገባትና አቅርቦት ከመጀመሩ በፊት እውቅና ከሚኒስቴሩ ሊያገኝ ይገባል፡፡
2. መሳሪያው ብልሽት ቢያጋጥመውና ተጠቃሚው የመሳሪያውን እሽግ ሳይሰብር ሊያስተካክለው የማይችል ከሆነ በመሳሪያው መጠቀሙን ወዲያውኑ አቋርጦ ብልሽቱ ያጋጠመበትን ጊዜ በምርመራ መዝገቡ ላይ መመዝገብና በ2 ሰአት ውስጥ ለሚኒስቴሩ ለአገልግሎት ማእከሉ በስልክ ማስታወቅ አለበት፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/u0obhb

https://t.me/AboutJustices
@AboutJustices


Max Planck Institute Law Internship in Germany 2024

Link: https://scholarshipscorner.website/max-planck-institute-law-internship/

Duration: 8 and 12 weeks

Interns enrolled in a degree program at a university will normally be reimbursed € 450 per month.

Deadline: 1st June 2024.


Репост из: About Laws ስለህጎች🇪🇹
ስለ ኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ የምንዳስስ ይሆናል፡፡
በዚህ ክፍል ላይ ስለ ጋብቻ አይነቶች እና ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እንመለከታለን፡፡
ቤተሰብ ትልቅ ተቋም በመሆኑ የህግ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ የቤተሰባዊ ግንኙነት ከሚመሰረትባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ጋብቻ ነው፡፡
ጋብቻን እና ተያያዥ ጉዳዮች በፌደራል ደረጃ የሚዳኙት ወይም የሚገዙት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ዓ.ም ነው፡፡
በዚህ አዋጅ መሰረት በሶስተ አይነት መልኩ ጋብቻ ሊፈፀም እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ እነዚህን የጋብቻ አይነቶች ከመመልከታችን በፊት ጋብቻ ለመፈጸመም ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን እናያለን፡፡፡
አንድ ሰው ጋብቻ ለመፈፀም በቅድሚያ ሊያሟሏቸው የሚገቡ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ቅድመ ሆኔታዎች አሉ፡፡
የመጀመሪያ በተጋቢዎች መካከል ነጻ ፍቃድ መኖር ነው ፡፡ 2ኛው ተጋቢዎች 18 አመት እድሜ የሞላቸው መሆን ያለበት ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግን በፍትህ ሚንስትሩ ፍቃድ ሲሰጥ 16 አመት ለጋብቻ የተፈቀደ ጊዜ ይሆናል፡፡
3ኛው ደግሞ በተጋቢዎች መካከል የስጋ እና የጋብቻ ዝምድና አለመኖር ነው፡፡
4ኛው ተጋቢዎቹ በሌላ ጋብቻ ውስጥ አለመሆናቸው ወይም በጋብቻ ላይ ሌላ ጋብቻ ያለመፈጸም ነው፡፡
5ኛው ተጋቢዎች በፍርድ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው
6ኛው እና የመጨረሻው ቅድመ ሁኔታ
ለሴት ልጅ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ቀሪ ከሆነ በኋላ ወይም ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ለ180 ቀን ወይም ለ 6 ወር ያህል ሌላ ጋብቻ እንዳትፈፅም የተደነገገ ክልከላ ነው፡፡
ቀደም ሲል እንደገለፅኩላችሁ ሶስት የጋብቻ አይነቶች አሉ፡፡
1ኛ. በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ወሳኝ ኩነት በመሄድ የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡
2ኛው. በሃይማኖት ስርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህ ማለት ደሞ በቤተክርስቲያን ስርአት፤ በሼርያ ህግ እና በሌሎችም የሃይማኖት ስርአቶች ሊፈጸም የሚችል የጋብቻ አይነት ነው፡፡
3ኛው እና የመጨረሻው የጋብቻ አይነት ደግሙ በባህላዊ ሰርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህም በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ ባህላዊ ስርአቶች የሚፈፀም የጋብቻ አይነት ነው፡፡
በቀጣይ ክፍል ደግሞ ስለጋብቻ ውጤቶች የማቀርብላችሁ ይሆናል፡፡
የነጺ ሎው via Alternative legal enlightenment/ALE*
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
#አለሕግ #Alehig
@NegereHig
https://t.me/NegereHig


Репост из: About Laws ስለህጎች🇪🇹
159_በመንደር_የንግድ_ቁጥጥር_የአሠራር_ሥርዓት_መመሪያ_ቁጥር_159_2016.pdf
436.8Кб
#AddisAbaba

አዲሱን " በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ 159/2016 " የተያያዘውን ፋይል ከፍተው በዝርዝር ያንብቡ።
#አዲስ_አበባ_ንግድ_ቢሮ
@NegereHig
https://t.me/NegereHig


Репост из: LLB. CANDIDATES (Bachelors of Law).
የፌደራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_የሰበር_ሥነ_ሥርዓት_መመሪያ_ቁጥር_17_2015_.pdf
610.3Кб
በመቃወሚያ ላይ በተሰጠ ብይን ቅሬታ ያለው ወገን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር/ይግባኝ አቤቱታ በሚያቀርብበት ጊዜ መጀመሪያ ጉዳዩን አይቶ ብይን የሰጠው ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን እና ብይኑ የጸናበትን ውሳኔ ከሰበር አቤቱታቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ቅሬታ የሚቀርበው በአፈጻጸም ላይ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ሲሆን አፈጻጸሙ የተጠየቀበት ፍርድ፣ የአፈጻጸም ማመልከቻ እና በማመልከቻው መሰረት በአፈጻጸም ጉዳይ የተሰጠ ትዕዛዝ/ዞች ከአመልካች አቤቱታ ጋር ተያይዞ መቅረብ ያለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ወደ ሰበር ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮች የክርክር አመራር ሥርዓትን በተመለከተ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ ከዚህ በታች የተያያዘውን የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አያይዘናል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት


#ፍርድ ቤቶች ሚቀበሏቸው ሕጋዊ የቅጣት ገደብ ምክንያቶችን
#መሠረቱ
👉አንድ ቅጣት የሚገደበው ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ጥፋተኛ በተባለበት ውሳኔ በእስር ላይ ሳይደረግ ለጊዜው ቅጣቱ እንዳይፈጸምበት በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል ወደ መደኛ ማኅበራዊ ሕይወቱ ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን ፍርድ ቤት ሲያምንበት ነው።
👉ገደብ ከተሰጠ በኋላ የታሰበውን ውጤት ያላስገኘ እንደሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊሻር ይችላል።
#ቅጣት የሚገደበው
1️⃣ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ከሆነ፤
2️⃣ጠባዩ አደገኝነት እንደሌለው ከታመነ፤
3️⃣ጥፋቱ በመቀጮ ወይም በግዴታ ሥራ ወይም ከሦስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት የሚያስቀጣ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው የሚወስንበትን ቅጣት ሳይፈጽም ለተወሰኑ ጊዜያት ጠባዩ ቢፈተሽ የሚታረም መሆኑን እምነት የጣለበት እንደሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቅጣቱ ሳይወሰን የተወሰነ የፈተና ጊዜ ይሰጠዋል።
4️⃣ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት እንደማያደርግ ፍርድ ቤቱ ካመነ ቅጣቱን ሊገድብለት ይችላል።
#ቅጣት የማይገደበው
1️⃣ጥፋተኛው ከዚህ በፊት በጽኑ እሥራት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት ከነበረ እና አሁንም በተከሰሰበት ጉዳይ እነዚህ ቅጣቶች የሚፈጸሙበት ከሆነ፤
2️⃣ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ የፅኑ አሥራት የሚፈረድበት ከሆነ፤
3️⃣ቅጣቱ ታግዶለት ለፈተኛ በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ አስቦ አንድ ወንጀል ከፈጸመ፤
4️⃣ቅጣቱ ቢገደብለት የሚታሰበውን ዓይነት መልካም ውጤት እንደማይገኝ ፍርድ ቤቱ ያመነ እንደሆነ።
ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከመገደቡ በፊት ስለተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፣ የነበረው ጠባይ፣ የአኗኗሩና የሥራው ሁኔታ ምን እንደነበረ ምርመራ ተደርጎ ማስረጃ እንዲቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።
👉የሚወሰነው የቅጣት ገደብ ከ2 ዓመት ሊያንስ ከ5 ዓመት ሊበልጥ አይችልም።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
#laws2016

https://t.me/NegereFej
#ነገረ_ፈጅ


የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡

" የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውንም ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን እንደሚኖርበትና የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን እንዳለባቸውም ይገልጻል።

አንድ የሃይማኖት ተቋም በራሱ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ለዚሁ ሥራ የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ እንዳለበትም ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ ይኖርበታል ተብሏል።

በተጨማሪም የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስምና አድራሻ፣ የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነትና መጠን፣ እንዲሁም ስጦታው ወይም ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ የሃይማኖት ተቋማቱ ጨምርው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
#TikvahethMagazine


የገጠር_መሬት_አስተዳደርና_አጠቃቀም_ረቂቅ_አዋጅ.pdf
978.6Кб
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ


252231 ዋስትና.pdf
892.4Кб
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከላይ በተጠቀሰው መዝገብ ቁጥር የሚከተሉትን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል

ፍርድ ቤት እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰርት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 9/1 የተከለከለዉን በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት የሚቆጠር ስለመሆኑ፡፡

ተጠርጣሪው የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄዉ ውድቅ ከሆነ በኋላ የዋስትና ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ይህንኑ አዲስ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለዚያዉ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ ሥነ ሥርዓታዊ መብት የአለዉ ስለመሆኑ፡፡

ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ያለቀ ከሆነ ተጠርጣሪው በድጋሚ ዋስትና ለመጠየቅ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑና በድጋሚ የሚያቀርበዉ የዋስትና ጥያቄ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ሳይመረመር በደፈናዉ ጥያቄዉ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል የተያዘዉ ሰዉ ክስ ሳይመሰረትበት ላልተወሰነ ጊዜ ታስሮ እንዲቆይ የሚያደርግ ትእዛዝ/ዉሳኔ መስጠት ስነስርዓታዊ አለመሆኑን አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል

https://t.me/NegereHig href='https://t.me/Ethiopialegalinfo' rel='nofollow'>/a>


#Daily_Tips

የኢትዮጵያ አርሶ እና አርብቶ አደር #የገጠር_መሬቱን በዋስትና አሲዞ #መበደር እንዲችል ተወስኗል!

#አዋጁ:- ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ ይችላል።

#ለማስታወስ፦ በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት " መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው "። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው " ለመንግስት እና ለህዝብ " ነው።

Source: tikvahethiopia
#Ethiopianbusinessdaily


የገጠር_መሬት_አስተዳደርና_አጠቃቀም_ረቂቅ_አዋጅ_Stamped.pdf
1.0Мб
ምክር ቤቱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ  ***
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባው አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡

የውሳኔ ሃሳቡን ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ ሲሆኑ የረቂቅ አዋጁን መሻሻል አስፈላጊነት እና በምርመራው ሂደት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡

የአርሶና አርብቶ አደሩን እና ከፊል አርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ አገሪቱ ከደረሰችበት ዘርፈ ብዙ እድገት ጋር እኩል ለማራመድ እንዲቻል፣ የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማደራጀትና ለተጠቃሚው በአግባቡ ለማሰራጨት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር መንግስት እና የመሬት ተጠቃሚዎች አስተማማኝ የሆነ መረጃ የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የተፈጥሮ ሃብቶችን በዘላቂነት በመጠበቅና በማልማት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ፣ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ማረጋገጥና አካታች ስርዓት መደንገግ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አድርጎ አፅድቆታል፡፡


#Ethiopia

ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡

ከተመሩት ረቂቅ አዋጆች መካከል አንዱ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ነው።

የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አዋጁ በስራ ላይ ከዋለ 6 አመት ያስቆጠረ መሆኑንና አሁን ካሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር ማጣጣም ማስፈለጉን ገልጸዋል።

የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሀይል ምልመላና መረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሁሉንም ባካተተና ብዝሀነትን በጠበቀ መልኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ፦

➡ የደሞዝ ጭማሪ፣

➡ የደሞዝ እርከን፣

➡ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ማትጊያና ማበረታቻ ስርአት፣

➡ የሰራተኞች ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስልጠና አሰጣጥ ስራ ስምሪት እና ነጻ ገለልተኛ ስርአት መገንባት፣

➡ የመንግስት ሰራተኛነት ውል ማቋረጥና ማራዘም የሚሉና ሌሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 13/2016 ሆኖ በሙሉ ደምጽ ለሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

ሌሎች ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመሩ ረቂቅ አዋጆች ምንድናቸው ? በዚህ ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Ethiopia-05-14-8

@tikvahethiopia


ብርበራ 

ብርበራ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችን ፣ በወንጀል ድርጊት ምክንያት የተገኙ ቁሳቁሶችን ፣ ምርመራ ለሚደረግበት ጉዳይ ጠቀሜታ ያላቸውን ሌሎች ማናቸውም ማስረጃዎች ለመፈለግ እና ለመያዝ በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ወይም የተጠቀሱት ነገሮች ተደብቀውባቸዋል በሚባሉ በሌሎች ሰዎች ቤቶች ውስጥ የሚከናወን የወንጀል ምርመራ ተግባር ነው፡፡ ብርበራ ለማድረግና በሚደረግበት ወቅት የሚከተሉትን መርሆች መከተል አስፈላጊ ነው።

ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም  የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር የሰዎችን ቤት መበርበር አይችልም።

✔ ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። በፍርድ ቤት የተለየ  ትእዛዝ ሲሰጥ ብቻ ከዚ ሰአት ውጭ ሊካሄድ ይችላል።

✔ ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን  እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም።

✔ መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መዝግቦ መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል።

✔ ብርበራ የሚያደርገው ብርበራ ከሚደረግበት ሰው ጋር ተመሳሳይ ፆታ ባለው ሰው ነው።

✔ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ፖሊስ አስፈላጊውን ሀይል ብቻ ይጠቀማል።

by Daniel Fikadu
https://t.me/Ethiopialegalinfo
@Ethiopialegalinfo
#Ethiopialegalinfo


#ኢራቅ

የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ።

በአዲሱ ሕግ ፦

➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤

➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤

➡️ " ሆን ብለው " እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የሕጉ ዓለማ ፥ " የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው " ተብሏል።

ረቂቁ መጀመሪያ ላይ ግብረሰዶማውያን #በሞት እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ መሻሻሉ ነው የተሰማው።

የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ " አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል።

#አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል ሕጉን ፤ " ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው " በማለት ሕጉን ተቃውማለች።

" ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል" ብላለች።

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጮች #ቢቢሲ እና #ሮይተርስ መሆናቸውን ይገልጸል።

@tikvahethiopia


EFAA BYLAW FINAL PDF.pdf
480.3Кб
ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ
***********************

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በቅርቡ ለሚያካሂደው ጉባኤ ዝግጅቶችን እያደረገ ያለ መሆኑ ይታወቃል::

በዚሁ ጉባኤ ላይ ከሚቀርቡ ሰነዶች አንዱና ዋነኛው የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ነው:: በመሆኑም መላው የማህበሩ አባላት ይህ ሰነድ የማህበሩን ህጋዊ አቋም ፤ የአመራር አደረጃጀት እና አስራር የሚወስን ወሳኝ ሰነድ መሆኑን በመገንዘብ በአግባብ በማንበብ እና ሀሳባቸውን በማደራጀት መስጠት እንደሚገባቸው ታምኖበታል::

በመሆኑም የማህበሩ አባላት መተዳደሪያ ደንቡ የተሻለ እና ማህበሩን የሚያጠናክር ሆኖ እንዲወጣ የበኩላቸውን እንዲወጡ ማህበሩ ጥሪውን ያቀርባል::

መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ይፋዊ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::

ፌስቡክ- https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=9R9pXO

የቴሌግራም ገፅ- https://t.me/ethiopianfederalbarassociation

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሚያዝያ 18 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ፤


ይህ የፍትህ ሚኒስቴር ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር ‹‹ንቃተ ህግ›› በሚል ርዕስ ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 5:30-6:00 ሰአት በፋና ሬድዮ 98.1 ኤፍ ኤም የሚያቀርበው ፕሮግራም ነዉ፤ እኟም  ፕሮግራሙን ትከታተሉ ዘንድ ጋብዘናችኋል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=p_kfUBEkK5Y


239841 - Stamped.pdf
932.4Кб
የስራ ላይ ጉዳት ካለ በግልጽ ዳኝነት ካልተጠየቀበት ካሳ ሊወሰን አይገባም የሰ/መ/ቁጥር 239841
#Daniel Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)/




የትዳር አጋሩ በተደጋጋሚ በስለት በመውጋት እና ልጁን በመደብደብ ያቆሰለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

የትዳር አጋሩ የሆነችውን የግል ተበዳይ ባል አግብተሽ ልጆቹን ይዘሽ ወደ ውጪ ልትሄጂ ነው በሚል ምክንያት በስለት በመውጋት የግድያ ሙከራ በማድረስ እና ልጁን በኤሌክትሪክ ገመድ ጀርባዋ እና እግሮቿን ደጋግሞ በመምታት ያቆሰለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ።

መሃመድ ፈረጃ ምራ የተባለው ተከሳሽ የትዳር አጋሩን በኮልፌ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ ቤቴል ወይራ ሰፈር አከባቢ፤ ከተር እየተባለ በሚጠራ ስለታማ የምንጣፍ መቁረጫ የተለያዩ የሰውነት አካሏን ደጋግሞ በመውጋት የግድያ ሙከራ አድርሷል።

በተጨማሪም የ15 ዓመት የሆነችው ልጁን በመጥረጊያ እንጨት፣ በመጋረጃ መስቀያ ብረት፣ በኤሌክትሪክ ገመድ ደጋግሞ በመምታት እጇ፣ ጭንቅላቷ እና እግሯ እንዲያብጥ አድርጎ ተሰውሮ ነበር።

ግለሰቡ በክትትል ተይዞ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦበት ክርክር ተደርጎ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@TikvahethMagazine

Показано 20 последних публикаций.

789

подписчиков
Статистика канала