መውደድ ዒባዳህ ነው ❗🔸ዲናችን ላይ አንድ ነገር "መልካምና ጥሩ" የሚባለው ቁርኣንና ሐዲሥ እንዲሁም የመጀመሪያው የኢስላም ትውልድ መልካም ነው ያለው ነገር ብቻ ነው።
በቁርኣንም ይሁን በሐዲሥ "መውሊድ አክብሩ" የሚል ትዕዛዝ አልተላለፈም፣ ሰሓባዎችም ይሁን ተከታዮቻቸው መውሊድን *አላከበሩም* ፣
አራቱም የዲን/የፊቅህ መሪዎች (እነ ኢማም አሽሻፊዒይ)ም ይሁን ስድስቱ የሐዲሥ ኪታቦች ጸሃፊዎች (እነ ቡኻሪይና ሙስሊም) መውሊድ ይከበር ብለው ያስተላለፉትና የተናገሩት ምንም ነገር የለም።ሰፊና ወይም ሚንሃጅ ላይ (ባቡል- ወይም ኪታቡል-መውሊድ የሚል ርእስ አለ እንዴ? ¡ )
🔹ይልቅ መውሊድ የተጀመረው ምርጡ እና የመጀመሪያው የኢስላም ትውልድ ካለፈ በኋላ አራተኛው ክፍለ-ዘመን ላይ ነው።መሰራጨት የጀመረውና በስፋት የታወቀውም ሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ላይ ሲሆን ያሰራጩትና ያስፋፉት ሰሜን ዒራቅ አካባቢ የሚገኙ ክርስቲያኖች የዒሳን ልደት ሲያከብሩ ያዩ "ፋጢሚዩን" የሚባሉ ዲንን ለግል ዓላማቸው ይጠቀሙ የነበሩ፣ አንዴ እንኳ ሐጅ አድርገው መዲናንም ዘይረው የማያውቁ ከዲን የራቁ ባለስልጣኖችና ፖለቲከኞች ናቸው!። ይህም የታሪክ መጽሐፍት ላይ በሰፊው የተዳሰሰ ጉዳይ ነው!።
ስለዚህም መውሊድ የነቢዩ ﷺ ውዴታ መገለጫ ነው ብሎ ማመን ትልቅ ስህተት ነው።የነቢዩ.ﷺ ውዴታ ዒባደህ ከመሆኑ አንጻር ነቢን ﷺበዚህ መልኩ መውደድ ይቻላል ብሎ መናገርና ማመን ዲኑ ላይ ህግ ማውጣት ነው፤
🔸ኢስላም ላይ ደግሞ ያለ ግልጽ ማስረጃ ህግ ማውጣት አይቻልም።
ሲጀምርም ከእንደዚህ ዓይነት ነገሮች አንጻር ዲኑ ምሉእ ነው። እኛ ዲኑን መከተልና የተደነገጉ ነገሮችን መተግበር እንጂ አዲስ ህግ የማውጣት መብት የለንም።
ስለዚህ መውሊድ ሱንናህ እና ትክክለኛ የነቢዩ ﷺ ውዴታ መግለጫ ሊሆን አይችልም።
🔹"ደጋግ ቀደምቶች በሄዱበት ብቻ እንሂድ፣ ለነሱ የበቃቸው ለኛም ይብቃን፣ ከቆሙበት እንቁም፣ ባልዋሉበት አንዋል፣ ያላሉትን አንበል፣ እውነት የነቢዩﷺ ወዳጆች ከሆነን ልክ ሰሓባዎች ይወዷቸው በነበረው መልኩ እንውደዳቸው!፤ መቼም ከሰሓባዎች በላይ እኛ እርሳቸውን አንወድም! ታዲያ ሰሓባዎች ያላደረጉትን ነገር ለምን እናደርጋለን?!...?
ከነሱ የበለጠ እናውቃለን? ወይስ የኛና የነሱ መንገድ ይለያያል?!
🔅("አደራችሁን የእኔን መንገድ/ሱንናህ ተከተሉ፣ አላህ የመራቸው የቅን ተተኪዎቼንም መንገድ ተከተሉ... አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ...")
ይህ የነቢያችንﷺምክር ነው።
ከልቡ እሳቸውን የሚወድ ምክራቸውን ይተገብራል፤ ሰሓባዎቻቸውን ይከተላል።
✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም@ዛዱል መዓድ
12/3/1442ዓ.ሂ
-------------//--------------
🌐
https://telegram.me/ahmedadem~
🔗
https://www.facebook.com/yenegew/~~~📶
http://www.youtube.com/c/ZadulMaadአላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197