Ezedin Sultan


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ወገን ምግብ ብቻ አይደለም expired የሚያደርገው፣ ሀሳብም expired ያደርጋል!

ብዙ ልትሰራቸው ያሰብካቸው ሀሳቦች በጊዜው ወደመሬት ማውረድ ካልቻልክ ጊዜ ያልፍባቸዋል።

ካላመንከኝ እስቲ የቀደመ የሀሳብ መዝገቦችህን ገለጥ አድርግና ዛሬ ላይ ቢሆኑ ብለህ አስብ፣ አይሆኑም አይደል?!
በቃ expired አድርገዋል!

የጊዜው ፍጥነት ደግሞ፣ አብረህ መራመድ ካልቻልክ የሀሳብ shelf life እያሳጠረው ነው! ሁኔታዎች ቶሎ ቶሎ ነው የሚቀያየሩት ወደ Action በጊዜ ካልገባህ በቃ ቅርጫት ላይ መጣል ነው😥

ሌላ አስገራሚው ደግሞ ሀሳብ ወደ ተግባር በጊዜ ካልገባን የኛን ሀሳብ ይዘው ሌሎች ወደ ስራ ይገባሉ። ለማንም ያልተናገርነውን ሀሳብ ተቀድመን ሌሎች ሰርተውት አይተን አናውቅም?! ኧረ እናውቃለን . . .

ስለዚህ እኛ የምናስበውን ሌሎች ሊያስቡት ይችላሉ ማለት ነው፣ ምን ማሰብ ብቻ ቀድመውን እውን ሊያደርጉትም እንዲሁ!

ስለዚህ ሀሳቤ እንዳይሰረቅ ብለህ ይዘሀው expired ከሚያደርግ የሆነ "ቁልፍ" አበጅለትና ለምን EBC ባዘጋጀው የስራ ፈጠራ ውድድር አትወዳደርበትም።

ካሸነፍክ ገንዘብ ታገኛለህ፣ እውቅና ታገኛለህ፣ ኔትወርክ ትቀጥላለህ፣ ካልተሳካም ሀሳብህን በደንብ መግለፅና ማሻሻል ትለማመዳለህ። (ሰው እውቅናውን ለመቀፈል እየተጠቀበት አይደል፣ ምን ችግር አለው አንተ ለስራ ፈጠራህ ብትጠቀመው👍

ዐረቦች الحركة يزيد البركة/ في الحركة بركة ሲሉ፣ ስልጤዎች ቀበል አድርገው "ያትረክባን ፈረንካ" ብለዋል አሉ😂
(ለዓረብኛውና ስልጥኛው ይቅርታ ካበላሸሁ😁
ይተርጎም እንዴ 😍


😊ሰላም እህቴዋ ሸዋበር ያለሁት እኔ ላንቺ ምን እማልሆነዉ አለኝ

አረፋ ደረሷል🤝ማለቴ ገብቷል ብዬ ምርጥነቱን ስታይዉ ምመሰክሪለት ምርጥ ቅቤ ና አይቤ ይዤ መጥቻለሁ
ቅቤዉን ......ለማንጠር ጊዜ ያጠረሽ እንደሆነ በአማና ና ፅድት ባለ መልኩ አንጥረን እናቀርባለን !
አንቺ ብቻ እንደሁሌዉ😉ተደዋወይኝ😇

0966120340
+251949723012
Eman Kenzulah


" ደም ስትለግሱ ሳትጎዱ ዉድ የሆነውን የማታውቁትን የሰው ልጅ መታደጋችሁን  እወቁት" - ዶ/ር ሰኢድ አንዳርጌ

" ደም ለጋሾች ደስ ይበላችሁ !

ትላንትና ምሽት አንዲት የስምንት ወር ነፍሰጡር እናት እጅግ ከፍተኛ እና ባልተጠበቀ ሁኔታ ደም መፍሰስ ስላጋጠማት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ ቀዶ ሕክምና ከአራት ሰዓት በላይ በአከናወነው በዚሁ ቅፅበት ደግሞ የ8 ሰዉ ደም ማግኘት በመቻላችን ሰበብ #እናትም #ልጅም መትረፍ  ችለዋል።

ከስራ ባልደረቦቼ  በተጨማሪ ይህን አጋጣሚ ሳያዩ ደምን የሚያክል ዉድ ስጦታ ለሚሰጡ ሁሉ በያሉበት ምስጋናዬ  ይድረሳችሁ።

ደም ስትለግሱ ሳትጎዱ ውድ የሆነውን የማታውቁት የሰው ልጅ መታደጋችሁን  እወቁት፤ ለዚህም ታላቅ ክብር ይገባችዋል ! "

(ዶክተር ሰኢድ አንዳርጌ)

Via ALI AMIN

@tikvahethiopia


እስቲ መልሱልኝ?! ((እንወያይበት

አንድ ሙስሊም አውራጎዳናዎች ላይ ወጥቶ፣ በመድጅድ ወይም በሚድያ ቀርቦ እየሰሱስ ጌታ አይደለም፣ ፈጣሪ ልጅ ዬለውም፣ ገብርኤል አያድንም፣ ሚካኤል አይጠብቅም ብሎ አስተምህሮ ቢሰጥ . . .
የሌሎች እምነቶችን አስተምሮ እየነቀፈ ወይስ የራሱን አስተምህሮ እየሰበከ?!
ተግባሩ የሚያስወግዝ ወይስ የሚያስመሰግን?!


#Update

የተሻሻለው የ " ንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያ " ሊወጣ ነው !

ከስልሣ ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ የወጣውን አዲሱን የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያዎች ውስጥ እና የመጀመርያው የሆነው በዚህ ዓመት ፀድቆ ሥራ ላይ እንደሚውል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

የንግድ ሕጉ ማስፈጸሚያ ይሆናል የተባለው ይህ የመጀመርያው መመርያ የ " አክሲዮን ማኅበራት " ን የሚመለከት ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ፤ " የአክሲዮን ማኅበራት ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር መመሪያ " በሚል የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ተዘጋጅቶ በመጠናቀቁ በዚህ በጀት ዓመት ይፀድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

መመርያው ምን ይዟል ?

- በንግድ ሕጉ ላይ " የመተዳደሪያ ደንብ ያስፈልጋል ? አያስፈልግም ? " የሚለውን ጉዳይ ለማብራራትና በቀላሉ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎችና በሁሉም ፈጻሚ ተቋማት ወጥ በሆነ መንገድ እየተተረጎመ እንዲፈጸም ለማስቻል በሚረዳ መልኩ በመመርያው እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡

- መመርያው አክሲዮን ማኅበራት ሲደራጁ ገንዘብ ከሕዝብ የሚሰበሰብበት መንገድ ላይ ምን መሆን እንዳለበት በግልፅ ያመላክታል። ኅብረተሰቡ እንዳይበዘበዝ እንዴት መተዳደር እንዳለበት በዝርዝር የተቀመጡ አንቀጾችን አካቷል፡፡

አደራጆች የምሥረታ ሒደት ለማካሄድ የሚያስከፍሉት አስተዳደራዊ ወጪ የሚዋጣው ገንዘብ ከአምስት በመቶ መብለጥ እንደሌለት በረቂቅ መመርያው ተመላክቷል፡፡

በምሥረታ ሒደት ከፈራሚዎች አስተዳደራዊ ወጪን ለመሸፈን ገንዘብ የተሰበሰበ እንደሆነ፣ ማኅበሩ ሲመሠረት የምሥረታ ወጪን ለማኅበሩ ማስተላለፍ የሚቻለው የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ክፍያ የምሥረታ ወጪውን ለመሸፈን ያልበቃ መሆኑን የምሥረታ ኦዲተር ካረጋገጠ ብቻ ነው።

በምሥረታ ኦዲተር ሪፖርት መሠረት ለአስተዳደራዊ ወጪ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቀሪ ገንዘብ ያለ እንደሆነ ማኅበሩ ሲመሠረት ፣ ለማኅበሩ ገቢ መደረግ ይኖርበታል። ይህም ቀድሞ ለአገልግሎት ተብሎ የተሰበሰበን ገንዘብ ከብክነት ያድናል።

- አደራጆች በአክሲዮን ምሥረታ ወቅት ከፈራሚዎች ሚሰበሰበውን መዋጮ በባንክ በዝግ ሒሳብ ሲያስቀምጡ በገበያው ላይ ካለው የወለድ ምጣኔ አንፃር ተመጣጣኝ የሆነ ወለድ እንዲያፈራ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው።

- የማኅበሩ ምሥረታ በስኬት የተጠናቀቀ እንደሆነ ዋና ገንዘቡና ያስገኘው ወለድ ለማኅበሩ ገቢ መደረግ አለበት።

- የግል አክሲዮን ማኅበር ሚመሠረተው በመሥራቾች እንደሚሆን ይደነግጋል። መሥራቾች በባለአክሲዮንነት ከሚያገኙት መብት ውጪ በመሥራችነታቸው ምክንያት የሚከፈላቸው የአገልግሎት ክፍያ አይኖርም።

- በአክሲዮኖች ላይ #ከአንድ_መቶ_ብር (100) ያነሰ ዋጋ የተጻፈባቸው አክሲዮኖች ያላቸው ማኅበራት፣ ይህ መመርያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ቢያንስ ወደ አንድ መቶ ብር በማሳደግ መመሥረቻ ጽሑፋቸውን አሻሽለው ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

- የአክሲዮን ኩባንያዎች የሚያደራጁ ሰዎች ያለባቸው ኃላፊነት ምንድነው የሚለውም በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን በአዲሱ የንግድ ሕግ የአክሲዮን ኩባንያዎች የኤሌክትሮኒክስ ስብሰባ ማድረግ የሚችሉ በመሆኑ፣ ይህንን ለማስፈጸም ዝርዝር ጉዳዩ በዚህ መመርያ ተገልጿል።

"  የቦርድ  ስብሰባ  " የሚደረግበት የኤሌትሮኒክ ዘዴ የተሰብሳቢዎችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል ፤ የውይይቱን የድምጽ ቅጂ በትክክል መያዝ የሚችል መተግበሪያ ያለውና ፤ ሚስጢራዊነትንም መጠበቅ የሚችል መሆን አለበት።

በመመስረቻ ጽሑፍ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በስተቀር እያንዳንዱ የቦርድ አባል በዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ ላይ በአካል የመገኘት መብት ያለው ሲሆን፣ የቦርድ ስብሰባን በኤሌትሮኒክ ዘዴ ለመሳተፍ ዳይሬክተሩ ጥያቄ ካላቀረበ በቀር፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊያስገድድ ወይም በአካል የመሳተፍ መብቱን ሊገድብ እንደማይችች ተቀምጧል፡፡

- ከመመርያው መውጣት በኋላ ብዙ አክሲዮን ያላቸው ኩባንያዎች በቀላሉ ስብሰባቸውን እንዲያካሂዱ ዕድል ይሰጣቸዋል።

- የአክሲዮን ዝውውሮችን በተመለከተ በዚህ መመርያ ግልጽ ድንጋጌ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በተለይ የግለሰብ አክሲዮንን ለማስተላለፍ #የትዳር_አጋር_ስምምነት ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡

"በግል የአክሲዮን ማኅበር" ውስጥ በግለሰብ የተያዘ አክሲዮንን ፦
- በሽያጭ ፣
- በስጦታ ፣
- በመያዣ
- በሌላ በማንኛውም መንግድ ለማስተላለፍ በሕግ ወይም ደግሞ በመመሥረቻ ጽሑፍ ከተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ አስተላላፊው በአስገዳጅነት ያገባ ከሆነ የትዳር አጋሩ ውል ለማዋዋል እና ሰነድን ለመመዝገብ ' ሥልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ ' ስምምነቱን መግለጽ አለበት።

ያላገባ ከሆነ / ከሆነች አግባብ ካለው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ተገቢውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል በሚል መመርያው ይደነግጋል፡፡

- ሁሉም የአክሲዮን ማኅበራት ይህ መመርያ ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ድረገጽ ማበልጸግና በድረገጹ ላይ በሕጉ መሠረት ተገቢነት ያላቸውን መረጃዎች ማስቀመጥ አለባቸው። ይህንን ድንጋጌ የማይፈጽም የአክሲዮን ማኅበር የንግድ ፈቃዱ ሊታገድ እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡

- አክሲዮን ለመሸጥ ስለሚወጡ #ማስታወቂያዎች በመመርያው ላይ ተቀምጧል።

ይህም ፤ " በማንኛውም በሕዝብ ማኅበር በምሥረታ ሒደት አክሲዮን ለመሸጥ በሚተላለፍ ማስታወቂያ ስለ ታሳበው የንግድ ሥራ አዋጭነት በጠቅላላው ከመግለጽ በስተቀር ስለሚያስገኘው የትርፍ መጠን በምን ያህል ጊዜ ለኢንቨስትምንት የተከፈለው ገንዘብ እንደሚመለስ ወይም ሌሎች በተጨባጭ ሊረጋገጡ የማይችሉ መረጃዎችን መስጠት አይቻልም " በሚል ተጠቅሷል፡፡

በማንኛውም #ዋና_ገንዘብ በማሳደግ ሒደት በግል ማኅበር ወይም በሕዝብ ማኅበር፣ ለሕዝብ አክሲዮን ለመሸጥ የሚደረግ ማስታወቂያ ማኅበሩ አስቀድሞ ያገኘውን ትርፍ የሚገልጽ ከሆነ፣ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ዓመታት የትርፍ ውጤት መግለጽ ግዴታ አለበት፡፡

ነገር ግን ማኅበሩ #ለወደፊት የሚኖረውን አትራፊነት በቁጥር ወይ በመጠን መግለጽ አይቻልም።

ሚኒስቴሩ (ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር) ወይም አግባብ ያለው ሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት አሳሳች ናቸው ብሎ ከወሰነ፣ አክሲዮን ለመሸጥ ለሕዝብ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች እንዲቋረጡ ለማዘዝ ይችላል።

.
.
.

መመርያው በአጠቃላይ ከአክሲዮን ምሥረታ ጀምሮ እስከሚፈርስበት ጊዜ ድረስ #ዝርዝር የአሠራር ጉዳዮችን በመተንተን የቀረበ ነው።

በአዲሱ የንግድ ሕግ መመርያ የማውጣት ሥልጣን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡

መመርያን ያዘጋጀው በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሲሆን በተለይ #የሕዝብን_ገንዘብ ተቀብለው የሚያስተዳድሩ የአክሲዮን ማኅበራት ላይ መጠነኛና ቁጥጥር ለመዘርጋት የሚያስችል ነው፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ የረቂቅ መመርያው ዝግጅት ተሳታፊ የሕግ ባለሙያ አቶ ፈቃዱ ጴጥሮስን ዋቢ በማድረግ ያወጣው)

@tikvahethiopia


እስልምናን በቀለለ አገላለፅና ተደራሽ በሆነ መንገድ እንዴት ለሌላው ማህበረሰብ እናዳርሳለን?!🤔


ወገን መንግስት ወደላይ እያደገ(የእርዳታ እህል እየቸበቸበ፣ ወርቅ በህገወጥ መንገድ ሰንሰለት ፈጥሮ እየሸጠ)😡
እኛ ደግሞ ስንዴያችንም ወርቃችንንም ተነፍገን ወደታች እያደግን ነው?!🙄


ጮማ ጮማ ዜናዎች ህዝቡ እየሰማ አይደለም ነው?
ወይስ አውቆ እያሳለፈው እንዳልሰማ እየሆነ?

በተለይ የገንዘብ ሚኒስትሩ ቀጣይ የበጀት አመት መንግስት ስራ ቅጥር አያደርግም ማለታቸውና

አሜሪካና WFP እርዳታችን በፌደራልና ክልል ባለስልጣናት ሰበብ ላልተፈለገ አላማ እየዋለ ስለሆነ እርዳታ መስጠት አቁመናል ያሉት ነገር (እንደው ህዝቡ እንኳ ባይጮህ ጥቅማቸው የቀረባቸው ባለስልጣናት እንዴት ዝም አሉ)

ሁለቱም ርዕሰ ጉዳዬች የኑሮ ውድነቱን ይበልጥ በማናር ረገድ ሚና ዬላቸውም ትላላችሁ?!


የምትችሉ ተሳተፉ

በቅርቡ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ለማወዳደርና ለመሸለም ETV ነጋድራስ የተሰኘ መርሀግበር አስተዋውቋል። ምዝገባውም ከሰኔ 1-10 ድረስ እንደሚቆይ አሳውቀዋል።

እንዲህ አይነት ውድድሮች ላይ ማሳተፍ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያስገኛል። በዋነኝነት ሀሳብን ማደራጀት፣ መግለፅና ለሌሎች ማስረዳት ክህሎትን ያሳድጋል፣ ሀሳቦቻችን ላይ invest የሚያደርጉ ባለሀብቶችን ለማግኘት ያግዛል፣ ልምድ ባላቸው ዳኞች ሂስ በማግኘት ይበልጥ ሀሳቦቻችንን ለማዳበር ያስችላል፣ ከሌሎች የስራና የሀሳብ ባለቤቶች ጋር network እንድንቀጥል ምክንያት ይሆናል። ሌላም ሌላ . . .

ETV ያስተዋወቀው መርሀግብር ደግሞ የገንዘብ ሽልማቱ ከተለመዱት ከፍ ያለ ነው። ይህ ደግሞ ሀሳቦቻችንን ተግባራዊ ለማድረግ አጋዥ ነው።

በቅርቡ አዋሽ ባንክ ባደረገው የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ለነበሩ አምስት ግለሰቦችና ድርጅቶች ያለ ማስያዣ(ኮላተራል) የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ፈቅዶ አመቻችቷል። በርግጥ ትልቅ እድል ነው!

እንዳያመልጣችሁ፣ ሊንኩን ኮሜንት ላይ


ባይሆንስ?!🤔

ሁሉም ሰው ስኬትን ይናፍቃል። በተሰማራበት ወይም ሊሰማራበት በሚፈልገው የስራ መስክ ላይ ውጤታማነትን ያስባል፣ ያቅዳል። እስከቻለውም ይታትራል።

ሆኖም ነገሮች እኛ ባሰብነው፣ ይሆናል ብለን በወጠነው መንገድ ብቻ ላይሄዱ ይችላሉ። አንዳንዴ በእኛ ድክመት፣ ሌላ ጊዜ ከእኛ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ይሰናከልብናል።

ዘውትር ስናቅድ፣ ወደ ተግባር ስንገባ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ጉዳይ አለ፣ ባይሆንስ?!
አዎ እንዳሰብከው ባይሆንስ?! እንዳቀድከው ባይፈፀምስ?! ምን አማራጭ አስቀምጠሀል?!

ብዙዎቻችን አይሆንምን መስማት ፈፅሞ አንሻም፣ በተለይ አስራዎቹና ሀያዎቹ የእድሜ ክልል በዚህ ደዌ የተጠቃ ነው። ለዛም ይመስለኛል ይህ እድሜ ክልል ላይ ከልፋት የዘለለ ብዙም ውጤታማነት የማይታየው . . . መድከም፣ መሮጥ፣ መድከም ብቻ ይሆናል!

መቼም ብዙ ነገር አቅዳችሁ ባይሆንምን ከግምት ባለመክተታችሁ የደረሰባችሁ ከፍተኛ የሆነ ቅስም መሰበር ይኖራል፣ ገንዘብ አገኝበታለሁ ብላችሁ ደጁ የጠናችሁት ሰው ሌላ የማታውቁት ሆኖባችሁ ተስፋችሁን የተሟጠጠባችሁ አትጠፉም። የተጋነነ ትርፍ አስባችሁ፣ ከሚገባው በላይ ጠብቃችሁ አየር አፋሽ የሆናችሁበትም አጋጣሚ ይኖራል።

እንዳሰብከው ባይሆን?! ብሎ ጥያቄን የሚያነሳብን እድገታችንን የማይፈልግ፣ ውድቀታችን የሚናፍቀው አድርገን እንመለከታለን። አንዳንዴም በእኛ ስኬት የተመቀኘ አድርገንም ልንወስደው እንችላለን🙄

ክፉ መካሪ በደመነፍስ እንድትጓዝ የሚያደርግህ ነው። በባዶ ተስፋና ሞራል ግፍ፣ ቀጥል፣ ማንንም አትስማ የሚልህ ነው (እንደጊዜው አነቃቂዎች😁። ከምክንያታዊነትና ስሌት ስሜትህን እንድትከተል የሚገፋህ ነው!

በተቃራኒው ስላማከርከው ስራ ባይሆኖችን እንድታይ፣ አለፍ ሲልም አስቀድመህ እንድትዘጋጅና መውጫ መንገዶችን እንድታስቀምጥ የሚያግዝህ ትክክለኛ መካሪህ ነው። ባለ ውለታህ፣ ውድቀትህን የማይፈልግ ሀዋርያህ ነው። አጥብቀህ ያዘው!

የስራ እቅዶቻችንና የገንዘብ ማግኛ መንገዶች ለመሆን እድል እንዳላቸው ሁሉ ላለመሆንም እድል አላቸው። ድርሻቸው ቢለያይም። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የቅርቡ ኮቪድ ነው።

ቢመርም፣ ውስጣችን ባይፈልግም፣ ተነሳሽነታችንን የሚያዳክም ነው ብለን ብናምንም እኛ ባሰብነው መንገድ ባይሆንስ?! ብለን በማሰብ ተጠባባቂ እቅዶችን (Plan B, C . . . ) ማዘጋጀት ግድ ይለናል።

ከገንዘብ ኪሳራ በላይ ትልቁ ኪሳራ የሞራል ስብራት፣ የተስፋ መሰናከል ነው። ከተገቢው በላይ መጠበቅ (over expectation) የሚፈጥረው ጉዳት፣ የሚያስከትለው ተፅእኖ በቀላሉ አይሻርምና ሁሉንም በልኩ!

https://t.me/EzedinSultan14




ምን ገጠመህ?

ሰው በግሉ የሚገጥመው ጉዳቱ ለራሱ ወይም ቅርብ ላሉ ሰዎች ብቻ ነው። ኡማው የሚገጥመው ግን ጉዳቱ ሰፊውን ማህበረሰብ ብሔር፣ አከባቢ፣ ፃታ፣ የእድሜ፣ የእውቀትና የሀብት እርከን ሳይለይ ሁሉንም ያዳርሳል።

ትላንት መጅሊሱ ይዞልን በመጣው መርዶ አላህ በሚያውቀው እጅግ ውስጤ ቆስሏል፣ ሀሳቤንና ምልከታዬን ለማስፈር በስልክና በላፕቶፕ ብሞክርም ሀሳቤ ፈፅሞ ሊሰበሰብ አልቻለም። ከዝሁር ቡሀላ እስከ ዛሬ ንጋት ከራሴ ጋር አልነበርኩም። ከፍተኛ ድብርት/ጘፍላ/፣ ራስ ምታት፣ ተስፋ መሟጠጥ ስሜት ተጫጭኖኝ ነበር።

ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰፊው ማህበረሰብ ምን እንደተደገሰለት አለመረዳቱ፣ በሀላፊነት ያሉ ሰዎች የሌሎችን ተቃራኒ ሀሳብ፣ ምልከታና ትችት ከመስማት ይልቅ ሁሉንም በአንድ ቋት በመክተት የኡማውን አንድነት በማይፈልጉና የቀደመውን መጅሊስ ለመመለስ የሚታትሩ አድርጎ መመልከታቸው እጅግ ያሳዝናል።

አርቆ ለሚያስተውል፣ ነገን ዛሬ ላይ ሆኖ ለመመልከት የሚሻ የትላንቱ ክስተት ነገ ዛሬ ላይ ካለንበት በላይ ምስቅልቅል ይዞብን እንደሚመጣ ግልፅ ብሎ ይታየዋል።

ጆሮዬ ላይ የሚያቃጭለው ከስር ያለው የቁርአን አንቀፅ ነው

هُوَ الَّذِي أَخْرَجَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ مِن دِيَارِهِمْ لِأَوَّلِ الْحَشْرِ ۚ مَا ظَنَنتُمْ أَن يَخْرُجُوا ۖ وَظَنُّوا أَنَّهُم مَّانِعَتُهُمْ حُصُونُهُم مِّنَ اللَّهِ فَأَتَاهُمُ اللَّهُ مِنْ حَيْثُ لَمْ يَحْتَسِبُوا ۖ وَقَذَفَ فِي قُلُوبِهِمُ الرُّعْبَ ۚ يُخْرِبُونَ بُيُوتَهُم بِأَيْدِيهِمْ وَأَيْدِي الْمُؤْمِنِينَ فَاعْتَبِرُوا يَا أُولِي الْأَبْصَارِ

እርሱ ያ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያን የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው ማውጣት ያወጣቸው ነው፡፡ መውጣታቸውን አላሰባችሁም፡፡ እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ (ኀይል) የሚከላከሉላቸው መኾናቸውን አሰቡ፡፡ አላህም ካላሰቡት ስፍራ መጣባቸው፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ መርበድበድን ጣለባቸው፡፡ ቤቶቻቸውን በእጆቻቸውና በምእምናኖቹ እጆች ያፈርሳሉ፡፡ አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! "አልሀሽር 2

ልዋጭ ላይሰጠን፣ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስተማመኛ ሳይኖር፣ ከቃል የዘለለ በሁለቱም ወገን የተደረገ መግባቢያ ሰነድ ሳንይዝ 300 መስጅዶች በእጆቻችን ለማፍረስ ተስማምተን ከመምጣት በላይ ምን አሳዛኝ ነገር አለ!

መጅሊስን በጠበኩት ከፍታ አላገኘሁትም፣ ግን እኔ ለጀሊሉ አንድ ተራ ምስኪን ባርያው ነኝ፣ ዘውትር ሙስሊሞችን የሚጎዳ ነገር ከተግባርም ይሁን ከሴራ እንዲጠብቅልን ዱአ ላይ ነኝ!
አላህ ሆይ አንተው ስማን!




የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ይሰራል-የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ሰኔ 1/2015(ኢዜአ) ፡- በኢትዮጵያ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እንደሚሰራ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ።

5ተኛው አግሪ ፉድ እና የምግብ ማሸጊያ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።

በንግድ ትርኢቱ መክፈቻ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድን ጨምሮ አምባሳደሮች፣ የንግዱ ዘርፍ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በንግድ ትርኢቱ ከተለያዩ አገራት የተወጣጡ ከ130 በላይ የንግድ ትርኢት አቅራቢዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ቻይና፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድስ፣ ሕንድ፣ ጣልያን፣ ተርኪዬ፣ ኦስትሪያ፣ ቡልጋሪያ ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጆርዳን እና ኬንያ በንግድ ትርኢቱ የተሳተፉ የውጭ አገራት ናቸው።

የንግድ ትርኢቱ በግብርና፣ በምግብ ማቀነባበሪያ፣ ፕላስቲክ፣ ሕትመት እና የማሸጊያ ኢንዱስትሪ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ የንግድ ትርኢቱ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጠቀሜታ አለው።

በተለይ ወቅታዊ የንግድ እድሎችን ለማወቅ እና በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላሉ አዳዲስ ለውጦች በበቂ ሁኔታ ለመረዳት ጠቃሚ እድሎችን እንደሚፈጥርም ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎችን ከውጭ የምታስመጣ መሆኑንና ለዚህ ደግሞ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በየአመቱ እንደምታጣ ነው የተናገሩት።

ይህን ሁኔታ ለመቀየር በ'ኢትዮጵያ ታምርት' ንቅናቄ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ ይህ የንግድ ትርኢት በምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎች ያሉ ልምዶችን ከየሀገራቱ ተሞክሮ አንፃር ለመቅሰም ያግዛል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የምግብና መጠጥ ማቀነባባሪያና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየሰራች እንደምትገኝም ተናግረዋል።

የንግድ ትርኢቱ አዘጋጅ አቶ ነብዩ ለማ የግብርና ኢንዱስትሪውን በቴክኖሎጂ በማዘመን ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ብለዋል።

በተለይ በቴክኖሎጂ ሽግግር አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት እሴት ጨምሮ ለማዘጋጀት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር ወደ ስራ ለመግባት ያስችላል ነው ያሉት።

በንግድ ትርኢቱ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ኩባንያዎች መካከል የጣሊያኑ ንግድ ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሪካርዶ ዙኮኒ የንግድ ትርኢቱ በኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት በር ከፋች መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይ በዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን በርካታ እድሎች ያሉ በመሆናቸው በቀጣይ ተሳትፏቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ሌላኛው የንግድ ትርኢቱ ተሳታፊ ጀማል መሀመድ በበኩሉ በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ለውጦች የልምምድ ልውውጥ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።

ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየውን የንግድ ትርኢት ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።




የሸገር ከተማ ‹‹ሕገ ወጥ›› ያላቸውን ግንባታዎች ማፍረስ እንደሚቀጥል ተገለጸ

- የሚፈርሱት ቤተ እምነቶች በራሳቸው ተቋማት እንዲፈርሱ የደረጋል ተብሏል

በኦሮሚያ ክልል በተመሠረተው የሸገር ከተማ አስተዳደር ሕገ ወጥ ናቸው ያላቸውን ግንባታዎችን ማፈረሱን እንደሚቀጥል የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ መናገራቸውን ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 1፣ 2015 መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ በትላንትናው እለት በፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ ልዑክ ከርእሰ መስተዳድሩ ጋር ውይይት አካሄዷል፡፡

በዚህ ውይይት ወቅት አቶ ሽመልስ በሸገር ከተማ ውስጥ ካት 800 ተቋማት መካከል 665 ተቋማት ‹‹ከፕላን ውጭ የተሠሩ በመሆናቸው›› አዲስ ለሚገነባው ከተማ ‹‹የማይመጥኑትን›› ቤተ እምነቶች ‹‹በሕጋዊና ከተማውን በሚመጥኑ ተቋማት ለመተካት›› እየተሠራ መሆኑን መናገራቸው በመግለጫው ተመላክቷል፡፡ ይህን በመተካት ሂደት በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኩል ውይይት በማካሄድ የእምነት ተቋማቱ ራሳቸው እንዲያፈርሱ ይደረጋል ማለታቸውም ነው የተገለጸው፡፡ በዚህም ከዚህ በኋላ መንግሥት ተቋማቱን ‹‹ማፍረስ እንደሚያቆም›› ሽመልስ ተናግረዋል ተብሏል፡፡

ዝርዝሩን ያንብቡ https://ambadigital.net/2023/15451/




ምን እንስራ?

ስራ መጀመር/መቀየር የሚፈልጉ ሰዎች የሚያነሷት ጥያቄ ናት። መልሷ እንደ ካፒታል መጠን፣ አከባቢ፣ የግለሰቡ ልምድ፣ እንደ ጊዜውና በሌሎች ምክንያቶች ቢወሰንም እኔ ከተመለከትኩበት አውድ ልጠቁማችሁ።

ምን ልስራ? ብላችሁ ስትጠይቁ አስከትላችሁ ማወቅ ያለባችሁ ከበድ ያለ ጥያቄ አለ። ሰው ምንድነው የሚፈልገው?

እኛ የመሰለንን፣ ወይም በህሊናችን የሳልነውን አሊያ ሌሎች ሰዎች በሌላ አከባቢ ሲሰሩት ያየነውን ለመስራት መጣደፍ ጉዳቱ/ኪሳራው ያመዝናል። ትንሽ ቆም ብለን ሰው/ተጠቃሚ/ ምንድነው የሚፈልገው? ብለን መጠየቅና በደንብ መገንዘብ፣ መለየት እንዲሁም ከተቻለ በቁጥርና በሙከራ የዳበረ መጠነኛ ጥናት ማድረግ ወሳኝ ነው።

እንደ ጥቅል ግን አብዛኛው ዝቅተኛና መሀከለኛ ገቢ ያለው ሰው አስማሚ ፍላጎቶች አሉት። የተወሰነውን ልጠቁማችሁ . . . .

1ኛ. ዕለታዊ ፍጆታ፦ ኑሮ እየተወደደ ነው። ውድነቱ በሁሉም መስክ ህዝቡን ሰቅዞ ይዞታል። ገበያ በሰአታት ልዩነት ይቀያየራል። በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ዋጋ እየናረ፣ በተቃራኒው በተለይ የተቀጣሪው ክፍያ እያደገ አይደለም። ስለዚህ ሰዎች ወጪያቸውን ለመቀነስ ይሞክራሉ። በተቻለ መጠን ለመኖር ወደሚገደዱበት ፍጆታ ይወሰናሉ። ስለዚህ በዚህ ጊዜ ስራ መስራት ያሰበ ሰው እለታዊ ፍጆታ ሽያጮች ላይ ቢያተኩር መልካም ይመስለኛል። ሸቀጥ፣ ምግብ ቤት፣ እህል ንግድ፣ ወጭ ቀናሽ አልባሳት የመሳሰሉትን ሊያካት ይችላል።

2ኛ. ርካሽ፦ ሰዎች እንደ ገቢያቸው ግዢያቸው ይወሰናል። ጥራትና ዋጋ ትይዩ ናቸው። በምንከፍለው ዋጋ ልክ ተመሳሳይ ምርት እንኳ ቢሆን የዋጋ ልዩነት አለው። ኑሮው ሲበረታ ሰዎች ጥራትን ከማማረጥ ይልቅ ዋጋ ላይ የበለጠ ትከረት ያደርጋሉ። ረከስ የሚል ነገር ይፈልጋሉ። ጥራቱ ዝቅተኛ የሆነ በርካሽ ዋጋ ለማቅረብ ከማሰብ ጥራቱ ሻል ያለ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መንገዶችን ማሰብ የተሻለ ነው።

እንደ ነጋዴ ደግሞ ከገበያ ዋጋ ማርከስ የሚቻለው የግድ ጥራትን በመቀነስ ብቻ አይደለም። ምርታማነትን/አቅርቦትን በማሳደግ ወጪን መቀነስ ይቻላል፣ ጊዜያቶችን ጠብቆ በጅምላ በመግዛት ንረትን መቀነስ ይቻላል፣ የግዢ ሰንሰለቱን በማሳጠር(ደላላ፣ ወኪል አከፋፋይ. . . ) በመቀነስ ዋጋን ማሻሻል ይቻላል። በሌሎችም ምክንያቶች ወጪዎቻችንን በመቀነስ ከተፎካሪዎቻችን የተሻለ ዋጋ አድርገን ደንበኛ መሳብ እንችላለን።

3ኛ. ቅርብ፦ ከነዳጅ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የትራንስፓርት ዋጋ እየናረ ነው። አንዳንዴ ከእቃው ዋጋ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ ትራንስፓርት ሰጪዎች አሉ። የሆነው ሆኖ የምንከፍተው ቢዝነስ በተቻለ መጠን ለሰዎች ተደራሽ የሚሆንበትን መንገድ ጎን ለጎን ማሰብ ይፈልጋል።
ለምሳሌ፦ ኹድራ(በድሬ ቋንቋ ነው😁፣ ሽንኩርት ቲማቲም፣ ድንች የመሳሰሉት የሚነግድ ነጋዴ አንድ ሰፈር ላይ የሚገዙ ሰዎችን አስተባብሮ በአንድ ትራንስፓርት(የትራንስፓርት ወጪው በራሱ የተሸፈነ) ቢያደርስላቸው ከሌላው ተፎካካሪ ነጋዴ እሱን ይመርጡታል! ለምን? ወጪ፣ ድካምና ሀሳብ ስለሚቀንስላቸው

ለምሳሌ በቅርቡ የጀመረውን "ሠረገላ" ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል። እያልኩ ያለሁት Delivery Service ለብቻው ከፍ ባለ ክፍያ ስጡ ማለቴ ሳይሆን፣ የማድረሻ መንገዶችን ከተቻለ በነፃ ካልሆነም በዝቅተኛ ወጭ አድርሱ ነው። ሩቅ አድርጋችሁ አታስቡት . . . ይቻላል!

4ኛ. ጅምላ፦ ሸማች የብሩ ዋጋ ቀን በቀን ዋጋ እያጣበት ስለሚሄድና፣ የዋጋ ንረቱን ለመቋቋም ጅምላ ግዢ እየተበራከተ ይሄዳል። ስለዚህ በተቻለ መጠን ሰዎች በጅምላ ሲገዙ የዋጋ ቅናሽ ወይም ሌላ ልዩ ጥቅም ይፈልጋሉ። ስለዚህ በጅምላ ለሚገዙ ሰዎች የዋጋ ቅናሽ ወይም ፓኬጅ አሊያ ስጦታ ማዘጋጀትና ሰዎችን ማርካት ወሳኝ ነው።

5ኛ. ዱቤ፦ ዱቤ የለም የሚለው አባባል መስሪያ ጊዜው እየቆመ መሄዱ አይቀሬ ነው። ሰዎች ኑሮን ለማሸነፍ ተወደው ሳይሆን ተገደው ወደ ዱቤ ስርአት መግባታቸው አይቀርም። ለምን? ወጪያቸው ከገቢያቸው እየተመጣጠነ ካልሄደ የተከሰተውን የበጀት ጉድለት በምን ይሞሉታል። በዱቤ ነው! (መቼም በጉቦና ሙስና አትሉኝም!

ስለዚህ የደንበኞቻችንን የደንበኝነትና የታማኝነት ደረጃ በመለየት በጊዜያቶች የተገደበ የዱቤ አገልግሎት መስጠት ከሌላው ተመራጭ ያደርገናል። እንኳን እኛ ባንኮችም ይህ ጉድለት በጊዜ የተረዱት ይመስላል። ዳሽን ባንክ "ዱቤ አለ" የሚል አሰራር ጀምሯል፣ ቴሌብርም እንዲሁ አገልግሎት ስትፈፅሙ የጎደለባችሁን ይሞላል። ቡሀላ ከናንተው ቢወራረድም😁

እነዚህ አምስት ነገሮች የኑሮው ጫና የፈጠራቸው ናቸው። በመንግስት አያያዝ ደግሞ ኑሮው እየባሰ እንጂ እየቀለለ መሄዱን እንጃ፣ ስለዚህ ሀሰቦቹን ብናስተውላቸውነ ከራሳችን ጋር አርቀን ብናስኬዳቸው እላለሁ!
(ሀሳብ መስጠት ይቻላል!👍

https://t.me/EzedinSultan14




እስከ ነገ አራት ሰአት ከመጅሊስ ጉዳይ እጃችንን አንስተናል፣ ወደ ቀደመ አጀንዳችን ስንመለስ!

ጨብሰቅ ያሉ ሰዎች የተሰበሰቡበትና ስለ ስራ ለማውጋት የከፈትነው ስለ ስራ የሚል ፌስቡክ ግሩፕ አለ!

ግሩፑ ውስጥ ሁሉም አይነት ሰዎች ተሰባስበዋል፣ በደንብ ካቀናነው ለወደፊቱ ብዙ መጠቃቀም ይኖረዋል፣ ለማንኛውም ያልተቀላቀላችሁ በጊዜ ተቀላቀሉን፣ ቡሀላ አናስገባም እንዳንል
በ5 ወር ውስጥ 6700+ በላይ አባላትን አቅፏል!

ተቀላቀሉ ሀሳብ፣ ልምድ እንለዋወጥ! ምርትና አገልግሎታችንን በነፃ እማስተዋውቅ፣ እንሽጥ እንግዛ!

ዳይ ወደ ስለ ስራ!
ሊንክ👇👇👇
https://www.facebook.com/groups/1153093882014917/?ref=share&mibextid=NSMWBT

Показано 20 последних публикаций.

616

подписчиков
Статистика канала