ምርጥ ታሪክ ፅፌ አቀረብኩላችሁ!!
አንድ ኩራተኛ የሆነ ሰው ጥሩ ልብስ ለብሶ በኩራት ታጅቦ እራሱን እየቆለለ፤ በአንድ ገበያ ይዘዋወር ነበር። ታድያ ፈሳሽ ጁስ የምትሸጥ ሴትዬ በአጠገቡ ስታልፍ ይመለከታል። ጠራትና
"ምንድነው የምትሸጭው አላት?"
እሷም: "ፈሳሽ ጁስ ነው ጌታዬ" አለችው
እሱም፡ አሳይኝ
በእንስራ የያዘችውን ፈሳሽ ከጀርባዋ ላይ ለማውረድ ስትሞክር ድንገት የሰውየው ልብስ ላይ ይህ ፈሳሽ ይደፋበታል። ሰውየው ከባድን ቁጣ ተቆጣ። እንዲህም አላት
"የዚህን ልብስ ዋጋ እስከምትከፍይኝ ከዚህ ቦታ የትም አልሄድም" ሲል ዛተ። ሴትየዋም እያለሳለሰች ትለማመጠው ጀመር።
"እባክህ ተወኝ ጌታዬ ምክንያቱም እኔ ምስኪን ነኝ" አለችው። ሰውየውም
" እስክትከፍይኝ የትም አልሄድም" አላት። እሷም ዋጋውን
"ስንት ነው?" ስትል ጠየቀችው። እሱም
"1000ብር" ሲል መለሰላት። እሷም...
"እኔ እኮ ደሃ ሴት ነኝ ከየት አመጣለሁ" አለችው። እሱም..
"ምን አገባኝ" በማለት ፍፁም ጭካኔውን አበረታባት። እያስፈራራትና እየዛጠባት ሳለ፤ አንድ ወጣት በመንገድ ሲያልፍ ይመለከትና
"ምን ሆነሽ ነው?" ሲል ጠየቃት። እሷም የተከሰተውን በደንብ አስረዳችው። ወጣቱም እንዲህ አለ...
"ብሩን እኔ ሰጥሃለው" ብሎ አንድ ሺህ ብር በማውጣት ለሰውየው ከፈለው። ኩራተኛው ሰውየም ብሩን ቆጥሮ ተረክቦ ሊጓዝ ሲል፤ ወጣቱ ልጅ...
"ተረጋጋ እንጂ ወደየት ነው!?" አለው። ሰውየውም..
"ምን ፈለግክ!?" አለው። ወጣቱም...
"የልብስህን ዋጋ ወስደሃል አይደል!!" አለው። ሰውየውም..
"በሚገባ እንጂ!!" አለ። ወጣቱም...
"ታድያ ልብሱ የታለ?" ሲል ጠየቀው። ሰውየም
"ለምን!?" አለው። ወጣቱም...
"የልብስህን ዋጋ ሰጥተንሃል፤ ስለዚህ ልብሱን ስጠን አለው። ሰውዬውም..
"ራቁቴን ልሄድ ነው!?" አለው። ወጣቱም...
"አይመለከትኝም! ምን አገባኝ!!" አለው። ሰውዬውም..
"ልብሱን ካልሰጠውህስ?" ሲለው ወጣቱ..
"ገንዘብ ትከፍለናለህ አለው" ሰውዬውም
"አንድ ሺ ብሩን ነው አለ?" ወጣቱም...
"አይይ አይደለም። እኛ የምንልህን ነው" ሲል መለሰለት። ኩራተኛውም ሰው እንዲህ አለ...
"እንዴ የከፈልከኝ እኮ አንድ ሺ ነው" ወጣቱም..
"ስለከፈልኩት አያገባኝም አለው" ሰውዬውም...
"ስንት ነው ምትፈልገው?" አለው። ወጣቱም...
"ሁለት ሺህ ብር" አለው። ሰውዬውም...
"ይህ ብዙ ነው!!" ሲል ተናገረ። ወጣቱም...
"እንግዲህ ልብሱን ስጠና!!" አለው። ሰውዬውም...
"ልታዋርደኝ ፈልገህ ነው ራቁቴን" አለው። ወጣቱም....
"ሴትየዋን ልታዋርድ እንደፈለግከው አዎ!!" አለው። ሰውየውም ..
"ይህ በደል ነው!!" አለ። ወጣቱም....
"እንዴ አሁን ስለ በደል ታወራለህ!! ድንቅ ነህ" አለው። ሰውየውም በማፈር የተባለውን ብር ለወጣቱ ከፈለው።
ወጣቱም ይህ ሁለት ሺህ ብር ለምስኪኗ ሴት ስጦታ መሆኑን አውጆ በደስታ ሸኛት።
#የእለቱመልዕክቴ ከ ጅብሪል
ክርክሮችን ለመፍታት #ጥበብ ሁነኛ መፍትሄ ናት!! ህይወትም ኩራትና እኔ የበላይ ነኝ የምንልባት የፋከራ መድረክ አይደለችም።
ወደ ግሩፕ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ!!
Join our best channel !!!
@jibrilhonaliyat @jibrilhonaliyat