Halal islamic lovers ❤ story


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ።
ይህ Ĥªłåĺ islamic lovers story ነው።
በቻናላችን ላይ........
❤ ኢስላማዊ ታሪኮች
❤ ሀዲስ
❤ ጣፋጭ የፍቅር ታሪኮች
❤ ኢስላሚክ መዝናኛ
❤ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።
@Halal_islamic_lovers_storye 👈 discuss group
@Halal_islamic_lovers_story 👈 main channel
Share....

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


❝ይድረስ ለኢድ ሶላት ለሚወጡ እህቶች❞
〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖

☞ የኢድ ሶላት ለወንድም ለሴትም የተደነገገ ኢባዳ ነው። ሴቶች ልክ እንደ ወንዶቹ ለኢድ ሰላት መውጣታቸው የተወደደ ተግባር ነው። እንዲወጡም ታዘዋል። ነገር ግን በምትወጣበት ሰአት እነዚህን መስፈርቶች ልትጠብቅ ይገባል።

①⇘ወፍራም፣ ሰፊ፣ ረጅምና ሁሉ ሰውነቷን የሚሸፍን አለባበስ መልበስ አለባት!
②⇘ሽቶ የሚባል ነገር በፍፁም ሊነካት አይገባም!
③⇘አቅሟ በቻለው ሁሉ ከወንዶች መራቅና ከነሱ ጋር ሳትጋፋ የመንገዱን መሀል ሳይሆን ጫፍ ጫፋን ይዛ መሄድ አለባት!
④⇘በተክቢራም ይሁን በሌላ ፅምፇን ዝቅ ማድረግ አለባት!
⑤⇘ጫማዋ ከፍ ብሎ ሲንቋቋ ሰውን የሚጣራ መሆን የለበትም!
⑥⇘የልብሷ ከለር ደመቅ ብሎ የሰውን አይን የሚስብና ጌጣ ጌጦች ያሉበት መሆን የለበትም!
⑦⇘እራሷ ከመፈተንና ሰውን ከመፈተን ጥንቃቄ ልታረግ ይገባል!
⑧⇘ በአረማመዷ፣ በአነጋገሯና በእይታዋ ሀያእ የተላበሰች ልትሆን ይገባል!

☞ምክንያቱም ኸይር እሰራለሁ ብላ ወንጀል ከመሸከም፣ የጀነት ሰበብ አደርሳለሁ ብላ የጀሀነም ሰበብ እንዳታደርስ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባታል።

☞ በአሁን ሰአት ግን ለኢድ ሶላት ብለው በሚመጡ አንዳንድ ሙስሊም እህቶች እያፈርን አንገታችን እየተደፋ ነው። እስልምና እንዲሁም ሙስሊሞችን እያሰደቡ ነው።

☞ልብሷ ከራሷ ተጣብቆ፣ ሰውነቷን ወጣጥራ፣ ፊቶቿ እግሮቿና እዶቻን ከፍታ፣ ሽቶ ተለቅልቃ፣ ቻፕስቲክ ተቀብታ፣ ቅንድቧን ተቀንድባ፣ የተቀባችውን ሂና እያሳየች፣ የኢትዮጵያ ባንድራ ግምባራ ላይ አስራ፣ ወደ ግራና ቀኝ የሚያወዛውዝ ጫማ ለብሳ፣ ድምፇ ከፍ አድርጋ እየሳቀች፣ ከወንዶች እኩል እየተጋፋች፣ ወንዶችን አፍጣ እያየች፣ በየሱቁ እየተዘዋወረችና ሌሎችም ሙሀለፋቶች በመፈፀም እራሷም ተፈትና ሌላውንም ፈትና፣ እራሷ ወንጀል ውስጥ ከታ ሌላውንም ዘፍቃ የወንጀል መአት ተሸክማ ወደ ቤቷ የምትመለስ አለች።

✑እንዲህ አይነቷ እህት ምናለ እቤቷ በተቀመጠች!


⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱
https://t.me/Halal_islamic_lovers_story


🌙እንኳን ለ 1444ኛው የ ኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! ⭐️


አሏህ አክበር! አሏህ አክበር ! አሏህ አክበር
ላኢላሀ ኢለሏህ አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወሊላላሊሀምድ !

የነገዋ ቀን በሙስሊሙ ማህበረሰብ በጣም ምርጥ ቀን ነች! ነብያችን ሙሀመድ ሰ ዓ ወ የአረፋ ቀን ጠዋት ወደ ሰላት ስትሄዱ ምግብ አትብሉ ብለዋል!

ይህ ቀን የመስዋትነት ቀን ነው " ኢብራሂም ልጁን እስማኢልን ለዕርድ ያቀረበበት ቀን ነው!

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለኢደል አድሀ አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ይሁንላችሁ ይሁንልን

SHARE |




እስቲ ፆመኛ የሆነ❤
Опрос
  •   ❤
  •   አይደለሁም 😔
60 голосов


የአረፋ ቀን ፆም!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ማክሰኞ ሰኔ 20 ነው።

ጆይን፡‐ @Halal_islamic_lovers_story


👉ይሄ ሁሉ ሰው በአንድ ቦታ ላይ ፣ ለአንድ አላማ ፣ በአንድ አይነት አለባበስ፣ በአንድ ቋንቋ ወደ ጌታው እየተጣራ ይገኛል። እዚህ ቦታ ላይ ባለስልጣንም ሆንክ ተርታው ማህበረሰብ ነጭም ሆንክ ጥቁር ድሃም ሆንክ ሀብታም ምንም ልዩነት አይኖርህም።

👉ሱብሀነአላህ!! አላህ ዘንዳ ሁሉም እኩል ነው። ሀብታም፣ ደሀ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ ባለስልጣን ሁሉም እኩል ነው ምንም ልዩነት የለም። አላህ ዘንድ የሚጠቅመው ኢባዳ፣ ሰላት፣ ፆም፣ መልካም ስራ የተባለ ነገር ሁሉ ነው፤ሌላው እዚሁ ዱንያ ላይ የሚቆይ ትርፍ የሆነ ነገር ነው።


ያ ረብ! ለናፈቁ ባሮችህ ወፍቃቸው፤ የወፈቅካቸውንም ሐጀን መብሩር አድርግላቸው።🤲🤲🤲




Masha allah👏👏👏👏🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦




🥵አይኔ ነው ወይስ ይንቀሳቀሳል 👀


እስቲ ቀጣዩ ክፍል ይለቀቅ ምትሉ❤️


አይነ በሲሩ አፍቃሪ

ልብ አንጠልጣይ ትረካ _ ክፍል – 2

ደራሲና ተራኪ – አብዲ ኢኽላስ

👉 https://t.me/Halal_islamic_lovers_story


ቀረብ ሲላቸው ይሰማቸዋል።"እንደዚያ በለኛ እኔ የምን ሽፍታ አገኘህ እኮ ብዬ ነው እሺ!" አሉና ወደ ውስጥ ዘለቁ። የሳሎኑ ግርማ አስደነቃቸው እጅግ የተንጣለለ ቤት ሲያዩ ተመሰጡ።ዙሪያ ገቡ መቃኘት ጀመሩ።ምራቃቸውን ሲውጡ ከጉሮሮአቸው ሲያልፍ ይሰማል።ጋሽ አክመል መቀመጫ ፈለጉ ውስጥ ያሉ ኻዲሞች ቦታ ሰጡዋቸው።ከአረብያኑ ተቀመጡ።የሚጠጣ መጣላቸው፤ ሻልም አለበሷቸው፤ ጫማቸውንም አውልቀው ከዳር አስቀመጡላቸው።አደብ የተሞላ ሙሉ እንክብካቤ በዚህ ጊዜ አህመድ ከጓዳ መጣ። ኢስላማዊ ሰላምታ አቅርቦላቸው ራቅ ብሎ ቁጭ አለ። የት እንደመጡ፣ ማን እንደሆኑ ለመጠየቅ አልደፈረም።ብቻ ፈገግ ብሎ ያስተውላቸዋል። ጋሽ አክመል ጉሮሮአቸውን ጠራርገው ንግግራቸው ጀመሩ።"እጅግ ያማረ እና የተዋበ ህይወት ነው ያለህ አላህ ባለው ላይ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ" አሉት።አህመድ በአሚን ተቀበላቸው። "ግና የምትንጎራደድ ወይዘሮ አትታየኝም" አሉት።አህመድም " እ ትዳር ማለቶት ነው" ብሎ ጠየቃቸው። ጋሽ አክመል " የምን አዳር እኔ ለአዳር አልመጣሁም እሄዳለሁ" አሉት።አህመድ ድምፁን ከፍ አድርጎ "እ ሚስት ማለቶት ነው ያልኩት" አላቸው።ጋሽ አክመልም"አዎ ሚስት ቢጤ ማለቴ ነው"አሉት። አህመድም መልሶ " እ አይ አላገባሁም" አለ ድምፁን ቀንሶ እየተሽኮረመመ።

" አልገባሁም ይሄ ሰው ያመዋል እንዴ ዛሬ ውስጥ እኮ ነው ያለኸው እስኪ ጥራቸው " አሉ። አህመድ ወደ እሳቸው እየቀረበ "አይደለም አይ ሚስት አላገባሁም ነው ያልኮት" አላቸው። እሳቸውም ሰሙት "እንደዛ ነው እንዴ እንግዲ ይቅርታ አድርግልኝ እማዳመጫዬ ላይ ችግር ስላለ ድምፅ መለየት ይሳነኛል። እወታደር ቤት መድፍ ጮሆብኝ ነው።እዛ ነው እንዲ የሆንኩት" አሉት።አህመድም " እ ችግር የለውም ጠጋ ልበሎት ስለማይሰማ" አላቸው። "ጥጋቦት ስለማይስማማኝ ጆሮዬን እኮ ነው ያልኩህ ሌላ አላልኩም"አሉት። አህመድም በደንብ እየተጠጋቸው " አይደለም ጠጋ ልበል ነው ያልኩት እ ይቅርታ" አለና ከአጠገባቸው ተቀመጠ።ጋሽ አክመል " እንግዲህ ራሴን ላስተዋውቅህ እኔ አክመል እባላለሁ። የአባትህ የወታደር ቤት ጓደኛ ነኝ" ብለው ገና ሳይጨርሱ አህመድ አይኖቹ በእንባ ተሞሉ። ነግረውት ነበርና አባቱ በውትድርና አለም ላይ ሳለሁ አንድ ጓደኛ ነበረኝ ግራ እጁን ለኔ ሲል ፈንጅ ላይ አስቀምጦ የኔን ህይወት ለመታደግ እጁ የተቆረጠ የምወደው። በህይወቴ እሱን ባገኘው ሌላ ምመኘው የለም አንድ ነገር ቃል ገብቼለታለሁ ያን ቃሌን ሳልሞላ ሞት እንዳይቀድመኝ እሰጋለሁ ይሉ ነበረ የአህመድ አባት ታድያ ጎንበስ ብሎ የጋሽ አክመልን እጅ ሲመለከት እውነትም ግራ እጃቸው በቦታው የለም አባቱ ረጅም ግዜ ሲያፈላልጓቸው የነበሩትን ያን ውዱ ጓደኛቸውን አጠገቡ ስላያቸው በደስታ ባባቱ ደግሞ በትኩስ ሀዘን እንባ አይኑን ጋረደው ድንገት ሳያስበው ተነስቶ ግንባራቸውን ሳማቸው

ክፍል-3
ይቀጥላል....



@Halal_islamic_lovers_story


አይነ በሲሩ አፋቃሪ

ክፍል-2

ደራሲና ተራኪ- አብዲ አኽላስ

ሱለይማን አስፍልቱን ለመሻገር እየሞከረ ሳለ ሲኖትራኩ በፍጥነት ወደ እሱ ቀረበ:: በዚህ ጊዜ ነበር መርየም የደወለችለት ::ስልኩ እንደጠራ ባለበት ደርቆ ቀረ:: በፍጥነት ስልኩን አንስቶ በፈግታ ተሞልቶ በጉጉት ተንገብግቦ "ሄሎ" አላት:: በዚህ ጊዜ ማየት የተሳነው እንደሆነ የተረዳው የሲኖትራኩ ሹፌር በከፍተኛ ጥብና ስልት በውሀ የረጠበውን አስፍልት ሊንሸራተት ሳይሰጋ የአስፍልቱን ጥግ አስታኮ በፍጥነት አለፈው:: ኡማ ልባቸው አረፍ አለላቸው፣ፈገግ ለማለት ሞከሩ ሱለይማን ያለውን ታሪክ አያስተውለውም ክላክሱም በሀይል ከተማውን አደብልቆት ያለፈውን የሲኖትራክ ድምፅ እንኳን ለሱ ምንም አይደለም:: የመርየምን ድምፅ ሰምቷልእና መርየም ለሁለት ቀናት ያክል ድንገት በበላችው የተመረዘ ምግብ አማካኝነት ሆስፒታል እንደነበረች ነገረችው::

በእርግጥ ለሱለይማን እንኳን ከፍተኛ ህመሟን ቀርቶ ጉንፋኗን መንገር እንኳን ከባድ እንደሆነ ታውቃለች:: ግና ሁለት ቀን የጠፍችበትን ምክኒያት ቀለል ያለ ቢሆን ክፉኛ እንደሚጎዳ ተረድታለች:: ለዚህም እውነቱን መናገር መረጠች:: ሱለይማን በድንጋጤ ልቡ ራደ:: አሁን ስላለችበት ሁኔታ ደጋግሞ ደጋግሞ ጠየቃት ደህንነቷን ጠንከር ባለ መሀላ አረጋገጠችለት:: ያኔ ልቡ ተንፈስ አለ:: በእርጋታ ቁጭ ለማለት ሞከረ:: አላወቀውም አስፋልት ላይ ነበር:: ኡማ በፈገግታ ተሞልተው እንዴት ያለ ፍቅር ነው ሲሉ ተገርመው በአጃኢብ ስሜት ወደ አስፍልቱ ሄደው ሱለይማንን እጁን ይዘው ወደ ዳር አመጡና ከአጠገባቸው የረጠበ ድንጋይ ላይ ካርቶን አስደግፈው አስቀመጡት:: ይህን ጊዜ ማን ምን ያድርግለት፣ማን ወዴት ይውሰደው ፣ለምን ይዘውት መጡ፣ምን ተፈጥሮ ነው፣ ሱለይማን አያገባውም::

እሱ በሀሳብ ካናዳ ነጉዷል:: ከእሷ ጋር ሌላ ታሪክ ውስጥ ነው::ኡማ ይህንን ስለሚያውቁ አይደለም ሊወቅሱት ሰላም ሊሉት እንኳን ጊዜ ሊሻሙት አልፈለጉም:: ስራቸውን ቀጠሉ እሱም ስራውን ቀጠለ:: ከዚህ መንደር በ 2 ኪ· ሜ ርቀት የሚገኘው አንድ ፀጥ ያለ ሰፈር ወደ እዛ እንግባ አንድ መልካም፣እጅግ የተወደሰ ሰው ወዳለበት ወደነ አህመድ ሰፈር:: ሰፈሩ በሙሉ የእነ አህመድ ሰፈር ተብሎ ይጠራል:: አህመድ በሰፈሩ ላይ ታዋቂና እጅግ ተወዳጅ ሰው ነው:: በሀብት ማማ ላይ ጣሪያ የነካ ከመሆኑም በላይ እጅግ ቢዝነስ አዋቂና ተቋራጭ ስራዎችንና ጨረታዎችን በስልትና በጥበብ አሸናፊ ነው:: አይደለም የሰፈሩ ሰው የሩቆቹ እንኳን ወዳጅ ይቅርና ባላንጣ ጠላቶቹ ተፎካካሪዎች እንኳን ይመሰክሩለታል:: ጉምቱ የንግድ ሰው ነው:: እጅግ የተሳካለት እና ከአባቱ የወረሰውን የንግድ ጥበብና ከፍተኛ ገንዘብ አማክሎ የሀብት ማማ ላይ የተሰቀለ ታላቅ ሰው አህመድ መልከ መልካም እጅግ የተዋበ ቁመናና ተክለ ሰውነት የተላበሰ ወጣት ነው:: ለጋ ወጣት የመንደሩ ሰው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለአህመድ ዱዐ ሳያደርግ አያልፍም:: እሱን ያልመረቀው አዛውንት ለሱ ዱዐ ያላደረገ ሹማምንት የለም::

ሁላቸውም የመስጂድ ኢማሞች ሳይቀሩ ያደርጉለታል::ይኸውም አህመድ የተሳካለት በጥበቡ እና በንግድ አዋቂነት ስልቱ ሳይሆን በሰጪ እና በለጋሽነት መሆኑ ን እራሱ ይመሰክራል:: ሁል ጊዜ ጁመዐ ጁመዐ የምግብ ሶደቃ የልብስና የቁሳቁስ እደላ ያደርጋል:: አህመድ ለነገዬ ብሎ ሳይሰጋ፣ ድህነትን ሳይፈራ፣ ማጣት ሳያስበረግገው መስጠትን ይሰጣል:: እጅግ አብዝቶ ፣ አትረፍርፎ ይሰጣል:: ከእቤቱ የገባ ሳይሞላለት አይወጣም:: የመንደሩ ሰው በህመም፣ በችግርም፣ በድግስም፣ በደስታውም ጊዜ አህመድን ይፈልጋል:: ለጎደላቸው ይሞላል:: ከዚህም አልፎ የተጣላን አስታራቂ ፣ የተጠራበት ሁሉ ኺያጅ ነው። አህመድ ከፍታ ላይ ሆኖ እንኳ ማንንም አይንቅም ለሁሉም ክብር ይሰጣል። እጅግ የተንጣለለ ውብ ቤቱ ውስጥ ድሆች ሲንጎራደዱበት ማየት የተለመደ ነው። በሩ በአደገኛ አጥር አይታጠርም፤ ለሁሉም ክፍት ነው ሁልጊዜም። ታዲያ አህመድ እነዚህ ሁሉ የተሟላ ውብ ስብዕናና ማንነቱ ጎን ግን አንዲት ደካማ ጎን አለችው።ይኸውም እስካሁን ድረስ ወደ ትዳር ታጭቶ አላገባም፣ አልወለደም ብቻውን እቤት ውስጥ ይኖራል፤ ከአገልጋይ(ኻዲሞች) ጋር በተደጋጋሚ እጅግ ብዙ ጊዜ ለሚስትነት የቀረቡ ሴቶች በህይወቱ ውስጥ መጥተው የነበሩ ቢሆንም እሱ ግን ዞር ብሎ ሊመለከት አልቻለም።

ለዚህ ብቸኛ ምክኒያቱ ደሞ ከቅርብ ጊዜ በፊት በሞት የተለዩት አባቱ ናቸው። አህመድ አባቱን ይወዳል፤ አሳምሮ ይወዳል።እናትም አባትም ሆነው ያሳደጉት ከትቢያ አቧራ ላይ ተነስተው እዚህ ማማ ላይ ያደረሱት አባቱ እጅግ ይወድ ነበር።እሳቸውን በሞት ካጣ ጊዜ ጀምሮ ውስጡ ሰላም ማግኘት አቅቶታል።አህመድ ለአባቱ የሚገባውን ማድረግ ችሏል፤ በሚገባ ኻድሟቸዋል፤ ጡሯቸዋልም ጭምር ግና የአባትን ሀቅ መክፈል ፍፁም አይቻልምና ለብዙዎች ብርቅ የሆነውን የ90 አመት የዕድሜ ባለፀጋነትን እንዲጎናፀፉና የመጨረሻ የእርጅና ደረጃ ላይ ቢደርሱም እንኳን አባት ናቸውና አልጠገባቸውም። ከዚህ ሁሉ እጅግ በዲን የተሞሉትና በአደብ ያነፁት እኚህ ውድ አባት አላህ ወደ ራሱ ሊወስዳቸው ህመምን አቅልሎ፤ ያለምንም የህመም ስሜት በድንገት ነውና አህመድ ሳያስበው ሳይሰናበቱት ቁጭት ቢጤ ከልቡ ተሰንቅሯል።በዚህም ምክኒያት ለማግባት ዕድል አላገኘም፤ ለራሱም ጊዜ አልሰጠም።ዛሬ ግን ቀኑ የደረሰ ይመስላል። የግቢው በር ተንኳኳ ጋሽ አክመል ናቸው፤ ጋሽ አክመል የዚህ ሰፈር ሰው አይደሉም፤ ጋሽ አክመል እጅግ የጠና እድሜ ላይ የሚገኙ፤ ከወገባቸው ጎበጥ ያሉ ፤ በእርጅና ጉስቁል ያሉ፤ አረንጓዴ ግን የድሮ እንደሆነ የሚያስታውቅ ሙሉ ሱፍና ከተጨራመተ ጫማ ጋር ተጫምተውት አማይማ ከላያቸው ላይ ጣል አርገው ከበሩ ተሰይመዋል።

ጥበቃው በፍጥነት ሄዶ ከፈተላቸው።አሉት"እንዴት ዋልክ ልጄ ይህ ቤት የአህመድ ቤት ነው"ሲሉ ጠየቁት፤ጥበቃውም"አዎን" አላቸው።ወደ ውስጥ እንዲገቡም ጋበዛቸው።አህመድ ጋር እንዲ ነው ማንም ከውጪ ሆኖ አይስተናገድም ውስጥ ድረስ እንዲዘልቅ ይፈቀድለታል። ወደ ውስጥ አስገባቸው። ጋሽ አክመል ብዙም ጆሮአቸው አይሰማም።ከርቀት ያለን ድምፅ መስማትና መለየት ይሳናቸዋል። እጅግ ከአጠገባቸው ካልሆነ በስተቀር ድምፅ የተነገራቸው አይለዩም። ጥበቃውም ወደ ክፍላቸው ይዟቸው ገባ።ከሳሎን ደረሱ ጋሽ አክመል የጥበቃው ፊት ላይ ያለችን ትንሽ ቁስል ተመልክተው ትኩረታቸውን እዛ አደረጉ። አይናቸውን አጨምጭመው ከተመለከቱት በኃላ እንዲ ሲሉ ጠየቁት"ፊትህ ላይ የወጣብህ ነገር ምንድነው ልጄ"? አሉት።አንድም የባህል ሀኪም ስለሆኑ ቁስል ባዩ ቁጥር አያልፉም። ጥበቃውም " አይ ሽፍታ ነው" አላቸው ቀለል አድርጎ። ጋሽ አክመል ግን የመስማት ችግር አለባቸውና "ሽፍታ ነው ያልከኝ የምን ሽፍታ ደግሞ የሚያቆስል ሽፍታ ከየት መጣ ከተማም ሽፍታ አለ እንዴ" አሉት።ዘበኛውም ደንገጥ ብሎ ወደ አጠገባቸው ቀርቦ"አይደለም ቁስል ነው ቁስል"አላቸው።


ኡማ ከመቀመጫቸው አስነስቶ ያበረገጋቸው ጉዳይ የሱ በፍጥነት መምጣት ወይም በመከፋት ስሜት ውስጥ መዋለሉ አይደለም ። ድንገት ሳያየው ከቀኝ አቅጥጫ እየበረረ በመምጥት ላይ ያለው እቃ የጫነ ሲኖትራክ ነው እንጂ ። ሱለይማን ሲኖትራኩን አያሰተውልም ካለበት ስሜት ሆኖ ካለው ጫጫታና ግርግር አንፃር አስፓልቱን ያለማስተዋል እየቆረሰወደ እሳቸው እየመጣ ነውና ።
ሲኖትራኩ ባለበት ፍጥነት በፍፁም መቆም እንደማይችል አስተውለዋል ። ሱለይማን ወደእሳቸው ይጋልባል። ሲናትራኩም በሀይል ተምዘግዝጎ ወደ እርሱ ይከንፋል ። ኡማ መቀመጥ አልቻሉም። ተነስተው መጮሁን ተያያዙት ሲኖትራኩ እጅግ ቀረበ ሱለይማንም በመርየም ሀሳብ ውስጥ ክንፍ ብሎ ዙሪያ ገባውን ማዳመጥ አቁሞ በፍጥነት ወደእሳቸው መሀላ አስፓልት ላይ ደረሰ። ኡማ ጩኸታቸውን አቀለጡት።
·


ክፍል ሁለት
ይቀጥላል....



@Halal_islamic_lovers_story


አይነ በሲሩ አፍቃሪ

ክፍል – 1

ደራሲና ተራኪ – አብዲ ኢኽላስ

ሱለይማን አይኖቹ ማየት የተሳናቸዉ የቀን ጨለማ የሆነበት ሰላሳዎቹን በማለፍ ላይ ያለ ለጉልምስና የተጠጋ ወጣት ነው። ሱለይማን ምንም እንዃ አይኖቹ ማየት ቢሳናቸው እንኳ ልቡ ግን በብርሃን የተሞላ ነው ።አብሶ ለመርየም ያለው ፍቅር በቃላት የሚገለፅ አይደለም ።ከሁሉ በላይ የሚዐጅበው መርየምን አንድም ጊዜ አሳይቱአት አያዉቅም እሷም አይታዉ አታውቅም ። ካናዳ ውስጥ ከሚገኝ አንድ ትልቅ ካምፓኒ ውስጥ ምትሰራው መርየም እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ በአስገራሚ ግጥምጥሞሽ ተዋውቃው እጅግ ሀያል በሆነ የፋቅር አክናፍ ውስጥ እየቀዘፉ ይገኛሉ ።

ሌላ ህይወት ሌላ አለም ፈጥረዉ በራሳቸው ምህዳር በራሳቸው ምህዋር ዉስጥ ሱለይማን ከመላው ቤተሰቡ ጋር በማያውቀው ሁኔታ ተቆራርጦአል እንዴት አንደሆነ እንኳን አያውቅም በቃ እሱ የሚያውቀው ነገር ቢኖር አንድ ሰሞን እጅግ ዉብ የነበረ ህይወት እንደነበረው ነው ።እጅግ የተዋበ ደስተኛ ቤተሰብ አንደነበረው ድንገት እንዴት እራሱን እዚህ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ትቢያ ከተሞላ ፉራሽ ውሰጥ ከወየበ ቲሸርትና ከአሮጌ ሱሪ እጅግ ከተጨራመተ ጫማና ደቃቃ ህይወት ውስጥ እንዳገኘው በፍፁም ማወቅ አልቻለም ። አይኖቹንም ቢሆን እንዴት እና ለምን እንዳጣቸው ማስታወስ ተስኖታል ያይ እንደነበር ግን ያዉቃል ።ይህን ማሰብ ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። አሁን ግን በነዚህ ችግሮች ውስጥ ተተብትቦ ላይ ታቹን መባከን እንዲያቆም ከላይ ልዩ ስጦታ ተሰጥቶታል። መርየም በፍቅሯ አክናፍ በሀይል የነደደላት ቀንሌቱን ያለርሷ አልነጋልህ ያለው እጅግ ልዩ እና ውብ ፍቅር ውብ ፋጥረት።

መርየም እና ሱለይማን እጅግ የሚያስቀና የፍቅር አለም ውስጥ ናቸው ።በየቀኑ በየሰዓቱ በየደቂቃው ይደዋወላሉ የርሷን ድምፅ ለሰዓታት ሳይሰማ መቆየት አይችልም እሷም ብትሆን ስራ ስትገባ ስትቀመጥም ሆነ ስትነሳ ስትወጣ ትደውልለታለች በየደቂቃው ስልኩን ክፉት አድርጎ የሚጠብቀው የርሷን ስልክ ነው ከርሷ ዉጪ ምድር ላይ ሰው የሌለው እስኪመስለው ድረስ በርሷ አለም ዉስጥ ክፉኛ ተነድፎ ሌላ ነጎድጓድ ዉስጥ ነግዷል ስልኳ ሲጠራ ልክ ከአመታት በኋላ ገና እንደደወለችለት እንጂ ከትንሽ ሰአታት በፊት ያናገራት አይመስልም ልክ እንደ ህፃን ልጅ አመታትን ወደታች ቁልቁል ተጉዞ ይቦርቃል ይደሰታል የጥርሱ ፍልቅልቅታም ያኔ ፋንትው ብሎ ይታያል


አጃኢብ ያሰኛሉ ያስቀናሉም ጭምር መርየም እና ሱለይማን በጥቂት ጊዚያት እጅግ ውብ የሆነ ፍቅር
አሁን ትልቁ ችግር መርየም በቅርብ ለመምጣት ማቀዱአ ነው። ሱለይማን ደግሞ ከዛሬ ነገ እነግራታለሁ እያለ የአይኑን ማየት አለመቻል አልነገራትም። ብዙ ቀናት ዳር ዳር ቢልም እንኳን ልትረዳለት አልቻለችም ብዙ በተቀየጡና በተቀነባበሩ ቃላት ቢያወራት እንዃን ሀቁ ሊገባት አልቻለም እንዴት አድርጋ ማየት አይችልም ብላ ትመን እሷ እስትንፋሷ በሙሉ ሱለይማን ሆኑአል እሱም የሌት ቀን ህልሙ እሷ ሆናለች። ይፈቃቀራሉ የሚለው ቃል ለነሱ መጠቀም እንደ ስድብ ይቆጠራል ምክንያቱም ከዛም አልፈው ሩቅ ከተጓዙ ሰነባብተዋል እና ከመፈቃቀር አልፈዉ በስትንፋስ ደረጃ የአንዳቸው የመኖር ምከንያት እስኪመስሉ ድረስ ይፈላለጋሉ ከአቅም በላይ ሱለይማን ከገባበት እና ድንገት እንዴት እንደተፈጠረ ፍፁም ከማያውቀው ብቸኝነት ፍንትው አድርጋ ያወጣችውና ያለፈ ታሪኩን መርሳት ዳግም ያስረሳችው መርየም ነች ለርሷም ቢሆን አገር ቤት ያለውን ቆርጣ የጣለችውን ህይወቷን በብዙ ምክንያቶች ተተብትባ ከብዙ ችግሮች በኋላ አልፋ አልመለስበትም ያለችውን ሀገሯን ዳግም እንድትቃኝ አሰኛት ይኸውም የሱለይማን ፍቅር ነው።

ታዲያ በቅርብ ጊዜ ወደ እሱ ለመምጣት ማቀዷን ከነገረችው ጊዜ ጀምሮ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይሰማዋል። አንዴ ደስ ይለዋል አንዴ ደግማ እንዳያጣት ይሰጋል። እጅግ የሚአጅበው ደግሞ ሱለይማን እስኪያያት ድረስ ነው የናፈቀው። ሱለይማን እኮ ማየት አይችልም ።ግና መጥታ በአይኑ እንደሚያያት ነው እየተሰማው ያለው አይቷት ፍቅሩን እንደሚጠግብ ናፍቆቱን እንደሚወጣ እየተሰማው ነው ። ግን እንዴት? እይታ በተነሱ አይኖቹ ሺ ጊዜ ቢመኛት እንኳን አይኑ ጨልሟል ሊያያት አይቻለውም። በልቡ ላይ የሳልትን ናት ብሎ ያሰባትን እሷን ያግኝ እንጂ መርየምም ብትሆን ሀገሬ ገብቼ የተውኩትን አለም ዳግም እኖረዋለሁ፣ የተበታተነብኝን እሰበስባለሁ ፣ ወደ ፍቅር ህይወቴ እመለሳለሁ ብላ ያሰበችው ምን አልባት አይኖቹ የሚያዩ እንጂ ማየት የተሳነውን ሱለይማንን አይደለም። እንዴት ትሁን ቅርብ አቅዳለች። ሱለይማን ከመርየም ስልክ ውጪ ሌላ ስልክጠራ ከተባለ የአንድ ሰው ብቻ ነው የኡማ ሀለውያ ። ኡማ ሀለውያ ሱለይማን ኸትሮ ሲጠራቸው ኡማ ብሎ ነው።በሀረሪ የሀደሬ ባህል ቋንቋ ኡማ እናቴ እንደማለት ነው።ታዲያ ትውልድ እና እድገታቸው የህይወት ረጅሙ ጉዟቸው ሀረር የሆኑት በነፃነትና በድፍረት የተሞሉት ኡማ በዚህ ሰአት አጠገቡ ያሉ ከጌታው ቀጥለው ብቸኛ አፅናኝ ናቸው። ኡማን ይወዳቸዋል።

ችግር ሲያጋጥመው፣ አንዳች ነገር ሲከፋው ፣ ውስጡ ድብርትና ባዶነት ሲሰማው ኡማ ጋር ሄዶ ይቀመጣል።
ይዘንብ የነበረው ዝናብ ጋብ በማለቱ አካባቢው ነግሶበት የነበረው ዝምታ በጩኸት ተሞልቷል። የመኪናና የሰው ጫጫታ አይሎ ይሰማል።ከተማው እንደወትሮው ሞቅ ደመቅ ማለት ጀመረ።ቀዝቀዝ ብላ የወጣችው ፀሀይ በሂደት ራሷን አሙቃ ለምድር ሙቀቷን መለገስ ጀምራለች ። ዝም እና ጭሽ ብሎ የነበረው የሰው እርምጃና ሩጫም በሰው ግርግር ተሞልቷል። ባልቴቶቹ ጥግጥጋቸውን ይዘው በዝናብና በበረዶ
በብርድ ለታሸው ሰው ትኩስ ነገር ማቅረብ ጀምረዋል። ችፕስ፣ የተቀቀለ ድንች እና ድንች ስኳር። ነጩን ድንች በሚጥሚጣ በቆሎን ጨምሮ ለሰው መቅረብ ጀምረዋል። ከሴቶቹ መሀከል ደግሞ አንዷ ኡማ ናቸው። ኡማ በቆሎ ይዘው ከቦታቸው ተሰይመዋል። ትኩስ በቆሎ ለበረደው ጥርስ ላለው ጥብስ ሊያቀርቡ የበቆሎ ጥብስ ።
ኡማ በገበያ አለም ውስጥ ሆነው በመሸጥ ላይ ሳሉ ድንገት አይናቸው ውስጥ አንዳች ነገር ገባ ብሌናቸው ላይ ሳይሆን እይታቸው ላይ ሱለይማን።
ሱለይማን በፍጥነት እየተራመደ ወደ እሳቸው ሲንደረደር ተመለከቱት። ደንግጠው 100ኪሎ የሚመዝነውን ከባድ ሰውነታቸውን ለማንሳት ከእጃቸውጋ መዳፋቸውን መሬት አሰደግፈው መታገሉን ተያያዙት ።

ኡማ ደንግጠዋል ምክንያቱም ሱለይማን ማየት ሳይችል እንኳ እየመጣ ያለው በፍጥነት ነው። ሱለይማን እንዲህ የሚመጣው ሁል ጊዜም በአንዳች ምክንያት ነው።ይኸውም መርየም ካልደወለችለት ። በየደቂቃው መደወል ያስለመደችው መርየም ዛሬ ከደወለች ሁለተኛ ቀኗን አስቆጥራለች። በነዚህ ሁለት ቀናት ለደቂቃም ቢሆንም እንኳን ሱለይማን እህል አልቀመሰም ፣ እንቅልፍ በአይኑ አላዞረም ፈገግ እንኳን አላለም። እዛች ደሳሳ ጎጆ ውስጥለብቻው ተቀምጦ የሷን መደወል በንቃት ሲከታተል ነበር።ትላንት እሁድ ስለነበር ኡማ አልመጡም ነበርና። የሚያወያየው ሰው አጥቶ ብቻውን በሀዘን ተቆራዶ ናፍቆቱን አሳለፈ። ዛሬ ግን እሳቸው ስለመጡለት የውስጡን ሊያወጋቸው እየተንደረደረ ወደሳቸው እየመጣ ነው ።


ያላንተ መኖር አልችልም/ ያላንቺ መኖር አልችልም🙄🤔

እንደዚህ የምትባባሉ ሰዎች ብቸኛ ልላችሁ የምችለው ነገር lol🤣 ነው🙌🏾

እሱ or እሷ ያንተ/ያንቺ Oxygen ወይም ደግሞ ውሀ አይደለም/አይደለችም

i know እንዲህ ስትባባሉ ደስ የሚል ስሜት ይሰማቹሀል ምናምን ግን በቃ it's sax

after breakup በጣም ታዝናላችሁ ሁሉ ነገር ያስጠላቹሀል ልባችሁ ይሰበራል ግን እመነኝ/ኚኝ አትሞትም ወይም አትሞቺም መኖር ይቀጥላል...
እኔንጃ ያፈቀረውን በማጣት ምክንያት የሞተ ምታቁት ሰው አለ??


አይነ በሲሩ አፍቃሪ ልብ አንጠልጣይ አዲስ ተከታታይ ትረካ 👉ደራሲ እና ተራኪ፦ አብዲ ኢኽላስ
Опрос
  •   በፅሑፍ ብቻ ይቅረብ
  •   በድምፅ ብቻ ይቅረብ
  •   በሁለቱም ይቅረብ
11 голосов

Показано 20 последних публикаций.

285

подписчиков
Статистика канала