Yaya Beshir
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ከትላንት ዛሬ ከዛሬ ነገ እየባሰበት ሲሄድ እንጂ
መፍትሄ ሲበጅለት ኣናይም። ቀውሱ ብሄርን መሰረት ያደረገ ቢሆንም ኣሁን
ደግሞ ሃይማኖታዊ ገጽታ እንዲይዝ በመንግስት ባለስልጣናት ጭምር
እየተሰራበት ይገኛል። የተከበረው የኦሮቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖታዊ ክብሩ
ተደፍሮ የፖለቲካ መሳሪያና የግጭት መቀስቀሻ እየተደረገ ነው። መስጊዶችን
የሚያቃጥሉና ይህንን ድርጊት ፈጽመው በእብሪት ከበው ሃይሎጋ የሚጨፍሩ
ወገኖች ክርስትያኖች ናቸው ለማለት ያዳግታል። የፖለቲካ ኣላማ ያላቸውና
ኦሮቶዶክስ ክርስትናን የፖለቲካ ፍላጎታቸው ማርኪያ መሳሪያ በማድረግ በሌላ
ሃይማኖትና ብሄር ላይ ጦርነት ያወጁ ወገኖች ናቸው። የሚገርመው ይህ ሁሉ
ሲሆን ኣቀነባባሪዎቹና ችግሩን ኣለባብሰው ለማስቀረት የሚዳክሩ ወገኖች
የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር መሆናቸው ነው። እነዚህ ወገኖች መስጊድ
ሲቃጠልና ድርጊቱን የፈጸሙ ነውረኛ ወንጀለኞች በድል ኣድርጊነት ሲጨፍሩ
እምብዛም መተንፈስ ኣቅቷቸው ሰለባ የሆነው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ወንጀሉን
ሲያወግዝ ግን ከተሸሸጉበት ጥሻ ብቅ ብቅ እያሉ ዘራፍ ይላሉ። ሙስሊሙ
ህብረተሰብ ሃይማኖቱ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት በሰላማዊና ብሰለት በተሞላበት
ኣግባብ በመቃወሙ ኣድናቆትና ድጋፍ ሲገባው እነዚህ ወገኖች "ኣማራ ክልል
ላይ ለተቃጠለው መስጊድ ኦሮምያ ያለው ሙስሊም ምን ኣገባው" ብለው
ይጠይቃሉ። እንዲህ ያለው ሂፖክሪሲ ነው ኣገሪቷን ለመናድ እየገዘገዘ
የሚገኘው።
@ElemooJaarraa@OMNDAMEEJIMMA