اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته.
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم.
እባኮትን ይቺን ፅሁፍ በእርጋታ፣ በሰከነ መንፈስ፣ከልባችሁ አንብቡ።
#መለየት_ከፍቅራቸው!
የኢሻ ሰላት ከሰገዱ በኃላ ወሬና ጨዋታ አይወዱም።የተከበረ አካላቸውን በሰሌን ላይ ያሳርፉታል።አይናቸው እንጂ ልባቸው አይተኛም።የሌሊቱ መጀመርያ ሰአት ላይ ይነቃሉ። ለሊቱን በዱኣ ያሳልፉታል። በጣም ረዥም ሰአት በሰላት ውስጥ ይቆማሉ።እግራቸው እስኪያብጥ ድረስ።ለህዝቦቻቸው ሲሉ ያለቅሳሉ ፂማቸው እስኪርስ ።ሆዳቸው የሲቃ ድምፅ እያወጣ።በዚህ መልኩ የሱብሂ አዛን(የለሊቱ ማለቂያ ሰአት ላይ የሚሰገድ ሰላት)ደርሶ አዛን ይላል።ሱናቸውን ሰግደው በቀኛቸው ጋደም ይላሉ። አይናቸው እንጂ ቀልባቸው/ልባቸው አይተኛም።ከደቂቃዎች በኃላ ኢቃም(የሰላት ማስጀመርያ ጥሪ)ሲሰሙ ይነቃሉ።አማኞችን ያሰግዳሉ።ከዛ በኃላ አይተኙም።
ጠዋት የሚቀመስ ነገር ካለ ለቤተሰባቸው ይጠይቃሉ። ካላገኙ በዛው ለመፆም ነይተው ፆማቸውን ይውላሉ።ካገኙ ብቻቸውን መመገብ አይወዱምና ከሰው ጋር በአንድ ይበላሉ። ቀኑን ሰዎችን በማስተማርና በመጣራት ያሳልፋሉ ።ከመስጊድ ሲመለሱ ቤተሰቦቻቸውን በስራ ያግዛሉ። ፆማቸውን በአንድ ቴምር አንዳንዴም በውሃ ብቻ ለማፍጠር ይገደዳሉ።ሁሉንም ሚስቶቻቸው ይዘይራሉ፤ጥቂት ግዜ ያሳልፉና ተራዋ የደረሰችዋ ቤት በፍቅር ያሳልፋሉ።
የኛ ነብይ በጨረፍታው እንዲህ ናቸው።ሰሃቦቻቸው ከኚህ ውድ
ነብይ ጋር መለየት ፍፁም አይችሉም ነበር።
🖌እስቲ ይቺን ሃዲስ ያንብቧት።👇
📚ሰሂህ ሙስሊም ኪታብ ቁጥር 4 ሀዲስ ቁጥር 903
ኢብን መስዑድ እንዲህ ይላል፡- “በአንድ ምሽት የአላህ መልዕክተኛን አጅበን ነበር ሆኖም ግን ጠፉብን። በሸለቆውና
በተራራው ሁሉ ፈለግናቸው ( በጂኖች) ተወስደዋል ወይም በምስጢር ተገድለዋል አልን፤ #ሰዎች_አሳልፈውት_የማያውቁት #አስከፊ_የሆነ_ሌሊትንም_አሳለፍን፤ በነጋ ጊዜም ከወደ ሒሪ አቅጣጫ ሲመጡ አየናቸው፤ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!
ጠፍተውብን ፈለግነዎት ግና ልናገኝዎት አልቻልንም በመሆኑም ሰዎች አሳልፈውት የማያውቁት #አስከፊ የሆነ ሌሊትንም
አሳለፍን አልናቸው።
🖌ሰሃቦች ፍቅራቸው/ነብዩ ለአፍታ ሲለዩዋቸው እንዴት እንደሚጨነቁ አያችሁ!
🖌አንድ ሰሃባ ከረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጋር ሁሌ ይቀማመጣል።ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን ሱብሃነላህ ለአፍታ ከሳቸው ተለይቶ መቆየት ከብዶት ይመለሳል።"ከርሶ ለአፍታ #መለየት_አልቻልኩም።በመጭው አለምም ላላገኞት እችላለው"። አላቸው።"ከወደድከው ጋር ነክ" ብለው አፅናኑት ነብዬ።
ሰሃባው ለሰአት እንኳ መለየት የከበደው አመታትን በምን ይሆን የሚያሳልፈው።😢
የበኒ ነዲርኒ ሴት የነበረች አንዲት ሰሃባ በኡሁድ ጦርነት ላይ ባሏ መሞቱ ተነገራት፤ነብዩ እንዴት ናቸው ብላ መለሰች።ወንድሟ መሞቱንም ነገሯት የረሱልን ሰላም መሆን ጠየቀች ውድ አባቷ መሰዋቱን አረዷት።ነብዩን አሳዩኝ ብላ መለሰች።ስትመለከታቸው #እርሶ #ደህና_ከሆኑ ሌላው መከራዎች #ኢምንት ናቸው አለች።
🖌ተደግፈው የሚያስተምሩበት አንድ የዛፍ ግንድ ነበረ።ሌላ መደገፊያ ተሰርቶላቸው ይህን ግንድ ለመጨረሻ ግዜ ተለዩት። ጀርባቸው፣እጃቸው ከዚህ በኃላ ላይነኩት ሆነ።አስቡት ግንድ ነው አፍ አውጥቶ አይራቁኝ አይል፤ እርሳቸውን ላለማጣት ሮጦ አይሄድ ፤ፍቅሩ ጠንቶበት በናፍቆት ሊጠወል ነው።ጀርባቸው #ሲለየው ግን #ፍቅሩ_አንሰቅስቆ #አስለቀሰው። ውዴ በተከበረው እጃቸው አቅፈው አባበሉት።
#መለይት_ከፍቅራቸው
አይቀሬው ሞት መጣ…
ወቅቱ ረሱላችን ሊሞቱ አንድ ቀን ብቻ የቀራቸው ግዜ ነበረ። ሙስሊሞችን የሱብሂ ሰላት አቡበከር አስ ሲዲቅ ረዲየላሁ ዓንሁ ተተክቶ ማሰገድ ጀመረ። ረሱላችን በዓኢሻህ ረዲየላሁ ዓንሃ ጓዳ ጋደም ብለው ነበረ።ነብያችን ግርዶውን ገርበብ አድርገው ሲሰግዱመለከቷቸው። ለኡማቸው ቅን መንገድን ይጓጉ የነበሩት ነብይ በረድፍ እየሰገዱ መሆኑን ሲያውቁ ፈገግ አሉ።አቡበክር ረሱላችን ለማሰገድ ሊመጡ ስለመሰለው ወደኃላ አፈገፈገ። ሰሃቦች ስሜቱን ተጋርተው በደስታ ሰላታቸውን ሊያቋርጡ ደረሱ። ረሱል እንዲቀጥሉ ምልክት ሰጧቸውና ግርዶውን መለሱ።
የረሱል ለደቂቃ ጤናማ መሆን ሰሃቦችን ምን ያህል ያስደስታቸዋል
ከፍቅራቸው መለየትስ እንዴት ያስችላቸው ይሆን።ለኡማው የመጨረሻ ትልቅ ኑዛዜ አስተላለፉ « #ሶላታችሁን በተገቢው ሁኔታ ስገዱ። አገልጋዩቻችሁንም #በመልካም አያያዝ ያዙ።» ደጋግመው አስተላለፉ።
መልካም ሆነው ኖረው ወደ አላህ መልካም ሆነው ለመጨረሻ ግዜ ተለዩዋቸው።በረቢዑል አወል 12 ኛው ቀን ላይ በሰኞ እለት ወደ አላህ ተመለሱ።ዑመር መሞታቸውን ሲሰማ ራሱን መቆጣጠር አቃተው ማመን እስኪያቅተው ድረስ።ኢብን አባስም ተዝለፍልፎ ወደቀ።
በረሱል ሞት መዲና በሃዘን ተሸፈነች።አነስ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዲህ ብሏል:–«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም #ወደ_መዲና_ከገቡበት ቀን የበለጠ #አስደሳችና_ብሩህ ቀን አይቼ አላውቅም።እርሳቸው #ከሞቱበት ቀን የበለጠም #አስከፊና_ፀለምተኛ ቀን አይቼ አላውቅም»።
የእዝነቱ ነብይ፣የጥሩ ስነ ምግባር ሟሟያ፣የአላህ ወዳጅ፣የአላህ ውድ ፣የአላህን ሃቅ ጠባቂ አስጠባቂ፣ ለሱ የሆኑለት ለሳቸው የሆነላቸው፣ ለጠላቶቻቸው የበቃቸው፣ ሌት ከቀን ለህዝቦቻቸው መመራት ያለቀሱ፣ ቻይ፣ ታጋሽ፣ አዛኝ፣ተናናሽ፣ ውብ፣ጀግና፣ይቅር ባይ ምስጉን፣ አመስጋኝ፣ ለነፍሳቸው ብለው የማይበቀሉ፣ ድሃ ወዳጅ፣ ምስኪን ጠባቂ፣ ሰላም ወዳድ ሁሉን አክባሪ፣ጥበበኛ፣አዋቂ፣እኛን የናፈቁ፣ቸር ሆነው ኖረው ታላቅ ሆነው አላህን የተገናኙት የሰው ልጆች አይነታና አለቃ…
#ውዳችን_ሃቢቡና_ሙሀመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
ዑማውን/ህዝባቸውን የተለዩበት ቀን ምን ያህል ከባድ ነው!ሳናያቸው አምነንባቸዋለን ሳናያቸው ፍቅራቸው ያንገበግበናል!
ዛሬም የማያምኑባቸው የሚሰድቧቸው ያልሰሩትን የሚቀጥፉባቸው አሉ። እነዚህን ሰዎች ወዳጅ አድርገን መያዝ እፍረት ነው።
#ፊዳከ_ሃያቲ_ያረሱሊ😔
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
" #ጙረባእ_እንሁን!"
ጆይን ሼር
@Only_islamy