#የአገልጋዮች_አገልጋይ
(ሉቃ 22:7_18፤ 24፤ ዮሐ 13:1-17)
ከእግዚአብሔር አብና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ዛሬም እንደተለመደው ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ክፍል በሥዕላዊ ጽሑፍ እንመለከታለን።
አንድ በዝምታና በትንሽ ብርሃን የተሞላ አደራሽ አስራ ሁለቱን ደቀመዛሙርትንና አለቃቸውን በውስጡ ይዟል ። ክፍሉ ውስጥ ሁለት ከመሬት ትንሽ ከፍ ብሎው የተቀመጡ ሁለት አግዳሚዎች ከፍት ለፊት ይታያሉ፣ አሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርትም ከግራና ቀኝ ሆነው በአግዳሚው ላይ ተሰይመዋል፣ መሃል ላይ የተዘረጋው ሼልፍ ላይ ተለቅ ተደርጎ የተጋገረ እንጀራ (ሕብስት ) ይዟል፣ በአጠገቡም ጽዋ ይታያል። በቤቱ ውስጥ ዝምታው ደስ የምል የተረጋጋ መንፈስን ይዘራል ፣ ግርጌ ላይ የተንጠለጠለው ጦዓፍ (ችቦ) ከውጭ የሚመጣው ጨለማ ቤቱ ውስጥ እንዳይነግሥ ከልክሏል ። ቤቱ ደስ በሚል ብርቱካናማ ብርሃን ተውቧል። ከጠዋፉም አጠገብ የእግር ማስታጠቢያና የእግር ማድረቂያ መሃረብ ይታያሉ፣ በአጠቃላይ በዚያ ቤት ውስጥ "ግብዣ" እንዳለ ያስታውቃል ።
ግብዣውም ተጀምሮ ከጨረሱ በኋላ እግራቸውን መታጠብ ነበረባቸው ። የሁሉም ሐዋሪያት አሳብ "ማነው ከሁሉም አስቀድሞ እግራችንን የሚያስታጥበን?? ማነው ታናሹ? ማነው የአገልጋዮች አገልጋይ?? ብሎ ሁሉም ይጠባበቅ ነበር።
እናም
👴🏻ጴጥሮስ በልቡ አንዲሀ ይል ነበር
🤔"መቼም ቢሆን እኔን እየጠበቁኝ አይሆንም። በእድሜና በእውቀት እበልጣቸዋለሁ። አድስ ነገር ማመጣው ራሱ እኔ ነኝ። አይ አይ እኔ እንኳ ከፉክክሩ ውጭ ነኝ።"" ብሎ ይጠባበቃል።
ሁሉም በዝምታ ተውጦአል፣ አይኖችም ሁሉ👀 ወደ ማስታጠቢያው ያያሉ😳።
ይሁዳም በአሳቡ
👳🏽🤔"ምን እነዚህ ፣ይሄኔኮ ብር መጠየቅ ብሆን ኖሮ ፣ እንደምናምን ከበውኛል። ሆዳም ብቻ።"
👱🏻👨🏻 ዮሐንስና ያዕቆብ ደግሞ የዛን ሰሞን የሚንስተሪነት ማመልከቻ በእናታቸው በኩል ለመምህሩ አስገብተው ነበሪና ፣እንዲህ ይባባላሉ።
ዮሐንስ "ስማ ያዕቆብ ፣ተነስተህ እንዳታስጀምር።"
ያዕቆብ "እሺ ወንድሜ ።ከተነሳውማ ያንን ማመልከቻ ውሃ በላው። ጭራሹንም እንደ ታናሽ አድርገው ነው ሚቆጥሩን አታስብ አልነሳም።"
ዮሐንስ "ጎሽ ጎበዝ፣ ገብቶሃል ማለት ነው።" ብለው ያንሾካሽኩ ነበረ። ሁሉም እራሱን ከማስታጠብ አግልሏል ።
ኢየሱስ የሁላቸውንም አሳብ ያውቅ ነበርና ፣በውስጡ ይገረማል ።
እራሱንም
"በሰማይ ዙፋን ላይ ፣ ከፍ ካሉ ሁሉ ከፍ ብሎ ባለው ዙፋን ላይ ሆኖ፣ በማይገመት ብርሀን ውስጥ አንዳች የመለኮት ጉድለት ሳይኖርበት ከአብ እኩል በዙፋኑ ላይ ሆኖ እራሱን ያይ ነበር።
6 "እርሱ የመለኮት ባሕርይ አለዉ፤ ይሁን እንጂ ፥ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርውን የመለኮት ባሕርይ እንደ ያዘ መቅረት አልፈለገም።
7"ይልቁንም ያለውን #ክብር በገዛ ፈቃዱ ትቶ አገልጋይ መሆንን መረጠ።
8"እንደ ሰው ሆኖም በትሕትና ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት ድረስ ፥ ያውም #በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
( ወደ ፈልጵስዩስ ሰዋች 2:6-8)
ይህንን ሁሉ አሰበና ፥ለራሱ ዝምታውን ያይረብሽ ብድግ ብሎ ተነስቶ ፣የለበሰውን ልብስ አውልቆ። ያ ያደፈውን የአገልጋዮች አገልጋይ የሚለብሰውን ለብሶ ፣
4"......ልብሱን አስቀመጠ፤ ፎጣም አንስቶ በወገቡ ታጠቀ። 5 ከዚህ በኋላ በመታጠቢያ ሳሕን ውሃ አድርጎ የደቀመዛሙርቱን #እግር ማጠብ ጀመረ፤ በታጠቀውም ፎጣ እግራቸውን አበሰ።
( የዮሐንስ ወንጌል 13:4-5)
ወገኖቼ እዚህጋ ቆም ብለን እናስብ፥
🌊ኢየሱስን ፈጣሪ ነዉ። የሁሉም ነገር ፈጣሪ።
የከዋክብት🌟
የሰው ልጆች 👨👩👧👦
የእጽዋት 🌿☘🍂🍃
የእንስሳት🐑🐏🦍🐘
ሰማይና ምድርን 🌊
ባህርና የውሃ ምንጮችን💨🌩
እና ሰማይን በዘረጋ እጁ፣ከዋክብትን በሰሩት እጆቹ፣ እኔ፣አንተና አንቺን የጥበብ መደምደሚያ አድርጎ በሰሩት ጣቶቹ እግር ሊያጥብ፣🙈
❓ እኛስ ዛሬ ትንሽዬ ስልጣን ወይም ውድ ልብስም ለብሰን እነኳን ጎንበስ ማለት ምነኛ ይከብደናል?!
❓መንገድ ላይ የወደቁ ወገኖቻችን እንዳያቆሹን ምን ያህን እንጸየፋቸዋለን?!
❓እግር ማጠብ ይቅርና ትንሽ #ደሃ፣ #ችግርተኛ፣ #አሮጌ ልብስ የለበሰውን ወገናችንን #ሰላም ማለት አልከበደንም??
❗️እናም በእነዚያ ሙታንን ያስነሱ ፣ ድንቅና ታአምራትን ባደረጉ እጆቹ፤ የእነዚያን ሰዋች እግር ሊያጥብ ጎንበስ አለ።
‼️‼️አይገርምም‼️⁉️
ሁሉም ተደነቁ ፣ ገርማቸው ፣ ማመን አቃታቸው ። ጴጥሮስ እንቢ አለ።
እኔም እደነቃለሁ ‼️
ምክኒያቱም
ያታላቅ አምላክ
ከሰማይ ሰማያት ዙፋኑ
⬇️
ወደዚች አስጠልታ ምድር
⬇️
ያውም ስጋን ለብሶ
⬇️
ሕፃን ሆኖ በሰው(ሴት) ማህፀን ውስጥ አድሮ
⬇️
በበረት ተወልዶ
⬇️
የአገልጋዮቹን እግር አጥቦ
⬇️
ተገርፎልኝ ፣ቆስሎልኝ
⬇️
ሙቶልኝ
⬇️
ያውም የመስቀል✝ ላይ ሞት።
ሰለዚህ በጣም ብገረም አይገርምም🤷♂።
አጠበላቸው፣ በአውአራ የተበላሸውን እግራቸውን አጥቦ አደረቀላቸው።።
🔹ወገኖቼ እኛስ ዛሬ ማንን ነው መርዳት ያለብን???
🔸እራሳችንን ብቻ ምንወድድ ከሆነ ማጥፊያችን እራሳችን ይሆናል
፲፫'እናንተ 'መምህርና ጌታ ' ትሉኛላችሁ ፤ እኔ መምህርና ጌታ ስለሆንሁ ያላችሁት ትክክል ነው።
፲፬'እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ፥ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን መተጣጠብ ይገባችኋል ።
(የዮሐንስ ወንጌል ፲፫:፲፫_፲፬)
በትዕግስት ስላነበበችሁ ጌታ ይባርካችሁ ።🙏
"እንግዲህ ከመካከላችሁ የበላይ ሊሆን የሚፈልግ የሁሉም አገልጋይ ይሁን።"
(የማርቆስ ወንጌል 10:44)
መልካም ግዜ
ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ share ያድርጉና ይደግፉን🙏
share
Join
@samaritanclub@samaritanclub