የኦርቶዶክስ ልጆች እኛ ኦርቶዶክስ ነን


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላለን ጸንተን #ሃይማኖታችንን_እንጠብቅ።”
— ዕብራውያን 4፥14
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ #የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ #መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ #አንሄድባትም አሉ።”
ኤርምያስ 6፥16

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


“በቸርነትህ #ዓመትን ታቀዳጃለህ፥።”
— መዝሙር 65፥11
ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረው እንደቸርነቱ እኛም ዘመንን እየቆጠርን ከ2014 አመተ ምህረት ደርሰናል።
አንድ አመት 365 ቀናት እና በዓራት አመት አንድ ጊዜ 366 እየሆነ ከ2000በላይ ቆጥረናል አምላካችን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት እና ከመወለዱ ቡሃላ ዓመተ አለም እና ዓመተ ምህረት እያልን ከመወለዱ በፊት ያለውን ዘመነ ፍዳ ወይም ጨለማ በማለት አምላካችን ከተወለደ ቡሃላ የምህረት ዘመን በማለት ዘመነ ምህረት ( አመተ ምህረት) የብርሃን ዘመን* በማለት በቸርነቱ ለዚህ ዘመን በቅተናል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን አሜን አምላካችን ክርስቶስ ስሙ ከፍ ብሎ ከጽሐይ መውጫ እስከ ጽሐይ መግቢያ ድረስ በፍጥረቱ አንደበት የተመሠገነ ይሁን አሜን።
ቅዱስ ዮሐይስ መሸጋገሪያ ድልድይ ሆኖ ሐዲስ ኪዳንን ሰብኮልናል ቅዱስ ዮሐንስ እለተ በአሉ መስከረም አንድ ቀን ይከበራል ይህንን ስርዓት የሰራችው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ድንቅ ጥበቧ ነው። የክረምቱ ወር ተጠናቆ የበጋ(ብርሐን) ዘመን የሚመጣበት አዲስ ምእራፍ የሚጀመርበት መስከረም አንድ ቀን ነው። ታዳ ቅዱስ ዮሐንስ የነቢያት መጨረሻ የሐዋርያት መጀመሪያ ነበረ ስለዚህ በዓሉ የሚከበረው የክረምት(ጨለማው) ወርህ ተጠናቆ የብርሐኑ ወርህ ሲገባ መስከረም አንድ የምናከብረው። ስለዚህ ይህ የብሉይ ኪዳን ነቢይ መጨረሻ እና የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ሐዋርያ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናት/ምዕመን ሆይ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ወንጌል ሲመራ ታዳ ማለትም ወደ ዘመነ ሐዲስ ህዝቡን ሲያሻግር በመጀመሪያ አሮጌ ማንነታቸውን አይደለም ይዘው እንዲሻገሩ የሰበከው በቀጥታ ንስሃ ግቡ በሚል ነው ስብከቱን የጀመረው የመዳን ቀን አሁን ነው በማለት ጳጉሜ5ቀን የሰበካቸው አሮጌ ማንነትን ይዘው እንዲመጡ እንዲሻገሩም አልፈቀደላቸውም።
ውድ ኦርቶዶክሳዊ/ት ምእመን እኛስ?
2013 ይዘነው በመጣነው የሃጢያት ክምር 2014ንም መቀበል እጂጉን ለፈጣሪ ሃዘን አንሁን 365 ንጹህ ወረቀት ተሰጥቶናል 365 ንጹህ ወረቀት ላይ በጎ ስራወችን አስፍርበት መላካም ያልሆኑ ድንገት ካሰፈርክበት ለጲስ ተጠቀም እና አጥፋ ከዛም መልካሙን መዝገብ አከማች በቀራኒዮ የታረደው ኢየሱስ ደሙ ይከስሃል ንስሃ ካልገባህ ኢየሱስ አለሙን ነጻ ያወጣው በደሙ ነው ምድሪቱን ቀድሷታል በደሙም ታጥባለች ስለዚህ የቆሸሸው ማንነትህ በላጲስ(በንሰሃ) አጥፋና ቀጣይ 365.ንጹህ ቀን አለ በንስሃ ወደ ፈጣሪ እንመለስ አሜን

#ለምእመን_አካፍሉ

https://t.me/WE_ARE_ORTHODOX


​​​​🌼 ልጄ ሆይ አንተም እንደ ዘመኑ ተለወጥ

ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም #ተለወጥ።

ሮሜ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም #ለአእምሮ የሚመች #አገልግሎታችሁ ነው።
² የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ #በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም #አትምሰሉ።


ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ #ካለመታዘዘ ተለወጥ።


ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ #ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ #ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር #ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ #ጥላቻ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም #ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም #ተለወጥ።

ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ #ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ #ይለወጥ።

ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ #ተለወጥ

ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። #በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር #አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ #ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን #ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ #አትገኝ ።

በንስሐ ወደ በረቱ #የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን

🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድ
ርጉ!

https://t.me/WE_ARE_ORTHODOX


መልካምአዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት


አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
አዲስዓመት

ዓመት
አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመት


መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ከዳሪ
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ከዳሪ
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ከዳሪ
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ከዳሪ
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት
አዲስ አመት

ያሰባችሁት የሚሳካ ምርጡ በአልና አመት እንዲሆንልዎ እመኛለሁ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።

ቻናሉን ለመቀላቀል
🌼🌼🌼🌼
https://t.me/joinchat/TrUmCWDBL7C5Nes8
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kNtykg?subconfirmation=1
🌼🌼🌼🌼🌼


+ የአባቶች ድንቅ ጥበብ የተሞሉ መልሶች +

ባለ ብዙ ታሪኩ የወሊሶው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ያጠምቁና ያስተምሩ በነበረበት ሥፍራ አንድ በትዕቢት መንፈስ የሚሰቃይ ወጣት መጣና መፈክርነት ያዘለ ቃል ተናገረ:: ክብር ይግባትና ንግግሩ የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና የሚቃወም ነበር::

ወደ አባ ዲዮስቆሮስ ቀርቦ እንዲህ አላቸው :-
ወጣቱ :- "ድንግል ማርያም እኮ ብዙ ልጆች አሉአት"
አቡኑ :- "ባታውቀው ነው እንጂ ለአንተም እኮ እናትህ ናት!"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

የቦሩ ሜዳው መምህር አካለ ወልድ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ኢየሩሳሌምን ሲሳለሙ ድንገት የሌላ ሀገር መነኮሳት መጥተው በዱላ አጣደፉአቸው:: ነገሩን ሲጠይቁ ለምን በእግዚአብሔር ሦስትነት እንደማያምን ሰባልዮሳዊ
አንድ ጣታችሁን ብቻ ወደላይ ጠቁማችሁ ታማትባላችሁ? ለምን እንደ እኛ ሦስት ጣቶቻችሁን (እንደሚጎርስ ሰው) በአንድ ገጥማችሁአታማትቡም?" አሉና በቁጣ ጮኹ::

መምህር አካለ ወልድ በፈሊጥ እንጂ በፍልጥ የሚሆን ነገር ስለሌለ ቁጭ ብለን እንነጋገር አሉ::

"እኛ በአንድ ጣት ብናማትብም ሦስትነቱን እናምናለን:: አንድዋ ጣትም እኮ ሦስት አንጉዋዎች አሉአት:: አንድ መሆንዋ አንድነቱን ሦስቱ አንጉዋ ሦስትነቱን ያስረዳል::
የታችኛው አንጉዋ መሠረት ነውና የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መሠረት ይሆነው የአብ ምሳሌ ነው:: የመካከለኛው በሁለቱ ህልው የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው : የላይኛው ጥፍር የለበሰው ደግሞ ባዕድ ሥጋን የተዋሐደ የወልድ ምሳሌ ነው:: ሀገራችሁ ሔዳችሁ አስተምሩበት" አሉአቸው

(ይህ ትርጓሜ በወንጌል አንድምታ ላይ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን አወጣለሁ የሚለው በተተረጎመበት ሥፍራ ይገኛል)

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

ንቡረ ዕድ ክፍለ ዮሐንስን ደግሞ አንድ ወጣት መጥቶ
"ለእግዚአብሔር የአምልኮ ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት እንደሚሰገድ አውቃለሁ:: ግን በቅዱሳን ሥዕል ፊትና በፈጣሪ ፊት ስሰግድ እንዴት ለይቼ የጸጋ የአምልኮ እያልኩ መስገድ እችላለሁ?" አላቸው
ንቡረ ዕድ መለሱ
"አንተ ዝም ብለህ ስገድ እነርሱ የድርሻቸውን ይወስዳሉ!"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አቡነ ሺኖዳ ከሾፌራቸው ጋር ሲሔዱ ሾፌሩ መኪናውን ከመጠን በላይ አበረረው
ፓትርያርኩ እንዲህ አሉ
"ልጄ ስለምንቸኩል ቀስ በል”

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አንድ ታላቅ የጉባኤ መምህር ተጠየቁ
"ካህናት ዶሮና በግ ወዘተ ማረድ የማይችሉት ለምንድን ነው?"
"የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚፈትት ካህን እንደ ኦሪት ካህን የእንስሳ ደም አያፈስስም"
"ካህናቱስ መልካም ሴት ልጅስ ማረድ ለምን ትከለከላለች?"
"ሕይወት የምትሠጥ ሴት ሕይወት አታጠፋም"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አለቃ ለማ ልጃቸውን ለምን በጣም እንደሚገርፉት ተጠየቁ
"ልጄን እኔ ካልቀጣሁት እግዚአብሔር ይቀጣብኛል
የእግዚአብሔር ቅጣት ደግሞ ሞት ነው"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አንዱ መጥቶ አንድን የመጽሐፍ መምህር
"ጥምቀት ጋድ አለው ወይ?" አላቸው
እርሳቸውም መለሱ
"አምና ነበረው የዘንድሮን እንጃ"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አቡነ ዮሐንስ አንድን ሥራ ፈቶ የአብነት ተማሪዎችን
ሲማሩ ከሩቅ የሚያይ ወጣት አዩና
"አንተ አትማርም ወይ?" አሉት
"አይ አባቴ ምን እየበላሁ ልማር ብለው ነው?" አለ እየተቅለሰለሰ
አቡኑ መለሱ
"አሁን ምን እየበላህ ነው የምትደነቁረው?"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

አቡነ ጎርጎርዮስ በዝዋይ ሳሉ አንድ ወጣት ሰርቆ ሲያመልጥ አባርረው ይዘው ሰዎች አመጡላቸው
ዕቃው ከተመለሰ በኁዋላ ሌባውን ለሕግ አሳልፈው ሊሠጡ ሲቸኩሉ አይሆንም አሉአቸው:: ሰዎቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ወደ ፖሊስ እንውሰደው አሉአቸው
እርሳቸውም መለሱ
"ኦርቶዶክሶች ተሰራርቀው ተካስሰው መጡ ከሚል ስም ውጪ ምንም አናተርፍም"

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

ብፁዕ አቡነ ሰላማን አንዱ ባለ ሥልጣን ጉዳይ ሊያስፈጽሙ በሔዱበት ቢሮው "አንተ" ብሎ በማናገር ሊያቃልላቸው ሞከረ::
እርሳቸው እንዲህ አሉት
"የቤተ ክርስቲያኔን ጉዳይ ፈጽምልኝ እንጂ እንኩዋን አንተ ቀርቶ አንቺም ብለህ ጥራኝ

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

የደርግ መንግሥት እንዳሻው ሊዘውራቸው ተስፋ ያደረገባቸው ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በመሪው አማካኝነት እንዲህ ሲል ጠየቃቸው
"የቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን ወደ ሙዝየምነት የመቀየር ሃሳብ በመንግሥት በኩል ተይዞአል:: ይህንን ለማድረግም የእርስዎን ድጋፍ የግድ ነው"
ፓትርያርኩ መለሱ
"ምን ችግር አለ በቅርቡ የዓመቱ ሥላሴ ክብረ በዓል ስላለ ሕዝቡ ባለበት እናንተም ተገኝታችሁ አብረን ለምን አናወያየውም"
በዚህ ምላሽ ምክንያት እቅዱ ተሠረዘ

✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽✍🏽

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


++ የአዲስ ዓመት ሥነጹሑፍ !!

( ይችን ዓመት ተወኝ ! )

ከዓመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ፤
በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ፤
አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እያጎሳቆልኩኝ፤
አውቃለሁ አምላኬ ፍሬየን ለመልቀም እንዳመላለስኩህ፤
ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅየ ደርቄ ጠበኩህ ፤
ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም፤
ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አልለየኝም ከአለም።
የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ፤
የኔን ክፋት ተወዉ መልአክህን ሰምተህ ይችን ዓመት ተወኝ።

አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር፤
ብዙ ግዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር።
ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይኸ ጊዜ ሰምተኸኝ ነበረ፤
ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮየ አልፎ ባዲስ ተቀየረ ።
ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ፤
እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ።
የቃልህን ውሐ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳትታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ፤
ወደልቤ ሳይሰርግ ህይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈስሶ ቀረ።
ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ፤
በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ።
ብዙ ጥቅስ አገኝሁ ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ፤
ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁንኝ በበደል ተኝቼ ።
ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርጸኝ ተማሪ ብሆንም፤
ይችን ዓመት ተወኝ ተደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም።

እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ፤
ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መአዛ እንዲደርሰኝ።
የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሸከመኝ አትሰልቸኝ አደራ፤
ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት እየሰሩ ስሰራ።
አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ፤
ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ።
ቦታ የሚይዙት ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸው፤
ልክ እንደዘንባባ የተንዠረገገ ተጋድሎ ጽድቃቸው ።
ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው፤
እኔ አይደለሁም ቦታስ የምትይዘው የአንተው እናት ናት፤
ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት፤
ይችን አመት ተወኝ ከስሯ እሆናለሁ ባፈራ ምናልባት፤
ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት፤
ሺህ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንትህ ናት።
ይኸ ዓመት አልፎ ደግሞ ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ፤
እባክህ ጌታየ ይችን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ።

ጸሐፊ - (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)


ሰላም ውድ የተዋህዶ ልጆች 👏👏
የኢኦተቤክ አስተምህሮት የጠበቀ ማንኛውም አይነት ቻናል ካላችሁ አሁኑኑ ከፕሮሞሽናችን ይመዝገቡ። ለመመዝገብ👉 @habmisget

የተለያዩ ባነር ማሰራት የምትፈልጉ
👉 የቻናላችሁ ሎጎ ለ Facebook
👉ለ YouTube
👉 ለ Telegram
እንዲሁም ለዩቲዩብ ቻናላችሁ Thumbnail (ተምኔል)ማሰራት የምትፈልጉ

በዚህ አናግሩን👉 @habmisget

ቻናላችንን ለመቀላቀል👇
@ortodoxmezmur21
@ortodoxmezmur21


ጳጉሜን እኔና ጓደኞቼ
     *~★★~*

… ዘንድሮም እንደተለመደው ፌስቡክ ጳጉሜን መድረሷን ጠብቆ ከገጹ ቢያግደኝም። እኔ በቴሌግራም ቻናሌ እናንተ ደግሞ በፌስቡክ ገጻችሁ ማጥለቅለቃችንን እንቀጥላለን።

•••
እኔ ዘመዴ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ጓደኞቼ በሙሉ አንድ ላይ ሁነን መጪውን የወርሀ ጳጉሜን ፭ቱን ቀናት ልክ እንደ አምናው ካቻምናው ሁሉ ዘንድሮም ዘመነ ማቴዎስን አሳልፈን ዘመነ ማርቆስን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ዘንድሮ እንዲያውም በቋሚ ሲኖዶሳችን ጭምር ወርሀ ጳጉሜን በጾም፣ በጸሎትና በምህላ እንድናሳልፍ ሁሉ ዐዋጅ ታውጇል። አዲሱን ዓመትም በዚህ መልኩ እንቀበላለን ማለት ነው። እናም እኛም ከጾም ጸሎት ምህላው ጎን ለጎን አምስቷን ቀናት እንደልማዳችን በዚህ መልኩ እናሳልፍ ዘንድ አስበናል። ወስነንም ተዘጋጅተናል።
                     
፩፥ ጳጉሜ ፩  የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜ ፪  የክብረ ክህነት ቀን።
፫፥ ጳጉሜ ፫  የፊደል ገበታ ቀን።
፬፦ ጳጉሜ ፬ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን።
፭፦ ጳጉሜ ፭  ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያና ለአቅመ ደካሞች የሥጦታ ቀን።

•••
ጳጉሜ ፩ ፥ የማዕተብ ቀን ነው።

… የተዋሕዶ ልጆች አንገት በሙሉ በአንገት ማዕተብ ክር ያሸበርቃል። የመስቀል ዓይነት የፌስቡክና የቴሌግራም ቻናሎቻችንንም ያጥለቀልቃል። በዕለቱ ፌስቡክ ሌላ ወሬም የለም፣ ሌላ ፎቶም አይለጠፍበትም። ተዘጋጁ፣ ጳጉሜ ፩ እየጾምን፣ እየጸለይንም፣ ማዕተባችንንም አጥብቀን እናስራለን። የአንገት ማዕተብ የሌላችሁ ከወዲሁ ግዙ፣ አስባርካችሁም እሰሩም። አንገታችሁ ባዶ አይሁን።

•••
ጳጉሜ ፪ ፥ የክብረ ክህነት ቀን ነው።

… ለንስሐ አባቶቻችን፣ ለካህናት አባቶቻችን፣ ፍቅራችንን፣ አክብሮታችንን የምንገልጽበት ዕለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ የምንልበት፣ ቡራኬ የምንቀበልበት፣ ለበዓሉም ለአባቶቻችን ስጦታ የምንሰጥበት፣ ዕለትም ነው። እኔም አደርገዋለሁ። እናንተም አድርጉት። ተዘጋጁ።

•••
ጳጉሜ ፫፥ የፊደል ገበታ ቀን።

… አከተመ የዚያለት ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፊደላት ሲያሸበርቅ ይውላል። የዚያን ዕለት ልብሱ ሁሉ የፊደል ገበታ ነው የሚሆነው። በዓለሙ ሁሉ ስንነበብ እንውላለን። ፊደላችን የፌስቡክን ግድግዳ  አጥለቅልቆት ይውላል።

•••
ጳጉሜን ፬ ፥ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን።

… ይሄ ምንም ማብራሪያም ዝርዝርም አያስፈልገውም። በዚህ ዕለት ፌስቡክ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ የነፃነት ሰንደቅ ዓላማና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፎቶ አሸብርቆ የሚውልበት ቀን ነው ማለት ነው።

•••
ጳጉሜ ፭ ፥ ከሱሶች ሁሉ የመላቀቂያና፣ የመገላገያ ለአቅመ ደካሞችም የሥጦታ መስጫ ቀን እናደርገዋለን። እነ ሲጋራ በአደባባይ ይረገጣሉ። አልኮል፣ ጫት፣ ሺሻና ሀሺሽም ይወገዳሉ፣ ይረገማሉ። ከዝሙት እንሸሻለን። በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዘመን ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ሰማዕታትን፣ እንቀበለዋለን፣ እንቀላቀለዋለንም። ታዲያ እኛ ደስስ ሲለን ሌላ የሚከፋው እንዳይኖር ጉረቤቶቻችንን በዓሉን አዲሱንም ዓመት በደስታ ይቀበሉ ዘንድ ያለንን የምናካፍልበት ዕለትም ነው። ቢያንስ ቅቤ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ዶሮና እንቁላል እናበረክትላቸዋለን።

•••
ሰምታችኋል ጓደኞቼ ተዘጋጁ። ደግሞም እናደርገዋለን። አባቴ ይሙት እናደርገዋለን። ይሄን መልእክት የጻፍኩት ለጓደኞቼ መሆኑ ይሰመርበት። መንገደኞችን አይመለከትም። አከተመ።

ዘመድኩን በቀለ (ዘመዴ)


አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት

"ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?"
ቅዱሱ አባት መለሰለት

"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው

ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው

ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል

ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው
በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

⛪️⛪️⛪️⛪️

ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል።

⛪️⛪️⛪️⛪️

"ፍቅር እንዴት መቆጣት እንዳለበት አያውቅም"
ቅዱስ ማር ይስሐቅ

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል።
⛪️⛪️⛪️⛪️

“የሚጾሙ የሚጸልዩና የሚተጉ ድቃቂ ሳንቲም እስካላስወጣቸው ድረስ በምንም ነገር ላይ የሚገኙ በችግር ላይ የሚሰቃዩትን ግን ዞር ብለው የማያዩ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ" ቅዱስ ባስልዮስ

⛪️⛪️⛪️⛪️

"እኛ መነኮሳት ነን:: እኛ የሠለጠንነው ሰዎችን ለመግደል ሳይሆን ምኞታችንን ለመግደል ነው" አባ ጴኤሜን

★ ★ ★
አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ?
ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ?
ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ?
ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?
ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ?
መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ?
ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?
በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ?
የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ?
ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

ምንጭ: Orthodox Notes (ON)
ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 3 2011 ዓ ም


ሐዋርያት 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አጵሎስም በቆሮንቶስ ሳለ ጳውሎስ በላይኛው አገር አልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ፥
² አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ፦ ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት።
³ እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ በዮሐንስ ጥምቀት አሉት።
⁴ ጳውሎስም፦ ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው።
⁵ ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
⁶ ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው በልሳኖችም ተናገሩ፥ ትንቢትም ተናገሩ።
⁷ ሰዎቹም ሁሉ አሥራ ሁለት ያህሉ ነበር።
⁸ ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር።
⁹ አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በሕዝብ ፊት መንገዱን እየሰደቡ ባላመኑ ጊዜ፥ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፥ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር።
¹⁰ በእስያም የኖሩት ሁሉ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ ሁለት ዓመት ያህል እንዲህ ሆነ።
¹¹ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥
¹² ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።
¹³ አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፦ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።
¹⁴ የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት።
¹⁵ ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው።
¹⁶ ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።
¹⁷ ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
¹⁸ አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።
¹⁹ ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።
²⁰ እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።
²¹ ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ፦ ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።
²² ከሚያገለግሉትም ሁለቱን ጢሞቴዎስንና ኤርስጦንን ወደ መቄዶንያ ልኮ ራሱ በእስያ ጥቂት ቀን ቆየ።
²³ በዚያም ጊዜ ስለዚህ መንገድ ብዙ ሁከት ሆነ።
²⁴ ብር ሠሪ የሆነ ድሜጥሮስ የሚሉት አንድ ሰው የአርጤምስን ቤተ መቅደስ ምስሎች በብር እየሠራ ለአንጥረኞች እጅግ ትርፍ ያገኝ ነበርና፤
²⁵ እነዚህንም ይህንም የሚመስለውን ሥራ የሠሩትን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ ሰዎች ሆይ፥ ትርፋችን በዚህ ሥራ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።
²⁶ ይህም ጳውሎስ፦ በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል ሰምታችሁማል።
²⁷ ሥራችንም እንዲናቅ ብቻ አይደለም፥ እስያ ሁሉ ዓለሙም የሚያመልካት የታላቂቱ አምላክ የአርጤምስ መቅደስ ምናምን ሆኖ እንዲቆጠር እንጂ፥ ታላቅነትዋም ደግሞ እንዳይሻር ያስፈራል።
²⁸ ይህንም በሰሙ ጊዜ ቍጣ ሞላባቸው፦ የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት እያሉም ጮኹ።
²⁹ ከተማውም በሙሉው ተደባለቀ፥ የመቄዶንያም ሰዎች የጳውሎስን ጓደኞች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ከእነርሱ ጋር ነጥቀው በአንድ ልብ ሆነው ወደ ጨዋታ ስፍራ ሮጡ።
³⁰ ጳውሎስም ወደ ሕዝቡ ይገባ ዘንድ በፈቀደ ጊዜ ደቀ መዛሙርት ከለከሉት።
³¹ ከእስያም አለቆች ወዳጆቹ የሆኑት አንዳንዶች ደግሞ ወደ እርሱ ልከው ወደ ጨዋታ ስፍራ ራሱን እንዳይሰጥ ለመኑት።
³² ወዲያና ወዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ የሚበልጡት ስንኳ ስለ ምን እንደተሰበሰቡ አላወቁም ነበርና።
³³ አይሁድም ሲያቀርቡት፥ እስክንድሮስን ከሕዝቡ መካከል ወደ ፊት ገፉት፤ እስክንድሮስም በእጁ ጠቅሶ በሕዝብ ፊት እንዲምዋገትላቸው ወደደ።
³⁴ አይሁዳዊ ግን እንደ ሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ፦ የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ።
³⁵ የከተማይቱም ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ፦ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፥ የኤፌሶን ከተማ ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ የመቅደስ ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ ሰው ማን ነው?
³⁶ ይህንም የሚክደው ከሌለ፥ ጸጥ እንድትሉና አንዳች በችኮላ እንዳታደርጉ ይገባል።
³⁷ የመቅደስን ዕቃ ያልሰረቁ አምላካችንንም ያልሰደቡ እነዚህን ሰዎች አምጥታችኋቸዋልና።
³⁸ ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉት አንጥረኞች ግን በሰው ላይ ነገር እንዳላቸው፥ የመጋቢያ ቀንና አገረ ገዢዎች አሉ፤ እርስ በርሳቸው ይምዋገቱ።
³⁹ ስለ ሌላ ነገር እንደ ሆነ ግን አንዳች ብትፈልጉ፥ በተደነገገው ጉባኤ ይፈታል።
⁴⁰ ዛሬ ስለ ተደረገው፦ ሁከት ነው ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፥ ምክንያት የለምና።
⁴¹ ይህንም ብሎ ጉባኤውን ፈታው።




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ #ደስ_አለኝ።”
— መዝሙር 122፥1
በማለት ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ተናገረ።
ቤተክርስቲያን ቀራኒዮን ወክላ(በቀራኒዮ ጎለጎታ) ተመስላ ነው እኛም ዛሬ ወደቤተክርስቲያን በሔድን ጊዜ ሐዋርያት የሰበኩትን የተሰቀለውን ንጉሱ ክርስቶስን በቀጥታ አነጋግረነው እንደምንመጣ በልባችን ውስጥ ይዘነው በቀራኒዮ የተመሠለችው ቤተክርስቲያን ሔደን #አባትሆይ_ብለን ጸሎት አድርገን ተነጋግረን ቅዳሴውን ቀደስን ደሙን ጠጥተን ስጋውን በልተን ወደቤታችን እንመለሳለን ከዛ ፍጹም ሰላም ፍጹም እርቅ ፍጹም ደስታ ወደር የማይገኝለት የሚሰጠን ሰላምም አለ ለሰይጣን ፍራቻ የለንም ምክንያቱም መድሐኒታችን እንዲህ ነበረ ያለን

“ሰላምን #እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን #እሰጣችኋለሁ፤ እኔ #የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።”
— ዮሐንስ 14፥27
በማለት የተናገረውን መስቀል ስር እስከመጨረሻው ያልተለየው ተወዳጁ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ ጽፎልናል። እኛም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ልክ እንደ ነቢዩ #እንሒድ ሲሏችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ደስታ ሊሆንላችሁ ይገባል። ካልሆነ እናንተ እንሒድ ብላችሁ ኦርቶዶክሳዊት እህትሽን ወንድምሽን ወይም ኦርቶዶክሳዊ ወንድምህን እህትህን ይዘህ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሔድ ደስ ይበልህ ነቢዩ የተናገረው ምንምኳ ዘመነ ብሉይ ቢሆነ በዘመነ ሐዲስ ግን ቤተ ክርስቲያን እንሒድ ሲሉን ደስ የሚለን ሰው እንዳለን እንዲሁ ከደስታ ይልቅ የሚከፋን ሰወች በቁጥር አናሳ አይደለንም ገና እንሒድ የምትለን ልጅ ወደኛ ስትመጣ ምክንያት እንፈልጋለን ከዛም ያለ የሌለ ውሸታችንን እንደምክንያት በማቅረብ እንቀራለን። ግን የእግዚአብሔር ቤት የሚያስፈራራ ምን ነገር ኖሯት ነው? ወይስ ምክንያቱ ምን ይሆን?
አንዳንዴም ከዳቢሎስ ላይ ምክንያቱን እናሸክምና ሰዬጣን አስቀረኝ ለማለት እንናገራለን በመጀመሪያ ኦርቶዶክሳዊያን ልብ በሉ በመጀመሪያ ሰይጣን ወደኛ የሚጠጋው ባሰመርነው መሥመር ነው እንጂ እሱማኮ በመጀመሪያው በቅዱስ ገብርኤል የተወጋ
በቅዱስ ሚካኤል የተጣለ
በአምላካችን በመድሐኒታችን መስቀል ላይ የተቀጠቀጠ ከአንድም ሶስትጊዜ የተረገጠ ምንም አይነት ጉልበት የለለው እርኩስ መንፈስ ነው ይህንን እርኩስ መንፈስ ና ወደ እኛ የሚል ስራ የምንሰራ ከሆነ የማይመጣበት ምንም አይነት ምክንያት የለም ምክንያቱም

“በመጠን ኑሩ #ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ #ይዞራልና፤”
— 1ኛ ጴጥሮስ 5፥8
የሚዞረው ግን ሰነፉን ባገኝ ብሎጂ ቀራኒዮ ሔዶ በክርስቶስደም ሐይል ያገኘውን ምእመን አይደለም በቀራኒዮ ላይ ግን የሚያምነውም የማያምነውም ኢየሱስን ሊገድል ድንጋይ እና ብትር የያዙም ነበሩ ከዛ ውስጥ ግን ንጹህ ልብ ያለውም በፍቅሩ የሳበው ተወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ነበረ ስለዚህ ንስሃ ገብተን እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ቤተክርስቲያን እንቅረብ እንሒድ ሲሉንም ደስ ይበለን
የተከፈለልን የደም ዋጋ እንወቀው
ካሳ ቤዛ ሆኖ ሒወት የሰጠን የአባቶቻችን አምላክ ከጽሐይ መውጫ እስከ ጸሐይ መግቢያ በፍጥረቱ የተመሰገነ ይሁን አሜን

ኢሳይያስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² እነሆ፥ አምላክ መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ።
³ ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።
⁴ በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ።
⁵ ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ።
⁶ አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።

“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ #ደስ_አለኝ።”
— መዝሙር 122፥1


+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

"ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ "እንደኛ ስላልሆንክ አብደሃል" የሚሉበት ዘመን ይመጣል"
ቅዱስ እንጦንዮስ

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"
ቅዱስ ባስልዮስ

"ይህንን ካስታወስክ በሰው መፍረድ ታቆማለህ:: ይሁዳ ሐዋርያ ነበር:: ከጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ነፍሰ ገዳይ ነበር" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD)

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ

‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

"ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡

የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 26 2011
ጅማ ፣ ኢትዮጵያ


+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!


1ኛ ዮሐንስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።
² የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥
³ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።
⁴ ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።
⁵ እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል።
⁶ እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።
⁷ ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።
⁸ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።
⁹ በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።
¹⁰ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
¹¹ ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።
¹² እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።
¹³ ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።
¹⁴ እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።
¹⁵ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።
¹⁶ እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
¹⁷ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።
¹⁸ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
¹⁹ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
²⁰ ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
²¹ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።


♦️ ትትናሽ 🕊 ግሩም ♦️ ነው
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ትትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽ / 2 /
እናቱ ሆነሻል ለመድኃኒያለም / 2/


ንጽህት ስለሆነሽ -----እመቤት እመቤቴ
እንከን የሌለብሽ _እመቤቴ እመቤቴ
የፍጥረታት ጌታ እመቤቴ እመቤቴ
ባንቺ አደረብሽ __
እመቤቴ እመቤቴ
የድንግል መመረጥ _ እመቤቴ እመቤቴ
ዜናው አስገረመኝ እመቤቴ እመቤቴ
እሳቱን ታቀፍች
እመቤቴ እመቤቴ
የማይቻለውን _ እመቤቴ እመቤቴ



♦️ አዝማች ♦️

ምርኩዜ ልበልሽ ____እመቤቴ እመቤቴ
ጥላከለላዬ እመቤቴ እመቤቴ
ጋሻዬ ነሽ አንቺ
እመቤቴ እመቤቴ
ለኔስ መመኪያዬ _እመቤቴ እመቤቴ
ባለም እንዳልጠፋ _እመቤቴ እመቤቴ
ሕይወቴ መሮብኝ እመቤቴ እመቤቴ
እንደወይን _
እመቤቴ እመቤቴ
አጣፍጪው _እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል ድረሺልኝ _እመቤቴ እመቤቴ


♦️ አዝማች ♦️


የምስራቅ ደጃፍ ነሽ __
እመቤቴ እመቤቴ
የሁላችን ተስፋ _እመቤቴ እመቤቴ
እሙ ለጸሐይ ጽድቅ ____እመቤቴ እመቤቴ
የሁሉ ጠበቃ ____እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል የድል አክሊል___እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል የፅድቅ ስራ ____እመቤቴ እመቤቴ
ድንግል መሰላል ነሽ ____እመቤቴ እመቤቴ
የተዋህዶ ተስፋ _እመቤቴ እመቤቴ


ወስብሐት ለእግዚአብሔር ♦️ ወለወላዲቱ ድንግልወለመስቀሉ__ክብር __♦️♦️👏👏👏

♦️
♦️
♦️
♦️
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
♦️
♦️
♦️
♦️
♦️


የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

+ ከቅዱስ ኤፍሬም +


+ የተቀደሰው የሩጫ ውድድር +

እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሩጫ ብሔራዊ ኩራት በሆነበት ሀገር መቼም የሩጫ ነገር ብናወራ ሰሚ አናጣም:: ሮጦ ሀገር ማስጠራት : ሮጦ ብዙ ሀብት ማፍራትና ለሀገር መትረፍ የቻሉ ውድ አትሌቶቻችንን በፍቅር እናያቸዋለን:: "በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው ቅዱስ ቃል ለነፍስ ቢነገርም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን "ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው መርሕ "ሮጬ ባለፈልኝ" በሚሉ ተስፈኞች ይተገበራል:: (1ቆሮ 9:24)

ዛሬ ግን በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገ ቅዱስ ሩጫ ትዝ አለኝ:: በትንሣኤ ዕለት የተደረገ ቅዱስ እሽቅድምድም በዓይነ ሕሊናዬ መጣ::
ከዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል ሁለቱ የተሳተፉበት ዳኛም ተመልካችም የሌለበት የትንሣኤ ዕለት ሩጫ!!!

ሴቶች ወደ ጌታ መቃብር ደርሰው ሲመለሱ ጌታ በመቃብር እንደሌለ ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩአቸው::
ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሔዱ::

"ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ" ዮሐ 20:4

በዚህ ቀን በተደረገው ቅዱስ ሩጫ የ58 ዓመቱ ጎልማሳ ጴጥሮስ ከ28 ዓመቱ ወጣት ዮሐንስ ጋር ወደ ጌታ መቃብር ሮጡ:: ሐሙስ ማታ ጌታውን የካደው ጴጥሮስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታውን ከተከተለው ዮሐንስ ጋር አብሮ ወደ መቃብሩ ሮጠ::

ጴጥሮስ ሆይ ወደ ጌታህ መቃብር በሩጫ ስትገሰግስ ምን እያሰብህ ይሆን? ሐሙስ በካድከው ጊዜ ቀና ብለው ያዩህ ዓይኖቹ በሕሊናህ መጥተው ይሆን?
ወደ መቃብሩ ስትሮጥ "ጌታ ሆይ በአፌ ክጄሃለሁ በእግሮቼ ግን አልክድህም" ብለህ አስበህ ይሆን? "በባሕር ላይ ያራመድኸው እግሬ : አጎንብሰህ ያጠብከው እግሬ ወደ አንተ ለመሮጥ አይደክመውም" ብለህ ይሆን? መቃብሩ ሥር ተደፍተህ ለማልቀስ የሐሙሱን ዕንባህን በመግነዙ ለማበስ አስበህ ይሆን?

ብቻ ጴጥሮስ ከዮሐንስ ጋር ወደ መቃብሩ ሮጠ:: ዮሐንስ በጉልበቱ ገና ወጣት ቢሆንም : እንደ ጴጥሮስ ጸጸት የማይቆጠቁጠው ድል አድራጊ ቢሆንም ጴጥሮስ አብሮ ከመሮጥ ወደኁዋላ አላለም::

ብቻ መቃብሩ ልድረስ እንጂ ቢቀድመኝም እከተለዋለሁ:: እንደርሱ እስከ መስቀል ባልጸናም ለመቃብሩ ግን ዳግም እታገላለሁ ብሎ ጴጥሮስ ሮጠ::

በዚህ ቅዱስ ሩጫ አርብ የወንድ ለቅሶን ያፈሰሰው ዮሐንስ በዕንባ በደከሙ ዓይኖቹ በኀዘን በጠቆረ ፊቱ እያማተረ ወደ ጌታ መቃብር ገሠገሠ:: በዚያች ዕለት ጌታን እንዴት እንደ ገረፉት አይቶአል:: እንዴት እንደ ቸነከሩት ተመልክቶአል:: አሁን ደግሞ መስቀል ሥር ቆመው በዋሉ እግሮቹ ወደ መቃብሩ እየሮጠ ነው::

ወንድሜ ሆይ ጴጥሮስና ዮሐንስን ወደ ጌታ መቃብር ሲሮጡ እያቸው:: አንተና ጉዋደኞችህስ ወዴት ትሮጣላችሁ? የእናንተ እሽቅድምድም ወደ ጌታ መቃብር ነው? የት ለመሔድ ትፎካከራላችሁ? የት እንገስግስ ትባባላላችሁ?

ወጣቱ ዮሐንስ ጎልማሳውን ጴጥሮስን ቀድሞ ከጌታ መቃብር ደረሰ:: የጌታን መግነዝም አየ:: ወደ ውስጥ ግን ሳይገባ ቆሞ ጴጥሮስን ጠበቀው:: ጴጥሮስ ዘግይቶ ቢደርስም ከዮሐንስ ቀድሞ ወደ መቃብሩ ገባ::

ከእኔ የበረታ መንፈሳዊ ጉልበት ያለህ ወንድሜ ሆይ ብትቀድመኝ እንኩዋን አትፍረድብኝ:: ጨክነህ ጥለኸኝ ወደ ጌታ ማረፊያ እንዳትገባ:: የዘገየሁት ኃጢአት እግሬን አስሮት ነውና ብርቱው ወንድሜ ሆይ እባክህን ጠብቀኝ:: ድክመቴን አይተህ አትናቀኝ መጎተቴን አይተህ አትፍረድብኝ:: አደራህን ብቻህን ወደ ጌታ ደስታ እንዳትገባ:: አደራህን በንስሓ እስክበረታ ጠብቀኝ:: እንኩዋን አንተ አብረኸኝ ሩጫ የጀመርክ ወንድሜ ቀርቶ ከእኔ ቀድመው ሩጫቸውን የጨረሱት እንኩዋን ብቻቸውን ወደ ዘላለማዊ ደስታ እንዳይገቡ በገነት ሆነው እኔን ይጠብቁኝ የለ?

ነቢዩ እንደተናገረ :-
አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ፤
ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤
ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ፡
ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ። (መዝ 142:7)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 16 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ


Репост из: ቅዱስ ጳውሎስ ሃዋርያዊ አገልግሎት
የማቴዎስ ወንጌል ጥናት
ምእራፍ ስድስት(6)


ሐዋርያት 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በኢቆንዮንም እንደ ቀድሞ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገብተው ከአይሁድና ከግሪክ ሰዎች ብዙ እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ።
² ያላመኑት አይሁድ ግን የአሕዛብን ልብ በወንድሞች ላይ አነሣሡ አስከፉም።
³ ምልክትና ድንቅ በእጃቸው ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል ስለ መሰከረው ስለ ጌታ ገልጠው እየተናገሩ ረጅም ወራት ተቀመጡ።
⁴ የከተማውም ሕዝብ ተከፍለው እኵሌቶቹ ከአይሁድ እኵሌቶቹም ከሐዋርያት ጋር ሆኑ።
⁵ አሕዛብና አይሁድ ግን ከአለቆቻቸው ጋር ሊያንገላቱአቸውና ሊወግሩአቸው ባሰቡ ጊዜ፥
⁶ አውቀው ልስጥራንና ደርቤን ወደሚባሉት ወደ ሊቃኦንያ ከተማዎች በእነርሱም ዙሪያ ወዳለው አገር ሸሹ፤
⁷ በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር።
⁸ በልስጥራንም እግሩ የሰለለ፥ ከእናቱም ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ፥ ከቶም ሄዶ የማያውቅ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።
⁹ ይህም ሰው ጳውሎስ ሲናገር ይሰማ ነበር፤ እርሱም ትኵር ብሎ ተመለከተውና ይድን ዘንድ እምነት እንዳለው ባየ ጊዜ፥
¹⁰ በታላቅ ድምፅ፦ ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም አለው። ብድግ ብሎም ተንሥቶ ይመላለስ ነበር።
¹¹ ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ፦ አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል አሉ፤
¹² በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት።
¹³ በከተማውም ፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባን አክሊሎች ወደ ደጃፍ አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ።
¹⁴ ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥
¹⁵ እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።
¹⁶ እርሱ ባለፉት ትውልዶች አሕዛብን ሁሉ በገዛ ራሳቸው ጐዳና ይሄዱ ዘንድ ተዋቸው።
¹⁷ ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።
¹⁸ ይህንም ብለው እንዳይሠዉላቸው ሕዝቡን በጭንቅ አስተዉአቸው።
¹⁹ አይሁድ ግን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጡ፤ ሕዝቡንም አባብለው ጳውሎስን ወገሩ የሞተም መስሎአቸው ከከተማ ወደ ውጭ ጐተቱት።
²⁰ ደቀ መዛሙርት ግን ከበውት ሳሉ፥ ተነስቶ ወደ ከተማ ገባ። በነገውም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ወጣ።
²¹-²² በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ።
²³ በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው።
²⁴ በጲስድያም አልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፥
²⁵ በጴርጌንም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ አጣልያ ወረዱ፥
²⁶ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።
²⁷ በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
²⁸ ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።


ሐዋርያት 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።
² እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።
³ በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው።
⁴ እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄዱ።
⁵ በስልማናም በነበሩ ጊዜ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፤ አገልጋይም ዮሐንስ ነበራቸው።
⁶ ደሴቲቱንም ሁሉ እስከ ጳፉ በዞሩ ጊዜ፥ በርያሱስ የሚሉትን ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የሆነውን አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኙ፤
⁷ እርሱም አስተዋይ ሰው ከሆነው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባለው አገረ ገዥ ጋር ነበረ። ይህም በርናባስንና ሳውልን ወደ እርሱ ጠርቶ የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ፈለገ።
⁸ ጠንቋዩ ግን ኤልማስ፥ ስሙ እንዲሁ ይተረጐማልና፥ አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው።
⁹ ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ትኵር ብሎ ሲመለከተው፦
¹⁰ አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን?
¹¹ አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፥ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፥ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።
¹² በዚያን ጊዜ አገረ ገዡ የተደረገውን ባየ ጊዜ ከጌታ ትምህርት የተነሣ ተገርሞ አመነ።
¹³ ጳውሎስም ከጓደኞቹ ጋር ከጳፉ ተነሥቶ የጵንፍልያ ወደምትሆን ወደ ጴርጌን መጣ፤ ዮሐንስም ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
¹⁴ እነርሱ ግን ከጴርጌን አልፈው የጲስድያ ወደምትሆን ወደ አንጾኪያ ደረሱ፤ በሰንበትም ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ።
¹⁵ ሕግና ነቢያትም ከተነበቡ በኋላ የምኵራቡ አለቆች፦ ወንድሞች ሆይ፥ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ ብለው ላኩባቸው።
¹⁶ ጳውሎስም ተነሣና በእጁ ጠቅሶ እንዲህ አለ፦ የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ ስሙ።
¹⁷ የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብፅ አገር በእንግድነት ሳሉ ሕዝቡን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፥ ከፍ ባለችውም ክንዱ ከዚያ አወጣቸው።
¹⁸ በበረሀም አርባ ዓመት ያህል መገባቸው።
¹⁹ በከነዓንም አገር ሰባት አሕዛብን አጥፍቶ ምድራቸውን አወረሳቸው።
²⁰ ከዚህም በኋላ እስከ ነቢዩ እስከ ሳሙኤል ድረስ አራት መቶ አምሳ ዓመት ያህል መሳፍንትን ሰጣቸው።
²¹ ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፥ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን አርባ ዓመት ሰጣቸው፤
²² እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ።
²³ ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።
²⁴ ከመምጣቱ በፊት ዮሐንስ አስቀድሞ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ሰብኮ ነበር።
²⁵ ዮሐንስም ሩጫውን ሲፈጽም ሳለ፦ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔስ እርሱን አይደለሁም፤ ነገር ግን እነሆ፥ የእግሩን ጫማ እፈታ ዘንድ ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ ይመጣል ይል ነበር።
²⁶ እናንተ ወንድሞቻችን፥ የአብርሃም ዘር ልጆች ከእናንተ መካከልም እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥ ለእናንተ የዚህ የመዳን ቃል ተላከ።
²⁷ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤
²⁸ ለሞትም የሚያደርስ ምክንያት አንድ ስንኳ ባያገኙበት፥ ይገድለው ዘንድ ጲላጦስን ለመኑት፤
²⁹ ስለ እርሱም የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜ ከእንጨት አውርደው በመቃብር አኖሩት።
³⁰ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤
³¹ በሕዝብም ዘንድ ምስክሮቹ ለሆኑት ከእርሱ ጋር ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም ለወጡት ብዙ ቀን ታያቸው።
³² እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤
³³ ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና።
³⁴ እንደገናም ወደ መበስበስ እንዳይመለስ ከሙታን እንደ አስነሣው፥ እንዲህ፦ የታመነውን የዳዊትን ቅዱስ ተስፋ እሰጣችኋለሁ ብሎአል።
³⁵ ደግሞ በሌላ ስፍራ፦ ቅዱስህን መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም ይላልና።
³⁶ ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤
³⁷ ይህ እግዚአብሔር ያስነሣው ግን መበስበስን አላየም።
³⁸-³⁹ እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።
⁴⁰-⁴¹ እንግዲህ፦ እናንተ የምትንቁ፥ እዩ ተደነቁም ጥፉም አንድ ስንኳ ቢተርክላችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እኔ እሠራለሁና ተብሎ በነቢያት የተነገረው እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ።
⁴² በወጡም ጊዜ ይህን ነገር በሚመጣው ሰንበት ይነግሩአቸው ዘንድ ለመኑአቸው።
⁴³ ጉባኤውም ከተፈታ በኋላ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ገብተው ከሚያመልኩ ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፥ እነርሱም ሲነግሩአቸው በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አስረዱአቸው።
⁴⁴ በሁለተኛውም ሰንበት ከጥቂቶቹ በቀር የከተማው ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰሙ ዘንድ ተሰበሰቡ።
⁴⁵ አይሁድም ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ ቅንዓት ሞላባቸው፥ እየተሳደቡም ጳውሎስ የተናገረውን ቃል ተቃወሙ።
⁴⁶ ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው፦ የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘላለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።
⁴⁷ እንዲሁ ጌታ፦ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ አዞናልና አሉ።
⁴⁸ አሕዛብም ሰምተው ደስ አላቸው የእግዚአብሔርንም ቃል አከበሩ፥ ለዘላለም ሕይወትም የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ፤
⁴⁹ የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ።
⁵⁰ አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፥ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው።
⁵¹ እነርሱ ግን የእግራቸውን ትቢያ አራግፈውባቸው ወደ ኢቆንዮን መጡ።
⁵² በደቀ መዛሙርትም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።

Показано 20 последних публикаций.

213

подписчиков
Статистика канала