የሸይኽ አብዱል ዓዚዝ አረይስን ትምህረት በቻናሉ ሼር አድርጎ ብዙም ሳይቆይ በዛው ተመሳሳይ ነገር ሌሎችን የወቀሰው አስገራሚ ፍጡር!!
እዚህጋ ማነም ሠው ለምን የሸይኽ አብዱል ዓዚዝ አረይስን ትምህርት በቻናሉ ሼር አደረገ ለማለት አይደለም።
ከሰለፎችም ጀምሮ በሌሎች ዓሊሞች ሙብተዲዕነቱ የተገለፀ የአንድ ሠው ሁኔታ ሌሎቹ በዝርዝር ሳያውቁት ሳይገለፅላቸው ያወድሱ ሀዲስ ከሱ ይዘግቡበት ነበር።
እዚህ ሀገር ላይም ሰለፍዮች የዓብዱል ዓዚዝ አረይስን ሁኔታ በመልካም ብቻ ስለሚያውቁት ይወዱታል። አሁን ሸይኽ ጦሀን ለማንቋሸሸ የተነሳው ግለሰብም የሸይኽ አብዱል ዓዚዝን ንግግር ቻናሉ ላይ አስፍሯል።
በመሆኑም ይሄ አይደለም የሚያስወቅሰው ግን በተመሳሳይ ሌሎችን ለመወረፍ ሲታትር ማየት ያሳዝናል።
ሸይኽ ጠሀ ኸድር ሪያድ ሰዒድ የተሰኘን ሸይኽ ተዕድል አድርገዋል (አወድሰዋል) ሸይኽ ሪያድ ሰዒድ ደግሞ አልዩል ሀለቢን አወድሷል።
ስለዚህ እዚህ ሀገርም ኢኽዋንና ሙመይዓ የሚያደርጉትን የዲን ጥሰት አትፋለሙ ከተፋለማችሁ ነገር እየለቃቀምን እናንቋሽሻችኋል። #አጅብ!
በአንተ አባባል ይሄኛውንም ምን ልትለው ነው? አብዱል ዓዚዝ አረይስ አልዩል ሀለቢን ያወድሳል። ብቻም ሳይሆን ታላላቅ የውጭ ዑለሞች በርካታ ጥፋቶች እንዳሉበት ጠቅሰው ከሱ አስጠንቅቀዋል። ያን የማናውቅ ግን ብዙዎች ነን። የምናውቅና በመረጃው በትክክል የደረሰን ካለን ለማነም ብለን ሳይሆን ለአላህ ብለን እንጠነቀቃል። ከዛ ውጭ በዝርዝር በማነውቀው ሠው አንጠየቅም። የሀገራችን ዑለሞችም ቢሆኑ ስለ-አረይስ ምናልባት በደረሳቸው ልክ ብቻ ሙዓኸዛና ሙላሀዛ አለበት ብለው ይሆናል እንጅ ሙብተዲዕ ነው የሚል አንድም ፍንጭ አላወጡም። እስከምናወቅ ድረስ ደግሞ የሱና ሰዎች አንቻኮልም። ስለሆነም እንዲህ አይነት ተከሳቾችን እየለቃቀሙ በዲን ላይ ስሌት እየሰሩ ለመጫዎትና ኢኽዋንና ሙመይዓዎች የሚያደርጉትን የዲን ጥሰት ለማጥፋፋት መሞከር የበሽተኞች የስራ ድርሻ መሆኑን የሱና ሰዎች የነቁበት ጉዳይ ነው።
ስለሆነም ወደዚህኛው ስንመለስ ብዙዎቻችን ስለ ሪያድ ሰዒድ የዓብዱል ዓዚዝ አርረይስን ያህል እንኳ አናውቅም ነገሩን የሚለቃቅሙ ሰዎችም አያውቁም። የረብሻ ጥማት ግን ከዚህ ያደርሳል።
t.me/Abdurhman_oumer