Educational Material and Info


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


📊 Forex News | Trading Education | Market Analysis
Stay updated with the latest market movements and improve your trading skills.
promotion:
- @Johnacademy1
- https://tlmtr.io/p/3ZT3V0
-https://telega.io/c/EduInfoMaterial

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡

ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡

ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም።

ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል።

የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር ሊፈፀም የሚችል ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል፡፡ (ሰርኩላሩ ከላይ ተያይዟል፡፡)
#ATC




ከ47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አንድኛቸውም መስፈርት አለማሟላታቸው ተገለጸ‼️

ራስ ገዝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ዕድሳት መመሪያ የተቀመጠውን ዝቅተኛ መስፈርት አለማሟላታቸውን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ።

በሰኔ 2018 ዓ.ም. በተደረገው ግምገማ መሠረት ሁሉም ተቋማት መስፈርቱን ያላሟሉ ሲሆን፣ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተከትሎ ሰነዶቻቸውን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. እንዲያቀርቡ የ40 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል።

በዳግም ምዝገባው ሂደት ልዩ አደረጃጀት የተሰጠው ለኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ብቻ መሆኑም ተገልጿል።(ሪፖርተር)


#MoE

በ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች፣ በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ስማችሁንና ሪፈረንስ ቁጥራችሁን በማስገባት እስከ መስከረም 13/2019 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ያሉት ቦታዎች ውስን በመሆናቸው በተጠባባቂነት ከተያዙ መካከል የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ምደባ የሚካሔደው ክፍት ቦታዎች ባሏቸው ትምህርት ቤቶች እንደሚሆን ተገልጿል።

@Eduinfomaterial








Forward to yours freshman guys👆👆👆👆👆👆




AAU Info& Material dan repost
📚 የመጀመሪያ አመት የተፈጥሮ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአብዛሀኛው ግቢ ላይ የሚወስዷቸው የመጀመሪያ ሴሚስተር ኮርሶች ናቸው።👇👇👇👇👇



11 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.