ፋይናንስ ክፍል በጌምድር አካዳሚ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan



Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


📢 ለበጌምድር አካዳሚ ተማሪዎች ወላጆች/አዳጊዎች በሙሉ
በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የወርሃዊ ክፍያዎችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) በተማሪው የልጆች መለያ ቁጥር (Children ID) አማካኝነት በቀጥታ በ *889# አጭር ቁጥር ወይም በCBE Birr/CBE Mobile Banking ሞባይል አፕሊኬሽን መክፈል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
📅 የ2019 ዓ.ም የወርሃዊ ክፍያዎች ጊዜ ሰሌዳ
1️⃣ የጥቅምት ወር ከመስከረም 1/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም
2️⃣ የህዳር ወር ከጥቅምት 1/2019 ዓ.ም እስከ ኅዳር 05/2019 ዓ.ም
3️⃣ የታህሳስ ወር ከኅዳር 1/2019 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 05/2019 ዓ.ም
4️⃣ የጥር ወር ከታኅሣሥ 1/2019 ዓ.ም እስከ ጥር 05/2019 ዓ.ም
5️⃣ የየካቲት ወር ከጥር 1/2019 ዓ.ም እስከ የካቲት 05/2019 ዓ.ም
6️⃣ የመጋቢት ወር ከየካቲት 1/2019 ዓ.ም እስከ መጋቢት 05/2019 ዓ.ም
7️⃣ የሚያዝያ ወር ከመጋቢት 1/2019 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 05/2019 ዓ.ም
8️⃣ የግንቦት ወር ከሚያዝያ 1/2019 ዓ.ም እስከ ግንቦት 05/2019 ዓ.ም
9️⃣ የሰኔ ወር ከግንቦት 1/2019 ዓ.ም እስከ ሰኔ 05/2019 ዓ.ም
⚠️ ስለ ዘግይቶ ክፍያ ቅጣት እና የላቀ ማብራሪያ
የባንክ ሲስተሙ ከተቀመጠው የክፍያ ማጠናቀቂያ ቀን (ከየወሩ 5ኛ ቀን) በኋላ ክፍያዎችን የሚያስተናግደው በራስ-ሰር በሚታሰብ የቅጣት ክፍያ በመሆኑ፦ 🔹 ከ1ኛው እስከ 7ኛው ቀን መዘገየት፦ ሲስተሙ 100 ብር ቅጣት ይጨምራል።
🔹 ከዚያ በኋላ በየ7 ቀኑ፦ ተጨማሪ 50 ብር እየጨመረ ይሄዳል።
💡 ምሳሌ፦ ለጥቅምት ወር ክፍያ (መጨረሻ ቀን ጥቅምት 5)
👉 ከጥቅምት 6 እስከ ጥቅምት 12 ቢከፈል፦ የትምህርት ቤት ክፍያ + 100 ብር ቅጣት
👉 ከጥቅምት 13 እስከ ጥቅምት 19 ቢከፈል፦ የትምህርት ቤት ክፍያ + 150 ብር ቅጣት
👉 ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 26 ቢከፈል፦ የትምህርት ቤት ክፍያ + 200 ብር ቅጣት
👉 ከጥቅምት 27 እስከ ጥቅምት 30 ቢከፈል፦ የትምህርት ቤት ክፍያ + 250 ብር ቅጣት እያለ 50 ብር ቅጣት እጨመረ ይቀጥላል

ስለሆነም ወላጆች አላስፈላጊ ለሆነ ተጨማሪ የቅጣት ክፍያ እንዳይጋለጡና የልጆቻችሁን ትምህርት በስርዓት ለማስቀጠል የወርሃዊ ክፍያዎችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በወቅቱ እንድትፈጽሙ በትህትና እናሳስባለን።




በጌምድር አካዳሚ dan repost
​🚨 ጥብቅ መልዕክት ለበጌምድር አካዳሚ የተማሪ ወላጆች / አሳዳጊዎች 🚨

​ቀን፡ 06/01/2019 ዓ.ም

👉 ​ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት፡
የ2019 ዓ.ም የመደበኛ ትምህርት መማር ማስተማር ስራ ግቢው ውሃ የመቋጠር ችግር ስለነበረበት መስከረም 11 ቀን ይጀመራል ተብሎ የተገለፀ ቢሆንም፤ በተደረገው ከፍተኛ እርብርብ የግቢው ውሃ የተቋጠረበት ቦታ በአፈር በመሞላቱና የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ግቢው ጠፈፍ ብሏል።

​ስለሆነም ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያላችሁ መደበኛ ተማሪዎች በነገው ዕለት ሐሙስ (ቀን 07/01/2019 ዓ.ም) ትምህርት የሚጀመር መሆኑን አውቃችሁ በተለመደው የትራንስፖርት/ፊርማታ ቦታ እንድትጠብቁ ትምህርት ቤቱ ያሳስባል።

👉 ​የቅድመ መደበኛ (KG) ህፃናት ትምህርት፡
የቅድመ መደበኛ ህፃናት ትምህርት የሚጀምርበትን ቀን የመምህራኖቻቸው የኮሌጅ ስልጠና እንደተጠናቀቀ አያይዘን የምናሳውቅ ይሆናል።

​በጌምድር አካዳሚ
"ትምህርት በጥራት እንሰጣለን!"


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የተማሪዎች ሹራብ ለምትፈልጉ ወላጆች ሹራብ ስለመጣ አካዳሚ ከ3:00 እስከ 8:00 ባለው የምትገዙበትን ብር በጥሬው ይዘው በመምጣት መግዛት ይችላሉ እናመሰግናለን።

ማሳሰቢያ
👉 ዋጋ እንደየሳይዙ ስለሚለያይ ከ700 ብር እስከ 1,000 ብር ይዘው ይምጡ
👉 መጥተው መግዛት የሚችሉበት ጊዜ ከመስከርም 06 ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀን ሆኖ ልጆች መስከረም 11 ወደ ትምህርት ቤታቸው ሲመጡ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) እና አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁሶችን አሟልተው መሆን አለባቸው


በጌምድር አካዳሚ dan repost
​የተከበራችሁ የበጌምድር አካዳሚ ተማሪዎች ወላጆችና አሳዳጊዎች፤

​ጉዳዩ፡- የ2019 ዓ.ም የትምህርት መጀመሪያ ቀንን ማሳወቅን ይመለከታል

​በቅድሚያ ለ2019 ዓ.ም አዲስ የትምህርት ዘመን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!
​አካዳሚያችን ከተራራ ስር የሚገኝ በመሆኑ በተጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የሚመጣው ውሃ በተማሪዎች መሰለፊያ፣ በመተላለፊያ ቦታዎች እና በመጫወቻ ሜዳዎች ላይ በመታቁሩ ግቢው ለህፃናት ልጆቻችን ምቹና ፅዱ አልሆነም። ስለዚህ ልጆቻችን በጭቃና በተከማቸ ውሃ እንዳይሰናከሉና ለጤና ስጋት እንዳይጋለጡ ለማድረግ ሲባል ተቋማችን የጽዳትና ማስተካከያ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
👉 ​የ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች፡ ትምህርት የሚጀምሩበት ቀን ወደ መስከረም 11/2019 ዓ.ም የተዛወረ መሆኑን፤

👉 ​የቅድመ መደበኛ (KG) ህፃናት፡ መምህራኖቻቸው ከኮሌጅ ስልጠና እንደተመለሱ ትምህርት የሚጀምሩበትን ቀን አያይዘን የምናሳውቅዎ መሆኑን እናስታውቃለን።

​የማካካሻ ትምህርት ፕሮግራም (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል)፡

ከመስከረም 05 እስከ መስከረም 08/2019 ዓ.ም የሚታለፉትን 4 የትምህርት ቀናት ለማካካስ በሚከተሉት 4 የቅዳሜ ቀናት መደበኛ ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል፡

👉​መስከረም 16/2019 ዓ.ም (ቅዳሜ)
👉​መስከረም 23/2019 ዓ.ም (ቅዳሜ)
👉​መስከረም 30/2019 ዓ.ም (ቅዳሜ)
👉​ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም (ቅዳሜ)

​የልጆቻችን ደህንነትና የትምህርት ጥራት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሆኑ፤ ይህንኑ በመረዳት በተቀመጠው የትምህርት መጀመሪያ ፕሮግራም መሠረት እንድትከተሉ በአክብሮት እናስታውቃለን።

​በጌምድር አካዳሚ
"ትምህርት በጥራት እንሰጣለን!"


በጌምድር አካዳሚ dan repost
🌼 እንደ አደይ አበባ አዲስ ተስፋ... 🌼

​ዘመን መለወጥ የቁጥር መለወጥ ብቻ አይደለም፤ የሀሳብ፣ የጥንካሬ እና የህልም መታደስ እንጂ! አሮጌውን ዓመት ከነክፋቱ እና ከነፈተናው በጀርባችን ጥለን፣ የልጆቻችንን ብሩህ ተስፋ የምንቀርጽበትን አዲስ ገጽ በንጹህ ተስፋ እንከፍታለን።

​✨ በ2019 ዓ.ም፦

⭐️ ​በጋራ የለፋንላቸው የልጆቻችን ህልሞች የሚፈጸሙበት

⭐️ ​በትምህርታቸውና በስነ-ምግባራቸው የታሰቡ መልካም መንገዶች የሚከፈቱበት

⭐️ ​የወላጅ እና የትምህርት ቤት ትስስር ፍሬ አፍርቶ የልብ ምኞታችን ከእውነት የሚገናኝበት ስኬታማ ዘመን ይሁንልን!

የልጆቻችን ነገ የሚበራው በጋራ በምንጥለው የእውቀትና የፍቅር መሰረት ላይ ነው! 🌼 ከበጌምድር አካዳሚ ቤተሰቦች ጋር ወደ አዲሱ 2019 ዓ.ም የመስከረም ብርሃን።

​🌻 መልካም አዲስ ዓመት! 🌻
በጌምድር አካዳሚ


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የበጌምድር አካዳሚ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ ደንቦች እና መረጃዎች ማጠቃለያ (2019 ዓ.ም)

ለ 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንኳን አደረሳችሁ

📌የተማሪዎች አጠቃላይ ደንብና ግዴታዎች (ከኬጂ እስከ 8ኛ ክፍል)

✅ ዩኒፎርም ሙሉ በሙሉ መልበስ
⭐️ ለወንዶች፡ ኖርማል የፀጉር ቁርጥ ተስተካክሎ መገኘት
⭐️ ለሴቶች:- የፀጉር ሁኔታ ንጽህናው የተጠበቀ ለተማሪዎች ሊረብሽ በማይችለ መልኩ የተያዘ

🎒 የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች

ለኬጂ 1 ተማሪዎች
📘 ደብተር (በፕላስቲክ የተሸፈነ) — 5 ፍሬ ባለ50 ሉክ
✏️ እርሳስ — 4 ፍሬ HB የሚባል ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ
🎨 ከለር እርሳስ — 1 እሽግ
🧼 ማጥፊያ — 3 ፍሬ
✂️ የእርሳስ መቅረጫ — 3 ፍሬ
🧻 ሶፍት — 2 ጥቅል ABC ቢሆን ይመረጣል
🎨 የስዕል ደብተር — 1
👟 ክፍል ውስጥ የሚጠቀሙበት ነጠላ ጫማ በጣት የማይገባ ቢሆን ምቹ ነው ለህፃናት

ለKG 1 ወላጆች ማሳሰቢያ: ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት ከመምጣታቸው በፊት የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም እና ራሳቸውን ችለው የመመገብ ልምድ እንዲኖራቸው አስቀድመው ያዘጋጁ።

ለኬጂ 2 እና ኬጂ 3 ተማሪዎች
📘 ደብተር (በፕላስቲክ የተሸፈነ) — 6 ባለ 50ሉክ
✏️ እርሳስ — 4 ፍሬ HB የሚባል ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ
🎨 ከለር እርሳስ — 1 እሽግ
🧼 ማጥፊያ — 3 ፍሬ
✂️ የእርሳስ መቅረጫ — 3 ፍሬ
🧻 ሶፍት — 2 ጥቅል ABC ቢሆን ይመረጣል
🎨 የስዕል ደብተር — 1

ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች
📓 ራዲካል ደብተር (ባለ ብላስቲክ ሽፋን)
👉 ለ1ኛ,2ኛ,5ኛ,6ኛ,7ኛ,8ኛ ክፍል ብዛት 10 ደብተር ባለ 50ሉክ
👉 ለ3ኛ እና 4ኛ ክፍል ብዛት 11 ደብተር ባለ 50ሉክ
✏️ እርሳስ፣ ማጥፊያና መቅረጫ — ለ1ኛ እና 2ኛ ክፍል
🖊️ እስክርቢቶ — ከ3ኛ እስከ 8ኛ ክፍል
🧴 ኡሁ (ማጣበቂያ) — 2 ፍሬ (ለሁሉም የክፍል ደረጃ) ፈተናዎችን ደብተር ላይ ማጣበቂያ ለአመቱ የሚጠቀሙበት

⏰ የትምህርት የሚጀመርበት ቀን አስመልክቶ

ትምህርት የሚጀምርበት ቀን: በሚቀጥሉት 3ቀናቶች ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

📚 የቴሌግራም ቻናሎች
soft copy የመማሪያ መጻሕፍትን፣ የመለማመጃ ጥያቄዎችን፣ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን እና የተማሪዎች የሴክሽን ድልድል ለማግኘት የልጅዎን የክፍል ደረጃ በመጫን ይቀላቀሉ፡

🔹 የአካዳሚው ዋና ገጽ
🔹 ኬጂ 1
🔹 ኬጂ 2
🔹 ኬጂ 3
🔹 1ኛ ክፍል
🔹 2ኛ ክፍል
🔹 3ኛ ክፍል
🔹 4ኛ ክፍል
🔹 5ኛ ክፍል
🔹 6ኛ ክፍል
🔹 7ኛ ክፍል
🔹 8ኛ ክፍል
ፋይናንስ መረጃ:
የተማሪ ክፍያ ኮዶች እና የአጠቃቀም መመሪያ ለማግኘት
👉 የፋይናንስ ቻናል

📍 ጳጉሜ 04 / 2018 ዓ.ም

በጌምድር አካዳሚ


በጌምድር አካዳሚ dan repost
ውድ የአካዳሚያችን ተማሪዎች!

​ትምህርት ቤታችሁ በሚያምር መልኩ ተዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ ይገኛል። እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ወቅት በሰላም አደረሳችሁ!
​በየክፍል ደረጃው የምታሟሉትን የደብተር ብዛትና ዓይነት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በቀጣይ በዝርዝር የምናሳውቃችሁ ይሆናል። እስከዚያው ግን የትምህርት ቤት ደንብ ልብሳችሁን (ዩኒፎርም) በወቅቱ ማሟላት እንዳለባችሁ ታስቢ በማድረግ ተዘጋጁ።

​ማሳሰቢያ፦ የተቀደደ ወይም ቅርፁን ያጣ ሸሚዝ፣ ሱሪ፣ ጉርድ ቀሚስ እና ሹራብ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን።

​ቀሪ ዝርዝር መረጃዎችን በቅርቡ የምናሳውቅ በመሆኑ በትዕግሥት እንድትጠባበቁን እንገልጻለን።


በጌምድር አካዳሚ dan repost
ቀን:- 27/12/2018 ዓ.ም
​📢 ለበጌምድር አካዳሚ ተማሪ ወላጆች በሙሉ

​የተከበራችሁ የአዲስ እና የነባር ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች፤

​ትምህርት ቤታችን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል። በመሆኑም ከነገ ሐሙስ (ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም) እስከ ቅዳሜ (ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም) ባሉት ቀናት ውስጥ ተማሪዎችን በአካል በመያዝ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም (ሸሚዝ፣ ሱሪ ወይም ቀሚስ) መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

​📍 ቦታ፦ በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ
⏰ የአገልግሎት ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት

​📞 ለተጨማሪ መረጃ፦
​0912 85 08 39
​0982 49 81 30

​በጌምድር አካዳሚ


በጌምድር አካዳሚ dan repost
​📢 ለበጌምድር አካዳሚ ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ

​ርዕስ፦ ስለ 2019 ዓ.ም ምዝገባ ማጠናቀቅ፣ የመሸኛ አሰጣጥ እና የአመታዊ እረፍት አስፈላጊ መረጃ

​የበጌምድር አካዳሚ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ከ100% በላይ መጠናቀቁን እንገልጻለን። በመሆኑም የተቋማችን ሰራተኞች በሙሉ አመታዊ እረፍት የሚወጡ በመሆኑ፣ የመሸኛ አገልግሎት ለምትፈልጉ ወላጆችና ተማሪዎች የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች በጥንቃቄ እንድትከታተሉ እናሳስባለን።

​1. የመሸኛ አገልግሎት የሚሰጥባቸው የመጨረሻ ቀናት
​ተቋማችን ከሰኔ 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ መሸኛ ሲያስተናግድ የቆየ ሲሆን፣ በዚህ አመት የመጨረሻ የመሸኛ መስጫ ቀናት የሚከተሉት ብቻ ናቸው፦
​ማክሰኞ፡ ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም
​ረቡዕ፡ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም


​⚠️ ማሳሰቢያ፦ በእነዚህ ቀናት መጥታችሁ መሸኛ መውሰድ ያልቻላችሁ ወላጆች፣ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉት በመስከረም 2019 ዓ.ም ትምህርት በሚከፈትበት ጊዜ ብቻ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

​2. ለ6ኛ ክፍል ክልላዊ ተፈታኞች (የነበራችሁና ውጤት የምትጠብቁ)
​ምዝገባ ላላጠናቀቃችሁ፦
ምዝገባችሁን ከዛሬ ማታ ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ረፋዱ 5:00 ሰዓት ድረስ ብቻ እንድታጠናቅቁ ሲስተም የተከፈተላችሁ መሆኑን እናሳስባለን።

​መሸኛ ለምትፈልጉ፦ መሸኛ ለመውሰድ ስትመጡ የክልላዊ ፈተና ውጤታችሁን ፕሪንት (Print) አድርጋችሁ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል።

​3. ለ8ኛ ክፍል ክልላዊ ተፈታኞች
​የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ መሸኛ የምትወስዱ በመሆኑ፣ ስትመጡ የፈተና ውጤታችሁን ፕሪንት (Print) አድርጋችሁ ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ።

​4. ከKG እስከ 5ኛ እና ከ7ኛ ወደ 8ኛ ክፍል ለተዘወራችሁ
​የምዝገባ ቀን አልፎባችሁ መሸኛ ለመውሰድ የምትመጡ ወላጆች፦ የተማሪውን 2 (ሁለት) ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል።

​📌 አስቸኳይ ማሳሰቢያ፦
የተሰጡት ቀናት ለሁሉም ተማሪዎች እኩል የሚያገለግሉ በመሆኑ፣ ያለ እንግልት በወቅቱ መረጃዎችን እና መሸኛዎችን ይዛችሁ እንድትሄዱ አጥብቀን እንመክራለን። ከሐምሌ 29 በኋላ ሰራተኞቻችን በሙሉ አመታዊ እረፍት የሚወጡ በመሆኑ አስተናጋጅ እንደማይኖር ከወዲሁ እናሳስባለን።

​ከአክብሮት ሰላምታ ጋር!

በጌምድር አካዳሚ


በጌምድር አካዳሚ dan repost
ሐምሌ 23 እህት ወንድም ያላቸው ከኬጂ -6ኛ ክፍል አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ነገ በፈተና ይመለመላሉ የምታስመዘግቡ ወላጆች አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪውን የ2018ዓ.ም የትምህርት ካርድ እና እስክርቢቶ ይዘው ይምጡ ፈተናውን ያለፈ ተማሪዎች እዛው ላይ ምዝገባቸው ስለሚጠናቀቅ የልጆች 2ፎቶ የወላጅ 1ፎቶ ይዘው ቢመጡ መልካም ነው።


በጌምድር አካዳሚ dan repost
ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ይጠናቀቃል ዛሬ ያላስመዘገበ ከተቋማችን መቀጠል እንዳልፈለገ በመገንዘብ አዲስ ተማሪ የምንተካበት መሆኑን እንድትረዱ እናሳስባለን።

መሸኛ መውሰድ የምትፈልጉ ወላጆች የተማሪ 2 ጉርድ ፎቶ እና የመሸኛ ክፍያ 200 ብር ዛሬውን መጥተው መውሰድ ይችላሉ ከዛሬ ውጭ የሚያስተናግድ እንደማይኖር ከወዲሁ እናሳስባለን።


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የመጨረሻ የተላለፈ የምዝገባ መልዕክት


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ዛሬን ጨምሮ 2 ቀን ቀረው

ሐምሌ 19
ሐምሌ 20


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የተማሪዎች የደንብ ልብስ በተመለከተ


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ 3 ቀን ቀረው
ሐምሌ 18
ሐምሌ 19
ሐምሌ 20

የበጌምድር አካዳሚ ክቡራን ወላጆች/አሳዳጊዎች፤
አሁን ባለው ሁኔታ ዛሬ ሐምሌ 18 መሆኑ ይታወቃል፡፡ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 20 ሙሉ በሙሉ የሚያልቅ ስለሆነ፤ ነባር ተማሪዎች ምዝገባው ሳይጠናቀቅባቸው እንዲጨርሱ ክፍያ መክፍያ ኮዳቸውን ተጠቅመው ቅዳሜ፣ እሁድ ለሊትም ነው ሳይሉ በቀራቸው ቀን ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ በጥብቅ እናሳስባለን። የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ተፈታኞችም ቢሆኑ ውጤት እስኪለቀቅ ምዝገባቸውን አጠናቀው መቆየት ይችላሉ፤ ነገር ግን ሌላ ተጨማሪ ቀን እንደማይሰጥ እናሳስባለን።
እንደ አካዳሚያችን እምነት 100% ተማሪዎቻችን እንደሚያልፉ ነው፤ የማይሳካለት ተማሪ እንኳን ቢኖር ምዝገባው ለ6ኛ ክፍል እንደሚሆንላች እንገልፃለን።
ምዝገባው ቀን ተጠናቆ ሲስተም ከዘጋ በኃላ የትኛውንም ምክንያት እንደማንቀበልና መሸኛ በመስጠት እንደምናሰናብት እንዲሁም በወቅቱ ላልተመዘገቡ ተማሪዎች ቦታውን አዲስ ተማሪ የምንቀበልበት መሆኑን አጠንክረን እናሳስባለን።

አካዳሚው


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ 4 ቀን ቀረው
ሐምሌ 17
ሐምሌ 18
ሐምሌ 19
ሐምሌ 20


በጌምድር አካዳሚ dan repost
​📢 የበጌምድር አካዳሚ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ እና ወሳኝ ማስታወቂያ

​ክቡራትና ክቡራን ወላጆች/አዳጊዎች፤

​በቅድሚያ ለኬጂ 1 (እድሜያቸው 4 ዓመት የሞላቸው) ከአካዳሚው እህት/ወንድም ያላቸው ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም 129 ተማሪዎችን በመመዝገብ የመጀመሪያው ምዕራፍ ምዝገባ በስኬት ተጠናቋል።

​የቀጣይ ቀናት የምዝገባ ጊዜ ሰሌዳ እና አስፈላጊ መረጃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በመሆናቸው በጥንቃቄ እንድትከታተሉ እናሳስባለን።

​1️⃣ የኬጂ 1 አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ (እህት/ወንድም የሌላቸው)

​ቀን፦ ነገ ሐምሌ 16 / 2018 ዓ.ም
​ሁኔታ፦ ባሉን ውስን ቦታዎች ከአካዳሚው እህት/ወንድም የሌላቸው እድሜያቸው 4 ዓመት የሞላቸው አዲስ ህፃናት ምዝገባ ይከናወናል።

​⚠️ ማሳሰቢያ፦ ቦታው በጣም ውስን በመሆኑ እና ሲሞላ ወዲያውኑ የሚዘጋ በመሆኑ አቀድመው እንድታስመዘግቡ እንመክራለን። ህፃናት በአካል መገኘት አለባቸው።

​2️⃣ ከኬጂ 2 እስከ 8ኛ ክፍል (የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ)
​ነባር ተማሪዎች (ከሐምሌ 14 ጀምሮ የተጀመረ)፦
​በCBE Mobile Banking / USSD (*889#) በኩል በርካታ ወላጆች እየተመዘገባችሁ ትገኛላችሁ።

​🔴 የምዝገባ ማጠቃለያ ቀን፦ ሐምሌ 20 / 2018 ዓ.ም

​⚠️ ማሳሰቢያ፦ የዲጂታል ምዝገባ ሲስተሙ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ላይ ሙሉ በሙሉ ይዘጋል። ቀኑ ካለፈ በኋላ የትኛውንም ምክንያት የማንቀበል መሆኑን ከአክብሮት ጋር እንገልጻለን።

​አዲስ ተማሪዎች (ከኬጂ 2 እስከ 8ኛ ክፍል)፦
​ሲስተሙ ለነባር ተማሪዎች ሐምሌ 20 እንደተዘጋ፣ በነገው ዕለት (ሐምሌ 21 እና 22) ክፍት ቦታዎችን የመለየት ሥራ ተከናወኖ ከሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ክፍት ቦታዎች አዲስ ተማሪዎችን አወዳድረን የምንቀበል ይሆናል።

​📲 የክፍያ እና የምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ (CBE Mobile Banking)
👉​ወደ CBE Mobile Banking App ይግቡ (PIN ቁጥርዎን ያስገቡ)።
👉​Pay for የሚለውን ይምረጡ።
👉​ከዝርዝሩ ውስጥ School Fee የሚለውን ይምረጡ።
👉​Henon School Payment የሚለውን ይምረጡ።
👉​Enter Reference Number በሚለው ቦታ ላይ፦
​ለነባር ተማሪዎች፦ የልጅዎን የመለያ ቁጥር (ID Number) ያስገቡ።
​ለአዲስ ተማሪዎች፦ በእለቱ የሚሰጣችሁን አዲስ Reference Number ያስገቡ።
​Continue ሲሉ የልጅዎ ስም እና የሚከፈለው መጠን ይመጣል፤ ትክክለኛነቱን አረጋግጠው ክፍያውን ያጠናቅቁ።

​(በUSSD ለማጠናቀቅ *889# ደውለው step-by-step ትእዛዙን መከተል ይችላሉ)


​📞 ለተጨማሪ መረጃ እና እገዛ፦ ከጥዋቱ 3:00 እስከ 9:00 ብቻ የሚደውሉባቸው
​📱 ስልክ፦ 0998930393 | 0959614225 | 0959614870

​🔗 የቴሌግራም ዋና ቻናል፦ https://t.me/Begaimeder2008

​🔗 የፋይናንስ እና ክፍያ መመሪያ ቻናል፦ https://t.me/FinanceBegaimeder

​በጌምድር አካዳሚ

የላቀ የትምህርት ጥራት እና የእድገት ማዕከል!


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የ2019 ዓ.ም የትራንስፓርት ተጠቃሚዎች የክፍያ ተመን በየፌርማታው


በጌምድር አካዳሚ dan repost
የ2019 ዓ.ም ወርሃዊ ክፍያ እና የመመዝገቢያ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.