በሰፈሩ ታይቶ የማይታወቅ ለቅሶ እየተለቀሰ ነው። ከሞተች ሁለት ቀን አልፏታል የሚሰናበተው ሰው ስለበዛ ነው ቀብሯ ወደ ሶስተኛ ቀን የተሻገረው። እናቷ፥ አባቷ፥ ዘመደቿ፥ እልፍ ጓደኞቿ ባትቀበር ደስ እንደሚላቸው ያስታውቃሉ። እንደውም ንሰሀ አባቷ ተቆጥተው ነው ዛሬ ራሱ ለቀብር የተሰማሙት።
ቀብሯ ላይ ሆነን የሚያስተምሩትን ቄስ ለቀስተኛው አላቆም ብለው አስቸግረዋቸው ትንሽ ነገር ብለው ወረዱ።
የሚያስተባብሩት ቄስ ወደ እኔ ዞረው "ባለቤቷ አንተ ነህ አይደለ?" አሉኝ "አዎ" አልኳቸው "በል ያዘጋጃችሁትን የህይወት ታሪኳን አምጡ" አሉን። ክው ብለን ደነገጥን
ራሷ ፅፋ ያዘጋጀችውን የህይወት ታሪኳን እቤት ረስተነው መጣን!!! መደንገጤን ያዩ አጠገቤ የነበሩ አሮጊት "ኤድያ የምን የህይወት ታሪክ ነው?! እሷስ ጥላው ሄዳ የለም እንዴ፥ ደግሞስ ምን የተለየ ነገር ይኖረዋል በእንትን አመተምህረት ተወለደች፥ ተማረች፥ አገባች፥ ፥ወለደች፥ ሞተች ይኸው ነው" አሉ
ይኸው ነው?
ቀልድ ሊመስል ይችላል ግን ይኼ ነበረ ህልሟ ረጅም የህይወት ታሪክ አንዲኖራት። ለቀብር የመጡ ሰዎች አዝነው ሳይሆን ተደስተው ተነሳስተው እንዲመለሱ። ለካ እንደዚህም መሆን ይቻላል እንዲሉ ነበረ ፍላጎቷ።
ምናልባት ቀብሯ ላይ የሚነበብውን የህይወት ታሪኳን ራሷ የፃፈች የመጀመሪያም የመጨረሻም ሰው ልትሆን ትችላለች። መጀመሪያ እንደዚህ ማድረግ እንደምትፈልግ ስትነግረኝ ቀልዷን ነበረ የመሰለ፥ ከዛ ግን እያንዳንዱን ስኬቷን በስነስርዓቱ መዝግባ ማዘጋጀት ስትጀምር እንዳመረረች ገባኝ።
ሁሉም ነገር የተዘጋባት ሲመስላት ተስፋ ልትቆርጥ ስትል የሚያዘረታት ይሄ ለቀብሯ የሚነበበው ወረቀት ነበረ። መፅሀፍ ባሳተመች ቁጥር አንድ ልጅ ከሱስ ባላቀቀች ቁጥር...
ብቻ ግን አንዳንዴ ምን እንደሚያበረታን ሳስበው ይገርመኛል። ለሰው ቢወራ ሊያስቅ የሚችል ነገር እሷን ግን ከነበረችው የበለጠ ለሰው አሳቢ ደግ ለተቸገረ የምትደርስ አደረጋት።
ተራ ደራሲ ነበረች ከዛ ግን ቀስበቀስ ፅሁፎቿ ተፅዕኖ መፍጠር ጀመሩ ፥ እየደወሉ የሚያመሰግኗት በእሷ ፅሁፎች ችግሮቻቸውን እንደፈቱ የሚነግሯት ሰዎች ጨመሩ።
ግን ይሄን ሁሉ የለፋችበትን... እኔ ረስቼው መጣሁ። ይሄ ወረቀት መታተምም ካለበት ብቻ የሆነ መንገድ ሰው ጋር እንዲደርስ ማድረግ አለብኝ የሚል ቁጭት አንገበገበኝ።
ለነገሩ በብዙ ከመብከንከን ያተረፈኝ ነገር ቢኖር ይሄን ጉድ ቀና ብላ አለማየቷ ነው።
https://t.me/justhoughtsss