መጣጥፍ🖋


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ከደመናዉ በታች ሁሉም ያልፋል::

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ምልከታዎቼ- ክፍል ㄱ


ብንሄድ ይሻለናል....

ሰዉ ለካ ወዶ አይደለም ከዚች መከረኛ ዓለም ከሚወዱት ከሚወዳቸዉ መለየትን የሚመኘዉ... ዝም ብሎ ደስ ስላለዉ እኮ ራሱን አያጠፋም... የሚገባበት የሚያደርገዉ ቢያጣ እንጂ... ማን ሞቱን ይመኝ ነበር...

በህይወት ካሉ ዉሳኔዎች ሁሉ ራስን ለማጥፋት መወሰን እጅግ ከባድ ይመስለኛል...
በጣም ከባድ ዉሳኔ ነዉ... በራስ ላይ... በሚወዱት ላይ ጨክኖ ሳይሰናበቱ... ሄድኩ ሳይሉ መሄድ... ዳግም እንደማይገናኙ እያወቁ ቆርጦ መቼም ሊታረም ሊስተካከል የማይችል... ሁለተኛ እድል የሌለዉ ዉሳኔ መወሰን ነዉ::

እስኪ አስቡት ራስን ማጥፋትም ልክ እንደሌሎች ዉሳኔዎች ሁሉ ዳግመኛ እንደ አዲስ ታስቦበት ጥቅምና ጉዳቱ ታይቶ...ተለክቶ የሚወሰን ቢሆን...?

ስንት ነፍስ ወደ ምድር መልሱኝ ትል ይሆን? ስንቷስ በወሰነችዉ ዉሳኔ ተፀፅታ ረግማት ወደ ሄደቻት ምድር ትመለስ ይሆን?

ማን ያዉቃል... መቼም አልመለስም ብላስ በዉሳኔዋ የምትጸና የትኛዋ ነፍስ ትሆን?

በዛ ያለዉ ስቃይ ከዚህ ይብስ ይሆን?(ይህ ጥያቄ ሀይማኖተኞችን አይመለከትም)

ምናልባት... እንደዉ ለምናልባቱ ራሳችንን ከማጥፋታችን በፊት ከኛ የባሰ ስቃይ ዉስጥ ያሉ ሰዎችን ብናይ እንረጋጋ ይሆን... ሀሳባችንንስ ያስለዉጡን ይሆን?

እንደዉ... ለኛ የከበደንን ችግር የሚያቃልልን መልአክ ልንለዉ የሚቃጣን ሰዉ በህይወታችን ቢከሰትስ...?

ሁሉም ምልከታዎቼ ከመላምት አልዘለሉም ምክንያቱም ራሱን ያጠፋዉን ሰዉ አግኝቼ ልጠይቀዉ ስላልቻልኩ...

የመጨረሻ ልላችሁ የምፈልገዉ ነገር ግን ራስን ማጥፋት የሚታሰበዉን ያህል ቀላል አይደለም... በጣም ጠንካራ መሆንን ይጠይቃል ምክንያቱም በህይወታችን ዉስጥ እጅግ ከባዱ እና በራሳችን ላይ ደግሞ በጣም ጭካኔያዊ የሆነ ዉሳኔ ስለሆነ...

ለኔ በጣም ጀግና የምለዉ ሰዉ ግን በህይወቱ ከባድ ጊዜ ዉስጥ እያለ ራሱን ለማጥፋት ያላሰበ አልላችሁም... ይህ ሊሆን የሚችልበት እድል ጠባብ ነዉና... ግን ራሱን ለማጥፋት ወስኖ ሀሳቡን የቀየረ በማንኛዉም ምክንያት ሊሆን ይችላል ራሱን ያበረታ ያ ሰዉ ለኔ ጀግና ነዉ!!!


ለሚለወጥ ቀን የማይለወጥ ዉሳኔ....💔💔

ፀጋ🖋

https://t.me/memoir21


AK SIP Supervision Group 📚 dan repost
አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል።

አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ።

ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ።

ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት።

አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት !

እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት ከሱሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።

አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል።

በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree centigrade ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....

"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው?" ስትሉ ....

አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣
ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣
የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣
እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !

አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት:-

አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።

ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል።

ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው።

አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው።

አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን።

የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም።

የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው።

ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ።

ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው።

❤️🙏❤️ ውብ ቅዳሜ ❤️🙏❤️

     ┈┈••✦✦••┈┈┈
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🍁 Join : @Aksipspg
🍁 Join : @Aksipspg
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
         ┈┈┈••✦✦••┈┈┈


ልባም ሴት...?

ለእናንተ ልባም ሴት ማናት? በምንስ እንዴትስ ትገለፃለች...?

https://t.me/memoir21


Thoughts dan repost
ምክር አልፈልግም። "ሰው እንዴት የጎዳውን ሰው ይፈልጋል" የሚል ማሽሟጠጥም እንደዛው። እውነቱን ማወቅም አልፈልግም ምክንያቱም አውቀዋለኋ። የትኛውም አመክንዮ ጥፋቱን ማቃለል እንደማይችል ማመንም አልፈልግም። ልቤንም ተይ ይበቃናል በቃ ማለትም አልፈልግም። ምንድነው የምፈልገው ይቅርታ መባል? ይቅርታ ማድረግ? ክህደቱን መርሳት? ራሴን መውቀስ ማቆም? ወይስ መናፈቅ ማቆም? እንጃ ብቻ ግን ሰላሜ ናፈቀኝ እንደው ይቺን ጥንጥዬ ልቤን ሀይ የሚላት ይጥፋ?!


Thoughts dan repost
የአንዳንድ ሰው እንክብካቤ ደካማ አድርጎ ያስቀረናል የአንዳንድ ሰው ቸልተኝነት ደግሞ ይበልጥ ያበረታናል።ምናልባት ድርጊቱ ሳይሆን ልዩነቱን የሚያመጣው እኛ የመለስንበት መንገድ ነው።


በሰፈሩ ታይቶ የማይታወቅ ለቅሶ እየተለቀሰ ነው። ከሞተች ሁለት ቀን አልፏታል የሚሰናበተው ሰው ስለበዛ ነው ቀብሯ ወደ ሶስተኛ ቀን የተሻገረው። እናቷ፥ አባቷ፥ ዘመደቿ፥ እልፍ ጓደኞቿ ባትቀበር ደስ እንደሚላቸው ያስታውቃሉ። እንደውም ንሰሀ አባቷ ተቆጥተው ነው ዛሬ ራሱ ለቀብር የተሰማሙት።

ቀብሯ ላይ ሆነን የሚያስተምሩትን ቄስ ለቀስተኛው አላቆም ብለው አስቸግረዋቸው ትንሽ ነገር ብለው ወረዱ።

የሚያስተባብሩት ቄስ ወደ እኔ ዞረው "ባለቤቷ አንተ ነህ አይደለ?" አሉኝ "አዎ" አልኳቸው "በል ያዘጋጃችሁትን የህይወት ታሪኳን አምጡ" አሉን። ክው ብለን ደነገጥን

ራሷ ፅፋ ያዘጋጀችውን የህይወት ታሪኳን እቤት ረስተነው መጣን!!! መደንገጤን ያዩ አጠገቤ የነበሩ አሮጊት "ኤድያ የምን የህይወት ታሪክ ነው?! እሷስ ጥላው ሄዳ የለም እንዴ፥ ደግሞስ ምን የተለየ ነገር ይኖረዋል በእንትን አመተምህረት ተወለደች፥ ተማረች፥ አገባች፥ ፥ወለደች፥ ሞተች ይኸው ነው" አሉ

ይኸው ነው?

ቀልድ ሊመስል ይችላል ግን ይኼ ነበረ ህልሟ ረጅም የህይወት ታሪክ አንዲኖራት። ለቀብር የመጡ ሰዎች አዝነው ሳይሆን ተደስተው ተነሳስተው እንዲመለሱ። ለካ እንደዚህም መሆን ይቻላል እንዲሉ ነበረ ፍላጎቷ።

ምናልባት ቀብሯ ላይ የሚነበብውን የህይወት ታሪኳን ራሷ የፃፈች የመጀመሪያም የመጨረሻም ሰው ልትሆን ትችላለች። መጀመሪያ እንደዚህ ማድረግ እንደምትፈልግ ስትነግረኝ ቀልዷን ነበረ የመሰለ፥ ከዛ ግን እያንዳንዱን ስኬቷን በስነስርዓቱ መዝግባ ማዘጋጀት ስትጀምር እንዳመረረች ገባኝ።

ሁሉም ነገር የተዘጋባት ሲመስላት ተስፋ ልትቆርጥ ስትል የሚያዘረታት ይሄ ለቀብሯ የሚነበበው ወረቀት ነበረ። መፅሀፍ ባሳተመች ቁጥር አንድ ልጅ ከሱስ ባላቀቀች ቁጥር...

ብቻ ግን አንዳንዴ ምን እንደሚያበረታን ሳስበው ይገርመኛል። ለሰው ቢወራ ሊያስቅ የሚችል ነገር እሷን ግን ከነበረችው የበለጠ ለሰው አሳቢ ደግ ለተቸገረ የምትደርስ አደረጋት።

ተራ ደራሲ ነበረች ከዛ ግን ቀስበቀስ ፅሁፎቿ ተፅዕኖ መፍጠር ጀመሩ ፥ እየደወሉ የሚያመሰግኗት በእሷ ፅሁፎች ችግሮቻቸውን እንደፈቱ የሚነግሯት ሰዎች ጨመሩ።

ግን ይሄን ሁሉ የለፋችበትን... እኔ ረስቼው መጣሁ። ይሄ ወረቀት መታተምም ካለበት ብቻ የሆነ መንገድ ሰው ጋር እንዲደርስ ማድረግ አለብኝ የሚል ቁጭት አንገበገበኝ።

ለነገሩ በብዙ ከመብከንከን ያተረፈኝ ነገር ቢኖር ይሄን ጉድ ቀና ብላ አለማየቷ ነው።

https://t.me/justhoughtsss


ምላሽ በሌላቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ መኖር አድክሟቹ ያዉቃል? እንዳለ የማይገልፅ እንደሄደም ማያሳይ ሁኔታ ላይ መሆን፥ ስለሀሳብ እያሰቡ ሌላ ሀሳብ መጨመር፥
.
.
ስሜት ስሜትን እየወለደ ዋኝተዉ መዉጣት የማይችሉት ጥልቅ ወንዝ ዉስጥ ሰዉን ገፍትረን ከምንከት ስንወድ፥ስንጠላ፣ ስንናደድ ስንደሰት፥ሲከፋን ሲደክመን ብንናገርስ፥ምናልባትም ብዙ ተጀምረዉ ያልተጨረሱ ገፆችን መዝጋትን እንችል ይሆናል።

✍ጥንቅሻ

https://t.me/frindship_guadegint


አንድ ሰው በ 22 ዓመቱ ተመርቆ  ነገር ግን ጥሩ ስራ ከማግኘቱ በፊት 5 አመታትን ይጠብቃል። 

አንዳንዱ በ 25 ዓመቱ የአንድ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ይሆንና በ 50 አመቱ ይሞታል። 
 
ሌላው በ 50 ዓመቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ እስከ 90 ዓመት ድረስ ይኖሯል። 

አንድ ሰው አሁንም ትዳር ሳይመሰርት ከእሱ ጋር አብሮ የተማረ አብሮ አደግ ጓደኛው የሆነ ሰው ግን አያት ሆኖ ይሆናል። 
 
ኦባማ በ 55 አመቱ ከፕሬዚዳንትነት ጡረታ ሲወጣ፤ ትራምፕ በ 70 አመቱ ፕሬዝዳንት ሆኗል። 

በዚህ ዓለም ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የራሱ የጊዜ  ክልል ላይ ተመስርቶ ይሰራል።

በዙሪያህ ካሉ ሰዎች አንዳንዶቹ ከፊት የቀደሙህ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከኋላህ የቀሩ ሊመስልህ ይችላል። 

ነገር ግን ሁሉም የየራሱን ሩጫ፣ በራሱ ጊዜ እየሮጠ ነው።
 
የቀደሙህ በመሰሉህ ሰዎች አትቅናባቸው! 

የቀደምካቸው በመሰለህ ላይ ደግሞ እራስህን አትኮፍስ!

እነሱ በራሳቸው የጊዜ ክልል ውስጥ ናቸው፣ አንተም እንዲሁ በራስህ የጊዜ ክልል ውስጥ ነህ!
 
ስለዚህ ዘና በል!

ከማንም ወደኋላ አልቀረህም፤ አልቀደምክምም!
መልካም ዕለተ ሰኞ 🙏🥰🙏

https://t.me/frindship_guadegint


ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 dan repost
የነገ ትናንት ላይ ናችሁ አይደል....ዛሬ ላይ ማለቴ ነው...እኔ ግን የዛሬ ትናንት ላይ ነኝ....

ነገ....
ዛሬ....
ትናንት....

የ"ነገ" እና የ"ዛሬ" ሆሄያት አጥረው የ"ትናንት" ሆሄያት ለምን ረዘሙ....ነገ እና ዛሬ በሁለት ፊደል ስለተዋቀሩ አልያም ትናንት የሚለው ቃል ላይ አራት ፊደላት ስላሉ ነው ትናንቴ የሚከተለኝ...ነገዬ አጥሮ ነው ያልክ የራቀኝ...ቆይ ዛሬዬስ....

ከራሴ ጋር ጥልቅ ጭውውት ይዣለሁ...ትናንቴ ሙጫ ሆኖብኛል...የረሳሁት ሲመስለኝ መልኩን ቀይሮ አለሁ  ይለኛል....ትናንት ጠባሳ ሆኖ ያለቀ ነገር ነው ብዬ ሳልጨርስ  እንደ አዲስ ይመረቅዛል...ጠባሳ ያማል እንዴ...
...ከመቼ ጀምሮ...እንጃ ብቻ ያመኛል...

ችግሩ ጠባሳ ያልኩት ትናንቴ ገና ጠፈፍ ያላለ ቁስል መሆኑ ላይ ነው...ለዛ ነው በተነካ ቁጥር የሚያመኝ...


መች ጨረስኩ...አሁንም ጭውውቴን ቀጥያለሁ..."እንደዛ ባይሆን ኖሮ እንዲህ አይሆንም ነበር" እላለሁ ለሆነ ነገሬ...ቁስሉ እንደ አዲስ መድማት ይጀምራል...የነገ ትናንት ላይ ነኝ....ዛሬ ላይ ማለቴ ነው...ግን ጭንቅላቴ ዛሬ ላይ ሳይሆን የዛሬ ትናንት ላይ ነው...እናንተ እኮ አታፍሩም..."move on ምንድን ነው...በቃ አለፈ እኮ ..."...ትሉኝ ይሆናል...እሱ መች ጠፋኝ...ማለፉን ጠንቅቄ አውቃለሁ...ችግሩ ምን አድርጎኝ ነው ያለፈው የሚለው ነው....


የደማው ቁስሌን ከማከም ይልቅ "ደማባት እኮ ስታሳዝን" ብሎ የሚያልፈኝ በዛ....ደሜ እንዳይነካው ደሜን ዘሎ የሚያልፍም አልጠፋም...ቁስሌ መሽተት ሲጀምር እንዳይሸታቸው አፍንጫቸውን ይሸፍናሉ....አንዳንዶቹም አይናቸውን...ያኔ ነው የገዛ ቁስሌን ለማከም የሰነፍኩት...ያኔ ነው ለራሴ ቁስል አይኔን የሸፈንኩት...ሲቆይ እኔም እንደ እነርሱ አፍንጫዬን ሸፈንኩ...ሽታው ይረብሸኝ ጀመር...ትናንቴን አለባበስኩት....ንፋስ እንዳይገባው ጠፍሬ አሰርኩት...ለዛ ነው ዛሬ ላይ ሳይሆን የዛሬ ትናንቴ ላይ የቀረሁት...

የታፈነ ቁስል በእንጨት እስኪነካ አይጠብቅም...በትንሽ ሽንቁር ውስጥ ሽው የምትል ንፋስ ትበቃዋለች...ያማል...በጣም ያማል...ያኔ ነው ያሰርኩት ቁስሌን ማደንዘዝ የጀመርኩት...."ለምን ቆይ...አንቺ እኮ ራስሽን ማከም ትችዪ ነበር...ልክ አልሰራሽም..."....ይላሉ ገና ደከመኝ ከማለቴ... በጨርቅ የተሸፈነ አፍ ለወሬ ሲሆን ይበረገዳል....ሁሉም አስተያየት ሰጪ ይሆናል...ሁሉም አልቃሽ ይሆናል...አይናቸውን እንዳልጨፈኑ አይናቸውን ከፍተው ያነባሉ...

...ስለ እነርሱ ማሰብ ይብስ ነፍሴን ያቀጭጫታል....

ስለ እነርሱ ትቼ ስለ ሆሄያቱ ባሰላስል ሳይሻል አይቀርም ብዬ ወደ ቀደመው ነገሬ ተመለስኩ...

"ትናንት"....ላይ ሆሄያት በዙ..."ዛሬ"...እና "ነገ" ላይ ግን አነሱ....ለዛም ነው ትናንቴ የተጣበቀብኝ የሚል ድምዳሜ ላይ ከመድረሴ አንድ የቴሌዥጅን ማስታወቂያ  ከጭውውቴ አባነነኝ.......

"ከብዛት ጥራት እንዲሉ የተለያዩ  እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ...."....እያለ የሚጀምር ማስታወቂያ ነው...."ከብዛት ጥራት...."....ጋር ቀረሁ....ትናንት ሆሄው ስለበዛ "ጌታ" ዛሬ ደግሞ ሆሄው ስላነሰ "ባሪያ" አይደሉም አልኩት ለራሴ....


አንዳንዴ ፈጣሪ በምን በኩል አድርጎ ወደ እቅፉ እንደሚመልስ አይታወቅም አይደል....አዎ ካልጠራ ትናንቴ የጠራው ዛሬን ሊያኖረኝ ቢሆንስ... በቁስሌ በኩል አይቶኝ ቢሆንስ.....የፈራሁት ቁስሌን እርሱው እየፈታው ቢሆንስ.....በራሱ መንገድ እያደሰኝ ቢሆንስ...


እንዲያድሰኝ መፍረስ ግድ ከሆነስ....እንኳን አመመኝ....😊




✍Shewit




https://t.me/shewitdorka


ለማሰብ የከበዳችሁን ስቃይ ኖሬ ማለፌን አትዘንጉብኝ
ያሳለፍኳቸዉ ከባድ ጊዜያት ሆደ ባሻ ቢያደርጉኝም አትፍረዱብኝ
ዝም ብላችሁ ከዝምታዬ ጋር እስኪ ተዉኝ


💔 ፀጋ🖋 💔


ምልከታዎቼ - ክፍል ㄷ


ተሰብራችሁ ታዉቃላችሁ...ከሰዉ ተሸሸሽጋችሁ... ሳጋችሁ እንዳይሰማ አፋችሁን አፍናችሁ...ስቅስቅ ብላችሁ አልቅሳችሁ ታዉቃላችሁ?

በኔ ቦታ ነበራችሁ? ልትሆኑስ ትችላላችሁ? በሉ መልሱልኝ እንጂ...በሉ ተናገሯ...

"ያልፋል" ማለትማ ቀላል... ግን እስኪያልፍ እንደሚያለፋ ማን በነገራችሁ... በርቺ...ይቺ ምን አላት...ችግሮችሽን ሁሉ አልፈሽ እዚህ ደርሰሽማ ተይ እንጂ...ማለትማ ቀላል...

ግን ይህንን ሁሉ ስቃይ ችዬ ዛሬ ላይ በህይወት መገኘቴ በራሱ የአምላክ ተአምር መሆኑን ማን በነገራችሁ!

'ጠንካራ'...'የልጅ አዋቂ' የሚል ስያሜ ስትሰጡኝ ግን ምኔን ተመልክታችሁ ይሆን? በብዙ መፈተኔን ወይስ ስቃዬን ሸሽጌ ፊታችሁ መቆሜን...ምኔን አይታችሁ ይሆን?

ግን አስባችሁት ታዉቁ ይሆን? ለማሰብ እንኳን የከበዳችሁ ስቃዬን 'ጠንካራ' በሚባል ጠንካራ መሳይ ቃል ለመሸፈን እየሞከራችሁ እንደሆነ?
'የልጅ አዋቂ' እያላችሁ እንደ ልጅ መኖር የሚገባኝን ልጅነቴን እንዳሳጣችሁኝ?
ታዉቁ ይሆን...?


እኔ ግን እላለሁ እባካችሁ ከተቻላችሁ...አቅሙ ካላችሁ...'ጠንካራ' 'ከብረት የተሰራች' የምትሉኝን ነገር አቁሙ... በቃ ተዉኝ...ለችግሬ መፍትሄ መፈለግ ቢያቅታችሁ እንኳን እስቲ በህይወታችሁ ለአንዴ ተዉኝ...ችግሮቼን ሁሉ ለኔ ተዉልኝ...እባካችሁ ተዉኝ...

ቢያንስ ሸክሜን ባታቀሉልኝ እንኳን አታክብዱብኝ...የተጎዳዉ ሆኜ ሳለዉ 'ደህና ነሽ' እያላችሁ ዉስጥዉስጡን አትግደሉኝ::

ሰዉ መሆኔን...እኔም ልክ እንደ እናንተ ስሜት እንዳለኝ...
እንደሚከፋኝ🖤...እንደሚያመኝ❣...ተረዱልኝ💔

❤️‍🩹አትርሱኝ💔


ፀጋ🖋

https://t.me/memoir21


ምልከታዎቼ - ክፍል ㅈ

አንዳንዴ ግን መጥፎ አጋጣሚዎች ከሚጎዱን በላይ "እንዲህ ሆንኩ" "እንዲህ ደረሰብኝ" ብለን የምንነግረዉ ሰዉ ከአጠገባችን ማጣት እጅግ ይከብዳል...

ስሜትን ዉስጠትን የሚረዳ ወዳጅ ማጣት በጣም ይከብዳል...

ሰዉ ሆኖ ሰዉን መራብ በጣም ያስከፋል😥

ከደረሰባችሁ ችግር በላይ ሁሉንም በዉስጣችሁ አምቃችሁ መያዛችሁ ያቆስላችኋል...

ከሁሉም በላይ የሚከብደዉ ግን "ካለመኖር የማይሻለዉ መኖር" ነዉ!

"ጌታ ሆይ ማንም የለም ከጎኔ ብቻዬን ነኝ!" ብላችሁ እንዳታማርሩ አሉ ከጎናችሁ...አሉ ሁሌም አሉ...ጭንቀትሽ ምንድነዉ ንገሪኝ እያሉ...ሲከፋችሁ ህመማችሁን መተንፈስ ሲያሰኛችሁ ሮጣችሁ የምታዋዯቸዉ...ግን ችግሩ የእናንተ ህመም ተሰምቷቸዉ ያውቃል ወይ? ነዉ:: ገብቷቸዋል ግን የቁስላችሁ ጥልቀት...
እህ...ብሎ ለማዳመጥማ ዛፉም አጠገቡ ሄዳችሁ ብትጮሁ ይሰማል...

አንዳንዴማ በቁስላችሁ እንጨት ሊሰዱ የሚሞክሩም አሉ...አንዳንዶቹ ደግሞ ምን እንደሚባል የማያውቁ የእነሱ "አይዞሽ!" የምትል ቃል ብቻ ስንት ተአምር መስራት...ስንት ሸክም ማቅለል እንደምትችል የማያውቁ...አሉ...ብቻ አሉ...ኖረዉም እንደሌሉ የሚቆጠሩ...


ሰዉ እያለን የለንም ከማለት ይሰዉረን!!!

ፀጋ🖋

https://t.me/memoir21




Thoughts dan repost
"ክብደት መቀነስ ይፈልጋሉ፤ ወይስ የተስተካከለ አቋም?ስለዚህ መፍትሄው ቀላል ነው። ወደ ሞኬ ስፖርት ቤት ጎራ ይበሉ ፤ ሁሉንም በአይነቱ በተለየ አቀራረብ ያገኛሉ።" የሚል ትልቅዬ ባነር ሰፈራችን መውጫ ላይ ተሰቅሎ አየን ቅዳሜ ጠዋት።

  ባነሩ ላይ እንደሌሎች ጂም ቤቶች የመሮጫ እና የክብደት ማንሻ መሳርያዎች የሉም ያለው ጠቆር ያለ ጠብደል ሰውዬ ነው።

   እኔ ደግሞ ማትሪክ ተፈትኜ እቤት የተቀመጥኩበት ሰዓት ስለነበረ በማግስቱ ከጓደኞቼ ጋር ተሰብስበን ሄድን። ለመመዝገብ የሄደው ሰው ብዙ ነበረ። ይሄኔ 'በአይነቱ ለየት ያለ' ስላለ እኮ ነው እያልን እየሳሳቅን ሄድን።

የሰበሰበን የሰፈሩ ሜዳ ላይ ነበረ። ሁላችንንም በረድፍ ካስቀመጠን በኋላ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ወጣና ለንግግር መዘጋጀት ጀመረ። "ኦ ኦ ለስፖርት ነው ይሄ ሁሉ ወከባ" እያልን እያጉረመረምን እያለ ማውራት ጀመረ።

"ከመመዝገባችሁ በፊት ማወቅ ያለባችሁ ነገሮች ስላሉ ነው። በመጀመሪያ እንድታውቁ የምፈልገው ነገር ቢኖር የለመዳችሁትን አይነት ነገር እንዳትጠብቁ ነው።"

"በመቀጠል ልነግራችሁ የምፈልገው ከድሮ ጀምሮ የሚገርመኝ እና ብቀይረው የምፈልገው ነገር ነበር ይኸውም በየስፖርት ቤቱ በየጂሙ የሚለፋው ልፋት እና የሚባክነው ጉልበት ነው። ስለዚህ ጉልበታችንን ብረት ላይ ሳይሆን ፍሬያማ በሆነ ነገር ላይ ነው የምናፈስሰው ። ስለዚህ አሁንም ከእኔ ጋር መቀጠል የምትፈልጉ ነገ እንገናኝ እና እንጀምራለን" ብሎ ጨረሰ።

  በማግስቱ ከጓደኞቼ ውስጥ እኔ ብቻ ነበርኩ ለመሄድ የወሰንኩት። እንገናኝ ያለው ቦታ ላይ ስደርስ ጥቂት ሰው ነበረ የነበረው "በሉ እንሂድ መስክ ነው ዛሬ የምንወጣው" ብሎ ወዳዘጋጀልን መኪና ጠቆመን። ወደከተማ መውጫ አካባቢ ያለ ቦታ ነበረ የወሰደን።

ስንደርስ ወደሰፊ ሜዳ እየጠቆመን "ይሄ የደረሰ ሰብል የአንድ ሽማግሌ ገበሬ ነው። ዛሬ ይሄንን ሰብል በማጨድ ያከማቸነውንም ስብ እናቃጥላለን፤ ገበሬውንም እንረዳቸዋለን" አለን። ደስ ብሎን ስናጭድ ውለን፤ ላብ በላብ ሆነን፤ አንደተባልነውም ስባችንን አቃጥለን በምርቃት ተንበሽብሸን ተመለስን።

በቀጣይ ስንገናኝ ደግሞ እንጦጦ ሄደን እንጨት የሚሸከሙትን እናቶች ስናግዝ ዋልን፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንጨት ለሚሸጡ ሰዎች ፈልጠን ስናዘጋጅ ...ብቻ ምን አለፋችሁ ብዙ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን በጉልበታችን ረድተን፤ ሲደሰቱ አይተን፤ ሰውነታችንንም እያንቀሳቀስን ቆይተን ዩኒቨርሲቲ ተጠራሁ።

እያዘንኩም ቢሆን የግድ መውጣት ስለነበረብኝ ወጣሁ። ስወጣ ግን ለዚህ መልካም አስተሳሰቡ እንደምስጋናም ጭምር ለሞኬ አዲዳስ ጫማ ስጦታ ሰጥቼው ተለያየን።

እስኪ አስቡት ሁሉም ሰው በየስራ መስኩ ላይ ትንሽ ደግነት ቢጨምርበት እንዴት መረዳዳት እንደሚቻል።


መናገር......??

https://t.me/memoir21




"ፈጣሪዬ ሆይ በአቅሜ ፈትነኝ!"

የዛሬ ማለዳ አጭር ፀሎቴ ነበረች::

...ግን እኔ ችግሮቼ ከአቅሜ በላይ የሆኑ ሲመስለኝ እርሱ አቅሜ ምን ድረስ እንደሆነ ሊያሳየኝ ቢሆንስ የሚፈትነኝ...

"ልጄ አቅምሽ እኮ ይቺ ብቻ አይደለችም..." እያለኝ ቢሆንስ?

...ሁሌም ቢሆን ከፍጡር ፈጣሪ ይበልጣል...

ፀጋ🖋

https://t.me/memoir21


Noma’lum dan repost
Future Teller and Mind Reader play chess. Who’s winning
So‘rovnoma
  •   Future Teller
  •   Mind Reader
88 ta ovoz


ተከታታይ መጣጥፍ ይጀመር? ምላሻችሁ አዎ ከሆነ ከተዘረዘሩት ርዕሶች ዉስጥ ምርጫችሁ ምንድነዉ? አይ የምትሉም ከሆነ ምርጫችሁን አከብራለሁ🙏
So‘rovnoma
  •   "...እዉነት ቢያሳምም..." ክፍል 4 ይቀጥል
  •   ታላቅና ታናሽ (new memoir)
  •   My dream home💖 (new memoir)
  •   አይ ተከታታይ መጣጥፍ አንፈልግም😎
  •   ሌላ
9 ta ovoz


ምልከታዎቼ - ㅂ

በጣም የምትወዱትና የሚወዳችሁን ሰዉ "ካንተ/ካንቺ በፊት እኔን ያስቀድመኝ" ስትሉት ራስ ወዳድ እየሆናችሁ እንደሆነ ታዉቋችኋል?

"መኖር ደጉ" ከሚለዉ ብሂል ወይ ደግሞ "የሞተ ተጎዳ" ከሚለዉ አባባል ተነስታችሁ ሊሆን ይችላል እንደዚህ የምትሉት ወይ ደግሞ ልምድ ሆኖባችሁ...

ግን ምንም ቢሆን ያ ወዳጃችሁ የእናንተ አለመኖር እየተሰማዉ ቀሪ ዘመኑን ጎደሎ ሆኖ እንዲኖር እየፈረዳችሁበት ቢሆንስ?

እናንተ ይህን የማጣት ጎዶሎ ስሜት ሽሽት ቀድማችሁ ለመሸኘት ስትጓጉ የምታጎሉትን ሰዉ አስባችሁት ታዉቃላችሁ ወይ?

ምርቃት ይሁን እርግማን ባላዉቅም...ሞታችንን 'ሞቶ አንየዉ' ካልነዉ ሰዉ ጋር ያድርግልን::


ፀጋ🖋




https://t.me/memoir21

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

110

obunachilar
Kanal statistikasi