#
ተደቡር 💥የነብዩሏህ ዩሱፍና ሙሳ አስገራሚ መመሳሰሎችን ተደቡር ማድረጋችን ቀጥሏል ...
✨ «
ጃሂሊን» የሚለውን ቃል ሁለቱም ነብያት ሲጠቀሙት እናገኛለን ።
ሙሳ “አዑዙ ቢሏሂ አን አኩነ ‘ሚነል
ጃሂሊን’ ” ሲል ዩሱፍ ደግሞ "አስቡ ኢለይሂነ ወአኩን ‘ሚነል
ጃሂሊን’ " አለ ..
• قَالَ أَعُوذُ بِٱللَّهِ أَنۡ أَكُونَ 《
مِنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ》
• وَإِلَّا تَصۡرِفۡ عَنِّى كَيۡدَهُنَّ أَصۡبُ إِلَيۡهِنَّ وَأَكُن 《
مِّنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ》
✨
12 ቁጥር .. የያዕቁብ ልጆች
አስራ ሁለት መሆናቸውን ታውቃላችሁ .. የሚገርመው ታዲያ ሱረቱ ዩሱፍም በቁርአን “
12ኛ ሱራ” ነች! ። በሙሳ ታሪክ ደግሞ 12 የበኒ ኢስራዒል ጎሳዎች ነበሩ .. ድንጋዩንም በበትሩ ሲመታው
12 ምንጭ ነበር የፈጠረው ...
وَقَطَّعۡنَٰهُمُ 《
ٱثۡنَتَىۡ عَشۡرَةَ》 أَسۡبَاطًا أُمَمًاۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ إِذِ ٱسۡتَسۡقَىٰهُ قَوۡمُهُۥٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡحَجَرَۖ فَٱنۢبَجَسَتۡ مِنۡهُ 《
ٱثۡنَتَا عَشۡرَةَ》 عَيۡنًاۖ
✨“
ማጠጣት” የሚለውን ቃል በሁለቱም ታሪክ እናገኘዋለን ...
ሙሳ ወደ መድየን ሄዶ የተመለከተውን ክስተት ሲነግረን «ኡመተን ሚነናሲ ‘
የስቁን’/ መንጋዎቻቸውን ‘
የሚያጠጡ’ ሆነው አገኛቸው» ሲለን በዩሱፍ ታሪክ ደግሞ እስር ቤት በነበረበት ጊዜ ለአንዱ እስረኛ የህልም ፍችውን ሲነግረው « ‘
ፈየስቂ’ ረበሁ ኸምራ/ ንጉሱን ጠጅ ‘
ያጠጣል’» ሲለው እናገኛለን ። እዛም ማጠጣት ፤ እዚህም ማጠጣት .. ሱብሃነሏህ
• وَجَدَ عَلَيۡهِ أُمَّةً مِّنَ ٱلنَّاسِ 《
يَسۡقُونَ》
• 《
فَيَسۡقِى》 رَبَّهُۥ خَمۡرًاۖ
ይቀጥላል ..!
ቻናላችን 👉
t.me/tedeburr