ቅዳጅ ገፆች📜


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


"ቅዳጅ ገፆች" ባልኳት channel ውስጥ የልቤን እውነታ እና በጥቂቷ የአፍላ ወጣትነት ህይወቴ የተነሳውን ታሪክ እፅፋለሁ፤አቀርባለሁ።✨️⚜️✨️
ልጅነቴ፣ ጥላቻዬ፣ እምነቴ፣ መሰማቴ፣ ትንሽ ሐሳቤን በውስን ቃላቶች፤በቅዳጅ ገፆች ላይ የማሰፍርበትን ይችን ትንሿን ግን ሀሳባዊ እውነታዎችን በትልቁ የያዘችውን channel please join

Dm @Kal_awit fyi‼️

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ማን ነው እዚህ ታሪክ ላይ የተሳሳተው?📌

ሀሳባችሁን አጋሩ


.
.
.
"ሀሴት የምር እየሳቅሽ ነው?"

"አይ አብርሽ፤ ምን እንድል ጠብቅህ ነበር? 'አትተወኝ የኔ ፍቅር ይበቃናል' ወይስ 'ካላንተ መኖር አልችልም፤እሞታለሁ' እንድልህ?"

"ምንም ባይበዛ ይሄን አልጠበኩም።ልብሽ ሚሰበር መስሎኝ ነበር ለረጅም ጊዜ ይዤው የነበረው።አንቺ ግን..."

"ሰውነታችን በተለይም ነጩ የደም ህዋሳችን(WBC) አዲስ የpathogen invasion ሲያጋጥመው ይደነግጣል።በቶሎ ማገገም ይከብደዋል።ምንነቱን ለማያውቀው በሽታም በለው ምን ለመከላከል ጊዜ ይወስድበታል።ተጎድቶም ቢሆን ግን ያገግማል።ከጊዜያት በኋላ ግን ያን pathogen በድጋሚ መጥቶ detect ሲያረገው እንደ መጀመሪያው አይሆንም። Already ያንን ነገር experience ስላረገው አዲስ አይሆንበትም።so ራሱን ለመከላከል ዝግጁ አድርጎ ይጠብቃል። ደማችን ውስጥ ስላሉት antibodies ማሰብም ትችላለህ።እና ምን ልልህ ነው ከብርሀኑ ጎን ጨለማ መኖሩን ረስቼው አላቅም።ከፍቅር አንድ ቀን አለመፈቀር ይኖራል።ከዚ በፊት ብዙ ያፈቀርኳቸውን ነገሮች አጥቻለሁ።ከማንም በላይ ታውቃለህ ያን።ከመፈቀር አጠገብ መ:ሰልቸት፤ስሜት ማጣት አለ።እኔም ልክ እንደ white blood cell ራሴን ብዙ ጊዜ ለተጎዳሁበት ነገር ዝግጁ አድርጌ ነበር።ስሜትህን ካንተ በፊት ነው የተረዳሁት።እንድትሰማው እድል ሰጥቼህ ነው።"

"ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም።ግን አንቺ እንድትጎጂ አልፈልግም ነበር ማንም እንዲጎዳሽም አልፈልግም።"

"አብርሽ ቀለል አርገው።አትጨናነቅ።እኔ አልጎዳም በማፍቀሬ አልፀፀትም።በአንተ ውስጥ የሌለን ስሜት ልጭንብህም አልሻም።ፍቅር ከአንድ ወገን አይሆንም።ካልሆነ ልክ እንደ አጋም እና ቅንጭብ አንዱ ወጊ አንዱ ደሚ የሆነ ግኑኝነት ይፈጠራል።ስለዚህ ልክ ነህ።መቋጫ እናበጅለት።"

"አ...አዎ።"

"ብቻ አደራ እንደ ክፉ ex እንዳንተያይ።አንዳንዶች ስንት ነገር አብረው ያሳለፉትን ሰው እንደ አባታቸው ገዳይ አድርገው ሲተላላፉ ይቀፈኛል።ብቻ አንተም እንዲያ እንዳታረግ ካልሆነ ለእቴቴ ነግሬ ነው ማስመዘልግህ።ሃሃሃ..."

"እብድ ነሽ።እንዴት እንደዛ አረጋለሁ ምንም ቢሆን ትዝታ አለን የምንጋራው ደሞ እወድሻ..."
"አብርሽ እንደ ማይተዋወቅ ሰው እንዳንሆን ነው ያልኩት።ከዚህ በኋላ መመለስ የለም።መንገዳችን ተገንጥሏል።ትዝታችንም በየጓዳው ይቀመጣል።'የበፊት' ብለን የጣልነው ታሪክ አለ።ከንፁህ ጓደኝነታችን እና አሁን ከቆምንበት አፅናፍ መሀል ላይ የነበረውን ቆርጠን እንጥለዋለን።እንዲያ ማትችል ከመሰለህ ሁሉም ይቁም እና ሙሉ ታሪኩ ይሰረዝ።አቋምህን ግልፅ አርግልኝ።"

"እኔንጃ...ሀሱ መቻሌን አላውቅም።"

"ጥሩ። መልካም ቀን አብርሀም።መልካም ህይወት።"

ቆማ ጨብጣው ሄደች።ተመልሳ መጥታ ከእቅፉ እንደምትገባ ነበር ያሰበው።አልዞረችም።በተቃና እርምጃዋ እንደ ሁሌውም ቀና ብላ በፍጥነት ራመድ እያለች ከአይኑ ተሰወረች።እጎዳት ይሆን ብሎ የከፈተው መንገድ ተመዞ ተመዞ እሷን ሸኝቶ መለሰው።ጠብ! አንዲት እንባ አመለጠችው።

✍️🏼ቃል

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages

635 1 12 1 12

✨️ከፍቅር አንድ ቀን✨️


"የኔና ያንቺ ነገር ልክ ስርዓተ ነጥብ እንደሌለው ተራ ፅሁፍ ነው።እውነትነቱ እንደደበዘዘ ፣ማረፊያ እንደሌለው ፣አንባቢውን ሰቅዞ እንደማይዝ፣ደራሲው ስሜትን እንዳልዘራበት፣ባዶ የቃላት ስብስብ።እንደ ገደል ወንዝ ዝም ብሎ የሚፈስ እየሆነብኝ ነው።"

"ሃሃሃ...አብርሽ ለግጥሜ ሀሳብ እየፈለኩ ነው በለኝ ሂሂሂሂ...ምንድነው የምታወራው እንዴ?"

"ሀሴት እባክሽ ይበቃል።ለመረዳት ያሰፈሰፈ ጆሮ ይኑርሽ።አዳምጪኝ ከመሰማት በላይ መደመጥ ነው ምፈልገው።"

"አብርሽ እየሰደብከኝ ነው እንዴ? ጆሮዬንማ አትናገር ስንት የሰማሁበትን ደህና ዘመዴን ሃሃሃ...ሂሂሂ..."

"ለምንድነው ሳቅሽ ባዶ የሆነብኝ?የምር ያኔ ሱስ የሆነብኝ ሳቅ ዛሬ ለጆሮዬ ኦና የሆነብኝ ለምን ይሆን?"

"አይ አብርሽ። ልብም እኮ ፅኑ አይደለም ይለዋወጣል፤እንኳን ጆሮ።ምናልባት መልስ መፈለግ ያለብህ እኔጋ አይደለም ልብህ ላይ ጥያቄውን አስተጋባ መልሱን በተራው ያስተጋባልሀል።ሆሆ ከኔ ራስ ወረድ...ሃሃሃ..."

"ልክ ነሽ።ልቤንም ልሰማው ሞከርኩ።ህሊናዬንም ተሟገትኩት።ያ...ያ ልቤን እንደ ሰም በሙቀቱ ያቀለጠው ፍቅርሽ ዱካውም የቀረ እስከማይመስለኝ ድረስ ባዶ ሆኖ ነው ያስተጋባልኝ።"

"ግልፅነትህ ምርጡ quality'ህ ነው ታውቃለሃ!"

"አንቺስ ምን እያሰብሽ ነው? ልብሽ ምን ይላል ሀሴት?"

"የሚገርምህ የኔ ልብ እንዲያው ነው፤እንደ መጀመሪያው።ያኔ መናፈሻው ላይ ቁጭ ብለን ስናወራ እንዳየሁህ ነው አሁንም የማይህ።ነብልባሉ እንኳን ሊጠፋ ይቅርና ቀዝቀዝም አላለ።አሁንም ትላንትም የነበረኝ ልብ ገፆቹን ብትፈትሽ አንዳች የተለየ ቀለም አታገኝበትም።ቅድም 'ልብ ፅኑ አይደለም ይለዋወጣል' ያልኩት ምናልባት ለአንዳንዶች አይሰራ ይሆናል።ከይቅርታ ጋር በነጠላ ትምህርተ ጥቅስ ውስጥ የቅድሙ ንግግሬ ላይ 'አንዳንዴ' ምትለዋን ከፊት አስገባልኝ።ደራሲ ስርዓተ ነጥብ ትርታው ነው አሉ።የኔ ፍቅር ባዶ ቢመስልህም በአንተ ልብ ውስጥ ነው። እኔጋ ከነክብሩ ነው የተቀመጠው።"

"ይቅርታ ሀሴት እኔ ----"

"Wait አብርሽ አልጨረስኩም።ያፈቀርኩህ በምላሹ ምንም ጠብቄ አይደለም።አንድ ልብ እንደተጋራን ያኔ ነግረኸኝ ነበር።ያኔም ቢሆን ሰው በአንድ ልብ ሊያፈቅር አልችልም ስልህ የተጠራጠርከው የኔን ልብ ነበር።አስታወስከው ያንን ቀን? አበባ አምጥተህልኝ 'ከ50 አበባ ይልቅ ሁለት መፅሀፍ ብትሰጠኝ ይሻላል እኮ' ብዬህ በማግስቱ የመፅሀፍ bouquet አምጥተህ ያስታቀፍከኝ ቀን? ያወራነውስ ከልብህ ተፍቋል?"

"አስታውሰዋለሁ።"

"ያልኩት ይሄንን ነበር አንድ ልብ ተጋርተን ቢሆን፣በአንድ ልብ ምናፈቅር ቢሆን ዛሬ ሁለት ተቃራኒ ጫፎች ላይ ባልቆምን ነበር።"

"አፈቅርሽ ነበር።የእውነትም ነበር ልቤን የሰጠሁሽ።አሁን ግን እንደዛ አይደለም ሚሰማኝ... ያኔ ግን የምር ነበር።አሁን---"

"አታብራራው አብርሽ።ደራሲ ስለሆንክ ብቻ ቃላት አትምረጥለት።እንደወረደ ሲሆን ይሻለኛል።የጭቃ ላይ እሾህ ይበልጥ ያሳማል።"

"ሀሴት እወድሻለሁ። ግን አልቻልኩም። እንደ ድሮዉ መሆኑ ከበደኝ።መጀመሪያ የነበረው የብሽሽቅ ጓደኝነታችን ይበልጥ ቀላል ሆኖ አገኘሁት።ማፍቀሩ ግን...እንለያይ ሀሴት ይበቃል። toxic relationship ሆኖ ከሚቀጥል እዚጋ እንቋጨው።"

"ታስታውሳለህ Would you rather prefer to drink only one drink for the rest of your life or whatever you want but with a drop of pee? የሚለው ሀሳብ ላይ ተከራክረን መሸናነፍ ሲያቅተን በየጊቢው እየዞርን ፊርማ ስናሰባስብ ሃሃሃ... መቼም ምረሳው አይመስለኝም መጨረሻ የኔ በልጦ ሲገኝ 3 ቀን የዘጋኸኝማ ሃሃሃ...ሂሂሂ...።"



◇◇◇◇◇
.
.
.


አንድ ፅሁፍ ነበር ነገ ይለቀቅ ወይስ አሁን ይሁን ምን ትላላችሁ?🙄




Have you guys listened የዚን ዘፈን ግጥም በደንብ?🫶🏼🧎‍♀️🥹

ማን ሆነና ታዲያ - የጎጆዬ ማሾ፤🕯
የኑሮዬ ቅመም -የህይወት ጣዕም እርሾ።
አወይ መታደሌ - ልቤ አንቺን ወዷል፤💖
እንዴት በአይንና - በሀገር ይቀለዳል።

ምን ይሉት አባባል - አይወደኝም ማለት፤
አንቺ ማለት ለኔ - ሀሴት አለም ገነት።✨️
ቢሰምር ህይወቴ - ብደነቅ ቢያምርብኝ፤
አንቺን ብወድ ነው- ሌላ ባልኩ ይቅርብኝ።🫠

Michael's fan react for more😭🤌🏽


"ቀጥይ እንጂ" አለቻት አንደኛዋ

"ቆይ እስኪ ለመፍረድ እንዲያመቻችሁ ከስር ጀምራችሁ ስሙት ሆሆ..." ዝም አልናት

"ከዛ በቃ አባባሉ የሆነ የሰውን ነፃነት፣የማንነት ነቆራን አላማ ያደረገ መስሎ ተሰማኝ።ልጅቷ ምንም አረገች ምንም መብቷ ነው። 'የቆላችውን መቅመስ እንዳለበት' ስለተሰማው የምር ተናድጄ ነበር።እኔም በአጭር ቃላቶች ቅጥልልል አረኩታ።" ሁላችንም አልገባንም ነበር፤መጠየቅ ነበረብን።

"ማለት እንዴት አገኘሽው ማለቴ የተለያየ ባጃጅ ላይ አይደል አደል እንዴ የነበራቹት?" መጋረጃ ወጥራ ስታጠና የነበረችው ሀና መጋረጃዋን ጆሮዋ ላይ አስይዛ ጠየቀቻት።

"እንደ ጦጣ ዘላ ወጥታ ይሆናላ ኤደን አታረገውም አይባል መቼስ" ልክ ናችሁ ሀረግ ናት እንዲህ ያለችው።ለለመድነው የእንስሳ ቀልድ ፈገግ አልንላት።ስለ ኤዱ ግን ትክክል ነበረች።የክፍለዘመናችን ደፋሩዋ ሴት ነች።(ሳላስበው አጋነንኩታ!)

"No no, እኛ የነበርንበትን ባለባጃጅ ከፊት እየሄደ ካለው ጋር ቀረብ ብሎ ከጎን እንዲሄድ ጠየኩት።እንቢ እንዳይል የድሮ ጎደኛዬ ነው ሰላም ልበለው ቆየሁ ካየሁት ምናምን ብዬ አሳመንኩት።..."

"እሺ..." አልን በአንድነት።መመሰጣችንን ስታይ እግሯን አመቻችታ መግለጫ ምትሰጥ ይመስል ጉሮሮዋን ጠርጋ ቀጠለች
"...ከዛ ሹፌሩ ያልኩትን እስኪያረግ ከቦርሳዬ አንድ ወረቀት እና ማርከር አውጥቼ የሆነ ነገር ጎላ ጎላ አድርጌ ፃፍኩ።

ልክ ከዚያኛው ሹፌር ትይዩ ሲያረገኝ 'ሀይይይ' አልኩት ጮክ ብዬ ሁለመናው እየሳቀ አፀፋውን መለሰ።ከዛ 'ጥቅሱ ከጀርባ' አልኩት በዛው ድምፅ።

'ወደድሽው እንዴ'

'በጣም!! እስኪ በልልኝ በናትህ'

'የቡናሽን ማማር ማታ እቀምሰዋለሁ...' እንዳለ ያ በትላልቅ የፃፍኩበትን ወረቀት ከፍ አርጌ አሳየሁት።አቤት ፊቱ በስመአብ ...ከአደነጋገጡ ሀረግ ብታየው የጭላዳ መቀመጫ ይመስላል ነበር ምትለው።" አሁን አልቻልንም ቡፍ ብለን ሳቅን።ካካካካ...የፈተናው ጭንቀት በመስኮት ሹልክ አለ።ስቀን እንዳባራን ነበር ምን እንዳለችው የጠይቅናት

"ምንድን ነበር ግን የሚለው በማርያም?" አልኳት

"እንዳልኳችሁ ልክ 'የቡናሽን ማማር ማታ እቀምሰዋለሁ' ሲል ወረቀቴን ከፍ አረኩት።"

"እኮ ምን ይላል?"

"አር ቅመስ ብዬ ነዋ...." አባራ የተባለው የሳቅ ዝናብ ጎርፍ ሆነ ተመለሰ።ከጣራ በላይ ነበር የሳቅነው።በግራ በቀኝ ያሉ ጎረቤቶቻችን በአድማ በታኝ ክፋላችንን ሊያስመቷት ምንም አልቀራቸውም፤ የ"እናጥናበት " ስሞታቸውን በግርግዳው መወገር ተቀብለን ኡስ ኡስ መባባል ተባብለን ድምፃችንን ቀንሰን በሳቅ ነፈርን።

ከአፍታ በኋላ "ኡፍ መሳቁ አደከመኝ ልተኛ ሌሊት እነሳለሁ።" ስል ሁሉም በአንድ ድምፅ ያለ ተቃውሞ አፅድቀውት አጠፋፍተን ተኛን።አይ "አር ቅመስ"።

✍️🏼ቃል

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages


🍂🍁_The "አ* ቅመስ" story_🍁🍂


የአንድ የፈተና ሰሞን ሁሉም በየዶርሙ ከትሞ መፅሀፉ ላይ ተደፍቶ በሚያድርበት ወቅት እሷ ከሀረር ከመጣችው ጓደኛዋ ጋር ወጣ ብላ እንደምትመለስ አስታውቃኝ ወጣች፤ኤደን ክብረት።ከምሽቱ 4 ሰዓት ሲሆን ታኮ የታጠቀ የጫማ ቋቋታ ብሎካችንን አስበረገጋት።የብረት ኮቴ የተገጠመለት ፈረስ ድንገት ደንብሮ ወደኛ እየሮጠ እየመጣ ነበር የመሰለን።

በሩን በርግዳ ገባች።እሷኑ እየጠብቅን ስለነበር የበሩ የመበርገድ አንድምታ ማናችንንም የረበሸን አይመስልም።ገብታ ለበሩ ከቀረበው አንደኛው አልጋ ላይ መወርወር በሚመስል አቀማመጥ ዘፍ አለች።

ወትሮም ሀብታም ቤት ደረጃ ላይ የተነጠፈ ምንጣፍ የሚመስለው ከንፈሯ ጭራሽ ተዘርግፏል።

"ምነው የተሸበረች እንቁራሪት መሰልሽ?" animal science ምታጠናው ልጅ፤ሀረግ ቀደመች።ወሬዋ ሁሉ እንስሳን ያነሳል።ከእንስሳ ውጭ ማይማሩ እስከሚመስለኝ ምክሯ ሳይቀር በእንስሳ ነው።አንዴ አስታውሳለሁ ግሬዴ ዝቅ ብሎብኝ ሳለቅስ አግኝታኝ ያለችኝን "አይዞሽ ኪዳንዬ።ይህ እኮ በሁሉም ዘንድ የሚገጥም ነው።ነብር አንዲት አጋዘንን እያባረረ ድንገት ብታመልጠው 'ቲሽሽ ባይበላስ ቢቀር' ብሎ ተስፋ ቆርጦ አይመለስም እሷኑ አድብቶ ለመብላት ወይም ሌላ ለማደን ይሞክራል።ሸረሪትስ ብትይ በእነዛ ቀጫጭን እግሮቿ ቤት መስራት ደከመኝ ብላ ትተወዋለች? አተወውም።ውሻ ለአሳዳጊው እንደሚታመነው አንቺም ለአላማሽ በዛው ልክ ታመኚ እና ደገጋግመሽ ጣሪ።እንደ አዞ..." ምሳሌዎቿ ከዚህ አይወጡም።እንደዚው ናት፤ ሁሉም ወሬ ላይ።ያኮረፈችው እንስታችን ሌላ ጠያቂ ከሌለ አላወራም ነው መሰል አሁንም መሬቱን እየተመተመች ነው፤ ለማጎርጎድ ትንሽ ነው የቀራት።

"ኸረ ባክሽ ምን ሆነሽ ነው?" አልኳት።ቀና ብላ አይታኝ ለማውራት አፏን አሞጠሞጠች

"በሰላም ተዝናንተን ወጥተን በእግር walk እናርግ ስላት ማሲን፤ አይሆንም ይደክመኛል ብላ እንቢ አለች።እሷ ናት አንድም ያለ ዕድሜዋ ያንን ውፍረት ተሸክማ እርጉዝ ዝሆን የመሰለችው....በእግሯ ከመሄድ መንከባለል ነው ሚቀላት አሁንማ...በራሷ ስጋ ልኳንዷ ቤት ብትከፍት ራሱ 10 አመት ያለ እጥረት ያሰራታል።" አጉተመተመች።ሁላችንም በሁኔታዋ እና የማናቃትን ልጅ በገለፀችበት መንገድ ላለመሳቅ ስንታገል የፈጠርነው ፊት "ለመኮሳተር የሚጥር ጅል ጅብ" መስለን ቁጭ።(የሀረግ ዘይቤያዊ አነጋገር)

"ወደጉዳዩ እባክሽ።" አለቻት ሀረግ

"ከዛማ ኮንትራት ባጃጅ ይዘን ወደእሷ ማረፊያ መሄድ ጀመርን...መንገድ ላይ አንድ ባጃጅ
'የቡናሽን ማማር ማታ እቀምሰዋለሁ፣
እንዴት እንደቆላሽ ቀን አይቼዋለሁ።' ሚል ጥቅስ አላይ መሰለሽ።ከድሮም እንደዚህ የባጃጅ ጥቅስ ምናምን አልወድም፤ከrelegious ጥቅሶች ውጪ።የመሪ ዘዋሪው or whoever who put quoets on public taransports አስተሳሰቡን በተሳፋሪዎቹ ላይ የመጫን ወይም እወቁልኝ ሚል ነው ሚመስለኝ።የግል ሀሳቡን ለራሱ ከመሪው ጋር ይዞ የሚሄድ ታክሲ ላይ መግባቱ more comfort ይሰጠኛል።..." ወሬው ከመስመሩ እንዳይወጣ ማናችንም ሀሳብ ከመወርወር ተቆጠብን


እስኪ ምትወዱትን ሰው በ አንድ ቃል ግለፁት(አንዲት ቃል ብቻ)


✨️✨️✨️


"ምን ሆነሻል?" የያዘችውን መፅሀፍ ከሩቅ አይቶታል።ከ15 ቀን በፊት ከራሱው የወሰደችው መፅሀፍ፤ምን ሆኛለሁ?ሰላም ብሏት ቁጭ አለ።ቀኑ ቅዳሜ ነው፤"ቅዳሜ -ዘ-አቢዳን"። በየሳምንቱ ቅዳሜ ይገናኛሉ።ስለ ሳምንቱ፣ስለ መፅሀፍ፣ስለ ቤተሰብ፣ሶሻል ሚዲያ ላይ ስለሰሙት፤ስለ ኳስ(ስለዚስ እሱ ያወራል እንጂ እሷ አዳማጭ ነች። ) ሳይቀር ሚወያዩበትን ቀን፤ "ቅዳሜ ዘ አቢዳን"(ኪዳን እና አብርሃም ሲቀየጥ ሚወጣ ቃል ነው።ሌላ ትርጉም ይኖረው ይሆን?) ብለው ሰይመዋት በየሳምንቱ ይዘክሯታል ።እነሆ ዛሬም የዘውትር መዳረሻቸው የሆነው ካፌ ተገናኝተዋል።

በአይኑ አስተናጋጅ እየፈለገ "እንዴት እየሄደ ነው?እንዲህ መፅሀፍ ላይ ስትቆዪ አይቼሽ አላውቅም?ከበደሽ እንዴ!" ሚከብድ መፅሀፍ እንዳልሆነ ያውቃል።እስካሁን አለመጨረሷ ግን የምርም ገርሞታል። አስተናጋጁ መጥቶ ኖሮ ለሁለቱም ማኪያቶ አዘዘ።ከአፍታ በኋላም አስተናጋጁ የታዘዘውን ይዞ መጣ።

"የሳይኮሎጂ ይዘት ያለው መፅሀፍ ሳነብ ይሄ የመጀመሪያዬ አይደለም ታውቃለህ።በዛውም ልክ እንዲህ ያሉ መፅሀፍቶችንም አላዘወትርም።ልብወለድ ማነበውን ያህል እንዲህ አይነት ይዘት ያላቸውን 3 ወይም 4 ቢሆን ነው ያነበብኩት።አይገርምህም ይሄ ግን ተለየብኝ።" የቀረበላትን ማኪያቶ ፉት አለች።የዛሬው የመክፈቻ ርዕስ ይሄው መፅሀፍ መሆኑ ሆነ።

የመጀመሪያውን ዕትም 2016 ላይ ገዝቶ ከአንዴም ሁለቴ አንብቦታል።ከዚህ በፊት እንድታነበው ጠቆም አርጓት የነበር ቢሆንም ችላ ብላው ነበር፤በዛ ሰዓት የምትመርጠው ይዘት ስላልነበር።ከሁለት ሳምንት በፊት ግን በየሶሻል ሚዲያው የዝናው መቀጣጠል ስቧት "ልሞክረው" በሚል ስሜት ጠይቃው ሰጥቷት ነበር።
"ምን ተለየብሽ?" እሱም በረድረድ ያለውን ማኪያቶ ፉት ብሎ ትኩረቱን እሷ ላይ አረገ።

"አጠቃላይ ይዘቱ።እያንዳንዱ ርዕስ የተለያዩ ሰዎችን እያስታወሰኝ ነበር ማነበው።እስከዛሬ በዙሪያዬ የነበሩ ሳሉን አይቼ ኒሞኒያውን ሳልረዳላቸው በጭፍን treat ያረኳቸውን ሰዎች፤ከዚያም አልፎ መጥፎ ስም ሰጥተን 'እሷ/እሱ እኮ ፀባዩ/ይዋ ነው።' ብለን እስከነ ኒሞኒያቸው አንቅረን የተፋናቸው ሰዎች ስንት አሉ።የሰዎች ባህርይ አሁናዊ ሳይሆን ትላንታዊ መሆኑን፤ በአጠቃላይ አሁን ላይ ሰዎችን የማይበት እይታ ከመፍረድ ላቅ ያለ ሆኗል።"

"Interesting የገመትኩትን ሀሳብ ነው በትክክል የተረዳሽው።ግን አንቺስ ኪዳን?"

"እኔ ምን?"

"አንቺስ ምን ሆነሻል? መፅሀፉ ምን ሆነሻል ብሎ ነገረሽ።ከሌሎችም ባሻገር ራሳችንን እንድንጠይቅ የሚገፋፋ ሀሳብ ይመስለኛል።"

"እኔ...አብርሽ አላውቅም።የኔነቴ ማንነት በቅጡ ማውቀው አይመስለኝም።you know መፅሀፉ በደንብ ነው ችግሮቹን ያብራራቸው።But, I just can't find myself in this book." የምሯን ነበር።የምርም መፅሀፉ የጠቀሳቸው ሳሎች እንዲሁም ኒሞኒያዎች ከእሷጋ የሚጣጣሙ አልነበሩም፤ወይም አልተራዳችውም።

"ህምም...ምናልባት 'ደና ነኝ/ምን ሆንኩ?' ከሚሉት ወገን ራስሽን አስቀምጠሽው እንዳይሆን እእ?"

"No no, I know ደና እንዳልሆንኩ።ግን በቃ እኔን ወይም ትላንቴን የሚመስል ሀሳብ ማግኘት አልቻልኩም። "

"ምናልባትም ራስሽን አላወቅሽም ይሆናል።ሰዎች self knowledge የሚለውን ሀሳብ እንደ ተራ ነገር ሲቆጥሩት አያለሁ።ወደ ውስጣቸው መመልከትን አይሹም።እንደውም ስለ ራሳቸው እነሱ ከሚያስተውሉት በላይ ሌሎች observe የሚያረጉት ይበልጣል።አንዳንድ ሰዎች አጋጥመውሽ አያውቁም በጣም ንዴታም።ንዴት ስልሽ በጣም የሚረብሽ፣ግኑኝነትን የሚያበላሽ እና even ሌሎችን ሳይቀር negative energyን የሚያጋባ ንዴት ይዘው Anger issue እንዳለባቸው ስትነግሪያቸው 'ኸረ እኔ እንደዚህ አይደለሁም።ስራው ነው ፣ሚስቴ ናት፣ባሌ ነው እንድናደድ የሚያረጉኝ እንጂ እኔ እንደውም ሰላማዊ ሰው ነኝ' ብለው ይከራከራሉ ወይ ደሞ ስለ እነሱ መጥፎ ንዴታምነት የሆነ ሰው ሲያወራ ሲሰሙ ወደ ውስጣቸው ከመመልከት ይልቅ ራሳቸውን ከእውነታው ያርቃሉ።እንደውም ያወራውን ሰው ሳይቀር ስለ እነሱ መጥፎ ነገር ለመንዛት እንደተላከ ጠላት ይፈርጁታል። " በማኪያቶው ጉሮሮውን አርሶ የእሷን ሀሳብ ለመስማት ዝም አለ።

"ልክ ነህ እንደውም የራሳቸውን ነፀብራቅ በሌሎች ውስጥ ስለሚያዩት አሁንም ቢሆን ወደ ራሳቸው ከማዘንበልና ከመመልከት ይልቅ ትከከለኛ ማንነታቸውን ያሳያቸውን ሰው ይርቁታል፤ያርቁታል።" አለችው

"ለምን ይመስልሻል ያንን ሚያረጉት?"

"ofcourse ያላቸውን መጥፎ ስብዕና ሲያዩት ያስፈራቸዋል።ይሄ እኔ አይደለሁም ይላሉ so ሚያስፈራ እውነት ከመጋፈጥ ይልቅ ምቹው ውሸት ላይ ይንተራሳሉ።"

"በትክክል።ለዛ ነው ራስን መረዳት፤ወደ ራስ ውስጥ መመልከት አስፈላጊ ሆኖ ሚገኘው።አንቺ ሳታጤኝው የቀረሽውን ባህርይ ሌላው ቢነግረሽ ወይም ሊያሳውቅሽ ቢሞክር already ስለማታውቂው ሰው እንደሚያወራ አርገሽ ልትረጂው ትችያለሽ።Every little feeling, every little childhood memory does matter. You don't know መቼ affect እንደሚያረግሽ።ውስጥሽ እንዳለ ማታውቂው ስሜት የሆነ ጊዜ ላይ ገንፍሎ ወጥቶ አንቺንም በዙሪያሽ ያሉትንም ሊያቃጥል ይችላል።" ትንፋሽ ወስዶ አጤናት።ሀሳቡን እያብላላችው ነው።እሷም በበኩሏ ዝም አለች። ያለው ነገር ትክክል ነበር።

"ምናልባት...አንቺም ማመን ያልፈለግሽው ወይም የምርም ያላጤንሽው አንቺነት ይኖርሽ ይሆናል።አንዴ ለራስሽ እድል ስጪውና ለመረዳት ሞክሪ።መፅሀፉን ስታነቢ እንዳሰብሻቸውና እንደተረዳሻቸው ሰዎች ራስሽን መርምሪው 'ምን ሆኛለሁ?' ብለሽ ራስሽን ጠይቂ።"
ሀሳብ ውስጥ ዘፈቃት። የምርም 'ምን ሆኛለሁ?' ብላ አሰበች።

✍️🏼ቃል

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages


Forward from: ✍ዮኒ-ኣታን
‎ እነሆ ላንዳንዱ ነገር አይሰምርም።....  "ወይኔ....መቀለጃ ያርገኝ...." እያለ መበሳጨቱን ጀመረ። ከተቀመጥንበት ሬስቶራንት ግንባሩን እያላበው ለምግቡ የቀረበለትን ሶፍት እያነሳ ግንባሩን ይነክር ጀመር..... "ኧረ ተረጋጋ.." አልኩት ምንም እንኳን የተናደደበት ምክንያት እኔንም ቢያናድደኝም እንደሌላው ጊዜ ቱግ አላልኩም.....  ብዙውን ጊዜ ቶሎ ምናደደው እኔ ነበርኩ እሱ ደግሞ እያርገበገበ ንዴቴን ጣራ የሚያስነካ ልጅ...... መወለድ ቋንቋ ነው ይባላል....  እንደ ወንድሜ ነው ማየው..  ዛሬ በተገላቢጦሽ ተናዶ አገኘሁታ...ማን ሞኝ አለ...ምላሴ ላይ ለክፉ ቀን ያስቀመጥኩትን ነዳጅ አርከፈከፍኩለት........ በላይ በላይ ንዴቱ ይጨምራል እኔ ደሞ እስቃለሁ ሲለኝ ደግሞ "አይዞህ በቃ..... positive እናስብ maybe ገና ሊሄድ ይሆናል....." እለዋለው....  እሱ ደግሞ ቀንድ እንዳለው የደነበረ በሬ መረጋጋት አቅቶት "ገና ለ ገና ያበደርኩትን ብር መልስ እንዳልለው እኮ ነው...." ይላል.... "አንተ ኑሮህ አበደርክ" ብዬ እስቃለሁ.... ነገሩ የጀመረው ከኛ ጋር እንዲጫወት ብሎ የሰፈር ጓደኛውን ይጋብዛል ይሄን ጊዜ ጋደኛ ተብዬው 'አሁን ያለሁት #አዘዞ ነው አይመቸኝም....' ብሎ ስልኩን ይዘጋዋል...እኛም ካልተመቸው እኛ እንዝናና ብለን ካቅራቢያችን ካለው ሬስቶራንት ምሳ ልንበላ ገባን....ይሄኔ '#አዘዞ ነኝ' ያለው ሰውዬ እኛው ካለንበት ቦታ ታየ....  ይሄን ግዜ ጓደኛዬ ተናደደ...በንዴቱ ምክንያት እራሱ ለ አንድ መድበል የሚበቃ ግጥም አነበነበ
‎
‎"እቱ
‎የሄድክበቱ" ብሎ ጀመረ......."ኧረ በመድሃኒያለም 'እቱ' ለ ሴት ነው..." አልኩት.... ቀና ብሎ አየኝና "ቢሆንስ.... ገና አሮጊትም አድርጌው እገጥማለሁ....."አለ። " እሺ ባይሆን እኔ ላግዝህ...." አልኩትና ቃላቶቼን ሳቀባብል
‎"ምንም እንኳ ባንተምነው ስጋችንን ለዋጋ
‎     አለሁ ካለው ቀርቶ ተገኘ ከኔጋ''
‎አለ.........የግጥም ክህሎት እንዳለው ያወቀው ያኔ ነበር....  ንዴቱን እረሳና ፈገግ እያለ
‎"እቱ
‎የሄድሽበቱ
‎ከኔ ስንት ይርቃል
‎ እመጣለሁ ብለሽ መቅረትሽ ይጎዳል"....የሚል ፅሁፍ ቁጭ ብሎ ፅፎ አነበበለኝ..... "ለክፉ አትሰጥም..." አልኩት ደስ አለው።
‎ከአዟሪ ላይ ሻርፕ ካልገዛው ብሎ ትንሽ ተገለገለ።
‎
‎ ከጊዜያት በኋላ እንደዚ ብሎ መከረኝ
‎"ምን መሰለህ ዮኒ...አንዳንዴ ባልታሰበ ጊዜ ድብቅ ክህሎትህን ታወጣዋለህ...እኔም ያኔ ነው ገጣሚ እንደሆንኩ የገባኝ....'ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም' እንዲሉ አበው...." አለኝና ፊቱ ላይ ያሰፈረውን ፂሙን እያሻሸ "የ ግጥም መደብር ሰሞኑን አሳትማለሁ....ምስጋና ከምትለዋ አጭር ፅሁፍ ላይ ያንተ ስምን አካትቼዋለው...." አለ ትልቅ ውለታ የዋለልኝ ይመስል......"መድብል ለማለት ፈልገህ ነው...." አልኩት ሳቄ እየመጣ......"ዋናው መግባባታችን ነው መደብር ሆነ መድብል ለውጥ አያመጣውም....." አለና የወንበሩት ጀርባ ተደግፎ ተደላድሎ ተቀመጠ.....
‎የመከረኝን ምክር አሰብኩና...."ይሄኔ የዛን ለት ልጁን ባያገኘው ኖሮ እንደዚህ አይሆንም ነበር..."አልኩና እያዘንኩ በረጅሙ ተነፈስኩ
‎
‎
‎ ዮኒ
‎      ኣታን @yonatoz
‎
‎Share @Yonny_Athan
‎Share @Yonny_Athan‎


Forward from: Story's from my diary📝
ማልቀስ ፈልገሽ ማልቀስ ሳትቺይ ቀርተሽ ታውቂያለሽ?? ስላልፈለግሽ እንባ እንቢ ብሎሽ ሳይሆን በሰው ስለተከበብሽ.......ሰው  ፊት ካለቀስኩ እራሴን አስነቃለው ብለሽ እንባሽን ውጠሽ ታውቂያሰሽ ? ክብርሽን ላለማጣት ልውረድ ያለን  እንባ ለመመለስ ወደ ሰማይ አንጋጠሽ ታውቂያለሽ??  ምጥ እንደፀናባት ሴት መዳፍሽን ጨብጠሽ ቁና ቁና ተንፍሰሽ ታውቂያለሽ ??

ያ ነው ህይወት ማለት



https://t.me/storyweaver36
https://t.me/storyweaver36
https://t.me/storyweaver36


ዛሬ አንድ ጥያቄ ይዤ ነው ብቅ ያልኩት። እስከዛሬ ካነበባችሁት መፅሀፍ ሁሉ እይታችሁን የቀየረውን መፅሀፍ ሹክ በሉን።📚

እንደ challenge እዩት።View አርጋችሁ ምትወጡ ሰዎች እንዳትኖሩ አደራ።😁


Mine: አለመኖር🔥


በስመአብ እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ያለው ሰላም!!Have you guys noticed it?❤️‍🩹

እግዚአብሔር ማኖር ያውቅበታል የእውነት። let your burdens leave to him 🥹🙏🏼


🫶🏼ደህና እደሩልኝ🫶🏼

✍️🏼ቃል


✨️Emotions from my journal✨️



You, fighting for your mental health, trying to stay alive. You dying inside, everything keeps attacking your survival instincts hardly. And this society giving you "ተበላሸች ፣ ጋጠወጥ ፣ አይ ጉርምስና ፣ ደና ልጅ ነበረች!" and so many names and nicknames.

And even your family understand things in the way they wanted to and they keep ignoring or misunderstanding your pain. Losing anyone by your side makes your burden even more heavier. You might wish of dying. Even ሞት ignores your የመገላገል ኤሎሄ and let you die emotionally without dying physically.💔

Your younger self shouting for a small hug or a little talk to just find a shoulder to lie on. And everything and everyone can't see or might not want to see the war in your heart so all you gottta do is fighting on your own, healing by your own and weeping your full of emotions tears on your self. ❤️‍🩹

I know finding someone to do all the process and to make you escape all the traumas and the pains is the real luckiness, it's the biggest blessing. But doing all by yourself is an obligatory. You know life sucks like hell. Waiting for someone to let you up from the ground you've been laying down for a time is such a blast. You don't have to wait for someone to cross the wave by holding your hand. You don't have to wait for your ሙሴ in your life. In the hit-or-miss time of your mental health breakdown, waiting for your ሙሴ to parting your የህመም ባህር and let you stand on the healing land is foolishness. If you have to wait, it have to be only your God. People?? Nah, for your mental well-being only YOU AND GOD are responsible, not anyone.🤎

This is all i did. This is what i understood from my every and distinct breakdowns, pains, traumas, struggles and suffers. After all my breakdowns, I healed, I learned, I observed, I understood and habituated how to heal myself again and again. People saw this one, they saw my smile , heard my laugh, they observed, they gave attention to my happiness. And asked "ዛሬ ምን ተገኘ ባክሽ?" like all the things i went through is a moment of sudden, like all it happens is being happy , it's all about ዛሬ. ትናንት ምን እንደተፈጠረ ሳይሆን ዛሬ ምን ደስ እንዳሰኘኝ ነው ሚጠይቁት, they won't try to know what i felt before the happiness I got today.🎙


This is life, that was war. And there is, there was and there will be only you and Almighty God.🫶🏼⚜️

27-11-2017 E.c

✍️🏼ቃል


ፈገግ አልኩኝ በፈገግታሽ
ደሞ አዘንኩኝ ሳይ ሲከፋሽ
በየጫካ በየሜዳው
በየሳሎን በየጓዳው
ሊያይሽ ልቤ የሚዳዳው
ኩርፊያሽ ብርቄ እንደሳቅሽ
ደግነትሽን ስወድልሽ
በአለምሽ ውስጥ ስትደብቂኝ
በሳቅሽ ውስጥ ስታስቂኝ
መቼ መስሎኝ ላጣሽ ዛሬ
ተመለሺ ባክሽ ፍቅሬ
ከሄድሽ ወዲያ ላትመጪ
የፍቅር ፅዋን ባታጠጪ
ምን ነበረ ባልዋሸሺኝ
አንዴ ቀርበሽ ከምትሸሺኝ
ምነው ያኔ ባልዋሸሺኝ

እንደዚህ አይነት ምርጥ ግጥሞችን አጓጊ ታሪኮችን የተመረጡ ዘፈኖችን ትረካዎችን አንዳንድ የአእምሮ ጨዋታዎችን ለማግነት
👉@loves2512 በዚ ሊንክ ገብተው join ይበሉ አንድ ሰው ለኔ ብዙ ነው ለድጋፋችሁ አመሰግናለሁ 🙏


✨️ Random stuffs✨️

አንዴ ጓደኞቼ ስለ ometv(የtv ቻናል መስሎኝ በለመደ አፌ frequency ልጠይቅ እኮ ነው) እያወሩ ነበር እና ምን እንደሆነ ጠየኳቸው።"እንዴ እስከዛሬ አታውቂም?" ምናምን አሉኝ። እንደማላውቅ ተናገሬ መልስ መጠበቄን ቀጠልኩ።(እንኳንም አዳልጦኝ ምን አይነት ፕሮግራም ነው የሚያስተላልፉት አላልኩ)

ከዛማ "እየውልሽ የተለያዩ ሀገራት ላይ ያሉ ሰዎችን በvideo ምታወሪበት ነው።" አሉ ፤ ያስረዱኝ መስሏቸው።እኔ ጭራሽ ሌላ ሀሳብ።"ማለት በስልክ ነው? እንዴት ተዋውቀን?" ስል ጠየኩ። አንደኛዋ ቆይ "ላሳይሽ በእኔ ቆይ" ብላ ስልኳን አወጣች።ያለችው አይነት ስም ያለውን app ከፈተችና "እየውልሽ ከላይ ያለውን ወደግራ scroll ስታደርጊ በመረጥሽው ሀገር online ያሉ ሰዎች ይመጣሉ። ከዛ በvideo ማውራት።" ነውው አልኩና ሌላ ብጠይቅ ማገዶ ፈጅነቴን ነግረው ከሚያበሻቅጡኝ ብዬ ዝም አልኩ።

ከዛላችሁ የሆነ ቀን ላይ የapp'ኡ ነገር ትዝ ብሎኝ አወርጄ በfacebook አካውንቴ ከፈትኩት ያቺ ጓደኛዬ እንዳለችኝ አንዱን bulgaria ሚለውን ሀገር ነክቼ ወደግራ scroll ማድረግ። እንደው ያ በህልሜ እየመጣ ሚያሯርጠኝን ፍጡር የመሰለ ፣ እኛ ሰፈር ያለው 'ምርጉ' እንደሚሉት እብድ ፀጉሩ የተንዘረገገ ጥቁር ሰውዬ መጥቶ "ሄሎሎሎሎሎሎ!!" ብሎ መጮህ። እንደው ወይ እንደ Instagram ቀይዋ መዝጊያ በተን የለች፤ የተቀመጥኩት ጠራራ ፀሀይ ላይ፤ አንገቱ ላይ 'ወይንዬ' (አንድ ቤተኛ አይጥ አለችን።) የቦጨቀችውን ሺቲ ለብሼ ፤ ወይ በቃ camera'ውን በእጄ ሳልይዘው ሰውየው እያየኝ ውጣ አትውጣ app'ኡን ተያያዝኩት።አቤት ድንጋጤ፤አቤት ክው ማለት።እንደው በዘመኔ ድጋሜ እንዲህ ምደንግጥም አልመስልሽ አለኝ።

ለወትሮው ለቴሌ ደውዬ "ብሬ ለምን ተወሰደ?" ለማለት ባላነሱት ባላነሱት የምል ሴትዮ፤ዘመድ ሲደውል ደና፣አዎ፣እሺ፣ቻው ሚሉትን ቃላት መዝገቤ ቃሌ ውስጥ ሸክፌ ማወራ ልጅ ፤ ጭራሽ video call ? ታዲያ እንዲህ ቁርጭምጭሚቴን ቢነዝረኝ ይፈረድብኛል ቆይ?ሊያውም እንዲያ ያለ ሰውዬ ገጥሞኝ።

ይኸው እስካሁን ይሄው app ስልኬ ላይ አለ ግን እንደው በስተት እንኳን ገብቼ አላውቅም እግዚአብሔር ይመስገን። ዕድሜ ለዛ ሰው traumatize አረገኝ።


✍️🏼ቃል



https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages


‎ ሁሌም ስንጨቃጨቅ ያዩናል...."ስታስቀኑ" ብለው ማለፍ ደግሞ ልማዳቸው ነው። አላውቅም ለምን እንደሆነ ግን ሳንጣላ ከዋልን ወይ ያጎደልኩባት ወይ ደግሞ ያጎደለችብኝ ነገር ይኖር ይሆናል ብለን አስበን ምንጨቃጨቅ ሰዎች ሆነናል.... አንዳንዴ መጣያ ሰበብ እራሱ እንፈልጋለን... የሆነ ቀን የክረምቱን አየር እየማግን "ስማማ" አለችኝ.... "ወዬ"
‎"ከናንተ ቤት ብመጣ ግን ታሳድረኛለህ" አለች አኳኋኗ የነገር መሆኑን የነቃሁባት እኔ "እንዴታ አንቺን ያላሳደርኩ ማንን አሳድራሁ" አልኳት ያሰበችው ነገር እንዳልተሳካ ስላወቀች "እሺ እናትህ ማናት ቢሉህ ማናት ትለኛለህ"
‎"እህ ጓደኛዬ ነዋ" አልኳት...ትንሽ ዝም አለችና "እሺ ለኔ ብለህ አልጋህን ትለቅልኛለሃ.... አንተ መሬት ላይ ወይም ሶፋ ላይ ትተኛለሃ.... ደግሞ እኮ ሶፋ በጣም ይመቻል እኮ ብታይ..." አለች......  እኔም ትልቅ ችግር እንዳለብኝ ያወኩት ከዚ በፊት ከሌሎች ጓደኞቼጋ ለይምሰልም ቢሆን ማባብላቸውና ማቆላምጣቸው ነገር እሷ ላይ አድርጌው አላውቅም......  ትንሽ አቆላምጣት እና አደፈርሰዋለው።
‎
‎"ደግሞ በቤቴ መጠሽ መሬት ልወርድልሽ ያምርሻል.....  ባይሆን ሶፋ ያለሺው ላንቺ ቅርብ ይመስላል እዛ ላይ ትተኛለሽ...." ይሄኔ ደስ አላት ነገሯን ልትጀምረኝ ነው
‎"እህህህህ እንግዳ እኮ ነኝ..... ደግሞ እንግዳ ባልሆንስ ለኔ ስትል እኮ መሬትም እንኳ ማደር ነበርብህ.."
‎"እሺ ልጠጋልሽ" አልኳት....ለጊዜውም ቢሆን ተጨቃጨቅን እና ተጠጋግተን ልንተኛ ተስማማን.......  መስማማታችን ለሁለታችንም ምቾት የሰጠን አልመሰለንም መሰል በ ሶኬት ቦታ ተጣላን።
‎
‎ "ውይ ስታስቀኑ በማርያም" የሚሉኝ ጓደኞቼ "ምናለ 1 ቀን በኔ ቦታ ሁነህ ብታያት" ብዬ አልፋለሁ። እውነት ለመናገር ቀኑን ሙሉ ሳትሰድበኝ ከዋለች የሆነ ነገር እንደሆነች ነው ሚሰማኝ ይጨንቀኛል።
‎
‎አጤ ምኒልክ ነው አሉ....ህዝቡ ላይ ግብር ሲጨምር ህዝቡ ሲጮህበት.....ሲጨምር ሲጮሁበት ቆዩና አጤውም መጨመር ቀጠሉ ህዝቡም  ዝም አሉ.....  ይሄኔ አጤው የህዝቡን ዝምታ ፈራሁት ብሎ የጨመረባቸው ግብር ቀንሷል።
‎ እንዲያ ነው የኔና የሷ ነገር .... ዝም ከተባባልን ይጨንቀናል።
‎
‎
‎ እውነተኛ ታሪክ ላይ ነው የጨማመርኩበት!
‎
‎ ዮኒ
‎      ኣታን @yonatoz
‎
‎Share @Yonny_Athan
‎Share https://t.me/storyweaver36


✨️በቀጣዮቹ ቀናት ምን ይለቀቅ ቤተሰብ✨️
Poll
  •   አጫጭር ታሪኮች🗃
  •   ቅዳጅ ገፆች📓
  •   ሀሳባዊ Conversations🎙
116 votes


✨️እናቴ ሰርግ ያስቀናታል✨️
(ክፍል 7)--The last one

"...ከአገልግሎቴ ብርቅም የምሰራው በቤተክርስቲያኗ ህንፃ ስር ነበር።ክህነቴ መፍረሱን እና መውለዴን የሰማ የሰፈር ሰው ወሬው አላስቆም አላስቀምጥ አለኝ።በእያንዳንዷ ውሎዬ በዙሪያዬ ካሉት ሰዎች ጋር አንገት ለአንገት ተናንቄ መኖር ጀመርኩ።ከጓደኛ እስከ ዘመድ መስማማት አልቻልኩም ነበር።እህቶቼ ሳይቀሩ ጀርባቸውን ሰጡኝ።በመሀል አንዱ ጓደኛዬ ስለዝውውር መጠ:የቅ መከረኝ።እኔም በነገሩ አስቤበት የበላዮቼን ዝውውር ስጠይቅ አጓጉል ቦታ መደቡኝ፣መበቀላቸው ነበር።ሁሉንም እርግፍ አድርጌ እዚ ያለውን ወንድሜን ምንም አይነት ስራ ቢሆን እንዲፈልግልኝ ነገርኩት።መጠበቁ ስላላስቻለኝ ለመሄድ ተነሳሁ።እናትሽ እንድሄድ አልፈለገችም ነበር።እኔም እንዴት ያለሁበትን ሁኔታ እያወቅሽ አትሂድ ትይኛለሽ በማለት መስማማት አቃተን።በሽማግሌ ምናምን ልታስቀረኝ ሞከረች።ጭራሽ ሶስተኛ ወገን በመግባቱ እንዲያው ሳንስማማ ብድግ ብዬ ወደ እዚህ መጣሁ።" የመሰልቸት ገፅታ ፊቱ ላይ ብልጭ አድርጎ ፈጠን ፈጠን እያለ ማውራቱን ቀጠለ።
"...ከዛ በቃ መጀመሪያም ተጣልተን ስለሄድኩ መደወሉንም ስልክ ማንሳቱንም ተወችው።እኔም በጊዜ ሂደት እየተውኩት እና እየረሳኋት መጣሁ።ከእሙ ጋር ተዋወኩ።ተጋባን።አዲስ ህይወት ጀመርኩ።አደግ ስላልሽልኝ ከአንቺ ጋር ለማውራት ብቻ ነበር ምደውለው።አበቃ እሷም የራሷን ኑሮ ጀመረች እኔም እንደዛው።" ትከሻውን ሰበቀ


"ፐ!! በቃ አደል? ሲጀመር ፍቅር እንዲህ በአንዴ ይፋቃል እንዴ? እንዴት ቻልክበት? እሷ እኮ ከብዷት ነው የቀረው።አንተ አዲስ ህይወት ስትጀምር ነበር እሷ ጭለማዊ ኑሮን የጀመረችው።ብታያት እኮ አታውቃትም።ኑሮ እና ችግር ደቋቁሶ መልኳን ረግጦ ከ'ነበር' መቃብር ስር አውርዶታል።መጀመሪያ የነበረችውን ውብ ሴት ተቀብለህ የወየበ ፊትን አስታቅፈሃት ሄደሃል።አንተ አዲስ ስትለው ለእኛ ምፅዓት ሆኖብናል።እንዴት በአንዴ ይሄ ሁሉ?" ሲቃ ተናነቀኝ።እሱም ዝም አለ።እኔ ግን ቀጠልኩ
"...እናቴ ቆንጆ እና መልካም ሴት ነበረች አንተ ግን ለዚች ሴትዮ ስትል ተውካት አይደል?"
"ኪዳን! ይሄ የኔ ውሳኔ ነው።በእሙ ምክንያት አይደለም።እሷ እዚህ ውስጥ የለችም በራሴ ነው ሁሉን ያረኩት።"


ከዚህ በኋላ ምንም ማለት አልቻልኩም።የምለው ስለሌለ አልነበረም።በችግር የተቆላንባቸውን ጊዜያት አልነገርኩትም።አባትነቱ አምሮኝ በልጅ አፌ ምን ያህል ጊዜያት ለእግዚአብሔር "አባቴን መልስልኝ እባክህ" እንዳልኩት አልነገርኩትም።ባዶ ቤት ያለ ምግብ ቀርተን ስኳር ጠጥተን እንደዋልንም አያውቅም።ሌሎች ልጆች አባትሽስ ሲሉኝ የለም ማለቱ ምን ያህል ያደክም እንደነበርም አላወጋሁትም።እማምዬ ያየችውንም ፈተና አልሰማም።ግን በቃ ዝምምም አልኩ።ያን ማወቁ አይገ:ባውም ነበር ምክንያቱም እሱ አዲስ ህይወት ውስጥ ነውና።ፎቶዎቹን እንዳንጠለጠለ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ።


ያንን ምሽት እያሰብኩ ፀጥ ብዬ ቆይቼ ኖሮ እናቴ ወዝውዛ አባነነችኝ
"ኪዳን? እንቅልፍሽ ከመጣ ነይ ውጪና ተኚ።" በእይኗ እያሰሰችኝ በጣቶቿ እየዳሰሰችኝ ነበር።
"እማ?"
"እእ?"
"አባቴ እኮ አግብቷል።" ስሜቷን ለማንበብ ሞከርኩ።ምንም የለም።
"ያግባኣ መቸም ቆሞ አይቀር።" ፈገግ አለች።ምታዝን ወይ ምትደነግጥ ነበር የመሰለኝ።ለካ መጠበቁ አድክሟት ተስፋ ቆርጣለች።
"ግን እኮ አንቺ ቆመሻል።"
"ኸረ ተኝቻለሁ ሂሂሂ" አቤት ሳቅ በዚህ ፈገግታ ስንቱን አበሰችው፤ስንቱን ሸፈነችው፤ስንቱንስ ሸኘችው።ከቦርሳው ጎን ኪስ ውስጥ ለብቻ ያስቀመጥኳትን ፎቶ አወጥቼ ሰጠኋት ጋደም ካለችበት ቶሎ ቀና ብላ ተቀበለችኝ።


"ኧረረረ አንቺ እንዴት ነው ሚያምሩት።በሰርግ ነበር እንዴ? እእ?" ምን እየሆነች ነው አልኩ።
"አው ግን ያው ደስ ማይል ነበር።ሚዜዎቹ አያምሩ ፣ እንግዶቹ ራሱ ሲደብሩ።ቪዲዮውን ብታይውማ በmakeup የተንደሰደሱ ሚያሳስጠሉ ሰዎች ናቸው የሞሉት።" ሁሉን ነገር አጣጥዬ መንገሬ እኮ ነው።እንዳይሰማት።
"ጭራሽ ትልቅ ሰርግ ነበር እንዴ?"
"አዎ ግን ይደብራል እማ ቢቀር የሚያስብል ነበር።" አልተሳካልኝም።እንደውም ለማጣጣል በሄድኩት ርቀት ሁሉ ምን ያህል ሰፊ ድግስ እንደነበር ነው ሳወራ የነበረው።ረጅም ደቂቃዎችን ፎቶውን ስታይ ቆየች።ፊቷ ላይ ምንም የለም።ያዘነች አትመስልም።ለካ ተስፋ ነበር ስሜት የሚሰጠው።ተስፋ ያጣህበት ነገር ልክ ስርዓት ነጥብ እንደሌለው ድርሰት ነው።መቆሚያው ማያታወቅ ስሜትን የማይጭር።


"እማ..ምነው?"
"ምንም የሆነ ነገር እያሰብኩ ነው።"
"ምን እማ? ደበረሽ እንዴ?ባላሳይሽ ይሻል ነበር አይደል?"
"ኪዳን ምን እያሰብሽ እንደሆነ አውቃለሁ።እኔ በጭራሽ አልተናደድኩምም አላዘንኩምም።መጀመሪያውኑም አውቀው ነበር።ያፈቀረኝን ሰው ፍቅሩ ሲመነምን ማወቅ አልከበደኝም።ምንም ሙጣጭ ፍቅር አሁን በልቤ የለም።አባትሽ ስለሆነ ግን እወደዋለሁ።ትዝታ መልካም ነው።እሱ እንደሄደው ትዝታውንም ይዞብኝ ቢሄድ ኖሮ እንዲህ ባላልኩ ነበር።እኔ ተስፋን በልቤ አላኖርኩም።ያኔም አግብቻለሁ ሲለኝ አምኜው ነበር።ከዛ በፊት ነበር ልቡን ሌላ እንዳጠፋው ያወኩት አሁን ወይም እሱ ሲለኝ አይደለም።...ዋናው ላንቺ መኖሩ ነው።" አለች።
"እና ለምን ታለቅሻለሽ እሺ?"
"ታውቂያለሽ ሰርግ ያስቀናኛል።ቬሎ መልበስ እሻ ነበር።የሰው ሰርግ ራሱ እንባዬን ያስመጣዋል።ነጭ አለመልበሴ ይቆጨኛል።በተለይ ከእሱ ጋር እንዲሆን እመኝ ነበር። እና አሁን ላይ ምኞቴን አብሬ ያለምኩት ሰው እንዲህ ሆኖ ሳየው ቀናሁ።" በአንዲት ዘለላ እንባ ቋጨችው። ስንት አመት ያነባችለትን አንዲት እምባ መዝጊያ ሆነችላት።


✨️-----አበቃ።ይህ ከብዙ የህይወት ቅዳጅ ገፆች አንዱ እንጂ ሙሉው አይደለም።መኖር ግን ይቀጥላል።-----✨️

✍️🏼ቃል

https://t.me/Piece_of_pages
https://t.me/Piece_of_pages

20 last posts shown.

924

subscribers
Channel statistics