✨️✨️✨️
"ምን ሆነሻል?" የያዘችውን መፅሀፍ ከሩቅ አይቶታል።ከ15 ቀን በፊት ከራሱው የወሰደችው መፅሀፍ፤ምን ሆኛለሁ?ሰላም ብሏት ቁጭ አለ።ቀኑ ቅዳሜ ነው፤"ቅዳሜ -ዘ-አቢዳን"። በየሳምንቱ ቅዳሜ ይገናኛሉ።ስለ ሳምንቱ፣ስለ መፅሀፍ፣ስለ ቤተሰብ፣ሶሻል ሚዲያ ላይ ስለሰሙት፤ስለ ኳስ(ስለዚስ እሱ ያወራል እንጂ እሷ አዳማጭ ነች። ) ሳይቀር ሚወያዩበትን ቀን፤ "ቅዳሜ ዘ አቢዳን"(ኪዳን እና አብርሃም ሲቀየጥ ሚወጣ ቃል ነው።ሌላ ትርጉም ይኖረው ይሆን?) ብለው ሰይመዋት በየሳምንቱ ይዘክሯታል ።እነሆ ዛሬም የዘውትር መዳረሻቸው የሆነው ካፌ ተገናኝተዋል።
በአይኑ አስተናጋጅ እየፈለገ "እንዴት እየሄደ ነው?እንዲህ መፅሀፍ ላይ ስትቆዪ አይቼሽ አላውቅም?ከበደሽ እንዴ!" ሚከብድ መፅሀፍ እንዳልሆነ ያውቃል።እስካሁን አለመጨረሷ ግን የምርም ገርሞታል። አስተናጋጁ መጥቶ ኖሮ ለሁለቱም ማኪያቶ አዘዘ።ከአፍታ በኋላም አስተናጋጁ የታዘዘውን ይዞ መጣ።
"የሳይኮሎጂ ይዘት ያለው መፅሀፍ ሳነብ ይሄ የመጀመሪያዬ አይደለም ታውቃለህ።በዛውም ልክ እንዲህ ያሉ መፅሀፍቶችንም አላዘወትርም።ልብወለድ ማነበውን ያህል እንዲህ አይነት ይዘት ያላቸውን 3 ወይም 4 ቢሆን ነው ያነበብኩት።አይገርምህም ይሄ ግን ተለየብኝ።" የቀረበላትን ማኪያቶ ፉት አለች።የዛሬው የመክፈቻ ርዕስ ይሄው መፅሀፍ መሆኑ ሆነ።
የመጀመሪያውን ዕትም 2016 ላይ ገዝቶ ከአንዴም ሁለቴ አንብቦታል።ከዚህ በፊት እንድታነበው ጠቆም አርጓት የነበር ቢሆንም ችላ ብላው ነበር፤በዛ ሰዓት የምትመርጠው ይዘት ስላልነበር።ከሁለት ሳምንት በፊት ግን በየሶሻል ሚዲያው የዝናው መቀጣጠል ስቧት "ልሞክረው" በሚል ስሜት ጠይቃው ሰጥቷት ነበር።
"ምን ተለየብሽ?" እሱም በረድረድ ያለውን ማኪያቶ ፉት ብሎ ትኩረቱን እሷ ላይ አረገ።
"አጠቃላይ ይዘቱ።እያንዳንዱ ርዕስ የተለያዩ ሰዎችን እያስታወሰኝ ነበር ማነበው።እስከዛሬ በዙሪያዬ የነበሩ ሳሉን አይቼ ኒሞኒያውን ሳልረዳላቸው በጭፍን treat ያረኳቸውን ሰዎች፤ከዚያም አልፎ መጥፎ ስም ሰጥተን 'እሷ/እሱ እኮ ፀባዩ/ይዋ ነው።' ብለን እስከነ ኒሞኒያቸው አንቅረን የተፋናቸው ሰዎች ስንት አሉ።የሰዎች ባህርይ አሁናዊ ሳይሆን ትላንታዊ መሆኑን፤ በአጠቃላይ አሁን ላይ ሰዎችን የማይበት እይታ ከመፍረድ ላቅ ያለ ሆኗል።"
"Interesting የገመትኩትን ሀሳብ ነው በትክክል የተረዳሽው።ግን አንቺስ ኪዳን?"
"እኔ ምን?"
"አንቺስ ምን ሆነሻል? መፅሀፉ ምን ሆነሻል ብሎ ነገረሽ።ከሌሎችም ባሻገር ራሳችንን እንድንጠይቅ የሚገፋፋ ሀሳብ ይመስለኛል።"
"እኔ...አብርሽ አላውቅም።የኔነቴ ማንነት በቅጡ ማውቀው አይመስለኝም።you know መፅሀፉ በደንብ ነው ችግሮቹን ያብራራቸው።But, I just can't find myself in this book." የምሯን ነበር።የምርም መፅሀፉ የጠቀሳቸው ሳሎች እንዲሁም ኒሞኒያዎች ከእሷጋ የሚጣጣሙ አልነበሩም፤ወይም አልተራዳችውም።
"ህምም...ምናልባት 'ደና ነኝ/ምን ሆንኩ?' ከሚሉት ወገን ራስሽን አስቀምጠሽው እንዳይሆን እእ?"
"No no, I know ደና እንዳልሆንኩ።ግን በቃ እኔን ወይም ትላንቴን የሚመስል ሀሳብ ማግኘት አልቻልኩም። "
"ምናልባትም ራስሽን አላወቅሽም ይሆናል።ሰዎች self knowledge የሚለውን ሀሳብ እንደ ተራ ነገር ሲቆጥሩት አያለሁ።ወደ ውስጣቸው መመልከትን አይሹም።እንደውም ስለ ራሳቸው እነሱ ከሚያስተውሉት በላይ ሌሎች observe የሚያረጉት ይበልጣል።አንዳንድ ሰዎች አጋጥመውሽ አያውቁም በጣም ንዴታም።ንዴት ስልሽ በጣም የሚረብሽ፣ግኑኝነትን የሚያበላሽ እና even ሌሎችን ሳይቀር negative energyን የሚያጋባ ንዴት ይዘው Anger issue እንዳለባቸው ስትነግሪያቸው 'ኸረ እኔ እንደዚህ አይደለሁም።ስራው ነው ፣ሚስቴ ናት፣ባሌ ነው እንድናደድ የሚያረጉኝ እንጂ እኔ እንደውም ሰላማዊ ሰው ነኝ' ብለው ይከራከራሉ ወይ ደሞ ስለ እነሱ መጥፎ ንዴታምነት የሆነ ሰው ሲያወራ ሲሰሙ ወደ ውስጣቸው ከመመልከት ይልቅ ራሳቸውን ከእውነታው ያርቃሉ።እንደውም ያወራውን ሰው ሳይቀር ስለ እነሱ መጥፎ ነገር ለመንዛት እንደተላከ ጠላት ይፈርጁታል። " በማኪያቶው ጉሮሮውን አርሶ የእሷን ሀሳብ ለመስማት ዝም አለ።
"ልክ ነህ እንደውም የራሳቸውን ነፀብራቅ በሌሎች ውስጥ ስለሚያዩት አሁንም ቢሆን ወደ ራሳቸው ከማዘንበልና ከመመልከት ይልቅ ትከከለኛ ማንነታቸውን ያሳያቸውን ሰው ይርቁታል፤ያርቁታል።" አለችው
"ለምን ይመስልሻል ያንን ሚያረጉት?"
"ofcourse ያላቸውን መጥፎ ስብዕና ሲያዩት ያስፈራቸዋል።ይሄ እኔ አይደለሁም ይላሉ so ሚያስፈራ እውነት ከመጋፈጥ ይልቅ ምቹው ውሸት ላይ ይንተራሳሉ።"
"በትክክል።ለዛ ነው ራስን መረዳት፤ወደ ራስ ውስጥ መመልከት አስፈላጊ ሆኖ ሚገኘው።አንቺ ሳታጤኝው የቀረሽውን ባህርይ ሌላው ቢነግረሽ ወይም ሊያሳውቅሽ ቢሞክር already ስለማታውቂው ሰው እንደሚያወራ አርገሽ ልትረጂው ትችያለሽ።Every little feeling, every little childhood memory does matter. You don't know መቼ affect እንደሚያረግሽ።ውስጥሽ እንዳለ ማታውቂው ስሜት የሆነ ጊዜ ላይ ገንፍሎ ወጥቶ አንቺንም በዙሪያሽ ያሉትንም ሊያቃጥል ይችላል።" ትንፋሽ ወስዶ አጤናት።ሀሳቡን እያብላላችው ነው።እሷም በበኩሏ ዝም አለች። ያለው ነገር ትክክል ነበር።
"ምናልባት...አንቺም ማመን ያልፈለግሽው ወይም የምርም ያላጤንሽው አንቺነት ይኖርሽ ይሆናል።አንዴ ለራስሽ እድል ስጪውና ለመረዳት ሞክሪ።መፅሀፉን ስታነቢ እንዳሰብሻቸውና እንደተረዳሻቸው ሰዎች ራስሽን መርምሪው 'ምን ሆኛለሁ?' ብለሽ ራስሽን ጠይቂ።"
ሀሳብ ውስጥ ዘፈቃት። የምርም 'ምን ሆኛለሁ?' ብላ አሰበች።
✍️🏼ቃል
https://t.me/Piece_of_pageshttps://t.me/Piece_of_pages