የጥበብ ብልጭታ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


በዚህ ቻናል የተለያዩ ተከታታይ ታሪኮች ና መፅሐፍትን በ pdf ያገኙበታል

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


እመነኝ እዚህ ምድር ላይ ትልቁ ሀብት አንተ ነህ የገዛህዉ ቤት የምትነዳዉ መኪና ያጠራቀምከዉ ገንዘቡ ሌላም አሉኝ ከምትላቸዉ ነገሮች ሁሉ አንተ ትበልጣለህ እነሱን ነገሮች ሁሉ ያመጣሀቸዉ አንተ ነህ ስለዚህ ሁሌም የምተማመነዉ ባለህ ነገር ሳይሆን በራስህ ይሁን ወፍ ተመልከተሀት ከሆነ ዛፋን አምና ሳይሆን ክንፋን አምና ነዉ ቅርንጫፋ ላይ የምትቀመጠዉ አንተም ምንም የለኝም ብለህ የምትጨነቅ ወንድሜ አንተ እኮ አለህ ትልቁ ሀብት ራስህ ነህ የሚታየዉ ነገር ያመጣዉ የማይታየዉ የአንተ ተስፋ እምነት ህልም ልፋት ዉጤት ነዉ ስለዚህ ዋናዉ አንተ መኖርህ ነዉ አትጨነቅ


ምን ሆኛለሁ.pdf
41.0Mb
እዉነቱን ለመናገር ይህን መፅሐፍ ልልቀቀዉ አልልቀቀዉ ብዙ አስቤበታለሁ ከታተሙ ቅርቡ ጊዜ የሆናቸዉን መፅሐፍት በ pdf መልቀቅ ተገቢ ነዉ ብዬ አላምንም ግን ደግሞ እንደ ሀገር መፅሐፍ ገዝቶ የማንበቡ ባህላችን ደካማ ነዉ ይህ መፅሐፍ ደግሞ ሁሉም ሰዉ እንደ ግዴታ ሊያነበዉ የሚገባ መፅሐፍ ነዉ ይህን ካነባችሁ በሀላ ስለራሳቹ ና በዙሪያቹ ስላሉት ሰዎች አመለካከታቹ አለመቀየር አይችልም ከቻላችሁ ገዝታቹ አንብቡት




Forward from: የጥበብ ብልጭታ
ግርምቢጥ 🌀

​ክፍል አምስት 📖

​✨ የቅዱስ ዮሐንስ ገዳም ውስጥ ዛሬ ዓመታዊ በዓሉ የሚከበርበት ቀን ስለሆነ በገዳሙ ውስጥ ያሉ ምእመናን እና በገዳሙ አቅራቢያ የሚኖሩ በርካታ ምእመናን በሌሊት ማህሌት ገብተዋል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ሰለሞን ነው። በቆመበት ከእንቅልፍ ጋር ይታገላል። ጠንከር ብሎ ነው የሰነበተው፤ ከአለም ጫጫታ ርቆ ከራሱና ከመንፈሱ ጋር ብቻ በገዳም ቆይታው ራሱን አዳምጧል። መንፈሳዊ ህይወቱን አድሷል፤ ከፈጣሪውም ጋር ታርቋል። ⛪️🙏

​🕯️ አሁን ግን ሀሳቡን ሰብስቦ ማህሌቱን መሳተፍ ተሳነው። ከእንቅልፍ ጋር ሲታገል ቆይቶ እንቅልፍን አሸነፍኩ ሲል ደግሞ በሀሳብ ባህር ሰመጠ። ድል ያለ ሰርግ... እናቱ በደስታ ሰክረው ከፍ ዝቅ ሲሉ... እትዬ ብርቄ በኩራት ተዘፍቀው ታዳሚውን እያዩ እጅ ሲነሱ... ድንገት ያለበትን ረስቶ ፊቱ ላይ እስኪነበብ ድረስ በስጨት አለ። የማይሆን ሀሳቡ ቅዠት ይመስል በሚሰማ ድምፅ ተቁነጠነጠ። 💭😟

​💧 ድንገት በሁለቱም አይኖቹ እንባ መፍሰስ ጀመረ። "ከቆይታ በኋላ ድኛለሁ ስል፣ ወጣሁት ያልኩት ህመም ተመልሶ መጣ" እያለ ሀሳቡን ወደ ሌላ ለማድረግ ሞከረ። የሰነበተበት የቤተክርስቲያን ስርአት ረዘመበት። እንደምንም የቤተክርስቲያኑን ስርአት ከጨረሰ በኋላ ወደ በአቱ ሄደና መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ጀመረ። 📖⛪️

​📖 በአጋጣሚው የገለጠው መጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 29 ቁጥር 35 ላይ አረፈ። የያዕቆብና የራሄል ታሪክ... ያዕቆብ ራሄልን ወደደ፤ ሊያገባትም ተመኘ። እሷንም ለማግባት ለአባቷ ሰባት አመት አገለገለ። ነገር ግን የራሄል አባት ለያዕቆብ ራሄልን ሳይሆን ታላቋን (ሊያ) ሰጠው። የፈለገውን ያላገኘው ያዕቆብ ይህን ጉዳይ ሲጠይቅ፣ ራሄልን ለማግኘት ሌላ ሰባት አመት ማገልገል እንዳለበት ተነገረው፤ አደረገውና አገኛት። 📜✨

​🎯 ሰለሞን ይህን ሲያነብ ስሜቱ እየተቀያየረ ነበር። ልክ የታሪኩ መጨረሻ ላይ ሲደርስ "ይችላል!" ብሎ አጨበጨበ። "ልክ ነኝ! አደርገዋለሁ!" እያለም ደጋግሞ ጮክ ብሎ ተናገረ። ቆይቶ ነበር ወደ ራሱ መለስ ሲል ያለበትን ያስተዋለው። በሀፍረት አንገቱን ደፍቶ ተቀመጠ። "ካሁን አሁን ድምፄን የሰሙ ሊገስፁኝ ይመጣሉ" በሚል መሳቀቁ ሊገድለው ደረሰ። 😰🤐

​...ይቀጥላል...




መኖር ወደ ሞት የሚደረግ ፈጣን ጉዞ ነዉ ገና የተወለድን ቀን ወደ ሞት የምናደርገዉ ጉዞ ይጀምራል የ ኖርንበት አመት በጨመረ ቁጥር የምንኖርበት አመት እየቀነሰ ይመጣል
የምንኖረዉ በእግረ መንገድ ነዉ ወደ ሞት በምናደርገዉ ጉዞ እግረመንገዳችን እናማራለን በእግረ መንገድ ስራ እንጀምራለን እናገባለን እንወልዳለን ብለን ብለን ጉዞአችንን እንጨርሳለን ።


ዙቤይዳ - አሌክስ አብርሃም.pdf
33.8Mb
የቻናላችንን የመጀመሪያ መፅሐፍ የ አሌክስ አብርሀምን ዙቤይዳ አድርገነዋል ተዝናኑበት


ግርምቢጥ 🌀

​ክፍል አራት 📖

​✨ ጴጥሮስ የታምራት ሙዚቃ ልቡን ለሁለት ሰነጠቀው። አመነታና ያወጣውን ስልክ ወደ ኪሱ መልሶ በሀሳቡ ባህር ነጉዶ ሳያስበው ሰዓቱ አለፈ። ከሀሳቡም ሲመለስ የሰዓቱን መንጎድ ሲመለከት በድንጋጤ ከካፍቴሪያው ወጥቶ ወደ ቤቱ አመራ። እቤት እንደደረሰ ግን የካፍቴሪያው ሀሳብ በድጋሚ በጭንቅላቱ መመላለስ ጀመረ። አስቦ አስቦ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወሰነና ደወለላት። 🎶🏃‍♂️

​📞 ማክዳ፦ "ሄሎ"

​ጴጥሮስ፦ "ሄሎ ማኪ"

​✨ ማክዳ ምንም እንኳን ሁሉም ማኪ እያለ ቢጠራትም የጴጥሮስ ሲሆን ግን ይለይባታል። የሚጠራት ሳይሆን በስሟ የተጠራ ልዩ ዜማ የሚያዜምላት ነው የሚመስላት። ከደወለላት ዓመታት ተቆጥረዋል። የሷንም ስልክ ማንሳት ስላቆመና በሌላ ስልክ ብትደውልም እሷ መሆኗን ሲያውቅ ስለሚዘጋው ተስፋ ቆርጣ ትታዋለች። ብቸኛ ነገሩን ማስተካከል አቅም አለው ብላ የምታስበው ሰለሞንም "አይሆንሽም ተይው" ከማለት ውጪ ሌላ ምላሽ ከአንደበቱ ሲጠፋ ጭርሱን ተስፋ ቆርጣ ነበር። እና ይህ ሰው ነው ከአመታት በኋላ ስሟን እየጠራ የሚገኘው። 💔📱

​"ተደገመ ማኪ"

​እየተርበተበተች፦ "አ...አ...አ አቤት"

​"እንዴት ነሽ?"

​"አለሁ" አጭር መልስ ሰጠች።

​"አውቀሽኛል?"

​"አዎ"

​"ፈልጌሽ ነበር" የጴጥሮስ ድምፅ ላይም ፍርሃት ይነበባል። 😟

​"እና?"

​"ላግኝሽ"

​"እሺ"

​🚶‍♂️ ንግግሩን መቀጠል ከበደው፤ ስልኩን ለመዝጋት ቸኮለ። "እሺ በቃ ቦታውንና ሰዓቱን ቴክስት አደርግልሻለሁ" የሷን ምላሽ ሳይጠብቅ ዘጋውና ራሱን ለማድመጥ ሞከረ። "ምንድነው የሚሰማኝ?" የሚሰማውን እንኳን መለየት አቃተው። እንደ ምንም እየተደናበረ ከሁለት ሰዓት በኋላ ሰፈራቸው በሚገኙ ካፍቴሪያ እንገናኝ የሚል ቴክስት ላከላት። ያቺ ቤት ሁለተኛ ቤታቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፤ ለዛ ነበር እሱን ቤት የመረጠው። 🏠☕️

​⏳ ሰዓቱን ጠብቆ ወደተቀጣጠሩበት ቤት ሄደና ቦታ ያዘ። ማክዳ የለችም፤ 30 ደቂቃ አለፈ። ግን እሱ በስልኩ ቲክቶክ ላይ ተጠምዶ ስለነበር አልታወቀውም። ከስልኩ አይኑን የነቀለው ማክዳ መጥታ አጠገቡ ስትቀመጥ ነው። ተርበተበተ፤ ቃሉ ከአፉ ለመውጣት ሰነፋ መፋጠጥ ሆነ። በዚህ መሀል ዝምታውን ሰብራ፦

​"ለምንድነው የፈለከኝ?" አለችው። 👁️

​"ኧ... ደህና ነሽ?" አላት።

​"አለሁ! መቼም ለዚህ አይደለም የፈለከኝ" እንደ አራስ ነበር ተቆጣች። 😡

​"እራሱን ለማረጋጋት እየሞከረ፦ "ልክ ነሽ ግን ያው ሰላምታ ይቀድማል ብዬ ነው"

​💔 የሱን ንግግር እንዳልሰማች ሆና "ለምንድነው የተውከኝ?" የሚል ድምገተኛ ጥያቄ ጠየቀች። ያላሰበበት ጥያቄ ስለሆነ መረጋጋት ጀምሮ የነበረውን ድጋሚ መረበሽ ሆነ። ጥያቄውን ድጋሚ እያነሳች እንባዋ በሁለቱም አይኖቿ መፍሰስ ጀመረ።

​"እንዴ ማኪ" አላት።

​💧 "አታባብለኝ! መልስ ብቻ ነው የምፈልገው። እንዲህ ፊት ለፊትህ ተቀምጬ ይሄን ጥያቄ የምጠይቅበትን ቀን ሁሌም እጠብቀው ነበር። እባክህ መልስልኝ!" አለችው ።

እየተርበተበተ ​ያላቀደበትን ነገራት፦ "አንተ ልክ ነህ አትሆነኝም እኔ ነኝ የተሳሳትኩት" ብላ በተቀመጠበት ጥላው ሄደች። 🏃‍♀️🚶‍♂️

​ክፍል አምስት ይቀጥላል...




ግርምቢጥ 🌀

​ክፍል ሦስት 📖

​✨ ቤተክርስቲያን እንደደረሱም እትዬ ብርቅነሽ ነገሩን ቁርጥ አደረጉት። "ነገ ሽማግሌዎቹ ይመጣሉ፤ ትዳሩን እንቀበላለን" አሏት። ዳናዊት ያልጠበቀችው ባይሆንም በድንጋጤ ተዋጠች። "እንዴ እማ! ይህን መወሰን ያለብኝ እኮ እኔ ነኝ። አሁን ስርአቱ እንዲህ አይደለም፤ አውቄውና ወድጄው ነው ሽማግሌ የሚላከው" ብላ በትዝብት እያየቻቸው ለመከራከር ሞከረች። ⛪️🤨

​👵 እትዬ ብርቄ ግን አመረሩ። "ስርአቱስ እሱ አልነበረም! ዘመናዊነት ብላችሁ አበላሻችሁት እንጂ 'ተዋውቀን፣ ተፋቅረን' እያላችሁ ሰውነታችሁን በዝሙት እያረከሳችሁ ነው። እኔ ገና ሳልወለድ፣ ከእናቴ ሆድ ሳለሁ ነው የታጨሁት። አባቴ ከቅርብ ወዳጁ ጋር ሴት ልጅ ስትወልድ ለልጄ ብለው ቃል የተገባቡት ነው። ምን ጎደለብኝ? አተረፍኩ እንጂ አልከሰርኩም!" አሏት። በስተመጨረሻም ትዳሩን መቀበል ወይም የእሳቸውን እናትነት ማጣት ያላት ምርጫ እንደሆነ አስረግጠው ነገሯት። 👵🚫

​ዳናዊት ባትስማማም ተስማማች። ምሽቱን እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር አደረ። ጴጥሮስና ኤልዳናም በጉዳዩ ላይ ሀሳብ እንዲሰጡ አልተፈቀደላቸውም። 🌙🛌

​💍 በነጋታው ዳናዊት ከሰአት ስራ አስፈቅዳ ወደ ቤት ተመለሰች። የሽምግልና ስርአቱም በባህሉ መሰረት ተከናወነ፤ ለሰርጉም የአንድ ወር ቀጠሮ ተቆርጦ ተለያዩ። ነገር ግን አሁንም ሰለሞን ሄደበት ከተባለበት ገዳም አልተመለሰም። የሰለሞን መጥፋት ነገሩን ለሁሉም ግራ አጋቢ አድርጎታል። ዳናዊት ከዳኒ ጋር ያላት ግንኙነት ከመደዋወል አልፎ ወደ ተደጋጋሚ መገናኘት አምርቷል። አንድ ቀን ከስራ በኋላ ሻይ ቡና ተባብለው ወደ ቤቷ ከሸኛት በኋላ፣ መለያያቸው ላይ ሳታስበው ከንፈሯን ሳማት። 💋😲

​💧 በድንጋጤ "ውሃ" ሆነች። ምንም ማድረግ አልቻለችም፤ በዛው ቀን ማታ ዳኒን ደግማ ላለማግኘት ወስና ነበር፤ ነገር ግን አልቻለችም። ሁሉንም ከአቅሟ በላይ የሆነባትን ነገር ጊዜ ይፍታዉ ብላ ለጊዜ ሰጠችው። ጊዜያት ነጎዱ፣ ሰርጉም ተቃረበ። እትዬ ብርቄም ከሰለሞን ቤተሰቦች ጋር እየተናበቡ ወገባቸውን ታጥቀው ድግሱን ጀማምረውታል። 🥘👵

​🚶‍♂️ በዚህ ሁሉ ውስጥ ዝምታው ልክ እንዳልሆነ ያመነው ጴጥሮስ ወደ ሰለሞን ቤተሰቦች ሄደ። ሰለሞን በትክክል የት እንደሚገኝና ሂደቱ እንዴት እንደተጀመረ ለማጣራት ሞከረ። ቤተሰቦቹ ግን "ሰለሞን ራሱ ነው 'ልንጋባ ወስነናልና ሽማግሌ ላኩ፣ እኔ ለትዳሬ ፀሎት ለማድረግ ገዳም መሄድ አለብኝ' ያለን" የሚል መልስ ሰጡት። የሰለሞን የት እንዳለ አለመታወቅ ግን ለጴጥሮስ ሊዋጥለት አልቻለም። ❓🤔💭

​💔 ጴጥሮስ ከነሱ መልስ አንድ ካፌ ቁጭ ብሎ እንዲሁ ሲብሰለሰል 😔 አንድ ሲሸሸዉ የነበረዉን ነገር ለማድረግ ወሰነ፤ የልጅነት ፍቅረኛዉን የሰለሞንን እህት የቀድሞ ፍቅሯን ቀስቅሶ እዉነቱን ማወጣጣት። ✊🔥

​የሰለሞን እህት ማክዳ ለጴጥሮስ የመጀመሪያዉ ነች። ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀፋት፣ የያዛት፣ ያወራት፣ የሳማት የሄዋን ዘር 👩‍❤️‍👨። ገና 10 ኛ ክፍል እያለ ነበር 8 ኛ ክፍሏ ማክዳ ጋር በፍቅር እፍ ያለዉ። በሷ ምክንያት ከሰለሞንም ከእህቶቹም ጋር ደጋግሞ ተጣላ 😠። በእሷ የመጣን በአይኑ እንደመጣ ቆጠረዉ። በሰለሞንና በማክዳ የወንድምነትና እህትነት ጠብ ዉስጥ ዘራፍ ባይ ሆነ 🛡️። በማክዳና በእህቶቹ በተለይ በእኩያዋ ኤልዳና ኩርፌያ ዉስጥ ተደርቦ አኩራፊ ሆነ። የእናቱን "ሁለተኛ ከእሷ ጋር ባይክ" ቁጣ ከሰፈሪ የወላጅ ግሰፃ ይልቅ እንደ ደጋግሞ የሚሰማዉ ሙዚቃ ቆጠረዉ 🎧። በሷ ቤተሰቦችም "ልጃችንን አባለገ" በሚል እንደ እርጉም ዉሻ ተጠላ 🐕🚫። ብቸኛ ፌት ያልነሳዉ ጓደኛዉ ሰለሞን ብቻ ሆነ። 🏠🤝

​በእንዲህ አይነት ሁኔታ 12 ን ጨርሶ ሐዋሳ ዩንቨርስቲ ገባ። ማክዳም አስረኛ ክፍል ደረሰች። በሱ ከሰፈሩ መራቅ ቤተሰቦቿ የመገላገል ስሜት ተሰማቸዉ፤ ነገር ግን እነሱ በስልክ ቀጠሉ 📞💞። ጴጥሮስ በዩንቨርስቲዉ ከገኛቸዉ ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ቀስ በቀስ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ያልተገባ ድርጊት ማድረግ ጀመረ። በዚህ በሚሰማዉም   ፀፀት ማክዳን ራቃት 😞💔። ነገር ግን በዚህ ድርጊት ጠልቆ ከመግባቱ በፊት እራሱን አወጣ፤ ነገር ግን ከልቡ ወዳልወጣችዉ ማክዳ ዳግመኛ መመለስን አልፈለገም 🛑❤️‍🩹። እስካሁንም በእህቱ ጉዳይ እጁን ያላስገባዉ ይህን ላለመቀስቀስ ነበረ።

​አሁን ግን ወስኗል፤ ለማክዳ ለመደወል ስልኩን ልክ ሲያነሳ 📱  😰 ከተቀመጠበት ካፍቴሪያ ጎን ካለ ሱቅ የሚወጣ አንድ ዘፈን ጆሮዉ ጥልቅ አለ 🎶👂፦

​"እንኳን ልሄድ እኔ ራሴ ካለችበት፣
መጣች ቢባል ያን በደሌን ረስታው ድንገት፣
አይን የለኝም አይኗን በአይኔ የማይበት... 🙈

ትቻት ሄጄ ጥቅሜን አስበልጬ፣ ንፁህ ልቧን ያን ፍቅሯን ረግጬ... 💔

ሰላሟን ህመም ልዘራበት፣ አልሄድም ረስታኝ ትኑርበት!" 🚶‍♂️🕯️

​...ይቀጥላል...




ግርምቢጥ 🌀

​ክፍል ሁለት 📖

​✨ በነጋታው ከስራ መውጫ ሰዓት ላይ ደወለላትና ተገናኙ። ትንሽ ጊዜም አብረው አሳለፉ፤ ግን ብዙ ነገሮቹ አልጣሟትም። ከላይ ሲታይ የመሳቡን ያክል ስትቀርበው ምቾት አልሰጣትም። ዳኒ ረጅሙን ጊዜውን ያሳለፈው ለንደን ስለሆነ ኢትዮጵያዊነት ይርቀዋል። የኢትዮጵያ የሆነ እሱ ጋር ያለው የቆዳ ቀለሙና ቋንቋው ብቻ ነበር። ☕️❌

​🏠 እቤት እንደገባችም ሁሉም ከየዋሉበት ተሰብስበው የቀን ውሎአቸውን እያወሩ ባሉበት ሰዓት በሩ ተንኳኳ። ሦስት በሰፈሩ ውስጥ የሚታወቁ ሰዎች ገቡ። በዚህ ሰዓት የነዚህ ሰዎች መምጣት ግራ እንደገባቸው እንዲቀመጡ ጋበዟቸው።

የመጡትም ሽማግሌዎች "የመጣንበትን ጉዳይ ሳንናገር አንቀመጥም" አሉ። 🚪

​👵 እትዬ ብርቄ በድንጋጤ አይናቸውን ሁለት ሴት ልጆቻቸው ላይ አንከባለሉ፤ ልጆቹም በድንጋጤ እርስ በርስ ይተያያሉ።

"ምንድን ነበር የመጣችሁበት?" አለ ጴጥሮስ የእናቱን መፍዘዝ ተመልክቶ።

"ልጃችሁን ለልጃችን ብለን ነበር" አሉ።

"እስኪ ተቀመጡና እናውራ" ብሎ አስቀመጣቸው። ወደ ቤተሰቦቹ ተመለከተ፤ ይበልጥ ቃል አጥቷቸው አየ። ነገር ግን እናት እንደምንም ቃል አውጥተው

"ለመሆኑ የትኛዋን ልጄን ነው የፈለጋችሁት?" አሉ።

ሽማግሌዎቹ በአንድ ድምፅ "ዳናዊትን ነው" አሉ። 💍

​👤 "ማነው ለመሆኑ ይታወቃል?" ሲሉ ጠየቁ እናት።

ሽማግሌዎቹም "ልጁማ የታወቀ፣ የተከበረ፣ በእናንተም ዘንድ የተወደደ ሰለሞን ነው" አሉ። ሽማግሌዎቹ

ከዚህ በኋላ ቃል ማውጣት የቻለ አልነበረም፤ ሁሉም በተለያየ ሃሳብ ተወሰደ። ዳናዊት "እንዴት ቢንቀኝ ነው? አሳየዋለሁ" እያለች በንዴት ትብሰለሰላለች። ጴጥሮስ ይህን ጉዳይ በቀልድ መልክ አንድ ቀንማ "ሽማግሌ ልኬ ነው እህትህን የምወስድልህ" ያለውን አስታወሰ፤ ነገር ግን ቁም ነገር አድርጎ አልቆጠረውም ነበር። 🧊

​💔 ኤልዳና ድንጋጤ፣ ንዴትና መገረም በአንድ ላይ መቷታል። ሰለሞንን ትወደዋለች፤ በተለያየ ጊዜ ምልክት ብታሳየውም ሊረዳት አልቻለም። ብዙ ጊዜም እንዲቀርባት በር ከፍታለታለች፤ ነገር ግን አንድም ጊዜ እድሉን ለመጠቀም አልሞከረም። እትዬ ብርቄ ድንጋጤ ከደስታ ተደብልቆባቸዋል። ዝምታው ሲያይልባቸዉ

ሽማግሌዎቹ "ቀን ቀጠሮ ስጡንና ተማክራችሁበት ወስኑ" አሉ።

እትዬ ብርቄም ነቃ አሉና "አርቡ ተመለሱ" ብለው ሽማግሌዎቹን አሰናበቱ። 👋

​⏳ ዝምታ እንደነገሰ ለሰዓታት ቆየ። እትዬ ብርቄ ለዳናዊት "ምን ታስቢያለሽ?" አሏት።

ዳናዊት ቆጣ ብላ "ምን እንዳስብ ትፈልጊያለሽ እማ? ምን ያክል ቢንቀኝ ነው እንደ ዕቃ ካንቺ ጋር ተደራድሮ ሊወስደኝ የፈለገው? የምንስ ቀን ቀጠሮ ነው? ቅስማቸውን ሰብረሽ ማበረር ሲገባሽ!" ብላ ያለ ልማዷ እናትየዋ ላይ አፈጠጠችባቸው።

እናት "አረ ቀስ እናትሽ እኮ ነኝ አትርሺ፤ ለማንኛውም ተረጋግተሽ አስቢበት" ብለው አጀንዳውን ለመዝጋት ሞከሩ። 😡

​📱 ነገር ግን አጀንዳው እንዲህ በቀላሉ የሚዘጋ አልነበረም።

ኤልዳና "ዳኒ ግን ትንሽም ቢሆን ምንም የጀመራችሁት ነገር የለም?" ብላ ጠየቀቻት፤ ውስጧ ለተፈጠረባት ትልቁ ጥያቄ መልስ ፍለጋ።

ዳናዊት "ትቀልጃለሽ? ከሱ ጋር ነው ደግሞ የምጀምረው" አለቻት። ኤልዳና ራሷን በእህቷ ቦታ ማግኘት እንደዚህ ጊዜ ተመኝታ አታውቅም። 😔

​🏃‍♂️ "ምነው አባወራው?" አሉ እትዬ ብርቄ ጴጥሮስን።

"ይገርማል! ምን እንደምል ግራ ገብቶኝ እኮ ነው" አለ።

ወሬው ከዚህ በላይ አልዘለለም። ሁለት ቀናት ተቆጠሩ፤ ጴጥሮስም፣ ኤልዳናም፣ ዳናዊትም ሰለሞንን ለማግኘት ቢሞክሩም ሊያገኙት አልቻሉም። ስልኩ ዝግ ነው። ወደ መኖሪያው ጴጥሮስ ቢሄድም "ገዳም ብሎ ከአዲስ አበባ ወጥቷል" ተባለ። ⛰

​⛪️ ዳናዊት ንዴቷ አልለቀቃትም፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ የእናቷ ሁኔታ ሊገባት አልቻለም። ከዳኒ ጋርም ያን ያክል ምቾት ባይሰማትም የተጀመረው መደዋወል ቀጥሏል። ሐሙስ ከስራ እንደገባች እናት ብርቄ "እፈልግሻለሁ" ብለው ወደ ቤተክርስቲያን ይዘዋት ሄዱ። 🏃‍♀️

​...ይቀጥላል...






ግርምቢጥ 🌀

​ክፍል አንድ 📖

​✨ እለተ ሰንበት የማርያም እለት... ቤተሰቡ ከቤተክርስቲያን መልስ ተሰብስቦ ቡና መጠጣት ጀምሯል። በቤት ውስጥ አራት ናቸው። ☕️ እናት እትዬ ብርቅነሽ፣ የመጀመሪያ ልጃቸው ዳናዊት፣ ሁለተኛ ልጅ ጴጥሮስ እና ሶስተኛ ልጅ ኤልዳና። 🏠

​💪 ሁሉንም እናትም አባትም ሆነው ያሳደጉት እትዬ ብርቅነሽ ናቸው። ብዙ መከራ አይተው ነው እዚህ ያደረሷቸው። ሶስቱም ልጆች ያን ያክል የሰፋ የእድሜ ልዩነት የላቸውም።

​🎓 ከኤልዳና በቀር ሁሉም ትምህርታቸውን ጨርሰው ጥሩ የሚባል ስራ ይዘዋል። ኤልዳናም የኮሌጅ ተማሪ ነች። የ እናት "ልጆቼ ተማሩ" ምክር፣ "እድሜዬ እየሄደ ነው አግብታችሁ ሰርጋችሁን አሳዩኝ፣ የልጅ ልጅ አሳዩኝ" ወደሚል ከተሻጋገረ ሰነባብቷል።😎👰‍♀️

​❤️ በተለይ ይህ ምክር ዳናዊት ላይ ይጎላል። ዳናዊት "አፈር ሆና ሰው ያደረገችኝን እናቴን ሳላኮራ፣ ስራ ይዤ እሷን ሳልረዳ ወደ ግራ ወደ ቀኝ የለም" ብላ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ይቀርቡላት የነበሩትን የፍቅር ጥያቄዎች ባላየ እያለፈች ነው እዚህ የደረሰችው። አሁን ግን ልቧን ክፍት ለማድረግ ወስናለች። 🔓

​💼 የምትሰራበት የግል መስሪያ ቤት ባለቤት ልጅ በእሷ ላይ ፍላጎት እንዳደረበት ማየት ችላለች። ምንም እንኳን በጉዳዩ ላይ ገፍቶ ያደረገው ነገር ባይኖርም፣ የሱ ጉዳይ ገፍቶ ከመጣ ቢያንስ ቀርባ ልታየው ወስና እየጠበቀችው ነው። ⏳

​☕️ አቦል ቡና እየተጠጣ እትዬ ብርቅነሽ ቡና ወደምታፈላው ኤልዳና ዞር አሉና፦

"ግሩም ቡና! ባል ይውጣልሽ" አሏት። 💍

​"እንዴ እማዬ! የመጀመሪያው አሪፍ አልነበረም እንዴ? ያኔ ዝም ብለሽ..." አለቻት ኤልዳና እየሳቀች። 😄

"አንቺ ነክተሽው አሪፍ የማይሆን የለም" አሏት።

​🚶‍♂️ በዚህ መሀል ጴጥሮስ "እናትና ልጅ መልካም መወዳደስ" ብሎ ሊወጣ ተነሳ።


"ወዴት ነው የምትሄደው?" አሉት እናት።

"ጓደኞቼ ጋር" ብሎ በአጭሩ መለሰ። 🏃‍♂️

​"ጠብቀኝ!" ብላ ዳናዊትም ተነሳች።

"እንዴ! አንቺም?" አለቻት ታናሿ ኤልዳና።

"አልቆይም ሱቅ ነኝ" አለችና ወጣች። 🛍

​👵 እናት ዳናዊት ከጴጥሮስ ጓደኞች ጋር ያላትን ቅርበት አይጠሉትም። እንዲያውም የጴጥሮስን አብሮ አደግ ሰለሞንን ብታገባ ምን ያክል እንደሚደሰቱ በግልፅ ነግረዋታል። እሷ "ሰለሞን ወግ አጥባቂ ነው" ባይ ነች፤ የሁለቱን ክርክር ግን ጴጥሮስም ሆነ ሰለሞን አያውቁትም። 🤐

​📱 ዳናዊት እንደላችው ብዙ አልቆየችም፤ የሞባይል ካርድ ገዝታ ወዲያው ተመልሳ ተቀላቀለቻቸው። በመሀል ስልኳ ጠራ። ቁጥሩን አታውቀውም፣ ስለዚህ የማንሳት ፍላጎት አልነበራትም። ነገር ግን ሲደጋገም አነሳችው...

​"ሄሎ?" 📞

"ሀሎ" የሚል ጎርናና ድምፅ መለሰ። ድምፁን የምታውቀው መሰላት ነገር ግን እርግጠኛ አልሆነችም።

"ማን ልበል?"

"ዳኒ ነኝ"

​🎯 ግምቷ አልተሳሳተም፤ ነገር ግን እንዳወቀችው ማሳየት አልፈለገችም።
"ዳኒ ማለት?"

"ዳኒ ቢሮ..." ብሎ የአባቱን ስም በቢሮ ተክቶ ነገራት። 🏢

​"አንተ ነህ እንዴ?" አለችው። የባጥ የቆጡን ለፈለፈና በስተመጨረሻም "ለምን ነገ ከስራ ስትወጪ መክሰስ አልጋብዝሽም?" አላት። 🍰☕️

እሷም "እርግጠኛ አይደለሁም፣ ለማንኛውም መውጫዬ ላይ ቼክ አድርገኝ" አለች... በውስጧ ግን ለመጋበዝ ወስናለች። 💃

​...ይቀጥላል...

​በቀጣዩ ክፍል፦
የዳናዊት እና የዳኒ ቀጠሮ ላይ ምን ይፈጠር ይሆን? እናት የፈለጉት ሰለሞንስ የት ነው ያለው?

​ክፍል 2 ይቀጥላል

15 last posts shown.

203

subscribers
Channel statistics