ጠቃሚ መረጃ
የተሽከርካሪ ሽያጭ ውል ለማጸደቅ ወደ ሠነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በሚሄዱበት ጊዜ ከታች የተገለጹ መረጃዎችን ማሟላት ይኖርቦታል፡፡
የሚንቀሳቀስ ንብረት (መኪና፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ፣ የተሽከርካሪ ሞተር፣ የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ማሽነሪዎች፣ ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-
• በሻጭ ወይም በስጦታ አድራጊ ስም የተመዘገበ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ (ሊብሬ)፤
• የሻጭ እና የገዥ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
• ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ የውክልና ሰነድ
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፤
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው የጋብቻ ማስረጃ ወይም የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
• ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፤
• ለኮድ 1 እና 3 ከገቢዎች የሚሰጥ የግብር ክሊራንስ እና ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የሚሰጥ ደብዳቤ ጋር፤
• የሚንቀሳቀሰው ንብረት ከቀረጥ ነጻ መብት ያለው ሲሆን ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤
• የታርጋ ኮድ 5፣ 11፣ 35 እና ለመሳሰሉት ተሽከርካሪዎች ከሐይማኖት ተቋማት በስተቀር ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የማስተላለፍ የድጋፍ ደብዳቤ፡፡
እነዚህን የተለያዩ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የሽያጭ ወይም የስጦታ ውል አገልግሎቶች ለመሰጠት የሚፈጀው ጊዜ 45 ደቂቃ (ለእያንዳንዱ አገልግሎት በተናጠል) መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቋል፡፡
መረጃው የፌዴራል ሠነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
በፌስ ቡክ ገጻችንን ይከተሉን፡-
https://www.facebook.com/aadvlcalidetaየቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡-
https://t.me/DVLCAlidetabranch