ከሀይድ ደም ቀለም ውጭ ሌላም አይነት ቀለም ያለው ፈሳሽ ምን ይሆን
ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ና ከሀይድ ጋር ያለው ቁርኝት እንዲሁም የአመጣጥ ወቅቱና ሸሪዓዊ ብያኔያቸው
ይህ ፈሳሽ በብዙሃን እንስቶች ላይ የወር አበባቸውን በታከከ በተለይ በሶስት ዋና ዋና ጊዜያት ሊከሰት ይችላል ።
① ከሀይዷ (ከወር አበባዋ) መምጣት አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ የሚከሰት
② ከሀይድ ከመንፃቷ በፊት ከፍሰቱ በኋላ መጨረሻ ላይ የሚከሰት
③ የሀይድ ፍሰት አብቅቶ ከጠራች በኋላ የሚከሰቱ ናቸው።
የመጀመርያው
``````````
ከሀይድ በስተፊት ቢጫማ ወይም ቡናማ ቀለም ያለው ፈሳሽ ከፈሰሳት
ይህ ፈሳሽ በተለምዶ በወር አበባ መምጫ ግዜዋ በሀይድ ላይ በምትሆንበት ወቅት ወይም
~ በጥቂት ቀናት ቀድም ብሎና
~ ከሀይድ ህመም ወይም ቁርጠት ጋር ተጎዳኝቶ ከመጣ ከዚያም
~ ይህንንም ፈሳሽ ተከትሎ የሀይድ ደም ከፈሰሳት ይህ የሀይዷ (የወር አበባዋ) ባህሪና ሀይዷ ራሱ በመሆኑ:-
በዚህ ወቅት ከሰላትም ከፆምም ትታቀባለች ።
ይህም ማለት ይህ ቢጫ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከሀይድ (ከወር አበባ) ደም በአንድ ወይም በሁለት ቀናት ቀድሞ ከሀይድ ህመም (ቁርጠት) ጋር ከመጣና
~ ሀይዱም በሶስተኛው ቀን ከፈሰሳት ሁሉም በሀይድ ይቆጠራሉ።
ይህ የሀይድ አመጣጥ መጠይቅ (مسألة) እንግዲህ ጎላ ብሎ የታወቀና ሸይኽ ዐብዱል አዚዝ ኢብኑ ባዝም ረሂመሁላህ የጠቀሱት ጉዳይ ነው።
ሆኖም ሸይኽ ዐብዱል አዚዝ ኢብኑ ባዝ ራህመቱላሂ ዐለይሂ
ፈሳሾቹ ተከታትለው (ተያይዘው) መምጣታቸውን እንጂ ህመሙም አብሮ መገኘቱን መስፈርት አላደረጉም።
በተጨማሪም
የሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚንም የነበራቸው አባባልም ይኸው ነበር።
ይህ ቢጫማና ቡናማ ፈሳሽ ከሀይድ ጋር እስካልተያያዘ ድረስ ሙሉ በሙሉ ከሀይድ አይቆጠርም የሚል ነው። ረሂመሁላህ
ሁለተኛው
`````
ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከመንፃቷ በፊት ከሀይድ ፍሰት በኋላ መጨረሻ ላይ ከመጣ
የሀይድ መቆም በግልፅ ከመታወቁ በፊት በሰተመጨረሻ ላይ ይህ ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከታያት ባለመቸኮል "ቀሰተል በይዳአ" የተሰኘው ነጭ ፈሳሽ እስኪመጣት መጠበቅ ይኖርባታል።
ለዚህ የሚረዳን አስረጅ
ኢማሙ ማሊክ ረሂመሁላህ ዘግበውት ' ሙወጠእ ' በተሰኘው ድርሳናቸው ገፅ 130 ላይ እንደሰፈረውና
ኡሙ ዐልቀመህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዳወራችን
{ ሴቶች ወደ የምእመናን እናት ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ፣ ቢጫማ የሀይድ ደም ያለበትን ጥጥ በ "ዱርጅ" ማለትም በእቃ ውስጥ አድርገው ይልኩባትና ሰላት መስገድ ይችሉ እንደሆን ይጠይቋት ነበር።
እሷም "ቀስሰተል በይዳአ" ማለትም ነጣ ያለ ፈሳሽ እስክታዩ ድረስ አትቻኮሉ ትላቸው ነበር።
በአባባሏ የፈለገችውም ከሀይድ ፅዱ እስክትሆኑ ለማለት ነው። }
ሶስተኛው
`````
ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ የወር አበባዋ አብቅቶ ከፀዳች በኋላ የሚፈሳት ከሆነ
ከሀይድ (ከወር አበባ) ፍሰት በኋላ የሚመጣ ቢጫማ ወይም ቡናማ ቀለም ያለው ፈሳሽ ከወር አበባ አይቆጠርም።
ገላ ለመታጠብም የሚያስገድድ ስላልሆነ ዉዱእ በማድረግ ብቻ ሰላትንም ፆምንም መፈፀም ይቻላል።
ለዚህም አስረጃችን ኡሙ ዐጢየህ ረዲየላሁ ዐንሃ አንዳወራችን
« ከወር አበባ ከፀዳን በኋላ የሚመጣውን ቢጫማ ወይም ቡናማ ፈሳሽ ከምንም (ከወር አበባ) አንቆጥርም ነበረ ። »
https://t.me/abdulhalimibnushayk