ፋኖ ወደ ጎንደር ከተማ እንዲገባ ያስገደደውን ምክንያት ይፋ አደረገ!
የጎንደር ፋኖ የቴዎድሮስ ብርጌድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሃይላቸው በትናንትናው እለት ወደ ጎንደር ከተማ መግባቱን በሚመለከት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ባደረገው ቆይታም “ትናንት ጥቃት የከፈትነው ጎንደር ከተማ ውስጥ በፈለግነው ሰዓት መግባት እንደምንችል ለማሳየት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የታሰሩ አባሎቻችንን ለማስፈታት ነው” ብሏል።ጨምሮም እሁድ ዕለት በነበረው ውግያ ሦስተኛ እና ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም በመቶዎች የሚቆጠሩ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ እስረኞችን ማስለቀቃቸውን ገልጿል።
መከላከያ ሰራዊቱ "ፋኖ በጎንደር ከተማ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ ከ50 በላይ አባላቱን ገድያለሁ ፣ ከከተማዋም አባርሬዋለሁ" ብሏል። ህዝብ ግንኙነቱ ግን የተጠቀሰው ቁጥር “ሐሰት” መሆኑን በመግለጽ፣ በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በማስለቀቅ የመከላከያ ሠራዊቱ እና ንብረቶቹ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልፀው፣ ነገር ግን “ይህንን ሁሉ ስንፈጽም ያለመስዋዕትነት አይደለም፣ የተጠቀሰው ቁጥር ግን እጅግ የተገጋነነ ነው”ሲሉ ክህደት የማይታይበት ምላሽ ሰጥተዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ባወጣው መግለጫ በስም የጠቀሳቸው የፋኖ አመራሮች መገደላቸውን የገለጸ ቢሆንም፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ግን የተባሉት የፋኖ አባላት ያልተገደሉ መሆናቸውን እና በቅርቡም ራሳቸው መረጃ እንደሚሰጡ ገልፀዋል።
መከላከያ ባወጣው መግለጫ ወደ ከተማዋ ዘልቆ የገባው የፋኖ ሃይል በሸማቾች ሕብረት ሥራ ላይ ዘረፋ ፈፅሟል ሲልም ተሰምቶ ነበር።
የፋኖ የሕዝብ ግንኙነት ግን “ከተማዋን ለስድስት ቀናት ተቆጣጥረን በነበረበት ወቅት ምንም ነገር አልነካንም። አሁንም ባንኮችን ሳይቀር ተቆጣጥረን በነበረበት ወቅት ሸማቾች ጋር ልንዘርፍ አንችልም” ሲሉ ተናግሯል።
ነዋሪዎቹ በከተማዋ ዳርቻዎች እስከ ሰኞ ጠዋት ድረስ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር የገለጹ ሲሆን፣ የቴዎድሮስ ብርጌድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊውም በከተማው የተወሰኑ አካባቢዎች አሁንም የፋኖ ሃይሎች መኖራቸውን አረጋግጠዋል።
ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇https://t.me/ethelmeaia