💝 አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ 👳‍♂


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይኽ መንፈሳዊ ፅሁፎችን፣ መፅሐፍቶችንና ትምህርቶችን የምናጋራበት ቻናል ነው። ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ! የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ትዕግስት ብዙ ችግሮችን ይፈታል!
መፍትሔ የለም ባልክበት ጊዜም መለኮታዊ መፍትሔዎችን ያመጣል  እግዚአብሄር የማይለወጥ ፍቅር ነውና የምታልፍበትን መከራ ያውቃል
እግዚአብሄር መከራን በትዕግስት ተቀብሎ ቅዱስ ስሙን በሚያመሰግን ሰው ደስ ይሰኛል
ቅዱስ ፓሲዮስ
➤የጥበብ ወዳጇ ማን እንደሆነች ታውቃለህ ? ትዕግስት ናት! ትዕግስት በጽናቷና እርጋታዋ ምክንያት የጥበብ እውነተኛ ወዳጅ ናት !

➤ወንድሜ ሆይ ! እሳትን እኮ እሳት ጨምረህ አታጠፋውም ፤ እሳትን ለማጥፋት ውኃ ያስፈልግሃል ።

➤ስለ ሃይማኖት መከራከር እንዳለብህ ነው የምታስበው? ስለ እምነት መከራከር ቀይ መስመር ነው ፤ ፍጹም ቀይ መስመር። እባክህን ስለእምነት አትከራከር !

➤መረጋጋት ሁሉንም ነገር ይፈታል ! ረጋ በል!
     ብፁዕ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
"ስኬት ትዕግስት እና ጽናት ያስፈልገዋል። እናም በመሰላቸት ፣ በንዴት ፣ ትዕግስት በማጣት የተሸነፈ እና የማይቀጥል ሰው ሊሳካለት አይችልም: ምንም እንኳን በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ቢሆንም ለእርዳታ ወደ እናንተ እስኪመጣ ድረስ ጌታን ጠብቁ."
+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ +
🌿 @father_advice 🌿


ሕመም
ሕመም ከደስታ የበለጠ ብርቱ
፤ጥልቅ እና ጽኑ ነዉ።
በሕመም ዉስጥ ያለ ሰዉ የሚቆመዉ እዉን በሆነዉ ሕይወትና እዉን በሆነዉ በራሱ ፊት ስለሆነ የዓለም ደስታዎች በሙሉ ደካማ ና ዋጋ ቢስ ሆነው ይታዩታል።
©አቡነ ሸኖዳ ሳልሳዊ
🌿@Father_advices🌿


#ምርጡን_ከምርጦቹ_ተማር

ከነህሚያ
👉 ጸሎትን

ከማርያም
👉 አክብሮትን

ከማርታ
👉 ዝቅ ማለትን

ከጳውሎስ
👉 ማስተማርን

ከዳንኤል
👉 መታዘዝን ተማር

የተሸለሙትን ትሸለማለህ!!!

#የጽድቅ_መንገድ መጽሐፍ
#ሕይወት_እና_ክርስትና መጽሐፍ

ሁለቱም የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ አዳዲስ መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።


" ሰው ስለድካሙ ሊወድቅ ይችላል፤ የማይወድቅ ማንም የለምና ይሁን እንጂ አንድ ሰው ንስሐ መግባትና ከውድቀቱ መማር አለበት።"
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
🌿 @Father_advices🌿 


ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም፤ የነፍስ ምግብ እንጂ። አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም፤ ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም፤ ጠባዩን ለመግራት እንጂ። ይህ በመሆኑም  አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው።

ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ፤ ብቻውን አይጓዝም። ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ። ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ።

አቡነ ሺኖዳ


"አንድ ነፍስ አለህ ፤ ካገኘኸው ሁሉንም አተረፍክ ፣ ካጣኸው ሁሉንም አጥተሃል"

+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሽኖዳ


#ወዳጄ

1) በታቸለህ መጠን ስለራስህ ብዙ አታውራ

👉 ሌሎች እንዲያወሩ እድል ስጥ፣ በደንብ ለማዳመጥም ሞክር!

2) በራስህ ጉዳይ ብቻ ተጠመድ፣ ያን ጊዜ ለሌሎች ጉዳይ ጊዜ አይኖርህም!

3) ሁሉንም ካላሸተትኩና ካላወቅኩ አትበል!

👉 የማያገባህ ጉዳይ ብዙ ነው!

#ትምህርተ_ሺኖዳ መጽሐፍ
#አቡነ_ሺኖዳ_መልስ_አላቸው_መጽሐፍ


ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም።
እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምኞት ይረሳል።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✍


‹‹ተስፋ ለሕይወታችን አስፈላጊ ነገር ነው:: ሰው ተስፋ ካጣ ሁሉንም ነገር ያጣል። ተስፋ ያጣ ሰው ደግሞ በጭንቀት፣ በስቃይ፣ ግራ በመጋባት፣ ዓላማ በሌለው ጥበቃና በዛለ መንፈስ ውስጥ የወደቀ ስለሚሆን ሰይጣን በመዳፎቹ ውስጥ አስገብቶ መጫወቻ ያደርገዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚመራው ሰይጣን ነው እንላለን፡፡ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች ምን ጊዜም ተስፋ ስላላቸው በማንኛውም ሰዓት የሚኖሩት በተስፋ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት የሚኖሩት በተስፋ ነው፡፡ በመከራ ጊዜ ተስፋ አላቸው፤ ነገሮች ሲወሳሰቡ ተስፋ አላቸው፤ ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔር የዘገየ በሚመስልበት ጊዜና ነገሮች ሁሉ ጨለማ በሚመስሉበት ጊዜም ተስፋ ይኖራቸዋል፡፡››

(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ)


ራስህን የምታገኝበት ምርጡ መንገድ
ሌሎችን ለማገልገል ራስህን አሳልፈህ በመስጠት ነው
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
“ ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ
የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥”

ማርቆስ 10፥43

🌿 @Father_advices🌿 


#አቅም_ይፈልጋል

ትልልቅ ሐሳቦችን ለመኖር ንጹህ ልብ፣ ጠንካራ ፍላጎት፣ ብርቱ ስራና መከራን የመቋቋም አቅም ይፈልጋል!

ሁሉም ሰው ማድረግ የሚችለውን ማድረግ ጀግና አያደርግህም!

የትኛውም ሰው መጮህ ይችላል። ሁሉም ሰው ክፉ መናገር፣ ሰዎችን ዝቅ ማድረግና ሰዎች ላይ ፈጥኖ መፍረድ ይችላል። እነዚህ የትኛውም ሰው ማድረግ የሚችላቸው ቀላል ነገሮች ናቸው። እነዚህይ ማድረግ ጠንካራ አያስብልም። ነገር ግን ከባዱ ነገር ምላስን መግታት፣ ስሜትን መቆጣጠር፣ የቃላት ምርጫን ማስተካከል ነው።

የሚሰደብ ሰው ራሱን መቆጣጠር ካልቻለው ተሳዳቢው በላይ ጠንካራ ነው። ተሳዳቢውም ከሚሰድበው ሰው በላይ የሚያዋርደውና የሚጎዳው ራሱን ነው።

እንዲሁ በሐሳብ ብቻ መኖርም ማንም ሰው እያደረገው ያለ ቀላል ነገር ነው።

ለብዙዎች የሚከብደው ግን ባሰቡት ልክ መኖር ነው። ትልልቅ ሐሳቦችን ለመኖር ንጹህ ልብ፣ ጠንካራ ፍላጎት፣ ብርቱ ስራና መከራን የመቋቋም አቅም ይፈልጋል።

የተጠራህበት ቢሆን እንኳ እንዲሁ ጥሪህ ስለሆነ አትደርስበትም። መስቀል አለው። እሱን የመሸከም ጽናትና ትጋት ይፈልጋል። ይህን ግን ሁሉም ሰው ማድረግ አይችልም።

አንተ ከየትኞቹ ነህ? የትኛውንስ ትመርጣለህ? ሐሳብ ብቻውን የትም አያደርስም፤ ሁሉም ነገር ተግባራዊነትን ይፈልጋል። የሐሳብህን መስቀል ተሸክመህ በመጓዝ ከዓላማህ ድረስ። ክርስቶስ ያደረገው ይህንን ነው።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምርጥ 3ት መጽሐፍት ደግሞ ጥበቦቹን ያስተምሩናል።

#ሰይጣንን_አስርቡት አዲስ መጽሐፍ
#እስከማዕዜኑ 2ተኛ ዕትም
#ጠይቁ_ይመለስላችኋል 3ተኛ ዕትም
#የነፍስ_ምግብ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።

📕📕📕

Telegram - https://t.me/Father_advices


#ወንድሜ
አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዮናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ። ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል። የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ አባ ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም "ከመከራ መራቅ የሚወድ ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል። በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ። በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3

   አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ


#የተባረከች_አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች

#የተባረከች_ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች

#የተባረከ_ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል

#የተባረከች_ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች

#የተባረከ_አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም

#የተባረከች_አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች

#የተባረከች_ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች

#የተባረከች_እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች

#የተባረከች_እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደር እና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም።
       አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
@father_advices


ከሁለቱ በአንዱ ጀምር


👉እግዚአብሔርን የምትወድ ከሆነ ታውቀዋለህ፡፡
👉 እግዚአብሔርን የምታውቀውም ከሆነ ትወደዋለህ፡፡

👌ከሁለቱ በአንዱ ጀምር ወደ ሌላው ትደርሳለህ፡፡

   (አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)


#ተስፋ_ስላለህ_ደስ_ይበልህ!

በሕይወትህ፦

👉ትልቅ መከራ ፣
👉ችግር ፣
👉ሀዘን

ደርሶብህ ይሆናል

"ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?"
ብለህ አዝነህም ይሆናል።

ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር 👉"ተስፋ"
የሚባል ነገር መኖሩን ነው፡፡

ተስፋ የሕይወት ሞተር ነው!!

#ትምህርተ_ሺኖዳ መጽሐፍ
#አቡነ_ሺኖዳ_መልስ_አላቸው መጽሐፍ


"If you want to be constantly inflamed, mix with strong persons, and with those who are fervent in the Spirit, the meticulous and those who are full of love and faith. If you do not find strong persons to mix with, live with the life-stories of the saints..."

+ Pope Shenouda +

"ዘወትር እንዲነኩ ከፈለጉ ከጠንካራ ሰዎች ጋር እና በመንፈስ ቅንዎች ፣ ጥንቁቆች፣ በፍቅር እና በእምነት የተሞሉ ከሆኑት ጋር ህብረት ይፍጠሩ (ይቀላቀሉ)።
የሚቀላቀሉዋቸው ጠንካራ ሰዎችን ካላገኙ ግን ፣ ከቅዱሳን የሕይወት ታሪኮች ጋር አብረው ይኖሩ ... "
የቅዱሳ ታሪክ ለኛ ለልጆቻቸው ቅድስና፣ ንጽህና እና መንፈሳዊ ተጋድሎን የምንማርበት አለምን ድል የምንነሳበትን ጥበብ የምንቀስምበት ነው። ሰምተንም ይሁን አንብበን እንድንጠቀም የቅዱሳን አምላክ ይርዳን አሜን
+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሽኖዳ +


"Return to the readings which used to affect you in the past and to the contemplations, sermons, liturgies, and hymns. Know yourself and know the things which strengthen it, and cleave to them. Do not leave your soul without wood to kindle its fire"
+ Pope Shenouda +

'' ከዚህ በፊት ወደ አንተ ይነበብ ወደ ነበረው ንባቦች እና ወደ ማሰላሰሎች ፣ ስብከቶች ፣ ቅዳሴዎች እና መዝሙሮች ተመለሱ ፡፡ ራስዎን ይወቁ እና የሚያጠናክሩትን(የሚያበረቱበትን) ነገሮች ይወቁ እና ከእነሱ ጋር ተጣበቁ ፡፡ እሳቱን ለማቃጠል ነፍስህን ያለ እንጨት አትተው "
(የእግዚአብሔር ቃል ለህይወት ጣእም ፣ለመንገድ ብርሀን ፣ ለነፍስ ብቸኛ መድሀኒት ነውና ቃሉን ከማንበብ አንዘናጋ ነፍሳችን ትራባለችና )
+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ሽኖዳ +


#ይሁንልህ!

እግዚአብሔር፦
መተማመኛ ረዳትህ
የምታጌጥበት እንቁህ
መደገፊያና መመኪያህ
ክፋትን መመከቻ ጋሻህ
ቀን ሲከፋብህ መጠጊያህ
ጠላትህን መውጊያ መሳሪያህ
የደስታህ ሁሉ ምንጭ


ይሁንልህ! አሜን!

©አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ


ጉዞ ወደ እግዚአብሄር.pdf
2.1Mb
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
የትኛውም ኦርቶዶክስ ሊያነበው የሚገባ ድንቅ መፅሐፍ
ደራሲ
አብነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
ተርጓሚ ዲ/ን መምህር ግርማ ባቱ
ገፅ 131

ሌሎች እንዲያነቡት ማጋራት አይርሱ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

8 738

obunachilar
Kanal statistikasi