የጊራና ና የአካባቢው ሰለፍዮች ቻናል


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ዝም አን ልም እኛ በህይወት እስካለን
ባለችው አቅማችን እንፉለማለን
ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር
እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር !!
የቻናሉ አላማ በሰለፊያ ስም የሚነግዱ ከሀቅ ለተዘናበሉና ከጥመት ሰወችጋ (ከቢዳዓ ባልተቤቶችጋ)በድንጉዳይ አብረው የሚሰሩ ሰወችን መገሰፅ ከነሱ ማስጠንቀቅ የአህለሱና ወልጄማአን መንገድ ግልጥ ልጥ አድርጎ ማሳየት ነው።

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የሰለፍያ እውነታ የሚለው መፅሐፍ
በእጃችን ላይ ስለሚገኝ
ጊራና አካባቢ ያላችሁ በዚህ አድራሻችንን በዚህ ታገኙናላችሁ
👇👇👇
0920212707

0925588883

https://t.me/giranaselfiya


✅ ከጁመዓ ቀን ሱናዎች መካከል ❲ሱረቱል ከህፍን መቅራት❳
======================>

📖 سورة الكهف
📖 ሱረቱል ከህፍ


🟢 قال رسول الله ﷺ
ن قرأ سورة الكهف في يوم الجمعة أضء له من النور مابين الجمعتين''

🟢የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀ
ራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል።

➡️ በጁምዓ ቀን የቻልን ሱረቱል ከህፍንና ሌሎችም በሀዲስ የፀደቁ ሱ
ራወችን እንቅራ ተጠቃሚዎች እንሆናለን።

✔️መቅራት የማንችል ደግሞ ከውድ ቃሪኦች እናዳምጥ በማዳመጣችን በርካታ ጥቅሞችን እንጎናፀፋለን።

➲ አቀራራችን ይስተካከላል፤
➲ የሃርፍ አወጣጥ
እንማርበታለን፤
➲ ቁርኣን ለመቅራት ያነሳሳናል፤
➲ ከዚህም በላይ ደግሞ የአላህን እዝነት እናገኝበታለን። ኢንሻአላህ!

↪️ ከታች سورة ال
كهف በተወዳጅ የአለማችን ቃሪኦች ቀርቦላችኋል። በስማቸው መሠረት እየገባችሁ አዳምጡ!!!

አላህ ተ
ጠቃሚዎች ያድርገን!!!

➘➴➴ Join Us ⬇️
T.me/AbuYehyaAselefy/7786
T.me/AbuYehyaAs>elefy/7786b>


‏قال الامام ابن القيم – رحمه الله – :

" الذكرُ هو بابُ الله الأعظَم المَفتُوح بَينَهُ

وبين عبده مالم يُغلقه العبدُ بِغفلَتِهِ ".

مدارج السالكين ( ٢/ ٤٧٦ )

🔷 ታላቁ የዲን ሊቅ ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" ዚክር በአላህና በባሪያው መካከል የተከፈተ ትልቅ በር ነው ። ባሪያው በዝንጉነቱ እስካልዘጋው ድረስ "።

መዳሪጁ አስሳሊኪን ( 2/476 )

https://t.me/bahruteka


قال شيخ الإسلام - رحمه الله - :

" فإن الهُدى يَدُور معَ الرسول حيثُ دارَ ،

ويَدُور مع أصحابه حيث داروا " .

منهاج السنة : ( 5/261 )

↪️ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ – ረሒመሁላ – እንዲህ ይላል : –

" ቅናቻ መልእክተኛው በዞሩበት ይዞራል ። ሶሓቦቻቸውም በዞሩበት ይዞራል " ።

ሚንሃጁ አስሱናህ ( 5/261 )

🔷 በመሆኑም ቅናቻ የፈለገ መልእክተኛውንና ሶሓቦቻቸውን ይከተል ።

https://t.me/bahruteka


‏قال رسول الله ﷺ :

" اقتربت الساعة، ولا يزداد الناس
على الدنيا إلا حرصا، ولا يزدادون
من الله إلا بُعدا.. "

السلسلة الصحيحة ( 1510 )

👉 የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – እንዲህ ይላሉ : –

" ቂያማ ተቃርቧል ። ሰዎች ለዱንያ ያላቸው ጉጉትና ከአላህ መራቃቸው እየጨመረ እንጂ አይሄድም " ።
ሲልሲለቱ አስሶሒሓ ገፅ ( 1510 )

https://t.me/bahruteka


يا سلفيين كونوا كالجسد الواحد ولا تتعصبوا لأي أحد من البشر بل كونوا مع الحق

لفضيلة الشيخ الوالد ربيع بن هادي عمير المدخلي حفظه الله

المدة: 00:01:24



نسأل الله أن يوفقنا ويسددنا ويجعل هذا العمل خالصاً لوجهه الكريم

(المنهج السلفي الصحيح هو العصمة من الفتن)



https://t.me/abuabdurahmen
https://t.me/abuabdurahmen


👆👆👆
ጊራና አካባቢ ለምትገኙ


የሰለፊያ እውነታ የሚለው መፅሀፍ በእጃችን ላይ ስለሚገኝ

አድራሻችን በዚህ ቁጥር ደውላችሁ ጠይቁን።
👇👇👇
0920212707
0925588883


(ላይልዘሙኒ ለሚሉት ብዥታ መልስ)

አዳምጡት በተለይ በኢብኑ ሙነወር ብዥታ የተሸወዳቹህ!!!

አኽበስ በሆነው ፉአድ ሙሀመድ መርፌ የተሸወዳቹህ!!!

ፉአድ ሙሀመድ የእባቧ ራስ ነው!!!

ከንቅልፋቹሁ ንቁ



🔊 በሸይኽ አደም አዝ,ዙበይር (አነይጀሪይ)

https://t.me/abdu_somed
https://t.me/abdu_somed


ወሳኝ እና አንገብጋቢ ፈትዋ
======================

ጥያቄ :- ብር ወለድ ባለው ባንክ አስገብቶ ብሩ የወለደውን ወለዱን ብር አውጥቶ ለድሃ መስጠት ይቻላልን ?

ምላሽ :-
🎙 ፈዲለቱ ሸይኽ አብድል ሃሚድ ለተሚይ ሃፊዘሁሏህ


✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Abdulham


የሰዎች ውዴታ የማይገኝ (የማይሳካ) ግብ ነው!!
—————
ሰዎችን እንዲወዱኝ ብለህ መልፋትህ የማይሳካ ግብ ነው። ዛሬ እንዲወዱህ ብታስደስታቸው ያመሰግኑህ ይሆናል፣ ነገ ስታስከፋቸው ግን ያወግዙሃል። ታዲያ እድሜህ ሁሉ በሰዎች ማመስገንና ማውገዝ መሃል ሆኖ ያልቃል።

ከሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ቀደሰላሁ ሩሀህ) ባልደረባ የሆኑት ኢማም ኢብን ሀብ-ባል አል-በዕሊይ (ረሂመሁላህ) ወደ አንድ ተማሪያቸው በፃፉት ፅሁፍ ላይ በወርቅ ውኃ የሚፃፍ ድንቅ ንግግር እንዲህ በማለት ይናገራሉ:-

ከዚህ ቀደም ነግሬህ ነበረ፣ ታላቃችን የሆነው ሸይኹል ኢስላም ተቂዩዲን አቡል ዐባስ አሕመድ ኢብኑ ተይሚየህ (አላህ ያግዘው፣ ወደርሱም መልካምን ያድርግ!) አንድ ጊዜ 703 አመተ ሂጅራ ላይ ድካ የደረሰ የሆነን ምክር መክሮኛል። ከእርሷም እንዲህ ማለቱን ሸምድጃለሁ:-
“በንግግርህም ሆነ በስራህ የሰዎችን ውዴታ አታስብ። የሰዎችን ውዴታ መፈለግ የማይገኝ (የማይደረስበት) ግብ ነው። ዛሬ ሰዎችን ብታስደስት ያመሰግኑሃል፣ በነጋታው ደግሞ ታስቆጣቸውና ይወቅሱሃል፣ እድሜህ እነሱ ሲያመሰግኑህና ሲቆጡብህ ያልቃል። ለየትኛውም (ለመውቀሳቸውም ሆነ ለማመስገናቸው) እውነታ የለውም። ይልቅ አላህን የምትታዘዝበት የሆነ ነገር ከቀረበልህ የሚያወግዙህ አንድ ሺህ ቢሆኑ እንኳን እሱን አስቀድም፣ ምክንያቱም የላቀው አላህ ሸራቸውን ይበቃሃል።

ይህም ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በተረጋገጠው ነቢዩ እንደሚከተለው በተናገሩት ሀዲስ በመተግበር ነው:-
“ሰዎችን አስቆጥቶ አላህን ያስወደደ ሰው አላህ ከሰዎች ቁጣ ይጠብቀዋል።” [ትርሚዚይ 2414 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒይ ሶሂህ ብለውታል]

አላህን በማመፅ ላይ የሆነ ነገር ከቀረበልህ ከፊትህ የሚያወድሱህ ሺህ ሰዎች እንኳ ቢኖሩ ወየውልህ ተጠንቀቅ!! ተጠንቀቅ!!። የላቀው አምላካችን አላህ የሚያወድሱህ የነበሩ ሰዎችን መልሶ አንተው ላይ ይሾምብሃል። ነቢዩ ﷺ ይህን አስመልክተውም እንዲህ ብለዋል:- “አላህን በማስቆጣት ሰዎችን ያስደሰተ ሰው አወዳሾቹን ወቃሽ አድርጎ ይመልስበታል።” በሌላ ዘገባ እንዲህ ብለዋል:- “አላህ ጉዳዩን ወደ ሰዎች አስጠግቶ ይተወዋል፣ ሰዎች ደግሞ አላህ ዘንድ ካለው ነገር አንዳችም አያብቃቁትም።” [ትርሚዚይ፣ ኢብን ሂባንና እንዲሁም ኢብን አቢል ዒዝ በሸርህ ጦሃዊያ ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

ወላሂ በእድሜ ቆይታይ ለዚህች ምክር ብዙ አስገራሚ ፍሬዎችን አግኝቻለሁ!! አላህ ልባችንን እርሱን በመታዘዝና እርሱንም በመውደድ ይሰብስብልን!! እርሱም ለጋሽና ቸር የሆነ ጌታ ነው። [አን-ነሲሀት አል-ሙኽተሶህ 42-43]

አንተ ሐቅ ላይ መሆንህ ላይ እርግጠኛ ከሆንክ ለሰዎች ውዴታና ጥላቻ አትጨነቅ!! ሰዎችን ለሰዎች ጌታ ተዋቸውና በምትችለው መልካም ነገር ሁሉ ወደፊት ብቻ ተጓዝ!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


አዲስ ሙሓዶራ

ርዕስ – "የጥሜት ምክንያቶቹና መገለጫዎቹ"

በወንድም አቡብክር ዩሱፍ ሃፊዞሁሏህ

መስከረም ‐ 29 ‐ 2015

በቡኻሪ መስጅድ የተሠጠ ሙሓዶራ

#መጠን_12.29mb
#እርዝመት_53min

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


🔵እውቀት የዓሊም እና የጃህል መለያ ነው!! 📚

📚عن عبد الله بن عمرو بن العاص -رضي الله عنهما-، قال: سمعت رسول الله -صلى الله عليه وسلم- يقول: «إنَّ اللهَ لاَ يَقْبِضُ العِلْمَ انْتِزَاعاً يَنْتَزعهُ مِنَ النَّاسِ، وَلكِنْ يَقْبِضُ العِلْمَ بِقَبْضِ العُلَمَاءِ، حَتَّى إِذَا لَمْ يُبْقِ عَالِماً، اتَّخَذَ النَّاسُ رُؤُوساً جُهَّالاً، فَسُئِلُوا فَأفْتوا بِغَيْرِ عِلْمٍ، فَضَلُّوا وَأضَلُّوا».
متفق عليه

✅ ከዐብደላህ ዐምር ኢብኑል ዓስ: በተላለፈ ዘገባ ነቢዩንﷺሲሉ ሰማሁዋቸው ይላል:"አላህ ሸሪዓዊ እውቀትን ከሰው ልጆች መመንጨቅን መንጭቆ አይወስደውም።ነገር ግን ዑለማዎችን በሞት በመውሰድ እውቀትን ይወስደዋል  ።አዋቂ የሚባል እስከማይቀር ድረስ።ከዚያም ሰዎች የመሀይማን ቁንጮ የሆኑትን አዋቂ አድረገው ዪዛሉ።እነሱም ይጠየቃሉ ያለ እውቀት ፍርድ በመስጠት ጠመው ያጠማሉ።" ቡኻሪና ሙስሊም


⏺قال الله  تعالى{…ۗ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ}

☑️በል:«እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡(ዙመር 9)

📔قال ابن القيم  رحمه الله في نونية

👌العلم قال الله قال رسوله*
قال الصحابة هم أولو العرفان.
  ✅ ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለት በኑኒያው ውስጥ አንዲህ ብሎዋል:
👉"እውቀት ማለት አላህ ብሎዋል፣
👉መልእክተኛውምﷺብለዋል፣
👉ሰሃቦቹም ብለዋሉ ነው። የእውቀት ባልተቤት እነሱ ናቸውና።"በማለት ትልቅ መርህ አስቀምጦልናል።

🟣  የሱነህ ሰዎች የሚለዩት በመረጃ ነው!!


http://t.me/mustefatemam


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የባሰው መጣ! ሱፍይ ከሆንክ አህመቅ (የተጃጃለ መሀይም) ትሆናለህ ያሉት ሻፍዕይ ለዚህ ነው ለካ

የዚህ ሱፊ ንግግር ሲተረጎም #ሱፍዩ_እንዲህ_ይላል፦ የኛ ማስረጃችን ለነብዩ ውደታችን ነው ይሄ ብቻ በቂ ነው
#ምላሽ፦
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» [ ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 31 ]

#ሱፍዩም_ቀጥሎ_እንዲህ_ይላል፦ ነብዩ በኔ ልደት አትሰብሰቡ ቢሉን እንኳ እሳቸው ከሀቅ ተዘንብለዋል ብለን ሥለምጠረጥር እንሰበሰብ ነበር አለ

#ምላሽ፦
وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
(ሙሀመድ) ከልብ ወለድም አይናገርም። [ ሱረቱ አል-ነጅም - 3 ]

#ሱፍዩም_ቀጥሎ_እንዲህ_ይላል
ምክንያቱም ነብይ ከሀቁ ከተንሸራተተ አደብ (እሳቸውን ማክበር) ከመከተል ይቀደማል
#ምላሽ፦
ትእዛዛቸውን እየጣስቅ እያዋረድካቸው የት ላይ አከበርካቸው?
አላህ እንዲህ ይላል
أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን [ ሱረቱ አል-ፉርቃን፣- 43

✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/3448


#ከቶ_በዚህ_ዘመን፣
#ፍቺን_ምን_አበዛው_!?

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

ይከበር ነበረ፣ ትዳር ድሮ ድሮ፣
ለቤቱ ያስባል፣ ባል ሚስትም ጠንክሮ፣
ልፋት ሳያንሳቸው፣ ሁሉም ጥሮ ግሮ፣
ድምፅም አይሰማ፣ እንደ ዛሬ ሮሮ፣
======================
ትዳር ዛሬ ዘመን፣ ሁኗል የንግድ እቃ፣
መለወጥ መሸቀጥ፣ በሰዓት ደቂቃ፣
======================
በአንድ ቀን ትውውቅ፣ ተቻኩሎ መጋባት፣
በአንድ ቀን መጣላት፣ ደርሶ መለያየት፣
አክለፍልፎ ማግባት፣ አክለፍልፎ መፍታት፣
======================
ብዙ የለመደ ብዙ፣ የለመደች፣
ወንዱ ፀባይ የለው፣ ለትዳር አይመች፣
ሴቷ ኑሮ አይጥማት፣ እየተማረረች፣
======================
የራስን ጌጥ ትቶ፣ አሻግሮ ሰው ማየት፣
ጥሩ ሚስቱን ንቆ፣ መመኘት ሌላ ሴት፣
የባሏ ውለታ፣ መንምኖ እየታያት፣
የሌሎቹ ጎመን፣ ሥጋ መስሎ ታይቷት፣
======================
ሰው ሁኖ ሲፈጠር፣ ያገኘውን ጉዳይ፣
ደርሶ ዘገነናት፣ ከባሏ ላይ ሥታይ፣
ከኑር አልተሰራ፣ ይቺ ምን ትላለይ!?
======================
ሴት ልጅ በመሆኗ፣ ያለባት ጎደሎ፣
የሷ ችግር መስሎት፣ ቅቤ ልጥበስ ብሎ፣
ሚስቱን ያባርና፣ ይኖራል ኮብልሎ፣
======================
ሁለቱም ጠገቡ፣ በምኞት ማለሉ፣
ውሃ ቀጠነብን፣ ከሰል ጠቆረ አሉ፣
ውሃ ካልተነፋ፣ ትዳር"ን"ም ጠሉ፣
======================
ተገፍታም የገባች፣ የምንቸገረኟን፣
አመል የለሽ ማቱ፣ ገረጭራጫ ስኮን፣
ነግቶ ምታናድድ፣ የምታጨስ ባሏን፣
======================
ሳይፈልግ የገባ፣ ሲኖር ከወንዶችም፣
ለሴት ሸክም ሁኖ፣ የሚኖር ዘላለም፣
ይሄኔም ይዋጣል፣ ትዳር በፍች አለም፣
======================
ወይ አንዳንድ ሀሲድ፣ ምቀኛ ሆኗቸው፣
ማሻ አላህ ሳይል፣ ተስገብግቦ አይቷቸው፣
ተዋደው ቢኖሩም፣ ትዳር አምሮባቸው፣
የሚለዩም አሉ፣ ከሞቀው ቤታቸው፣
መቼም ዙሮ ዙሮ፣ ይሄው መፋታት ነው፣
ከቶ በዚህ ዘመን፣ ፍቺን ምን አበዛው!?

✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/3447


የቀዳሚው ሙፍቲ'ል ፊትነህ ነገር…
—————
ክፍል_② [ከአላማዎቹ በከፊል]
—————
ክፍል አንድን በሚከተለው ሊንክ ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/IbnShifa/2360

2ኛ, ያለ በቂ እውቀት እራሱን አጉልቶ የማውጣት አላማ!!
ይህ ደግሞ "እዩኝ እዩኝ" ማለት "ደብቁኝ ደብቁኝ" ማለትን እንደሚያስከትል አለመገንዘብም ይመስላል።

حبُّ الظهور يقسيم الظهور

"ታዋቂነትን መውደድ ወገብን ይሰብራል"
ይሁን እንጂ የስልጣን ጥማት ያሳበደው አካል እንዲህ ያለውን ነገር ቆም ብሎ የሚያስተውልበት ጊዜ የለውም።

ይህ እራሱን የማጉላት ተግባሩ ለመጀመሪያው አላማው የሚረዳው አላማ ነው። እንደሚታወቀው ስልጣን ፈላጊና ፖለቲከኛ የሆነ ሰው ከመሬት ተነስቶ አይደለም ወንበር ላይ የሚቀመጠውና ፈላጭ ቆራጭ፣ አዛዥ ነዛዥ የሚሆነው። ሰዎች ዘንድ በተለያየ መንገድ እውቅና ካተረፈ በኋላ ነውና ለዚህ አላማው ደግሞ አጋጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም ብቅ ብቅ እያለ እራሱን መልካም አሳቢ በማስመሰል ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል። ያው ሰይጣንም እራሱን መልካም አሳቢ በማስመሰል አይደል አባታችንን አደምንና ባለ ቤቱን ያሳሳታቸው።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ያለ አቅሙ ከመሻይኾች በፊት ቀደም ቀደም በማለት የተሳሳተ የእራሱን ብይን በመስጠት ጎልቶ መውጣት ይፈልጋል!።
በዚህም "ወላእ እና በራእን" ይመሰርትበታል። ያለ በቂ እውቀት ብይን ከመስጠቱ ባሻገር ሌላው ከባዱ አደጋ ይህ "ወላእ እና በራእን" መመስረቱ ነው።

የሰጠውን ብይን ትክክል እንዳልሆነ በመጥቀስ የሚኮንን እና እንዲታረም የሚጠይቅን አካል በሰለፊያ ጀመዓ ላይ ልክ እንደ አጥፊና ከሌሎች የጥመት ቡድኖች ጋር ስውር ትስስር እንዳለው አድርጎ በማቅረብ ከዙሪያው ያሉ ሰለፊይ ወንድሞችና ዱዓቶች በጥርጣሬ ዓይን እንዲመለከቱት የተለያዩ ውኃ የማይቋጥሩ አቃቂሮችን አጋኖ ለማሳየት እየሞከረ እንዲጠነቀቁት ያደርጋል። ከተሳካለትም ከሠለፊያ ጎዳና ውጪ እንዲደረግና ከጥመት ቡድኖች ነው ተብሎ እንዲፈረጅለት ያለ የሌለ አቅሙን ሁሉ ይጠቀማል። ይህ ሌላኛው በሰለፊያው ጀመዓ ውስጥ በተለያየ መንገድ ሊያባላና ብሎም ጀመዓውን ሊበታትን ዘርግቶት የነበረው የከሸፈው የፊትናው ሙፍቲ ሰንሰለት ነው።

ይህን ሴራውን ብዙ የጥመት ቡድኖች በተለይ ሙመይዓዎች፣ ኢኽዋኖች፣ ሙመይዐቱል ጁደድና ሀዳዲያዎች… "ተግባራዊ ይደረጋል፣ ይሳካለታል" ብለው በጉጉት ጠብቀውት የነበረ፣ ነገር ግን በአላህ ጥበብ ከዚያም በተለያዩ በሳል በሆኑ መሻይኾችና ሴረኛውን ሴራውን በማክሸፍ ረገድ አጥፈውት መሄድ በሚችሉ ወንድሞች የረቀቀ አካሄድ ሊከሽፍ ችሏል። ይህ ስግብግብ ጥማተኛ ከያዘው አላማ ውጭ እንዲህ ያለው ነገር ፈፅሞ አያሳስበውም። የተንኮለኞችን ተንኮል መላሽ የሆነው አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا ۞ وَأَكِيدُ كَيْدًا

«እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡» [አጥ-ጧሪቅ 15-16]
:
ሙመይዐቱል ጁዱድ እንደምትቀጥፈው ሰለፊይ መሻይኾች ዘንድ የቃዒዳ ሙስና ቢኖር ኖሮ ይህ ሰው ያለ በቂ ማስረጃና ያለ ጥፋታቸው ንፁህ ሰለፊዮችን ሙብተዲዕ እንዲባሉ ያደረገውን ጥረት በተቀበሉት ነበር። በዚህ ሰው አመካኝነት በሰለፊያው ጀመዓ ላይ ጥላሸት የመቀባት ጥረታችሁና ተስፋችሁም በአላህ ፈቃድ ተሟጦ ማብቂያው ላይ ደርሷል። የሱንና ዑለማዎች ጀርህና ተዕዲል የሚያደርጉት እንዲህ ያሉ ማንነታቸውን ደብቀው፣ የተለያየ አላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች በነገሯቸው ነገር ተንተርሰው ሳይሆን አስፈላጊውን ማስረጃና መስፈርት ካሟሉ በኋላና የኸበሩን ትክክለኛነት ካረጋገጡ በኋላ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮማ ገና ዑለማዎች የራሳቸውን ጥናት ሳያደርጉና ብይን ሳይሰጡባቸው በፊት እናንተም ቀደም ብላችሁ (አላማችሁን አላህ ያውቀዋል) በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ የሙብተዲዕነት ብይን እንዲሰጡባቸው ያደረጋችሁት ጉትጎታ በጊዜው በተሳካላችሁ ነበር። ዑለማዎች የራሳቸውን ጥናት ካደረጉና የእናንተው በወቅቱ የተናገራችሁት ኸበር ትክክል ሆኖ ካገኙት በኋላ የተብራራ ጀርህ በማድረግ ከሱንና ያፈነገጡ መሆናቸውን ግልፅ አደረጉ። እናንተ ደግሞ በተቃራኒው ሄዳችሁ ከራሳቸው ተጨመራችሁ። "ጀርህና ተዕዲል" በቦታውና መስፈርቱን ባሟላ መልኩ ከቀደምቶችም የመጣ፣ ተተኪዎችም የተገበሩት፣ ወደፊትም አይቀሪና የሚቀጥል ነው።
:
ታላቁ ዓሊም ኢማሙ ሸውካኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
የዚህ ህዝብ ቀደምትና ተተኪዎች፣ የሀዲስ ዘጋቢዎችንም ሆነ በሰዎች ደም፣ ንበረትና ክብር ላይ በሚመሰክሩ አካላት ላይ ጀርህ ማድረግ የሚገባውን ጀርህ ከማድረግ፣ ተዕዲል የሚገባውን ደግሞ ከመዐደል አልተወገዱም። ይህ ባይሆን ኖሮ ንፁህ በሆነችው ሱንና ላይ ውሸታሞች በተጫወቱባት ነበር። መልካሙ ከመጥፎው በተደበላለቀ ነበር፣ ትክክለኛው ከባጢሉ የትኛው እንደሆነ ባልተለየ ነበር፣ ውድቅ የሚደረገው ከሚፀናው ባልተለየ ነበር፣ ደካማው ከጠንካራው ባልተለየ ነበር…፣ ምክንያቱም ውሸታሞች በመልእክተኛው ﷺ ላይ ከመዋሸት አልተወገዱም።” [አል-ፈትሁ ረባኒይ ሚን ፈታዋ አል-ኢማም አሽ-ሸውካኒይ 11/583]

ይህ የኢማሙ ሸውካኒይ ንግግር ምንኛ ያማረና የዚህን ጊዜ የ"ጀርህና ተዕዲልን" ጉዳይ ተጨባጭ የሚዳስስ ነው። በተለይ በዚህን ጊዜ ሙመይዓዎች የቢድዐ ባለቤቶችን ወገብ የሚሰብረው "ጀርህና ተዕዲል" መሆኑን ስለሚያውቁ ለማጣጣል የተለያየ እርስ በርሱ የሚገጫጭ ንግግር እየተናገሩ ይዳክራሉ። ሲፈልጉ "ጀርህና ተዕዲል በዚህ ዘመን የለም" ይላሉ፣ ሲላቸው ደግሞ "ጀርህና ተዕዲል እንደ አገሌ አይነት ሰው ነው እንዴ የሚያደርገው?…" ይላሉ። ሌላ ጊዜ ደግሞ "ጀርህና ተዕዲል የሚያደርጉ መሻይኾችን የቃዒዳ ሙስና አለባቸው" በማለት ሊያጣጥሉና ውድቅ ሊያደርጉ ይፍጨረጨራሉ። በቁጭታችሁ ሙቱ! ጀርህና ተዕዲል ቀድሞውኑ የነበረ ወደፊትም የሚቀጥል ዲኑ የሚጠበቅበት አንዱ መሳሪያ ነው።

3ኛ, የእራሱን የሆነ የተለየ ቡድን የመመስረት አላማ!!
ከላይ በ2ኛነት የተቀመጠው አላማ ይህን አላማ በእጅጉ ይረደዋል። ምክንያቱም አንድ ሰው ያለ እውቅና ከመሬት ተነስቶ ቡድን መመስረትም ሆነ ማደራጀት አይችልም። ይህ ቡድን መመስረት ደግሞ ለመጀመሪያው አላማ ትልቁ መሳሪያና መዳረሻም ጭምር ነው። ቡድን ካደራጀ በኋላ ነገሩ አብቅቷል። ለምን ተነካ እያሉ እንደ ውሻ የሚጮሁ ጭፍን ሙሪዶችን መመልመል (ማሰልጠን) ብቻ ነው የሚጠበቅበት። ይህን ካደረገ በኋላ የሸረሪት ድር ያህል እንኳን ጥንካሬ በሌለው ብዥታው "ሀላሉን ሀራም ነው፣ ሀራሙን ሀላል ነው…" እያለ፣ የተመቸውንና ከአላማው ጋር የሚገጥመውን ምንም ያህል ግድፈት ቢኖርበት "ሱኒይ ነው፣" ያልተመቸውንና ከአላማው ጋር የማይገጥመውን ምንም እንኳን ለሱና ታጋይ ቢሆንም "ሙብተዲዕ ነው…" እያለ ውዳቂ ህጎችን ሲደነግግ እንደ ገደል ማሚቱ ዝም ብለው ማስተጋባት ነው ስራቸው። በቃ! በፍቅሩ ታውሯል!! ልክ በሀዳዲያና በሙመይዓ ጭፍን ሙሪዶች እንደታዘብነው ብታናግራቸው አያናግሩህም፣ ልክ እንደ ፈረስ ጋሪ እንዲህ ያለውን አካል በጭፍን ተከትለው ወደ ፊት መጎተት ብቻ ይሆናል ስራቸው። ይህ የፊትናው ቀዳሚ ሙፍቲም የቡድን አደረጃጀት አላማው ላይ የተሳካለት ሲመስለው ጊዜ ለሱንናው ታጋይ የሆኑ ኡስታዞችንና ከፍ ሲልም ታላላቅ በቢድዐ ሰዎች ላይ የእግር እሳት የሆኑ መሻይኾችንም በነገር ወጋ ወጋ ማድረግ ጀምሮ ነበር። የአለማቱ ጌታ ግን የተንኮለኞችን ተንኮል አንኮታኳች ነውና


የተወሰኑ ቡድኖች ለቀደር የሚሰጡት ትንታኔ

ቀደርን አስመልክቶ የተለያዩ አንጃዎች ከትክክለኛው መንገድ ባፈነገጠ ሁኔታ የተሳሳቱ ትርጉሞችን ሰጠዋል፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡-
1. ጀህምያ እና ጀብሪያ
እነዚህ ቡድኖች ባሪያው ተገዶ እንጅ በሚሰራው ስራ ምንም ዓይነት ምርጫ፣ ችሎታ፣ እቅድ እና ፍላጎት የለውም ይላሉ፡፡ የሰውን ልጅ ልክ በነፋስ እንደሚወዛወዝ ላባ ወይም ያለፍላጎቱ በነፋስ ሐይል እንደሚንቀሳቀስ የዛፍ ቅጠል ይመስሉታል፡፡ ይህ ከጀህምያ የሆኑ ጀብርያዎችና ሌሎችም የሚሉት ነው፡፡

2. ሙዕተዚላዎች [የጀህምያና የጀብሪያ ተቃራኒ የሆኑ ናቸው]
➧ ማንኛውም ሰው የአላህ ፍላጎት ሳይደበለቅ የራሱን ስራ የመፍጠር ችሎታ አለው ይላሉ፡፡ የባሪያው ስራ ከእራሱ ምርጫና ችሎታ ጋር እንጅ ከአላህ መሽአ ጋር ምንም አይነት ቁርኝት የለውም ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ወሰን በማለፍ ፡ አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ነገሮች ከተከሰቱ በኋላ እንጅ ቀድሞ አያውቀውም ይላሉ፡፡ ነገሮችን የሚያውቃቸው ባሪያው አሁን ስራውን እንዳስገኘው ነው ይላሉ፡፡ እነዚህ “አልቀደርየቱ አንኑፋት” በመባል የሚጠሩት የሙዕተዚላ ድንበር አላፊዎቸ ናቸው፡፡

↪️ የመጀመሪያው ቡድን ጀብሪያ ወይም ቀደርያ አንኑፋት በመባል ይጠራል፡፡ ይህ ቡድን ቀደርን ወይም የአላህን ውሳኔ ቢያጸድቁም በቀደር ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ ከባሪያው ላይ ኢራዳን ወይም ፍላጎትን ያራቁታሉ፡፡ በዚህ አመለካከት ተቃራኒ ሁለተኛው የሙዕተዚላ ቡድን የአላህን መሽአ እና ኢራዳ ውድቅ በማድረግ የባሪያውን መሽአ በማጽደቅ ላይ ድንበር አልፈዋል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች ጠማማና ታላቅ ስህተትን የፈጸሙ ናቸው፡፡

አህለሱና ወልጀማዓህ በኢማን፣ በቀደር ያላቸው መካከለኛ አቋም
ተገቢ የሆነ ጥላቻና ውግዘት ለቀደርዮች የአህለሱና ወልጀማዓህ መካከለኛ አቋም


ለባሪያው ችሎታን፣ ምርጫን እና ኢራዳን ያጸድቃሉ፡፡ ይሁን እንጅ የባሪያው መሽአ፣ ችሎታ፣ ምርጫ እና ኢራዳ ለአላህ መሽአ፣ ችሎታ፣ ምርጫ እና ኢራዳ ተከታይ መሆኗን ያምናሉ፡፡ አንድ ሰው በአላህ ኢራዳ እና በእርሱ መሽአ ካልሆነ በቀር ስራን መስራት አይችልም፡፡
ቀደርያ ውግዘትና ጥላቻ ይገባቸዋል
ቀደርያ፡ ከአላህ ጋር ሁለት ፈጣሪዎችን በማረጋገጣቸው የዚህ ኡመት መጁስ በመባል ተጠርተዋል፡፡
እነዚህ ቡድኖች “ሁሉም ሰው ያለአላህ መሽአና ፍላጎት የራሱን ስራ ፈጥሮ መስራት ይችላል” ይላሉ፡፡

➪ በዚህ ታላቅ የኢማን መሰረት - የቀደር እምነት - ላይ ትክክለኛውን ጎዳና በመልቀቃቸውና ነገሮችን በማደባለቃቸው ከሐቅ ባለቤቶች ከፍተኛ የሆነ ውግዘት እና ጥላቻ ደርሶባቸዋል፡፡ በቀደር ማመን ከኢማን መሰረቶች ነው። በቀደር ማመን ከኢማን መሰረቶች አንዱ እንደሆነ በጅብሪል ሐዲስ ላይ ግልጽ ተደርጓል፡፡ ጅብሪል ነብዩን ﷺ ስለኢማን በጠየቃቸው ጊዜ የሚከተለውን ምላሽ ሰጠውታል፡-
"الإيمان أن تؤمن بالله ومالئكته وكتبه ورسله واليوم اآلخر وتؤمن بالقدر خيره
وشره"
“ኢማን በአላህ፣ በመላኢካዎች፣ በመጽሐፎች፣ በመልእክተኞች፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፤ መልካም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔ (የሚከናወን መሆኑን) ማመን”

(ቡኻሪ፡ 4499, ሙስሊም፡ 10)

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

“እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡”

[ሱረት አል-ቀመር - 49]

የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"الحرص على ما ينفعك، واستعن بالله، فإن أصابك شيء فال تقل: لو أني فعلت كذا كان كذا ولكن قل قدر الله وما شاء فعل، فإن لو تفتح عمل الشيطان"
“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አንድ ነገር ከደረሰብህ “በዚህ መልኩ ብሰራው ኖሮ እንዲህ ይሆን ነበር፡፡” አትበል፤ ነገር ግን “አላህ የወሰነውና እርሱ የሻው ሆነ” በል፡፡ “ለው” (ይህ ቢሆን ኖሮ) የምትለው ቃል ለሰይጣን ተግባር (በር) ትከፍታለች፡፡”

ሙስሊም

➡️ በዚህ ዙሪያ የመጡ ግልጽ ሐዲሶች በርካታ ናቸው፡፡ ይህ የታወቀ መሰረት ነው፡፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው በዚህ ዙሪያ የአህለሱና ወልጀማዓ ዓቂዳ የሆነው ሐቅ በኪታብና በሱና መረጃዎች ተብራርቶ ግልጽ ሆኗል፡፡ ከዚህ መሰረት የተንሻፈፈ ከቁርኣንና ከሱና አፈንግጧል፡፡ መንሻፈፉን ያመጣው ከራሱ ነፍስ ወይም ከስሜቱ በኩል ያመጣው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ከቁርኣንና ከሐዲስ መረጃዎች ለማፈንገጥ ሙከራ ያደረገ አካል ሁሉ ከጥፋት ላይ መውደቁ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»

[ሱረቱ አል-አንዓም፣ - 153]

#ጥቅል_የቀደምት_ደጋግ_የአላህ_ባሮች_ዓቂዳ ከሚለው ሪሳላህ የተቀነጨበ

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


ወቅታዊ ተከታታይ ትምህርት

↩️↩️↩️ بدعة المولد

የ "መውሊድን ቢድዓነት"
በማስመልከት የተላለፈ ተከታታይ መልዕክት

ክፍል አስር
  ➚➶➹

ክፍል ❶ እስከ ❻  ለማግኘት ⬇️
https://t.me/AbuImranAselefy/5951

ክፍል ሰባትን ለማግኘት ⬇️
https://t.me/AbuImranAselefy/5953

ክፍል ስምንትን ለማግኘት ⬇️
https://t.me/AbuImranAselefy/5957

ክፍል ዘጠኝን ለማግኘት ⬇️
https://t.me/AbuImranAselefy/5961

🎙للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘሁሏህ


በዚህ ተከታታይ ትምህርት የቢድዓ ፅንሰ ሀሳብ ከስር መሰረቱ ተዳሷል።

➪ ሸሪዓችን በቢድዓ ዙሪያ ያስቀመጠው መርሆ ተብራርቷል።

ሙብተዲዖች ለፍልስፍናቸው የሚያመጧቸው ሹብሃዎች እና ትክክለኛ ምላሾች በትምህርቱ ቀርበዋል።
  ➧ ማስታወሻ እያያዛችሁ በደንብ ተከታተሉ! ለመውሊድ ሽንጡን ገትሮ የሚከራከር ሊገጥማችሁ ይችላልና እንዲሁም ራሳችሁን በትክክለኛው መንገድ ማድረጋችሁን ታረጋግጣላች!

https://t.me/AbuImranAselefy/5965




🔂 المجلس العلمي
من شرح الكتاب (الباعث الحثيث)
[ شرح في طبقات الراوي]

بمدرسة الإصلاح

لفضيلة الشيخ:
*حسين بن محمد السلطي*
- وفقه الله ونفع به -
https://t.me/medresetulislah
https://t.me/medresetulislah

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

198

obunachilar
Kanal statistikasi