الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው።
አስተያየት ለመስጠት= @esmael9

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: قناة أبي المسيب حمزة بن رشاد الحبشي
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የሴት ልጅ ሂጃብ እና ሀያእ ከሚለው ሙሃደራ የተወሰደ

👇ሙሉ ሙሃደረውን ለማግኘት👇

የሴት ልጅ ሂጃብ እና ሀያእ ክ 1
🔗https://t.me/abulmusayabhamza/46

የሴት ልጅ ሂጃብ እና ሀያእ ክ 2
🔗https://t.me/abulmusayabhamza/75

📮በአላህ ፍቃድ ክፍል 3 ይቀጥላል።


Репост из: قناة أبي المسيب حمزة بن رشاد الحبشي
📌المرأة في الجنة مع آخر أزواجها في الدنيا
📌ሴት ልጅ ጀነት ውስጥ ከመጨረሻ ባሏ ጋር ናት

🌴روى الطبراني في الأوسط من حديث أبي الدرداء رضي الله عنه :
أن النبي صلى الله عليه وسلم
قال:
📌ነብዩ ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም እንዲህ አሉ:
الْمَرْأَةُ لِآخِرِ أَزْوَاجِهَا
📌ሴት ልጅ ለመጨረሻ ባሏ ናት
📚 [(3/ 275) برقم (3130)، وقواه الشيخ الألباني في السلسلة الصحيحة (3/ 275) برقم 1281]

🔗https://t.me/joinchat/tp9jImGs-9M4NTVk


Репост из: መርከዝ አስ–ሱነህ በ ጎሞሮ❕❕ (دار الحديث السلفية في غمر( الحبشة
ቁ 2 እያለቀለት ነው
ቁ 1 ያላወረዳችሁ ቶሎ አውርዱ

🔗https://play.google.com/store/apps/details?id=com.amro.shabuqtadasunah


☄️ بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

📘 السؤال الخامس عشر:
(المجموعة الثالثة)

ما هو الدعاء الثابت في الجلوس بين السجدتين؟

ጥያቄ ፦

ተረጋግጦ የመጣ የሆነው በሁለት ሱጁዶች መሀል የሚባለው "ዱዓ"
ምንድነው ?

📘 الجواب:

الدعاء الثابت في ذلك هو ما جاء في حديث حذيفة رضي الله عنه، في السنن وأصله في صحيح مسلم، لكن هذا اللفظ في السنن: أن النبي صلى الله عليه وسلم جلس بين السجدتين فكان يقول:" ربي اغفر لي" يكرر ذلك "ربي اغفر لي" هذا أصح ما جاء في الباب، والله أعلم.

*═════ ❁✿❁ ══ ❁✿❁ ═*

መልስ ፦

በዚህ ነገር (ቦታ) ላይ ተረጋግጦ የመጣ የሆነው "ዱዓ" ከሑዘይፋ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ዘንድ የመጣ የሆነው "ሐዲስ"
ነው።

ሐዲሱም "ሱነን" ውስጥ የተዘገበ ሲሆን
(የሐዲሱ) መሠረት ግን "ሰሒ ሙስሊም"
ውስጥ (ይገኛል።)

ነገር ግን ይህ (ቀጣዩ) የሐዲሱ ቃላት
"ሱነን" ውስጥ (የተጠቀሰው ነው።)

ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)
በሁለት ሱጁድ መሀል ይቀመጡና
(እንዲህ) ይሉ ነበር ፦

" ረቢ ኢግፊርሊ" ( ጌታዬ ሆይ !ምህረትን አርግልኝ !) የሚለውን "ዱዓ" በመደጋገም ይሉ ነበር።

በዚህ ርዕስ ዙሪያ ከመጡት "ዱዓዎች"
ውስጥ ትክክለኛውም ይህ ነው።

የበለጠውን ዐዋቂ አላህ ነው !!!

*═════ ❁✿❁ ══ ❁✿❁ ═*

ታላቁ ሸይኽ አቢ አብዱረሕማን
ረሻድ ቢን አሕመድ አል–ዳለዒ

https://t.me/amr_nahy1

… ኢስማኤል ወርቁ …

موقع الشيـخ حفظـه الله :
https://www.sh-rashad.com/

*للاشتراك في قناتنا على التيلجرام اضغط على هذا الرابط 👇🏾👇🏾*

https://t.me/rshad11


📌ድብልቅልቁ የትምህርት ዓለም ዋይታ በእውነተኛው የኢስላም ብርሃን ሲፈታ📌

📝ተከታታይ ፅሁፍ

👉 ክፍል ( ሃያ አንድ ) 👈

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيم

... ሴት እህቶቻችን ከልጅነታቸው ጀምረው
በት/ቤት ውስጥ በርካታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። በዚህም የተነሳ መልካም ስነ-ምግባርን የተላበሰች እንስት ማግኘት እየከበደ ነው።

ጥሩ ስነ-ምግባር ያላቸው አማኝ ወንዶች ለትዳር አጋርነት (ለጋብቻ) ብለው ቢፈልጉ እንኳን እስከሚያጡ ድረስ የደረሱበት ሁኔታ ነው ያለው።

ምነው ሀገሩን የሞሉት ሴቶቹ አይደሉምን❓ ትሉ ይሆናል…ትክክል
ነው። በዝተው ታይተዋል ! እርግጥ ነው !ነብዩ እንደተናገሩትም ሴቶቹ ቢከፋፈሉ ለአንድ ወንድ ከ40 እስከ 50 ሴቶችም የሚደርሱበትም ጊዜ የደረሰ ይመስላል !!!

👉 ነገር ግን "አላህ" "በሒክማው" የጠበቃቸው እጅግ ጥቂቶቹ ሲቀሩ የሚመረጥ ጠፍቷል❗❗❗

እስቲ አስቡት ፦ በት/ቤት አክሮባት፣
ሩጫ ፣ ሰርከስ ፣ እጅ ኳስ ፣ እግር ኳስ... እያለች ተራቁታ ያደገች እንስት በቀላሉ ለመልካም ባልተቤትነት ትታጫለችን ???

ይህ አይነቱ የሴት ልጅ አስተዳደግ በእስልምና ውስጥ ትልቅ ጉዳት ያመጣል !!!

👉 ሴቶቻችን የአላህን ደብዳቤ (ቁርአንን) የሚቀሩበት ጊዜ አጥተው ከንቱ ሆነው ይቀራሉ። በዚህም የተነሳ በኢስላም ውስጥ ዓይናቸው በቁርአን የበራ ፥ የወለዱሃቸውን ልጆች /ا,ب,ت/እያሉ በማስቀራት የሚያሳድጉ ወላጆች ይታጣሉ።

👉 አላህን የሚፈሩ ፥ ለአላህ "ሸሪዓ" ያደሩ የነብዩን ሱና ያፈቀሩ እናቶችና
እህቶች ይታጣሉ።

ስለዚህም ለአላህ እጅ እግርን ሰጥቶ ከመታዘዝ ይልቅ እኮ ለምን❓መሆን የለበትም ! እያሉ "ከጀባሩ"ጋር ጦር የሚማዘዙ በዝተዋል !!
እንዲህም እያሉ የተወላገደ ትችታቸውን ይሰነዝራሉ ፦

👉 ኋላ ቀርነት ነው...!
👉 ፍትሐዊነት የጎደለው ድንጋጌ...!
👉 ከአንድ በላይ ማግባት...?
👉 አፈና ነው !!!
👉 መላ አካልሽን ተሸፈኚ ...?!
👉 ጥንት የቀራ የቁም እስር...!
👉 ከቤት አትውጪ ምን የሚሉት ነው ...❓
👉 አትሹሚ ! አትምሪ ! አሳብሽን አትግለጪ ! ፀጥ በይ ! ነፃነት ገፈፋ...!እኩልነት አሳጥቶ ሰብዓዊነትን አለመቀበል (አለመስጠትም) ነው።
እያሉ ያለቅሳሉ ... !!!!!

አምላካችን "አላህ"ሆይ ! ሁሉን የፈጠርክ ፣ ለሁሉም ግልፅም ሚስጥራዊም ጥበብ ያደረግክ ድንቅ ጥበበኛ ፍትሐዊ ፈራጅ ነክ❗

👉 ለራስም ቢሆን ትልቅ ውድቀትም ኪሳራም ነው።
ምክንያቱም ፦ አላህ ሴትን ሴት አርጎ ሲፈጥራት ደረጃዋን ከፍ የሚያደርግበትን ሰበቦችን አስገኝቶላትም ነው !!!

👉 ሴት በመሆኗ ብቻ ልዩ እንክብካቤን፥ እዝነትን ፣ ፍቅርን ክብርን ...
እንድትጐናፀፍ አደረጋት።

ታዲያ ዕንቁ የኢስላም ብርቅ ጆሮቿን ለኢስላም ጠላቶች የሰጠችጊዜና
ዓይኖቿን ደግሞ በአስመሳይ ክፉዎች ላይ ጣል ያረገች ጊዜ ይህንን ውድ የሆነ በእስልምና የተሰጣትን ታላቅ ስጦታና (ትኩረትን) ታጣለች❗
ይህ ደግሞ ትልቅ ኪሳራ ነው።

ለምሳሌ ፦

በእናትነት ከምታገኛቸው ለየት የሚያረጋት ስጦታዎች ውስጥ ፦

👉 ውለታዋ ተከፍሎ የሚያልቅ አለመሆኑ…
👉 ከአላህና ከመልዕክተኛው ቀጥሎ በወዳጅነት (በመወደድ) የምተከተለው እናት መሆኗ…
👉 ጀነት እንኳን ሳይቀር ከእግሯ ስር መሆኑና ሌሎችም በርካታ ያልተጠቀሱ ትሩፋቶችን በገዛ እጇ ታጣለች።

እንዴት❓ከተባለ ፦ ከላይ የጠቀስናቸውን በትምህርት ቤት ውስጥና ከት/ቤት ውጪ የሚደረጉ አላስፈላጊ በሆኑ አላህን ሊያስቆጣ በሚችል መልኩ የሚሰሩ ፤ ትምህርት የሚል ስያሜ በተሰጣቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የእናትነትን ወግ እንዳታይ ያደርጋታል !!!

ምክንያቱም ፦

👉 በስፖርት ውስጥ አድናቆትን ታተርፋለች…
👉 በስፖርት ውስጥ ማበረታቻዎች ይጎርፉላታል…
👉 ሁሌም የተሻለ በመስራት አድናቆቱን ፣ ሽልማቱን ፣ እውቅናውንና የዱኒያ ጥቅማ ጥቅሙ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ያልተገደበ ትግልን በማድረግ ላይ ትቀጥላለች።

ይህ ሁሉ ነገር ግን ሩህሩህ አምላክ አላህ አማኞችን እንዲህ በማለት የመከረበት ነው።!!!

( { "اعْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الْأَمْوَالِ وَالْأَوْلَادِ ۖ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الْكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا ۖ وَفِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ ۚ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُور ِ" } )
الحديد (20)

(( " ቅርቢቱ እይወት ጨዋታና ዛዛታ ፣ ማጌጫም ፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ።
እርሷ (እቺ ዓለም) ቡቃያው ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም ፣ ከዚያም ቡቃያው እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው ፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ቢጤ ናት ፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ፣ ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ። የቅርቢቱም እይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም። " ))
[አል-ሐዲድ (20)]

በአላህ ፍቃድ ክፍል ሃያ ሁለት
ይቀጥላል ፦

📝 … ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/amr_nahy1


🚧 አዲስ ሙሀደራ ነውና ይደመጥ።

🎼 تسجيلات الفرقان الإسلامية السلفية في الحبشة:- يسرها أن تقدم لكم هذه المادة وهي عبارة عن محاضرة
♻️ አዲስ ሙሀደራ ከአል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ።

🔖 بعنوان:- الإيمان وزيادته
🔖 ኢማን እና መጨመሩ

🚧 በሚል ርዕስ መደሙጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሀደራ።

🎙 للشيخ الفاضل أبي اليمان عدنان بن حسين المصقري حفظه الله
🎙️ በታላቁ ሼኽ:- አቡል የማን አድናን ቢን ሁሴን አል-መስቀሪ አላህ ይጠብቀው።

🌇 وكانت فجر يوم الجمعة
🌇 ጁመዓ ከፈጅር ሰላት በኋላ።

📆 بتاريخ - ٣٠ - ربيع الثاني - ١٤٤٣
📅 ረቢዒ ሳኒ - 30 - 1443 ሂጅራ

🕌 في مسجد الفرقان حرسها الله تعالى
🕌 በፉርቃን መስጂድ አላህ ይጠብቃት

تابعوا المحاضرات على الرابط
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
📲 አጠቃላይ ፕሮግራሞቻን በሶሻል ሚዲያ ለመከታተል:-

🖥️ በ Telegram~Channel
📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/7097

🖥 በ Facebook~page
🌐 https://www.facebook.com/Al.Furqan.Islamic.Studio


#صلاة

📖 #ســــــــورة_الـغـاشـيـة 📖


💺بصوت الشيخ المبارك :-
أبــي اليمان عدنان بن حسين بن أحمد المصقري
#حفـظه_الله_تعـالى_ورعاه

🕰 الــــدقيقة الزمنية : 2:01

📆 يوم الجمعة 1 ربيع الثاني 1443 هجرية

🎙ألقيت بدار الحديث السلفية بدار السلام حرسها الله
-------------------------------------------
جهود.الشيخ.المبارك.أبي.اليمان.tt
ساهم.معنا.في.نشر.القناة.tt
https://telegram.me/AbulYamman
#قناة_المشرف
http://T.me/AlMasqri
⬅️- *انشر* فمن دل على خير فله كأجر فاعله.


Репост из: አል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ
📮ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አቡል የማን ዐድናን አልመስቀሪ ወደ ሀበሻ መግባታቸውን ስናበስራቹ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው በአላህ ፍቃድ ጠዋት ከፈጅር ቡሃላ ሙሃደራ ስለ ሚኖራቸው ተሳተፉ ላልሰሙትም አሰሙ።

الحمدلله والصلاة والسلام على رسول الله وبعد:
فنرحب بشيخنا الجليل أبي اليمان عدنان بن حسين المصقري حفظه الله في أرض الحبشة أديس أبابا بين أبنائه وإخوانه ومحبيه فنقول حللت أهلا ونزلت وسهلا وطبت وطاب ممشاك وستكون له كلمة بإذن الله بعد صلاة الفجر في مسجد الفرقان فاحرصوا على الحضور وفقكم الله

ألا مرحبا شيخ علم وقور
كريم الأرومة والمعدن

أديس أبابا ومن حولها
بمثلك شيخ الهدى تعتن

تحييك أزهارها والورود
وشدو العصافير في الأفنن

تبين البشاشة في وجهها
وإن كتمت ما بها يعلن

فبشراك بشراك اثيوبيا
بشيخ على الدرب لا ينثني

تلين القلوب لتذكيره
وتهمي الدموع من الأعين

فأهلا وسهلا ومرحى به
وفي حبة القلب فاليسكن

📌فجزى الله شيخنا أبا اليمان خيرا على هذه الزيارة المتتابعة ومحبته لإخوانه فنسأل الله أن يدفع عنه كل سوء ومكروه

🖋أبو المسيب الحبشي سدده الله
مسجد الفرقان حرسها الله

🔗 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio


ኹጥባ ላይ አሚን ማለት…

.بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።


سئل الامام المحدث الشيخ الالباني رحمه الله تعالـــﮯ✔

;السائل :

هل يجوز التأمين عند الدعاء والخطيب يخطب؟

ጥያቄ ፦

ጠያቂው ፦ " ኹጥባ" አድራጊው ኹጥባ እያደረገ ("ዱዓ") በሚያደርግ ጊዜ "አሚን" ማለት ይቻላልን❓

الشيخ : هذا لا يجوز .

السائل : نعم ... والصلاة على النبي - صلى الله عليه وسلم -

الشيخ : لا يجوز لا صلاة ولا كلام ولا صلاة على الرسول لقول النبي صلى الله عليه وسلم": ( إذا قلت لصاحبك يوم الجمعة والإمام يخطب أنصت فقد لغوت ) .

السائل : ويدخل فيها الدعاء؟

الشيخ : كل شيء .

[الامام الالباني رحمه الله]

📚المصــدر : الهدى والنور (٢٦٢)]

(መልስ)

ሸይኽ ፦ "ይህ ነገር አይቻልም።

" ጠያቂው ፦ " እሺ ! በነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ " ሰለዋት" ሲወርድስ❓

" ሸይኽ ፦ " ሶላትም ይሁን ንግግር እንዲሁም በረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ " ሰለዋት" ማውረድም ቢሆን አይቻልም ። " ለነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግር ሲባል ፦

(( " የጁምዓ ዕለት ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛክ ፀጥ በል ያልከው የሆነ ጊዜ በእርግጥም ተጫውተካል ! " ))

ጠያቂው ፦ "ዱዓም በዚህ ውስጥ ይገባልን❓"

ሸይኽ ፦ " (አዎ ! ሁሉም ነገር (ይገባል።) "

📚 ምንጭ አል ሁዳ ወኑር (262)

【ታላቁ ኢማም መሐመድ ነስረዲን አልባኒ】

… ኢስማኤል ወርቁ…

https://t.me/amr_nahy1


ጋብቻን ማፍረስ …

☄️ بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

📘 السؤال السادس عشر:
(المجموعة الثالثة)

ما الفرق بين الطلاق الرجعي والطلاق البائن؟ وهل في الطلاق البائن عدة، وهل فيه مراجعة؟

ጥያቄ ፦

" አጠላቁ አል– ረጂዒ " (የመመለስ ፍቺና) " አጠላቁ አል–ባኢን " (ሙሉ በሙሉ ግንኙነት እንዳይኖራቸው በሚያደርገው ፍቺ) መሀል ያለው ልዩነት ምንድነው ?
አጠላቁ አል–ባኢን "ዒዳ" (መቁጠርና) መመለስስ አለውን ?

📘 الجواب:

الطلاق الرجعي هو: أن يطلق الزوج زوجته التي قد دخل بها طلقة واحدة أو طلقتين ولا تزال في العدة، فإذا طلق زوجته التي قد دخل بها، طلقة واحدة أو طلقتين، وهي لا تزال في العدة، فهو طلاق رجعي.

መልስ ፦

" አጠላቁ አል–ረጂዒ " (የመመለስ ፍቺ) ማለት ፦

ወንድዬው (ባል) ያገባት በሆነችው ባለቤቱ ላይ ከገባ (አብሮ መኖር ከጀመረና) ከዚያም አንድ ወይም ሁለት
ጊዜ የፈታት እንደሆነ በርሷ ላይ "ዒዳን"
የምትቆጥር ከመሆን ቅሮት የለውም።

ይህም " አጠላቁ አል–ረጂዒ"
(የመመለስ ፍቺ) ይባላል።

والطلاق البائن نوعان: منه ما هو بائن بينونة صغرى، ومنه ما هو بائن بينونة كبرى.

" አጠላቁ አል–ባኢን " (ሙሉ በሙሉ ግንኙነት እንዳይኖራቸው የሚያደርገው ፍቺ) ሁለት ዓይነት ነው።

1ኛው· " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ሱግራ" የሚባለው ሲሆን

2ኛው· " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ኩብራ" የሚባለው ነው።

فالبينونة الصغرى: أن يطلق زوجته التي دخل بها طلقة واحدة، أو طلقتين، ويتركها فلا يراجعها حتى تنتهي عدتها، فهذا طلاق بائن ولكن بينونة صغرى، فله أن يُعيدها بعد ذلك إذا أحب بنكاح جديد.

ومثله أن يطلق زوجته التي لم يدخل بها، طلقة واحدة، فإذا طلق زوجته التي عقد عليها ولم يدخل بها طلقة واحدة فإنها تصير بائنا بينونة صغرى، يستطيع ردها بنكاح جديد.

👉 "በይኑነተ ሱግራ" (የሚባለው ፍቺ) ፦

1· አንድ ወንድ ያገባትን ባለቤቱን
(አብሯት ገብቶ እየኖረ …) አንዴ ወይም ሁለቴ ይፈታትና "ዒዳዋን" ቆጥራ እስክትጨርስ ድረስ ሳይመልሳት ይተዋታል።

ይህ ዓይነቱ ፍቺ " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ ነገር ግን "በይኑነተ ሱግራ" የሚባለው ነው። ለርሱ (ለባልዬው) ከዚህ በኋላ ሊመልሳት የወደደ (የፈለገ) እንደሆነ እንደ አዲስ "ኒካሕ" በማድረግ
(መመለስ ይችላል።)

2· (ሌላው) ተመሳሳይ የሆነው ፍቺ ፦

አንድ ወንድ (ያገባትን) "ኒካሕ" ያሰረላትን ባለቤቱን (አብሯት ገብቶ መኖር ሳይጀምር) አንድ ጊዜ ከፈታት
(እቺ ሴት) "ባሂን" ትሆናለች።
ይህም ማለት "በይኑነተ ሱግራ"
ማለት ነው።

(ከፈለገ) አዲስ "ኒካሕ" በማድረግ
(መመለስ ይችላል።)

وأما الطلاق البائن بينونة كبرى: فهو أن يطلق زوجته التي دخل بها ثلاث تطليقات في مجالس متفرقة وكل طلقة منها في طهر، فهذا طلاق بائن بينونة كبرى ولا تحل له بعد ذلك حتى تنكح زوجا غيره.

👉 " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ኩብራ" የሚባለው ከሆነ …

እርሱ (ባልዬው) ያቺ ያገባት በሆነችው ባለቤቱ ላይ ገብቶ አብሮ እየኖረ …
በተለያየ ጊዜ ሦስት ፍቺን ከፈታትና
ሁሉንም ፍቺ ሲፈታት ደግሞ "ጣሂር"
(ከወር አበባ ደም) ንፁህ ከነበረች ይህ
ዓይነቱ ፍቺ " አጠላቁ አል–ባኢን " ሆኖ "በይኑነተ ኩብራ" የሚባለው ነው።

ከዚህ በኋላ ሌላ ባል አግብታ (እስከምትፈታ) ድረስ ለርሱ የተፈቀደች አትሆንም።

وقول السائل: هل في الطلاق البائن عدة؟
الجواب: نعم فيه عدة، البينونة الصغرى، والبينونة الكبرى، كلها فيها عدة، إلا التي طلقها قبل الدخول بها فليس عليها عدة، أول ما يطلقها تصير بائنا وليس عليها عدة، لقول الله تعالى: { يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نَكَحْتُمُ الْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمْ عَلَيْهِنَّ مِنْ عِدَّةٍ تَعْتَدُّونَهَا ۖ فَمَتِّعُوهُنَّ وَسَرِّحُوهُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا }.

አጠላቁ አል–ባኢን (በሚለው ፍቺ) ውስጥ "ዒዳ" መቁጠር አለን ?
ለሚለው ጥያቄው ፦

መልሱ ፦ አዎ ! ዒዳ አለው።

"በይኑነተ ኩብራ" እና "በይኑነተ ሱግራ"
ሁሉም ዒዳ አለው።

ባልዬው ካገባት በኋላ (አብሯት ለመኖር)
ሳይገባ በፊት የፈታት እንደሆነ በርሷ ላይ "ዒዳ" የለባትም ፤ (የሚለው ሲቀር …)

መጀመሪያውንም የፈታት እንደሆነ "ባሂን" ትሆናለች። በርሷ ላይ "ዒዳ" የለባትም።

ከፍ ላለው ለአላህ ንግግር ሲባል ፦

(( " እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ምእምናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኩዋቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም፡፡ አጣቅሟቸውም ፤ (ጉርሻ ስጧቸው)፡፡ መልካም ማሰናበትንም
አሰናብቷቸው፡፡ " ))
【አል–አሕዛብ(49)】

وقول السائل: هل فيه المراجعة؟ الجواب: تكون المراجعة على ما سبق بيانه، والله أعلم.

አጠላቁ አል–ባኢን (በሚለው ፍቺ) ውስጥ መመለስ አለን ? ለሚለው ጥያቄው ፦

መልሱ ፦ መመለስ የሚለው ነገር ማብራሪያው እንዳስቀደምነው ነው።

የበለጠውን ዐዋቂ አላህ ነው !!!

*═════ ❁✿❁ ══ ❁✿❁ ═*

ታላቁ ሸይኽ አቢ አብዱረሕማን
ረሻድ ቢን አሕመድ አል–ዳለዒ

https://t.me/amr_nahy1

… ኢስማኤል ወርቁ …

موقع الشيـخ حفظـه الله :
https://www.sh-rashad.com/

*للاشتراك في قناتنا على التيلجرام اضغط على هذا الرابط 👇🏾👇🏾*
https://t.me/rshad11


📌ድብልቅልቁ የትምህርት ዓለም ዋይታ በእውነተኛው የኢስላም ብርሃን ሲፈታ📌

📝ተከታታይ ፅሁፍ

👉 ክፍል ( ሃያ ) 👈

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيم

... አብዛኛው ታዳጊ እፃናት እስከወጣቱ ድረስ እግር ኳስ ጫወታ ተመልምሎ ወደ ስራ ሲገባ ፦

1ኛ. በልምምድና በጫወታ ሰዓት የሚያደርገው ልብስ አውራውን
(አፍረተ-ገላውን) ያሳይበታል ።
ይህ ማለት ደግሞ በእስልምና እነዲሸፍነው የታዘዘውን የሰውነት ክፍል ባልተፈቀደ ሁኔታ ለእይታ ማጋለጥ ማለት ነው።

2ኛ. አብዛኛውን ጊዜ በልምምድና ውድድር ምክንያት ሶላትን ጨምሮ አንዳንድ "ዒባዳ"ላይ ከባድ ጉድለቶች ይከሰታሉ ። "አላህ" የደረሰለት ካልሆነ በስተቀር ከነጭራሹ እስከመተውም ይደረሳል።

3ኛ. በፉክክር ውሰጥ ለሚከሰቱ አላስፈላጊ "ሸሪዓ"ያወገዛቸው ለሆኑ ድርጊቶች ይዳረጋል።

ለምሳሌ፦

👉 ገንዘብ አሲዞ በመጫወትና ቁማር ላይ መውደቅ …

👉 ለሽንፈት ላለመዳረግ ሲባል አላስፈላጊ ድርጊትን መፈፀም ፤ ወንድሙን ጠልፎ መጣል የመሰለ፥
አካሉ እንዲጎዳ በማድረግ በቀለኛ እንዲሆን ማድረግ ፥ መጣላት ፣
መሳደብ ፣ እውከት መፍጠርና መጎዳዳት ... "ሸሪዓ" ያወገዘውን ጠላትነትን በእስልምና ወንድማማቾች መካከል እንዲከሰት ምክንያት መሆን...

4ኛ. በትላልቅ መድረኮች ላይ በቪዲዮ መቀረፅ ፥ ሴትና ወንዶች ተቀላቅለው እንዲታደሙ በማድረግ ለሚደረገው አላህን የሚያስቆጣ ወንጀል ምክንያት መሆን ፤ በዚያ ቦታ ላይ ለሚከሰቱ ጩኅቶቾ ፣ ስድቦች ፣ ብልግና ለሆኑ ክንውኖች ፥ ዘፈኖች ፣ አንድነትን የሚሸረሽሩ ቀረሮች ፣ ግጥሞችና ፉከራ ... ጠቅሰን የማንዘልቀው
ለሆነው ክስተት አንድ አካል ሆኖ መገኘትን እውን ያደርጋል ።

👉 ይህ ድርጊት በጣም በሚያሳዝን መልኩ ሴት እህቶቻችንንም ያካተተ መሆኑ ነው ። እስቲ ቆም ብለን እናስተውል ፤ ከላይ ከብዙ በጥቂቱ ለማየት የሞከርነውን ጥፋት በፆታ ሴት ወደሆኑ እንስቶች ቀይረን እንመልከተው።

❌ የት/ቤት ስፖርታዊ አለባበስና የሴቶች ልጆቻችን ተሳትፎሃቸው ፦

👉 ት/ቤት ውስጥ በስፖርት አስተማሪ የስፖርት ልብስ አምጡ በሚል አስገዳጅ ትዕዛዝ የስፖርት ልብስ ያዘጋጃሉ። ከዚያም ውዷ የኢስላም እንቁ በተዘጋጀላት የስፖርት ልብስ የደመቀች ይመስል ትራቆታለች። በአስተማሪያቸው እጅ ከጭናቹ ወደዚህ ፥ ከወገብ ወደላይ ፥ ከጉልበት ሸብረክ እየተባሉ ይዳሰሳሉ ፤ታዲያ ይህ ሁሉ በስፖርት ትምህርት ስም የሆነ እውነት ነው።

👉 ግን ምን ችግር አለ❓ልብ ከታወረ ምን ይደረግ❓ፈጣሪ የቀናባት ባሪያ የሚቀናላት ባሪያ አጣች❗

አባትም❓እናትም❓ወንድምም❓
ዘመድም❓በቃ አሆ❗ሁሉም ፀጥ አሉ !!!

"ነብዩ" ግን ገና ቀድሞኑ "ደዩስ"
"ጀነት" አይገባም አሉ !!!

ደዩስ ደግሞ ማነው❓

ደዩስማ በቤተሰቡ (በቤተዘመዱ) በእህት ወንድሞቹ ወንጀል ሲሰሩ አይቶ የማይቀና (የማይቆች) ማለት ነው።

💫 ((عن عبدالله بن عمر (ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ)ﻗﺎﻝ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ : "ﺛﻼﺛﺔ ﻻ ﻳﻨﻈﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ ﺇﻟﻴﻬﻢ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﻘﻴﺎﻣﺔ : ﺍﻟﻌﺎﻕ ﻟﻮﺍﻟﺪﻳﻪ ، ﻭﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﺍﻟﻤﺘﺮﺟﻠﺔ ، ﻭﺍﻟﺪﻳﻮﺙ ،"))
ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ
ﺣﺴﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ

💫 (("አብደላህ ቢን ዑመር (አላህ ስራውን ይውደድለትና) ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አሉ በማለት አለ ፦
" የወላጆቹን ሐቅ ያጓደለ ፥ ወንዶችን የምትመሳሰል ሴትና በሴቶቹ የማይቀና ወንድ (እነዚህ) ሦስት ሰዎች እለት ትንሳዔ ቀን አላህ ወደ እነሱ አይመለከትም ።" ))

[ኢማሙ አሕመድና ነሳኢ ዘግበውታል]
(ኢማሙ አልባኒ ሐሰን ብለውታል)

አላህ ይጠብቀን!!!

📚 ታላቁ "ኢማም ሐሰነል በስሪ" በሴቶቻቸው የማይቀኑን ወንዶችን እንዲህ በማለት ወቅሶ ነበር ፦

قَالَ الحسَنُ البَصرِيِّ رَحِمَهُ اللهُ :

" أتدعُونَ نِساءَكُم لِيُزاحِمْنَ العُلُوجَ فِي الأسوَاقِ ؟! قَبَّحَ اللهُ مَن لا يَغَارُ ".

📚(إحيَاءُ عُلُومِ الدِّين ٤٦/٢).

ሐሰነል በስሪ አላህ ይዘንለትና አለ ፦

" በግብይይት ቦታ ላይ እንደ አህያ እንዲጋፉ ሴቶቻችሁን ትተዋላችሁን❓❗(በሴቶቹ) የማይቀና የሆነ ሰው "አላህ" ከሁሉም "ኽይር" ያርቀው።

[ኢሕያሁ ዑሉሚ አል-ዲኒ 2/46]

🔥 እስቲ ወገኖቼ ቆም ብለን እናስብ
(እንቆርቆር) የአብራካችን ክፋይ
የኢስላም እንቁ "የሁዳና ነሳራ" የአላህ ጠላት የሆኑ ካህዲያኖች "በፈበረኩላት"
እግር ኳስ ተጠምዳ ፤ የወደዱላት መስለው ባሴሩባት ፥ ያደነቋት መስለው በተሳለቁባት ፥ የጠቀሟት መስለው በጎዷት ነገር ላይ አሳልፈን
ሰጥተናቸዋል !!!

እንደፈለጋቸው እንዲያደርጓት ፈቀድንላቸው ፤ ብቻም አይደለም … ጭራሹንም እነሱ ከደከሙት በላይ ደከምንላቸውና ፍላጎታቸውንም ሞላንላቸው❗❗❗

አላህም የሚለው ይህንኑ ነው ፦

📖 (( "وَاللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَيُرِيدُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الشَّهَوَاتِ أَن تَمِيلُوا مَيْلًا عَظِيمًا" ))
النساء (27)

(( " አላህም በእናንተ ላይ ፀፀትን ሊቀበል ይሻል። እነዚያም ፍላጎታቸውን
የሚከተሉ የሆኑት (ከእውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ
ይፈልጋሉ … ። " ))
[አል-ኒሳህ (27)]

በአላህ ፍቃድ ክፍል ሃያ አንድ
ይቀጥላል ፦

📝 … ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/amr_nahy1


" ሱረቱል አል–ከህፍ "

☄️ بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

📘 السؤال الثاني عشر:
(المجموعة الثالثة)

هل ورد حديث في فضل قراءة سورة الكهف في يوم الجمعة؟

ጥያቄ ፦

"ጁምዓ" ዕለት "ሱረቱል ከህፍን"
ማንበብ በላጭ ስለመሆኑ
"ሐዲስ " መጥቷልን

📘 الجواب:

وردت أحاديث في فضل قراءة سورة الكهف مطلقا دون تخصيص يوم الجمعة وهي صحيحة.

وأما تخصيص يوم الجمعة فالزيادة التي وقعت في الحديث زيادة ضعيفة شاذة، كما تكلمنا عنه سابقا بالتفصيل.

فيستحب قراءة سورة الكهف مطلقا دون تخصيص ذلك بيوم الجمعة، والله أعلم.

*═════ ❁✿❁ ══ ❁✿❁ ═*

መልስ ፦

ዕለተ "ጁምዓን" ባለመለየት "ሱረቱል ከህፍን" ማንበብ በላጭ ስለ መሆኑ በልቁ "ሐዲስ" መጥቷል።
ይህ ትክክል ነው።

ዕለተ "ጁምዓን" መለየትና "ሱረቱል ከህፍን" ማንበብ በሚል ተጨማሪ ሆኖ
ሐዲሱ ውስጥ የመጣው (የሐዲሱ መልዕክት) "ደዒፍ" (ደካማና) "ሻዝ" (አውሪው ከሌሎች አውሪዎች
ይልቅ ብቻውን የተለየበት የሆነ)
ጭማሪ ነው።

ስለዚህም ነገር በማስቀደም በዝርዝር እንደተናገርነው… (ማለት ነው።)

"ዕለተ "ጁምዓን" ከመለየት ውጪ "ሱረቱል ከህፍን በልቁ ማንበብ
የተወደደ ነው !!!

የበለጠውን ዐዋቂ አላህ ነው !!!

ታላቁ ሸይኽ አቢ አብዱረሕማን
ረሻድ ቢን አሕመድ አል–ዳለዒ

https://t.me/amr_nahy1

… ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/rshad11


ሁሉም ነብያቶች የአላህን አንድነት በማወጅ ላይ ነው የመጡት !!!

አላህ እንዲህ ይላል ፦

(( " ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ " ))
【አል–አንቢያ (25)】

ታላቁ ኢማም ኢብን ዑሰይሚን

… ኢስማኤል ወርቁ…

http://t.me/amr_nahy1


ልጅህን አታታለው !!!

‏📌لا تغش إبنك ..

بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

▪️سئل العلامة الفوزان -حفظه الله-
- *هل يجب على الوالد أن يوقظ ولده لصلاة الفجر وأدائها في المسجد عند بلوغه السابعة ؟*

ጥያቄ ፦

ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ በሚል
ተጠየቁ ?

አባት ልጁን ሰባት ዓመት ሲደርስ ጊዜ
በመስጂድ ውስጥ የፈጅር (የሱቢሕ) ሶላት እንዲሰግድ (ከመኝታው)
መቀስቀስ ግዴታ ይሆንበታልን ?

*▫️فأجاب : إي نعم، يذهب به *إلى المسجد ليربيه على الصلاة وعلى الخير، هذه التربية الصحيحة*.
‏=
*✖️ولا يتركه في فراشه* ،
*↩️هذه تربية سيئة وقد غش *ولده*..
*ويريد الرفق به ويريد الرحمة، غشه.*

📝التعليق على إغاثة اللهفان- ٢ربيع الاول١٤٣٩هـقناة العلامة الفقيه صالح بن الفوزان حفظه الله
تهتم بنشر كل مايتعلق بالشيخ من علوم

መልስ ፦

እንዴታ አዎ ! በሶላትና በመልካም ነገር
ላይ ኮትኩቶ እንዲያሳድገው ዘንድ
ወደ "መስጂድ" ይውሰደው።

ይህ ትክክለኛ አስተዳገግ ነው !!!

በሚተኛበት ፍራሽ ላይ አይተወው !!

ይህ መጥፎ አስተዳገግ ነው !!
በእርግጥም ልጁን አታሎታል !

እርሱ በልጁ ላይ መራራትን
ይፈልጋልን … ?
ማዘንንም … ይፈልጋል ?
… ልጁን አታሎታል !!!

ታላቁ ሸይኽ ሷሊሕ አል ፈውዛን

https://t.me/amr_nahy1

… ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/g4448


📌ድብልቅልቁ የትምህርት ዓለም ዋይታ በእውነተኛው የኢስላም ብርሃን ሲፈታ📌

📝ተከታታይ ፅሁፍ

👉 ክፍል ( አስራ ዘጠኝ ) 👈

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيم

ባሳለፍነው ተከታታይ አምስት ክፍሎች
ዕፃናቶች በኢኽትላጥ ት/ት ምክንያት እየደረሰባቸው ያለው አሳሳቢ ጥፋት፤ ለወደፊቱ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ
ከባድ የሆነ መሸከም የማይችለው ፈተና እንደተጋረጠበት የሚያሳይ ነው❗❗❗

👉 "ኢኽትላጥ" ት/ት በወጣቶች ላይ ያደረሰውን ውድመት በተመለከተ በአላህ ፍቃድ በሰፊው እንደምንመለስበት ተስፋ በማድረግ ፤ ለአሁኑ ግን ለምልከታ ያህል ይህን ካልን ወደሌላው አስከፊ የትምህርት ቤት ጥፋት እንመለስና የተወሰኑ ነጥቦችን አላህ ባገራልን ልክ ለማየት እንሞክር።

2. (ትምህርትና የተለያዩ ወንጀሎች)

👉 ይህ ማለት ከኢኽትላጥ (ከሴትና ወንድ) ተደባልቆ መማር በተጨማሪ ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደ ወንጀል ሊያየው ያልፈቀደውና ቢያየው እንኳን እርምት ሊያደርግበት ፍቃደኛ ያልሆነበት አስከፊ ጥፋት ነው❗

👉 ከነዚህ ወንጀሎች ውስጥ "ኩፍር" ደረጃ የሚደርሱም አሉ !!!

አብዛኛዎቹ ወንጀሎች በትምህርት ዓይነት ውስጥ የሚከሰቱም ናቸው ፦

ለምሳሌ ፦

(ሀ) (የስፖርት ትምህርት)

👉 መቼስ ሳይታለም የተፈታ ነው❗
ምኑ እንደምትሉኝ ጥርጥር
የለውም ። በሰዎች አይምሮ ውስጥ
"ደሞ ስፖርትን መስራት የተከለከለ ነው የሚሉ መጡ እንዴ❓" በማለት የሚያስቡ ወይም እንዲያስቡ የሚያደርጉና የሚደረጉ ሰዎች መኖራቸው ...

👉 ነገሩ ወዲህ ነው❗አላህ እንዳለው እነዚህ ሰዎች በዓይናቸው ብቻ ማየትን መርጠው እንጂ በልቦኖቻቸው ቢያዩ ኖሮ
በስፖርት ምክንያት ጭኖቿን ፣ ደረቷን ... መላ አካላቷን ለእይታ አራቁታ የምትሮጠውን እንስት ከዕንቁዋና ጥቡቅዋ ዓኢሻ ጋር ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሮጡትን ሩጫ ባላነፃፀሩ ነበር ።

👉 እኛ የነብዩን ሱና በአላህ ፍቃድ በትክክል በመከተል ጥረት ላይ ያለን (ሱንዮች) ፤ እያልን ያለነው ያልተወገዙና ያልተከለከሉ የሆኑ የስፖርት ዓይነቶችን ሸሪዓን በማይጋጭ መልኩ እንስራው
ነው ። ካልሆነ ግን የመዘዙ ማሳረጊያ እሳት ነውና ፤ ይቅር እንራቀው ነው !!!

👉 በት/ቤት ውስጥ ብዙ ዓይነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አሉ።
እግር ኳስ ፣ ቅርጫት ኳስ ፣ የእጅ ኳስ ፣ ሩጫ ፣ ውሃ ዋና ፣ ሜዳ ቴኒስ ...በርካታ ነው ! እንደ ት/ቤቱ ከፍታና ዝቅታ ቢለያይም ፤ በተለይ አሁን ባለንበት ዘመን በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ስፖርታዊ መዝናኛዎች አንዲሁም ገንዘብ ማስገኛዎችና የሀገርን ባንዲራ ከፍ ማድረጊያዎች እየተባሉ የሚጠሩ እንቅስቃሴዎች እየተበራከቱ መጥተዋል።

👉 በዋነኝነት ብዙ ስፖርተኞችን ለመመልመል እንደ ግብሃት ተደርጎ የሚወሰደውም የት/ቤት ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ነው።
ታዲያ እኛ ሙስሊሞች የት/ቤት ውሎሃችንና ያለን ስፖርታዊ ተሳትፎ ምን ይመስላል❓ከሸሪዓ አንፃርስ የትና የት ነው ያለነው❓

👉 ሳንወሻሽ እውነቱን እንነጋገር ፤

ለምሳሌ ፦ እግር ኳስ

👉 መቼስ እግር ኳስ ሲባል ብዙሃናችን ግር ይለናል ፤ " ደሞ ብሎ ብሎ በኳስ❓የሚገርም ነው !!! ከሸሪዓ ጋር ምን ያገናኘዋል❓" የሚለውም እጅግ የበዛ ነው።

👉 ወንድም እህቶቼ ማንኛውንም ዲንን እንዲሁም ዱንያን የሚመስል ነገር ከመስራታችን በፊት በእስልምና እንዴት ይታያል? ሳይመስለኝ ወንጀል ላይ እወድቅ ይሆን...? ብለን መጠየቅ ፣ ማወቅና መገንዘብ መቻል አለብን።

{"فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ"}
(النحل (43)

(( " የማታውቁም ብትኾኑ የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ … !!! " ))
[ሱረቱል አል-ነሕል 43]

በአላህ ፍቃድ ክፍል ሃያ ይቀጥላል ፦

📝 … ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/amr_nahy1


☄️ بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

📘 السؤال الخامس:
(المجموعة الثالثة)

إنسان عليه كفارة يمين هل يجوز أن يُطعم عشرة مساكين دون أن يطبخ؟

ጥያቄ ፦

አንድ ሰው የማላ "ከፋራ" (ማካካሻ)
አለበት።አስሩን ምስኪኖች ሳያበስል መመገብ ይቻልለታልን ?

📘 الجواب:

إذا كان المراد يأتيهم بطعام جاهز من المطعم مثلا أو نحو ذلك فهذا جائز، ولا يُشترط أن يطبخ، المهم أن يطعم عشرة مساكين، وله أن يوكل من يثق به، يعطيه مالا ويقول له اذهب اطعم هؤلاء العشرة، فهذا جائز ومجزئ، مع أن الإنسان عليه أن يتحرى في باب الوكالة ولا يتساهل، والله أعلم.

*═════ ❁✿❁ ══ ❁✿❁ ═*

መልስ ፦

ለምሳሌ፦ በተዘጋጀ ምግብ ወይም የመሳሰለ በሆነ (ምግብ) ምስኪኖቹን በመመገብ ላይ መምጣቱን ከሆነ የተፈለገበት ይህ ነገር ይቻላል።

(ምግቡን) ማብሰሉ ቅድመ ሁኔታ አይደረግም!!

አሳሳቢው ነገር አስር ምስኪኖችን መመገቡ ነው።

የሚያምነው ለሆነ ሰው መወከልም ይችላል።

ለዚህ (ለሚወክለው) ሰው ገንዘብ በመስጠት ሂድና እነዚህን አስር ምስኪኖችን መግብልኝ !
ቢል የሚቻልና የሚያብቃቃ ነው።

ለሰው ልጅ ያለበትና የተገባ የሚሆነው "ውክልና" በሚለው ርዕስ ላይ ትኩረት
ማድረጉ ነው።

ችላ አይበል !!!

ታላቁ ሸይኽ አቢ አብዱረሕማን
ረሻድ ቢን አሕመድ አል–ዳለዒ

https://t.me/amr_nahy1

… ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/rshad11


🍥 « من قصص اليهود - الجزء الأول »
🍥 « ከአይሁዶች ታሪክ - ክፍል አንድ »

🗳 በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት መካሪ የሆን የጁመዓ ኹጥባ ትርጉም።

🎙 በኡስታዝ:- አቡ ቀታዳ አብደላህ ሙዘሚል አላህ ይጠብቀው።

🕌 በሱና መርከዝ {ቂልጦ - ጎሞሮ} አላህ ይጠብቃት።

📅 አርብ:- 17/03/2014 EC

🔗 https://t.me/merkezassunnah/1990
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
🔗 https://t.me/qanathabuqetada/4283


ሐሳን ኢብን ሳቢት ስለ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የገጠመው አስደማሚ ግጥም !!! አድምጡት ! …ኢስማኤል ወርቁ… https://t.me/amr_nahy1


Репост из: الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر
(ባለ ቅኔዎቹን …)

بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

📌ما معنى قول الله تعالى والشعراء يتبعهم الغاوون ؟

العلامة صالح الفوزان حفظه الله:

🔹السؤال:

ما معنى قول الله تعالى : (وَالشُّعَرَاءُ يَتَّبِعُهُمْ الْغَاوُونَ)؟

ጥያቄ ፦
(وَالشُّعَرَاءُ يَتَّبِعُهُمْ الْغَاوُونَ)

የሚለው የአላህ ንግግር (የቁርኣን አንቀፅ) ትርጉሙ ምንድነው ?

🔹الجواب:

نعم الشعراء يتبعهم الغاوون، اقرأ الذي بعده تعرف السبب: (أَلَمْ تَرَى أَنَّهُمْ فِي كُلِّ وَادٍ)، يعني الشُّعراء، ( فِي كُلِّ وَادٍ يَهِيمُونَ* وَأَنَّهُمْ يَقُولُونَ مَا لا يَفْعَلُونَ* إِلاَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَذَكَرُوا اللَّهَ كَثِيراً وَانتَصَرُوا مِنْ بَعْدِ مَا ظُلِمُوا )، فالذين اهتدوا من الشعراء كحسَّان بن ثابت، وغيره من شعراء المسلمين، هؤلاء استثناهم الله –عزَّ وجل- .

🔹رابط ملف الصوت المباشر:

መልስ ፦

"አዎ ! ባለ ቅኔዎችንም (ገጣሚዎችን) ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡"

ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የቁርኣን አንቀፆችን አንብባቸው ! ምክንያቱን ታውቀዋለክ።

እነርሱ በ(ንግግር) በየሸለቆ ሁሉ
ውስጥ የሚዋልሉ መኾናቸውን
አታይምን❕

👆

ገጣሚዎቹን (ባለ ቅኔዎቹን)
ማለት ነው !!!

(( " ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡

እነርሱ በ(ንግግር) በየሸለቆ ሁሉ
ውስጥ የሚዋልሉ መኾናቸውን
አታይምን❕

እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መኾናቸውን (አታይምን)❕

እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ አላህንም በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)፡፡
እነዚያም የበደሉ (ከሞቱ በኋላ)
እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ " ))
【አል–ሹዓራ (24፥27)】

እንደነዚያ አላህ የመራቸው የሆኑት "ሐሳን ቢን ሳቢትን" የመሳሰሉ
የሙስሊም ገጣሚዎችን አሸናፊና
የላቀ የሆነው አላህ ለይቶ (አውስቷቸዋል።)

ታላቁ ሸይኽ ሷሊሕ አል ፈውዛን

https://t.me/joinchat/ EX3ov2X9C8o1NDFk

… ኢስማኤል ወርቁ …

https://d.top4top.net/m_934lt21x1.mp3


Репост из: الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر
(ባለ ቅኔዎቹን …)

بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

📌ما معنى قول الله تعالى والشعراء يتبعهم الغاوون ؟

العلامة صالح الفوزان حفظه الله:

🔹السؤال:

ما معنى قول الله تعالى : (وَالشُّعَرَاءُ يَتَّبِعُهُمْ الْغَاوُونَ)؟

ጥያቄ ፦
(وَالشُّعَرَاءُ يَتَّبِعُهُمْ الْغَاوُونَ)

የሚለው የአላህ ንግግር (የቁርኣን አንቀፅ) ትርጉሙ ምንድነው ?

🔹الجواب:

نعم الشعراء يتبعهم الغاوون، اقرأ الذي بعده تعرف السبب: (أَلَمْ تَرَى أَنَّهُمْ فِي كُلِّ وَادٍ)، يعني الشُّعراء، ( فِي كُلِّ وَادٍ يَهِيمُونَ* وَأَنَّهُمْ يَقُولُونَ مَا لا يَفْعَلُونَ* إِلاَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَذَكَرُوا اللَّهَ كَثِيراً وَانتَصَرُوا مِنْ بَعْدِ مَا ظُلِمُوا )، فالذين اهتدوا من الشعراء كحسَّان بن ثابت، وغيره من شعراء المسلمين، هؤلاء استثناهم الله –عزَّ وجل- .

🔹رابط ملف الصوت المباشر:

መልስ ፦

"አዎ ! ባለ ቅኔዎችንም (ገጣሚዎችን) ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡"

ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የቁርኣን አንቀፆችን አንብባቸው ! ምክንያቱን ታውቀዋለክ።

እነርሱ በ(ንግግር) በየሸለቆ ሁሉ
ውስጥ የሚዋልሉ መኾናቸውን
አታይምን❕

👆

ገጣሚዎቹን (ባለ ቅኔዎቹን)
ማለት ነው !!!

(( " ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡

እነርሱ በ(ንግግር) በየሸለቆ ሁሉ
ውስጥ የሚዋልሉ መኾናቸውን
አታይምን❕

እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መኾናቸውን (አታይምን)❕

እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ አላህንም በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)፡፡
እነዚያም የበደሉ (ከሞቱ በኋላ)
እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ " ))
【አል–ሹዓራ (24፥27)】

እንደነዚያ አላህ የመራቸው የሆኑት "ሐሳን ቢን ሳቢትን" የመሳሰሉ
የሙስሊም ገጣሚዎችን አሸናፊና
የላቀ የሆነው አላህ ለይቶ (አውስቷቸዋል።)

ታላቁ ሸይኽ ሷሊሕ አል ፈውዛን

https://t.me/joinchat/ EX3ov2X9C8o1NDFk

… ኢስማኤል ወርቁ …

https://d.top4top.net/m_934lt21x1.mp3

Показано 20 последних публикаций.

202

подписчиков
Статистика канала