Фильтр публикаций


በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የአባ ሰንጋ በሽታ በመከሰቱ የአከባቢው ህብረተሰብ ስጋ ከመመገብ እንዲቆጠብ ተገለፀ!!

ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የእንስሳት ጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ወንድሙ አበበ እንደገለፁት ፣ ለቅዳሜ እርድ ከተዘጋጁ የእርድ በሬዎች ውስጥ አንድ በሬ በድንገት በአባ ሰንጋ በሽታ ምክንያት ሞቶ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

በሬው ከመሞቱ በፊት ከሌሎች በሬዎች ጋር የተቀላቀለ በመሆኑ ከዚህም ጋር ተያይዞ ሌሎች በሬዎች ላይ የበሽታው ምልክት ታይቷል ብለዋል፡፡

በአፍ ፣ በአፍንጫና በቂጥ እንዲሁም ላም ከሆነች በሽንት መሽኛ ቀዳዳ የደምና መሰል ፈሳሽ በሚታይበት ጊዜ የአባ ሰንጋ በሽታ መሆኑ ይጠረጠራል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አባ ሰንጋ ከሰው ወደ እንስሳ ፣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ገዳይ በሽታ ነው ያሉት አቶ ወንድሙ ፣ ከዞንና ከከተማ መዋቅር የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን እርድ እንዳይካሄድ ውይይት በማድረግ ተወስኗል ብለዋል፡፡

አቶ ወንድሙ አያይዘውም እርድ ከማገድ ባለፈ ለእርድ የተዘጋጁ በሬዎች በባለሙያዎች መታየት እንዳለባቸው ገልጸው ፣ የሞተውን በሬ አከባቢውን በማይበክል ሁኔታ ለመቅበር ከማዘጋጃ ቤት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ግብዓት የማዘጋጀት ሥራ በመሠራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የአከባቢው ነዋሪዎች የእንስሳት ኮቴ ተቆጥሮ የበሽታው ስርጭት ያለመስፋፋቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ማንኛውንም እርድ ማካሄድ እንደማይገባቸው ተናግረው ፣ ህብረተሰቡ ላልተወሰነ ጊዜ ስጋ እንዳይመገብ አሳስበዋል፡፡ላልተወሰነ ጊዜ የቁም የእንስሳት ከቦታ ቦታ ከማዘዋወር ህብረተሰቡ እንዲታቀብም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via - Bonga Communication affair

@addis_news


ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባፉት 3 ወራት 411 ጊጋ ዋት ሰዓት አመነጨ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ከመነጨው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 10 በመቶ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በጽህፈት ቤቱ የዕቅድ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ጥሩወርቅ ሺፈራው እንደገለጹት÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከመነጨው 4 ሺህ 98 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ውስጥ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 411 ጊጋ ዋት ሰዓት አመንጭቷል፡፡
በቅርቡ ኃይል ማመንጫት የጀመሩት ሁለት ዩኒቶች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 411 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት ወደ ብሔራዊ ኃይል ቋት ማስገባት መቻሉን የኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ አመላክቷል፡፡

@addis_news
@addis_news


ደብረ ብርሃን‼️
በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር-ቤት በወቅታዊ የፀጥታ ስጋት ምክንያት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱ ተገለፀ፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የከተማውን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በመገምግም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ገደቦች ያነሳ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል በከተማው የፀጥታ ምክር-ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጥለው የነበሩት ገደቦች የተነሱ በመሆኑ አሁንም በከተማው የፀጥታ ችግሮች እንዳይገጥሙ ማህበረሰቡ የፀጥታው ባለቤት በመሆን ራሱን፣ድርጅቱን እና አካባቢውን በትኩርት መጠበቅ እንዳለበት አሳስቧል፡፡

ማህበረሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን የሚያካራያቸውን ሰዎች መረጃ ይዞ በማከራየት፣ ፀጉረ ልውጦች ሲጋጥሙም ጥቆማ በመስጠት አጋርነቱን እንዲሳይ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በመጨረሻም ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ በመመሪያ በተከለከሉና ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የጦር መሳሪያ መያዝ እና የመከላከያና የልዩ ኃይል የደንብ ልብሶችን መልበስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታቋል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት
ጥቅምት 4/02/2015 ዓ.ም

@addis_news
@addis_news


#AmharaRegion

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች በራሳቸው አቅም ብቻ ተማምነው ወደፈተና ማዕከላት እንዲመጡ ጠየቀ።

በራሱ በመተማመን መፈተን ያልፈለገ ተማሪ ወደ ማእከላት ባይመጣ ይመረጣል ብሏል ቢሮው።

ከሰሞኑ በጥቂት ማእከላት የተፈጠረው ክስተት የአማራ ክልልን ህዝብና ተማሪዎችን የማይመጥን ድርጊት ነው ሲልም ገልጿል።

በቀጣይ ሳምንት ፈተና የሚወስዱት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከተጠናቀቀው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሂደት በመማር ፍጹም ለአሉባልታና ለወሬ ሳይበገሩ ፈተናቸውን በሰላም እንዲወስዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።

ለቀጣዩ ፈተና ከወረዳ ጀምሮ ያሉ አካላት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ተማሪዎች ዩንቨርስቲ የሚመጡት ፈተና ለመፈተን እንጂ ለሌላ ተልእኮ አለመሆኑን በመገንዘብ የተቀመጡትን ህግና ደንቦች አክብረው እንዲፈተኑ ጠይቋል።

@addis_news
@addis_news


#ጎጆ_መረጃ

አሳዛኝ ዜና😢📍

የ አንድ ተማሪ ህይወት አልፏል‼️

የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጭኖ ወደ ቤታቸው ሲወስዳቸው ከነበሩት ውስጥ አንድ ባስ ተገልብጦ የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል። ሌሎች ተማሪዎች ላይም ጉዳት ደርሷል።

የገለምሶ ት/ት ቤት ተማሪዎችን የጫና አውቶብስ ከራሚሌ በሚባል አከባቢ ተገልብጦ ነው ጉዳቱ የደረሰው።

ይህ አደጋ ቀን ላይ አከባቢ የደረሳ ብሆንም እስካሁን የሚዲያ አካላት እና መንግስት ምንም አላሉም😢

ምነጭ:- Abdii Sabaa

@addis_news


#ወልድያ!

የወልዲያ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሏቸው በነበሩ ህጎች ላይ ማሻሻያ አደረገ!

የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት ከነገ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የባጃጅ ማህበራት ፈረቃን በሚመለከት አስቀምጧቸው በነበሩ ህጎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

በዚህም መሰረት:-

▪️1. የከተማዋን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በቀን 1 የባጃጅ ማህበር ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ ተቀምጦ የነበረውን አሰራር በማሻሻል ከነገ ጀምሮ በቀን 2 የባጃጅ  ማህበራት አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።

በመሆኑም ነገ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም የጁና ፅናት የባጃጅ ማህበሮች እንዲሰሩና በቀጣዩ ቀን ማለትም ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ሀገሬና ብሌን የባጃጅ ማህበራት እንዲሰሩ በዚህ ፈረቃ መሰረት በቀን 2 የባጃጅ ማህበሮች አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኖ ማሻሻያ ማድረጉን የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።

ማሳሰቢያ:- ማንኛውም ማህበር የሌለው እና ዜሮ ዜሮ ባጃጅ በስምሪቱ እንዳይገኝ ሲል የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤቱ አሳስቧል። ከዚህ በፊት የከተማዋን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት የተቀመጡ ክልከላዎች ባሉበት የሚቀጥሉ ይሆናል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት

@addis_news
@addis_news


ተፈተዋል!!
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ በዋስትና ከእስር ተፈቱ!!

ከሁለት ሳምንት በፊት “ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል” የተከሰሱት ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ እያንዳንዳቸው 10 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ፤ ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 3፤ 2015 ከእስር ተለቀቁ። ከሁለቱ ተከሳሾች ጋር በአንድ መዝገብ ክስ የተመሰረተበት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ግን የተጣለበት የጉዞ እግድን የተመለከተ ሰነድ ለፖሊስ ባለመቅረቡ አለመፈታቱን ጠበቃው አቶ አዲሱ አልጋው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

ሁለቱ ተከሳሾች ዛሬ ከቀኑ አስር ሰዓት ተኩል ገደማ የተለቀቁት፤ በአዲስ አበባ ገነት ሆቴል አቅራቢያ ከሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሆነ የጋዜጠኛ መዓዛ ባለቤት አቶ ሮቤል ገበየሁ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@addis_news
@addis_news


ጥምር ጦሩዛሬ የሚያስቆመዉ አልተገኘም ራያ ግንባር ጀመዶ እና መሀጎ ዛሬ ነፃ ወጥተዋል።ይቀጥላል
።ጥምር ጦሩን አግዙ
ሌላ የድል ዜና ደርሶኛል ጠብቁኝ አጣርቼ እመለሳለሁ .........

@addis_news


ራያ ግንባር‼️ዋጃ‼️
ጥምር ጦሩ ከቆቦ 15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ዋጃን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል።
አላማጣው የነበረው የህወሓት አመራር ህዝቡን ጥሎ ሸሽቷል።


@addis_news


ራያ ግንባር✊

👉ዋጃ በጥምር ጦር ቁጥጥር ስር መሆኗ ታውቋል።አላማጣ ይቀጥላል።የአካባቢው ህዝብ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ የሚያኮራ ነው ተብሏል።

👉እስሚዛ ነፃ ወጥቷል።መሀጎና መረዋ ይቀጥላል።


@addis_news


በኢትዮጵያ የወሲብ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ድህረገጾችን ለማሳገድ በአንድ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ!

በኢትዮጵያ የወሲብ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ድህረገጾችን ለማሳገድ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመሩን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ ማህዲ ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።በአንድ ግለሰብ ተነሳሽነት የተጀመረዉ እንቅስቃሴዉ አሁን ላይ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል በሆኑ 15 በሚደርሱ ሌሎች አባላትም ድጋፍ ማግኘቱን ጣቢያችን ሰምቷል።

የማስታወቂያ ባለሙያ በሆነዉ አለማየሁ አጥናፍሰገድ በተባለ ግለሰብ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድህረገጾቹን ለማሳገድ እንዲሁም በህጻናት እና ወጣቶች አእምሮ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና በማስተማር እና ማህበረሰብን የማንቃት እንቅስቃሴ አንድ ብሎ መጀምሩን ለብስራት ራዲዮ ተናግሯል።በበርካቶች ተቀባይነትን በማግኘት ላይ ያለዉ ግለሰቡ ፤ የሚያስተላልፋቸዉን መልእክቶች የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ ማህዲ ተመልክተዉ አጋርነታቸዉን እንዳሳዩት ገልጿል።

ጉዳዩ ከመንግስት በቂ ትኩረት አልተሰጠዉም ያለዉ ግለሰቡ ይህን አላማ የሚደግፉ አካላት በፊርማ ማሰባሰቡ ላይ እንዲሳተፉ እና ጉዳዩን በቂ ትኩረት እንዲሰጠዉ የራሳቸዉን አስተዋጽኦ ያድርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አባሉ የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ የወሲብ ምስእሎቹን በኢትዮጵያ ለማሳገድ ፊርማ ማሰባሰብ ላይ መሆናቸዉን  ተናግረዋል። እንቅስቃሴው እስካሁን ድረስም 15 በሚጠጉ በምክርቤቱ አባላት ድጋፍ ማግኘቱንም አንስተዋል።

ተመሳዳይ እገዳን እና ህግን ከደነገጉ ሀገራት አንዷ ከሆነችዉ ዩጋንዳ እና ቱርክ ፤ በህጉ ዙሪያ ያስቀመጧቸዉን ድንጋጌዎች ለህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ማስገባታቸውም የምክርቤቱ አባል ተናግረዋል።

በአለማችን ላይ በርካታ ሀገራት ክልከላዉን እና ትዉልዱን በመጠበቅ ላይ ሲሆኑ ከነዚህም ዉስጥ ሰሜን ኮሪያ በተለምዶዉ ቪፒኤን በተሰኘዉ (virtual protected network) አማካኝነትም ዜጎች ድህረገጾቹን እንዳይጠቀሙ ካገዱ ሀገራት ትጠቀሳለች። ሌላኛዋ የሩቅ ምስራቅ ቻይና ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ድህረገጾቹን ሳንሱር ከሚያደርጉ ሀገራት ዉስጥ ስትሆን የሀገሪቷ አደገኛ አጥር በተሰኘ ፕሮጀክት ድህረገጾቹ ላይ ቁጥጥር እና ክትትል ታደርጋለች።

በተጨማሪነትም ኳታር ፣ ሶርያ ፣ ቱርክሜኒስታን ፣ ፓኪስታን ፣ ቱርክ ፣ ኦማን ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ጎረቤት ሀገር ኤርትራ ድህረገጾቹ ላይ እገዳ እና ቁጥጥር የሚያደርጉ ሀገራት ናቸዉ።ቼንጅ ዶት ኦርግ ላይ መሰባሰብ በጀመረዉ ፊርማ እስካሁን ከ 4መቶ በላይ ሰዎች ድጋፋቸዉን መግለጻቸዉ ተመልክቷል።

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ራዲዮ]

@addis_news
@addis_news


ፍ/ቤቱ ስንታየሁ ቸኮልን በ15 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ብይን ሰጠ

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ በ3/2/2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ቡራዩ ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ለሶስት ወር የሚቆይ 20 ሺ ብር ዋስትና ከፍለዉ መዉጣት ይችላሉ ተብለዋል። የግፍ እስረኛዉ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ፍ/ቤቱን ከዚህ በፊት 140 ሺ ብር በላይ የዋስትና ገንዘብ ከፍያለሁ ቢቻል በነፃ ልሰናበት ይገባል ሲሉ የተከራከሩ ሲሆን ፍ/ቤቱም የመጨረሻ 15 ሺ ብር በማፅደቅ ከእስር እንዲፈቱ ብይን ሰጥቷል።

መረጃው የአስካለ ደምሌ ነው

@addis_news


በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ዛሬ ለጣሊያን ተላልፎ እንደተሰጠ ተዘገበ፡፡
የ35 አመቱ ተመስገን ገብሩ በሰሜን አፍሪካ በኩል አድርጎ ወደአውሮፓ ሰዎችን በማዘዋወር ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት አባል እንደነበር ተገልጿል፡፡
ይህ ኤርትራዊ በቁጥጥር ስር የዋለው በአዲስ አበባ አየር ማረፊያ ሲሆን ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በጣሊያን ሲሲሊ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት የእስር ማዘዣ ትእዛዝ የተቆረጠለት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ በኢንተርፖል የሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተተው ተመስገን በአዲስ አበባ በኩል አድርጎ ወደአውስትራሊያ ሊጓዝ እንደነበር ስዊዝ ኢንፎ ዘግቧል፡፡

ከቀናት በፊት ተወልደ ጎይቶም የተባለው ሌላኛው ኤርትራዊ በአዲስ አበባ ተይዞ ለኔዘርላንድ ተላልፎ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ የእነዚህ ሁሉ የበላይ የሆነው ኪዳኔ ዘካሪያስ ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት አምልጦ ከጠፋ በኋላ አሁንም ድረስ እየተፈለገ ነው፡፡

@addis_news


በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም -የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን

በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም ሲል የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገለጸ፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩን አስመልክቶ በስተላለፈው መልዕክት÷ በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሀገር አለኝታ የሆነ ትውልድ የማፍራት ርዕይን የሚጻረር ነው፡፡

ስለሆነም ድርጊቱ በሰው ልጅ ላይ ከሚፈጸም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተለይቶ የሚታይ አይደለም ነው ያለው፡፡

መንግሥት ለዚህ ጉዳይ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የምዘና ሥርዓቱ የትምህርት ጥራትን ብቻ ሳይሆን የተማረ ሰው ሃይልን ከፍታ በሚያስጠብቅ እና የምዘና ስርዓቱን ስብራቶች ለዘለቄታው በሚጠግን መንገድ የመጓዝ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑም አንስቷል።

በመንግሥት እየተወሰደ ያለውን የስርዓተ ትምህርት ለውጥም ሆነ የምዘና ሥርዓት ውጤታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ አሠራሮችን መደገፍና ለተፈፃሚነታቸው መተባበር ለመንግሥት እና ለትምህርት አመራርና ተቋማቱ ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በእውቀት የበለፀገ፣ አመለካከቱ ያደገ፣ በክህሎቱ የተካነ እና ውጤታማ የሆነ ትውልድ የመፍጠር ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ እንደሆነ ማስገንዘቡንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ የምዘና ሥርዓቱ ያለበትን ትውልድ አጥፊ ችግር ለማረም በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡ #FBC

  @Addis_News
@Addis_News


UPDATE ጋዜጣዊ መግለጫ!!

የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመጀመሪያው ዙር ከ586 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ133 ማዕከላት ተፈትነዋል።

ፈተናው በተጀመረበት ወቅት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው አደጋ እና በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን አስታውቋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በደረሰው ክስተትም የመጀመሪያው ቀን ተፈታኞች ያልተፈተኑ መሆኑንና ያልተፈተኗቸውን ፈተናዎች በቀጣይ ዙር የሚፈተኑ ይሆናል።

ከፈተና ተገቢ ባልሆነ መንገድ ራሳቸውን ያገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ፡

•መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ - 1,700
•ከደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ - 1,226
•ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ - 2,711
•ከደብረታቦር ዩኒቨርስቲ - 7,150

በጠቅላላው 12,787 ተማሪዎች ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይም ውስን ፈተናዎችን በመውሰድ ጥለው ወጥተዋል፡፡

በተለይም በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ተፈታኞች ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ ሁከት በመፍጠራቸው የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፈተና አስፈጻሚዎችና በፀጥታ ሃይላችን ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማን እየገለጽን፣ ፈተናው መፈተን የሚፈልጉ ተማሪዎች እንዲቀጥሉና ችግሩ እንዲረግብ ሁሉም ላደረገው ጥረት ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ፈተና ጥለው የወጡትን ተማሪዎች በተመለከተ ፈተና መፈተን እንዳማይፈልጉ አሳውቀው ግቢ ለቀው የወጡ በመሆኑ በቀጣይ መፈተን የማይችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ትምህርት ሚንስቴር
@Addis_News
@Addis_News


በመላ አገሪቱ ፈተና ከተሰጠባቸዉ 133 የፈተና ጣቢያዎች ውስጥ በአብዛኞቹ ጣቢያዎች ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ቢጠናቀቅም ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ግን ፈተናውን አቋርጠው መውጣታቸው ተጠቁሟል።

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከተፈጠረዉ አሳዛኝ ክስተት እና በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ፈተና  ሳይፈተኑ ከወጡ ተማሪዎች በስተቀር በመላ አገሪቱ ፈተና ከተሰጠባቸዉ 133 የፈተና ጣቢያዎች ውስጥ በአብዛኛዎቹ ጣቢያዎች ምንም አይነት ችግር እንዳልተፈጠረም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ፈተናውን አቋርጠው ለወጡ ከ12 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥም በመግለጫው ተመላክቷል።

@Addis_News
@Addis_News


በስልጤ ዞን የአራት ዓመት ሴት ህፃን በጅብ ተበልታ ህይወቷ አለፈ

በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ ማዞሪያ ተብሎ ከሚጠራዉ የገጠር ከተማ የ4 አመት ሴት ህፃን በጅብ ተበልታ ህይወቷ ማለፉን የደቡብ ክልል ፖሊስ ሚዲያ ኮምኒኬሽ ዲቨዥን ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

መስከረም 27 ቀን ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ በርካታ ልጆች በመጫወት ላይ የነበሩ ሲሆን ከመካከላቸው የ4 ዓመቷ ልጅ ጅቡ አንገቷን ይዞ ሲሮጥ እንደነበር ተገልጾል፡፡በሰዓቱ በአካባቢው የነበሩ እማጮች ድምፅ በማሰማታቸው ጅቡ ህፃኗን ጥሎ የሮጠ ቢሆንም የህፃኗን ህይወት ማትረፍ አልተቻለም ተብሏል፡፡

በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ጅብ በሰዉ ላይ ጥቃት ሲያደርስ የሚስተዋል ሲሆን ህፃናት ከሌላዉ የህብረተሰብ ክፍል በበለጠ የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑት የሚደርስባቸዉ ጥቃት ለመከላከል አቅም የሌላቸዉ በመሆኑ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይከሰት ወላጆች ለህፃናት ልጆቻቸዉ ተገቢዉ ጥበቃ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡


በሳምራዊት ስዩም

@Addis_News
@Addis_News


" ፈተናው በሰላም ተጠናቋል " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 2/2015 ዓ.ም ድረስ ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የከተማው ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ቢሮድ ፈተናው በአዲስ አበባ በ9 የፈተና ጣቢያዎች መሰጠቱን አመልክቷል።

ፈተናውን 23,208 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለመውሰድ ተመዝግበው 22,533 የሚሆኑት መፈተናቸው ተገልጿል።

ፈተናውን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ያልወሰዱና ተገቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተማሪዎች በቀጣይ እንደሚፈተኑ በትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መቀመጡን ቢሮው አሳውቋል።

25,995 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እሁድ ጥቅምት 6/2015 ዓ.ም ፈተናውን ወደሚሰጥባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ኦረንቴሽን ከተሰጣቸው በኃላ ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብሏል።

@Addis_News
@Addis_News


በትላንቱ የመተከል ጥቃት የተገደሉ የጓንግ ወረዳ ተወላጆች!
            
1ኛ አቶ ሰማነህ ዘለቀ በቀድሞ መተከል አውራጃ ጓንጓ ወረዳ ተወልደው ያደጉት አቶ ሰማነህ ዘለቀ የወረዳውን ህዝብ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እና በጎ አድራጎት ተግባር ከማገልገላቸው ባሻገር በቀድሞ ስርዓት በመረብ ኳስ ስፖርት ጎጃም ክፍለ ሀገርን በመወከል ኤርትራ ክፍለ ሀገርን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በመሳተፍ ለጎጃም ክፍለ ሀገር፣ለመተከል አውራጃ እና ለጓንጓ ወረዳ በርካታ የጀግንነት ሽልማቶችን አበርክተዋል።

አቶ ሰማነህ ዘለቀ ትላንት ህይወታቸው እስኪያልፍ ድረስ በጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ፅቤት በማህበራዊ ዘርፍ ባለሙያነት ሲያገለግሉ ቆይተው በህክምና ሲረዱ ቆይተው አርፈዋል።
              
2ኛ አቶ ሂስ ሄጮ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ዳች ሉምቢያ ተወልደው በጓንጓ ወረዳ ዳች ትቤት የተማሩት እና ከጓንጓ ወረዳ ጨረቃ ቀበሌ ህዝብ ጋር ያደጉት አቶ ሂስ ሄጮ በማንዱራ ወረዳ በተለያዩ ሙያ ዘርፎች እና ኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

ለቤተሰቦች እና ለሁለቱ ወረዳ ህዝብ መፅናናትን ይመኛል።

@Addis_News
@Addis_News


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ።

ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በተረጋጋ ሁኔታ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናዎችን ይወስዱ ዘንድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ይወጣ!

በያዝነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ኩረጃን እና የፈተና ስርቆትን ለመከላከል መንግሥት የወሰደውን እርምጃ በአድናቆት ይመለከተዋል።

ኩረጃና የፈተና ስርቆት የታታሪ ተማሪዎችን ድካም ዋጋ የሚያሳጣ እኩይ ድርጊት ከመሆኑም ባሻገር ለሀገራችን እድገት እንቅፋት ነው ብሎ አብን ያምናል። ስለሆነም የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱን ለማዘመን የሚደረጉ ጥረቶች አጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል ከሚወሰዱ እርምጃዎች ጎን ለጎን ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

ይሁን እንጂ በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች የታዩት ክስተቶች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን አሳስበውታል። ትላንት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው አሳዛኝ ድንገተኛ አደጋ የፈጠረው መረበሽ ሳይበቃ ዛሬ በደብረታቦርና ደብረማርቆስ ዩንቨርስቲዎች ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የተፈጠረው አለመረጋጋት መፈጠር ያልነበረበት ነው በለን እናምናለን:: በምንም ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል። ፈተናን ሳይፈተኑ አቋርጦ መውጣት የታዳጊ ተማሪዎችን የነገ ተስፋ የሚያጨልም በመሆኑ መታረም ይኖርበታል።

የሚመለከታችሁ የተፈታኝ ተማሪ ወላጆች፣ መምህራን፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ተፈታኞች በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆነው ፈተናዎችን እንዲሰሩ የሚጠበቅባችሁን እንድትወጡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል።

በዚህ አጋጣሚ አንቂዎች እና ተጽእኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የተፈታኝ ተማሪዎችን ስሜት የሚረብሹ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ እንድትቆጠቡ አብን ጥሪውን ያስተላልፋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)
አዲስ አበባ፣
ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.

@Addis_News
@Addis_News

Показано 20 последних публикаций.

1 585

подписчиков
Статистика канала