"በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 'ሴትነትና ቁንጅና' የሚባል የእስር ፍርግርጋችንን እያስዋብን ተሟሙቀን የወንዶችን ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሆነናል...ሁሉም እስር ሰንሰለቱ ፈጦ አይታይም...እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ለራሱ ጭምር አይታይም...ማህበረሰቡ አንዲትን ሴት 'የብረት መዝጊያ ' የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፣ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም!
ስለዚህ የእነርሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት፣ አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሮዋንም ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል"
"ማምሻ ቆንጆ አይደለችም...እጣ ፋንታዋ አይንና ጥርሷ ላይ ሳይሆን እጆቿ ላይ እንዳለ ግን ተገልጦላታል። ወንድ በእግሮቿ መሀል ካላለፈ የሚያልፍላት የማይመስላት ሴት አይደለችም...አዎ!እንዲያልፍላት የግድ ወንድ በእግሮቿ መሀል ማለፍ የለበትም!"
ከእለታት ግማሽ ቀን..."ማምሻ"(ገፅ 182)
በአሌክስ አብርሀም
https://t.me/shewitdorka