የባንዳ ምላስ ጣፋጭ ነው፥ ሬትም ነው!
ባንዳ ማለት ባጭሩ ከህዝብ ክቡር የህልውናና የነፃነት አላማ በተቃራኒ ቆሞ ለጠላት የሚሰራ ማለት ነው። ባንዳዎች ጌቶቻቸውን ለማስደሰት የማያደርጉት ነገር የለም። ምላሳቸው ጣፋጭ ነው። በጠላትነት ለተሰለፉበት ወገን ደግሞ ምላሳቸው ሬት ነው። በተለይ ፊደል ቀመስ የሆነ ባንዳ እጅግ አስቀያሚ ነው። አደግዳጊነቱ ልክ የለውም። የዘመናችን የባንዳዎች ቁንጮ የሆነውን ዳንኤል ክስረትን እንመጣበታለን። ለዛሬው የአፈወርቅ ገብረየሱስን አደግዳጊነት እንይ👇👇👇
ባንዳው አፈወርቅ ገብረ እየሱስ ስለ ፋሽስት ጣሊያን ይህን ብሎ ነበር👉 “ዛሬ - የፋሽስት መንግሥት ባንድ አሳብ ባንድ ምኞት ባንድ ቃል ባንድ ፍቅር ሆኖ ስለሠራ ኢጣሊያን የመልካም ፖለቲካ ምንጭ አደረጋት፡፡ ከዚያች ምንጭ ዓለሙ ሁሉ ሊቀዳና ሊጠጣ ይመኝ ጀምሯል፡፡” ካለ በኋላ፤
“የኢጣሊያ ሠራዊት ከዚህ ሲደርስ ጥቂቶች በጣም ጥቂቶች ብቻ ወደ ዱር ተሰማሩ፡፡ … እንኳንስ እነሱ ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ሲያሰኝ የነበረው ንጉሥ አንበሳነቱ ቀርቶ ጥነቸል ሆኖ ፈርጥጦ መሄዱን ያውቃሉ፡፡ እነዚህ የዱር ትሎች መሸፈታቸው የድሃውን የአማኙን በሬ እየሰነደቡ ለመብላት ብቻ ነው፡፡ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡” በማለት በጀግኖች ላይ ተሳልቋል:: (ምንጭ፡- Bahru Zewde, “The Ethiopian Intelligentsia and the Italo-Ethiopian War, 1935-1941” The International Journal of African Historical Studies, Vol. 26, No. 2 (1993), pp. 271-295.)
ግን መጨረሻ ላይ እውነት አሸንፋለች። "የዱር ትሎች" የተባሉት ባለ ድል ሆነዋል! ፋሺዝም ተንኮታኩቷል! ምስጋና ለጀግኖች አርበኞቻችን!!!
አርበኝነት ይለምልም!!!
የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!
@Hailu Bitania