— ❗️/ BREAKING#
UPDATEየቀጠለ...
አምላክ ከተባለውና ከሚመለከውም ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው ። በማለት ምን ያክል በትዕቢቱ ጣራ ነኪ እንደሆነም ጨምሮ ያስታውቃቸዋል ። ለምን ከተባለ... "ሰከን" እንዲሉ ።
እነዚያ ሰዎች ስራቸውን ሁሉ ትተው ስራ ፈት ሆኑ ። ስራም ስለሌላቸው የሚጋፈጡትም ችግር ቀላል አልነበረም ።
ሰሞኑን ነው ፥ #
የምንነጠው_ጌታ_በቅርቡ_ይመጣል ። ብለው ስራ ምን ያደርግልናል አሉ... ለዚያም ነው የለም ! የለም ! ሊሰራ የማይወድ አይብላ ፤ ብለናቸው ነበር ፥ ከእናንተ አንዳንዶቹ ስራ ፈቶች እንደሆኑ ሰምተናል ብሎ ፥የማረምያ ምላሽም ሰጥቶአቸዋል ።
በማስከተልም ይሔ ተቃዋሚ የአመጽ ሰው ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ
እኔ አምላክ ነኝ ! እያለ አዋጅ ያስነግራል በማለትም ትንቢታዊ መልእክቱን ይነግራቸዋል ።
"መቼስ" ቤተመቅደስ ሲኖር ነው ። ዓመፀኛው የሚቀመጠው ፤ የመጀመሪያውና ሁለተኛ ቤተ መቅደስ የሉም ፤ ፈርሰዋል ። እነዚያን ማሰብ አይሆንም ። ታዲያ ስለ የትኛው ቤት መቅደስ ይሆን ? ብለው ፥ ያረጋጋቸው ይህ ሊሆን ይችላል ። ቤተመቅደስ የላቸውማ ! እስኪሰራ ደግሞ መጠበቅ ግድ ሊል ነው ። ለዚያም ይሆናል ተረጋጉ ፥ አትናወጡ ! በማለት በሐዋርያዊ ስልጣኑ እሺታን ያስመረቃጣቸው።
ያ እንዳለ ሆኖ አሁን እኛ ጥያቄውን ልናነሳ ይገባል ። አሁን እኛ እንደ ያኔው የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ አትናወጡ ፤ አትደንግጡ እንደተባሉት እንሆን ይሆን ?
በርግጥ አሁን መደንገጥስ የለብንምን ?እነርሱ ገና ቤተመቅደስ ሳይሠራ ገና ራዕይው እንደታየ በረገጉ ። እኛስ ከሁለት ሽህ ዓመታት በኋላ ያለን ፤ እንዲሁ ተፈፃሚነት ጋር የደረሰን ፤ ነንና ልንነቃ ግድ ይላል ።
እስራኤል 3ኛ ቤተ መቅደሴን እገነባለው ። በ 2024 ሰርቼ ፥ አጠናቅቄ አሳያችዃለው ስትል ብዙዎቻችን ሰምተናል ። ሙሉ ለሙሉው ቅድመ ዝግጅቴንም ጥንቅቅ አድርጌአለሁ ያውም ለመስዋዕትነት የሚቀርቡትን በጥንቃቄ የተዘጋጁትን ጊደሮችም ወደ አገሬ አስገብቻለሁ ። ብላ ለዓለም ሁሉም አሳውቃለች።
ወገኖች አሁን ያለነው በፈረንጆቹ 2024 ላይ እንደሆንን መናገሩ የሞኝ ወሬ ቢያስመስለውም ማባነኑን ፈልገነው ፤ የልብ ትርታችንን ቢጨምር ለማለት ነው ።
እውነት ! እውነት ! የተሰሎንቄ ዎቹ መደናገጥ ምነው አሁን በሆነስ አያሰኝም ?
ዘንድሮ ቤተመቅደሡ ለመገንባት ምንስ ጊዜ ፈጅቶባቸው ፤ ስለ ቴክኖሎጂ እገዛ ዮናስ እንደሆነለት፥ በአንድ አፍታ እንደበቀለለት ቅል ተኝተን ስንነሳ ህንጻ ተገንብቶ አልቆ የምናይበት ዘመን ላይ መሆናችንን ከግምት ይግባ ።
በዚህ ቤተመቅደስ በርግጠኝነት የሚቀመጠው ማን እንደሆነ በግልጽ ባይታወቀም ወይም ይኸው ተሰናድተዋል።
ይኸው ምድራችን ከዳር እስከ ዳር የምናየው ነው ። ለርሱም አቀባበል ለማድረግ ዓለም ሽርጉዷ ጦፏል ።
የተሰሎንቄዎቹ ሰዎች በጣም ፈጣኑ የምንል ከሆነ ፥ የእኛስ ደግሞ አያያዛችን በጣም ዘገያችሁ አያስብልም ? የኛስ ከመጠን በላይ በዛ ፥ የቤተክርስቲያን እንቅልፍ ልኩን አጣ ፤ ሁኔታዎችን እንዲህ እያየን እንኳ የነፍሳችን ጥማት ሌሎች ነገሮች ሆኑ ። በምናገኛቸው ማንኛውም የቅዱሳን ስብስብ ላይ "ትንፍሽ" እንዳትሉ ! የተባለ ይመስላል፥ ወይም ለተሰሎንቄዎቹ የተጻፈውን "እረረ" ገና ነው ! የተባለው ላይ ነን ። እንግዲህ ካሰብን ደግሞ ከጊዜው ጋር እየሄድን አይደለንምና ወቅቱን ማየት ግድ ይላል ።
የእሁዶቻችን የአምልኮ ፕሮግራሞችን ጨምሮ ቢያንስ እንኳን ንጥቀታችን እንደደረሰ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመጣ የሚያወራ እንደ ቋሚ መፈክር አይነት አንዲት አረፍተ ነገር እንኳን በመናገርና በማወጅ ቤተክርስቲያን ብታከናውነው መልካም ነው ። የዛሬው መልእክታችን ነው ።
— ❗️❗️
@CHRISTIAN_NEWS— ❗️❗️
የፍርድ/ /ቀን/
/#ንጥቀት_አለ/
Join us Telegram
@RAPTURE_TUBE@RAPTURE_FAMILY