ያአኺ ዱንያ ላይ ትልቁን ነፃነት ከፈለክ ለጌታህ ታማኝ ሁን❗️
እንዲያው የአሏህ ቃል የሚገርምኮ ነው ያአኺ❗️
ሱረቱል አል ዓዲያት ላይ
قل تعالي: وٱلعاديات ضبحا
እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት ፈረሶች እምላለሁ።
فٱلموريات قدحا
በሰኮናቸው እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም
فٱلمغيرات صبحا
በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
فأثرن به نقعا
በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም
ስለጀግኖች ፈረሶች ያወራልናል ወደጦር እየሄዱ ነውና ልብ የሚያንጠለጥል አካሄድ ላይ ናቸው።አንቀፅ 5 ላይ ምን ይለናል
فوسطن به جمعا
በጠላት ክቢ መካከል በእርሱ በጧት በተጋፈጡትም እምላለሁ።
ይለንናል ልክ አንቀፅ 6 ላይ
قل تعالي:إن ٱلإنسان لربه لكنود
ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው።
እህ❗️ትላለህ እነዚያ መዳረሻቸው ልብህን ያንጠለጠሉት የሚገሰግሱት ጠላት ጋ የተጋፈጡት ፈረሶች ፍፃሚያቸው ምን ሆነ❓ያ አኺ የቁርአን ትልቁ ውበቱኮ ይህ ነው።አሏህ ስለፈረሶች አይደለም ሊያወራህ የፈለገው።ስለኔና ስላንተ እንጂ።
አስተንትን አንተ የአሏህ ባሪያ ፈረስ ላሳዳሪው ምን ያህል ታማኝ እንደሆነ።ቀን አይል ማታ፤ ዳገት አይል ቁልቁለት፤ ውሃ አይል አቧራ ብቻ አሳዳሪው ወደጠቆመው አቅጣጫ ሳያንገራግር ይገሰግሳል ታማኝና እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ ታዛዥ ነውና።
እኔና አንተስ ለአሏህ እጅና እግራችንን ሰጠን ለመታመን ከፈረስ ያነስን ነን እንዴ⁉️
✍ቢንት ኢብራሂም
join👇
t.me/bintibrahimm