💓💓💓💓💓ሞሮ 💓💓💓💓💓
💓💓💓💓 ክፍል 30 💓💓💓💓
ቀናት ቀናትን እየወለዱ ወደ ሳምንታት ተቀየሩ ሳምንታትም ወደ ወራት ተገለበጡ ግዜ ማንንም ሳይጠብቅ እየነጎደ ሄደ.....
ከሰመሃል ጋር ያለን ጓደኝነት ከምንግዜውም በላይ ጨምሯል ከተዋወቅን ወደ ስድስት ወር ገደማ ሆነን በየቀኑ እንደዋወላለን እኔ አዲስ አበባ ከተመለስኩ ግዜ ጀምሮ ሁሌ አርብ ማታ ሸገር ትመጣለች ቅዳሜን ከቤተሰቦቿ ጋር ታሳልፍና እሁድ በጥዋት አብረን ቦሌ መድሃኒ አለም ቤተክርስቲያን እንሄዳለን ከዛ አስቀድሰን ከጨረስን በኃላ እንደለመድነው አንድ ካፌ ገብተን ቁርስ በልተን በእግር ወክ እያደረግን እኛ ቤት እንሄዳለን ቤተሰቦቼ ከሚባለው በላይ ወደዋታል። ቅዳሜ ማታ ሁሌ እናቴ ሰምሃል ነገ አትመጣም እንዴ እያለች መጨቅጨቅ ስራዋ አድርጋዋለች ከእህቴ ጋርም ጥረ ጓደኛሞች ሆነዋል እሁድ ቤት ስትመጣ የከበዳትን ታስረዳታለች። እህቴ ደግሞ ከኪያር ጋር የጠበቀ ፍቅር ውስጥ ገብተዋል ሁሌ እያየኃቸው መሳቅ ነው ስራዬ ኪያር አልፎ ኣልፎ ከሰሙ ጋር እየመጣ አብረን እናሳልፋለን።
ኤቤጊያም በየግዜው ትደውላለች እናወራለን ባህሪዋን ለማስተካከል እየጣረች እንደሆነ ነግራኛለች። ሰምሃልን አናግሪያት ከኤቤጊያ ጋር ታርቀዋል እንደበፊቱም ባይሆን ጥሩ ጓደኛሞች እንደሆኑ ኤቤጊያ ነግራኛለች።
የትምህርት ግዜ ተጠናቆ ፋይናል ፈተና ተፈትነው ወደ ሸገር ከመጡ በኃላም ከሰሙ ጋር ያለን ጓደኝነት ይበልጥ እየጠነከረ ሄደ። ለሷ ቃል ባገባሁላት መሰረት ማንነቴን በደምብ እያስተካከልኩ ነው እንደድሮ እየጀዘቡ ተኝቶ መዋል መሰላቸት ሱስ ውስጥ መዘፈቅ ሙሉ ለሙሉ አቁሚያለው ብዙ ግዜዬን አባቴን ቢሮ በስራ እያገዝኩት እውላለው አመሻሽ ላይ ከሰምሃል ጋር ወክ እናደርጋለን ወይ አንድ ቦታ ተቀምጠን እናወራለን ኪያር እና እህቴም ደስ ሲላቸው ይቀላቀሉናል። ኤቤጊያም ትምህርት ጨርሳ ስትመጣ እንዳገኛት ቃል አስገብታኝ ስለነበር አልፎ አልፎ አገኛታለው ሰምሃል የምትመክረኝን ምክር እኔም ለሷ መክራታለው ከዛን ግዜ ጀምሬ ስህተቷን ቀስ በቀስ እያረመች ትገኛለች።
ወደ ቀድሞ ማንነቴ ለመመለስ ብዙ ወራት ፈጀብኝ ቀላል ጉዞ አልነበረም። የድሮው ናኦድ ብሎ ማውራት ቀረ...ተመልሶ ስለመጣ በአልባሌነት ያቃጠልኩት ሁለት ይቆጨኝ ጀመር እንዴት እንዲህ እሆናለው እያልኩ ሁሌ ራሴን ወቅሳለው።
አዲስ አመት አዲስ የትምህርት ዘመን መጣ ያሳልፍኳቸው ድፍን ሁለት አመታት እየቆጩኝ እነሱን ለማካካስ በአዲስ ጥንካሬ እና ብርታት ለማማር ዝግጁ ሆንኩ። አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በ2006 አ.ም መስከረም 20 ላይ እንድንገባ አስታወቀ ያቋረጥኩትን የአራተኛ አመት ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህር በአዲስ መንፈስ ለመጀማር ዝግጁ ሆንኩ።
የተጠራንበት ቀን ደርሶ እንደነገ ወደናዝሬት ለመሄድ እየተዘገጃጀው ማታ ላይ ሰሙ ደወለች ናፍቃኝ ነበር አዲስ አመት ክፍለሀገር አያቷ ጋር ሁሉም ቤተሰባቸው ተሰብስበው ያከብሩ ስለነበር አዲስ አመት ከገባ አልተገናኘንም ቅርብ ቀን መስቀልን አክብራ ነበር የመጣችው። እሷም ነገ ልትሄድ እንደሆነና የያዘችው ሻንጣ ስለሚከብድ እኔ ከአባቴ ጋር አብረን እንደምንሄድ ስለምታውቅ እሷም አብራን እንድትሄድ ጠየቀችኝ አባቴ ደስ እያለው እንደሚያግዛት ነገርኳት። አባቴ ከስራ ተመልሶ እራት እየበላን እያለ ሰምሃል የያዘችው ሻንጣ ትልቅ ስለሆነ ነገ ከኛጋ እንደምትመጣ ነገርኩት ደስ እያለው ምነው ለበአል ሳትመጣ ቀረች አለኝ አይ አያቷ ጋር ነበረች ክፍለሃገር አልኩት እየሳቀ እሺ ችግር የለውም አብራህ ትሄዳለች ታግዛታለህ አለኝ። ግራ እየተጋባው እንዴ አንተስ አትወስደኝም እንዴ አልኩት አዪ... እንደው ነገ ነበር ሰርፕራይዝ ላደርግህ ያሰብኩት ግን ዛሬ ቢሆንም ችግር የለውም አለና የሆነ ትልቅ ቁልፍ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ እኔ እህቴ እናቴም ፍጥጥ ብለን አየነው የመኪና ቁልፍ ነው በደስታ ዘልዬ ወይኔ ባባ መኪና ልትሸልመኝ ነው አልኩት ከት ብሎ ሳቀና እረ... ቁልፉን ብቻ ነው መኪናውን ወደፊት አለኝ እእእይ ብዬ ወንበሩ ላይ ዘጭ ብዬ ተቀመጥኩ ከት ብሎ ሳቀና አው! መኪና ነው ሂድና ውጪ እየው አለልህ አለኝ እየበላሁ የነበረውን ምግብ ትቼ እየሮጥኩ ወደ ውጪ ሄድኩ እህቴም ደስ ብሏት ከኃላዬ ተከተለችኝ ባባ እየሳቀ ቀስ ብሎ መጣ።
ይቀጥላል.....
👍👍👍👍
https://t.me/New_life_20https://t.me/New_life_20